ታሪክ ለማታቁ ይህን ልንገራችሁ ። ድሮ፣ ድሮ በግብጻዊው ጻዲቅ አቡነ ገብረ መንፈስ (እኛ አቦ ነው ምንላቸው) ዘመን ምድረ ከብድ አቦ (ምድረ ቅዱስ አቦ )፣ ዝቋላ አቦ እና አዳዲ ማርያም እንደ አንድ ደብር ይታዩ ነበር ። የአዳዲ ማርያም አመቷ ሲከበር ባመት አንዴ የምድረ ከብድ ምዕመን የሆነ ቤተ ሰብ አንዲት ድንግል ሴት ልጁን መንኩሳ ማርያምን እንድታገለግል፣ ተጊጣ፣ ተሞሽራ ፣ እንሾሽላ ተብሎላት ላዳዲ ማሪያም ገዳም ምንኩስና ትታጭ ነበር ። ይህ ደሞ ትልቅ ክብር ነበር ።
እኔ እስከ ማቀው አቦነሽ የቡቂ ልጅ ናት ፣ ማለትም ዘርማንዘሯ የተቀበሩት ምናልባት በታላቁ፣ በቅዱሱ አቦ አፈር ውስጥ ነው ። ልብ በሉ ! አቦነሽ አለምክኒያት አይደለም ያቦ ልጅ ነሽ ተብላ የተሰየምቸው ! ገና ብዙ ብዙ ለዚያ ገዳም ስትሰራ ብሎም እዚያው ስትመነኩስ እንሰማለን !! ኬር !!!
አቦነሽ አድነው የነገው ምድረከብድ አቦ ገዳም እናት
Last edited by Horus on 07 Feb 2020, 04:31, edited 2 times in total.