Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39999
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በቋንቋ ዙሪያ ያለው አሳፍሪና አሳዛኝ ንትርክ፤ ቋንቋ ቴክኖሎጂ ነው፣ የማንነት ሳይሆን የኢንተለጀንስ መለኪያ ነው

Post by Horus » 04 Mar 2020, 01:28

የሰው ልጅ ማደን መማሩን እንደ እድገት ይታያል ። ግን ማደን ሰው ያደረገው ፍልስፍና ነው ተብሎ ብዙ አይባልም። ለምሳሌ ማነው ዉሃን የፈለሰው ፣ ምግብን የፈለሰፈው አንልም ። ግን ምግብ ማብሰል ፍልስፊና ነው።

ማነው እሳትን የፈለሰፈው አንልም ፣ ግን እሳትን መጠቀም ፍልስፍና ነው። የፍልሰፋ ውጤት ማለት ቴክኖሎጂ ይባላል። ሰው የሰራው ነገር ማለት ነው።

ብዙ የሳይንስ ሰዎች የመጀመሪያ የሰው ፍልስፍና፣ የሰው ቴክኖሎጂ የሚሉት ያፍ ቋንቋ መፈልሰፉ ነው ። ያፍ ቋንቋ ከድምጽ ቢሰራም የግንባታ ድምጸ ቅላጼውና ሰዋሲዉ ሰው የከወነው ቲክኖሎጂ ነው ።

ማለትም የመጀመሪያው ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ያፍ ቋንቋ ወይም ስፖክን ላንጉጅ ነው። ሁለተኛው ሰው የፈለሰፈው ቴክኖሎጊ ድምጽን በምልክት፣ በሰል ቀርጾ ከዚያም ሃሳብ ባንጎል ውስጥ ያለን ነገር ሁሉ አውጥቶ ኮሚኒኬት ማድረግ ነበር። ስለዚህ ፊደል ሁለተኛ የሰው ልጅ የፈጠረው ቴክኖሎጂ ነው።

በኢትዮጵያ 90 ቋንቁዎች አሉ ማለት 90 መናገሪያ ቴክኖልጂዎች አሉ ማለት ነው። በሳይንስ አለም ይህ ድግግሞሽ፣ ሪደንደንስ ይባላል። ቴክኖሎጂ መሳሪያ ስለሆነ አንዱ መሳሪያ ከሌላው፣ አንዱ ቴክኖሎጂ ከሌላው የዘመነ የረቀቀ የተሻለ ነው። የዘመነ ቴክኖሎጂ ሚጠቀሙ ህዝቦች ይገሰግሳሉ ። ኋላ ቀር ቴክኖሎጂ የሚሉ ኋላ ይቀራሉ ።

ዛሬ በኢትዮጵያ ካሉት 90 ቋንቁዎች ሁለት ሶስቱ የላቲን ፊደል። ውደ 85 የገዕዝ ፊደል ይጠቀማሉ ። የቱ ፊደል ነው የሚሻለው? ከላቲን ቀድሞ የተፈለሰፈው ቴክኖሎጂ ግ እዝ እጅግ የላቀ ቴክኖሎጂ ነው ።

የፊደል ቴክኖሎጂ ስራ አንድን ድምጽ በሰዕል ቀርጾ ኮድ ማደረግ ነው። በሰው አፍ የሚባሉት ድምጾች ሁሉ አናባቢ አናጋሪ ቃል መለያ ቫወልና ክኖሶናንት ባንድ ምልክት ቀርጾ የእስፔሊንግን ስራ በፊደል የሰራ ሌላ ቴክኖሎጂ የለም ።

ስለዚህ እነ ኦነግ ምናምን ያሻቸውን ዝቅተኛ የምልክት ቴክኖሎጂ ለፖልቲካና ክብር ሲሉ ይዋሱ፣ ሰው ግ ን ምን ግዜም የሚጠቀመው የቀለለውን እና ምቹ የሆነውን ቴክኖሎጂ ነው።

ወደፊት በኢትዮጵያ ሴም ቋንቁዎችና በግሪክ፣ ላቲን፣ እና ስንክሳር መሃል ያለውን ቅርርብ ስናሳይ እነዚህ የዝቅተኛው ላቲን አልፋቤት ቴክኖሎጂ ተበዳሪዎች ሲያፍሩ ይታየኛል ። ኬር !

Horus
Senior Member+
Posts: 39999
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በቋንቋ ዙሪያ ያለው አሳፍሪና አሳዛኝ ንትርክ፤ ቋንቋ ቴክኖሎጂ ነው፣ የማንነት ሳይሆን የኢንተለጀንስ መለኪያ ነው

Post by Horus » 04 Mar 2020, 02:02

ሌላ አንድ ነገር ላክልና የዛሬን ላቁም።

ቴክኖሎጂ አንዴ ተፈልስፎ ከዚያ ዝም ብሎ አይረሳም ። ራሱ ያ ተኢክኖሎጂ የራሱን የእድገት ሂደት ይዞ ይገሰግሳል ። አማርኛ በግዝ ከተቀረጸ በኋላ ዝም ብሎ አልኖረም ። በስንት ሺ መጻህፍት፣ ቅኔያት፣ ግጥም፣ ዜማ፣ ሰእል፣ ሌላም ሌላም አዳዲስ የላቁ ማለትም አጵግሬደድ ቴክኖሎጂዎችን እየወለደ አንድ ሙሉ ግዙፍ ካልቸር የፈጠረ የፊደል ቴክኖሎጂ ነው። የግ እ ዝ ፊደል አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ስልጣኔን ኮድ ለማድረግ ለማኖር የወሰደበት ዘመን አንድ ሺ አመት ይሆናል ። እስቲ እነ ኦነግ የላቲን ምልክትን ምን እንደ ሚያረጉት እናያለን ። የስልጣኔ መሳቂያ ነው የሚሆኑት ። ቴክኖሎጂ ያዳጋል ይሻሻላል ማለት በግእ ዝ ፊደል ላይ ልዩ የሆነን የኦሮም ድምጽ የሚቀርጽ ምልክት መስራት ነበር ኢተለጀንት ቢሆኑ። ትግርኛ ያ አድርጓል። ጉራጌና ያን አድርጓል። ወዘተ ፣

Horus
Senior Member+
Posts: 39999
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በቋንቋ ዙሪያ ያለው አሳፍሪና አሳዛኝ ንትርክ፤ ቋንቋ ቴክኖሎጂ ነው፣ የማንነት ሳይሆን የኢንተለጀንስ መለኪያ ነው

Post by Horus » 04 Mar 2020, 04:01

ቋንቋ መሳሪያ ነው ፣ ያለውም ዋጋ እንደ ተጠቃሚው ነው። አንድ ሰው ምንም የማያረግ የማልፈልገው መኪና ይዞ ቢቀመጥ እኔ ጉዳዬ አይደለም !! ይህን ተመልከቱ አንድ ቋንቋ ኢትዮጵያን ሲጠብቅ ወድጄ እማረዋለሁ ። እኔን የምያከብር ቴክኖሎጂ ለኔ ጀንክ ነው !!

Last edited by Horus on 05 Mar 2020, 00:14, edited 1 time in total.

Selam/
Senior Member
Posts: 16948
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: በቋንቋ ዙሪያ ያለው አሳፍሪና አሳዛኝ ንትርክ፤ ቋንቋ ቴክኖሎጂ ነው፣ የማንነት ሳይሆን የኢንተለጀንስ መለኪያ ነው

Post by Selam/ » 04 Mar 2020, 18:39

According to tribalist interpretation of identity, these women are Amhara:



...and Reuben Nsemoh is a born-again Spaniard

https://time.com/4542967/teen-coma-flue ... h-georgia/


Horus wrote:
04 Mar 2020, 04:01
ቋንቋ መሳሪያ ነው ፣ ያለውም ዋጋ እንደ ተጠቃሚው ነው። አንድ ሰው ምንም የማያረግ የማልፈልገው መኪና ይዞ ቢቀመጥ እኔ ጉዳዬ አይደለም !! ይህን ተመልከቱ አንድ ቋንቋ ኢትዮጵያን ሲጠብቅ ወድጄ እማረዋለሁ ። እኔን የምያከብር ቴክኖሎጂ ለኔ ጀምክ ነው !!


Post Reply