Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40031
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጎሳ ፌዴሬሽን የሚባለው ተረት እየፈራረሰ ነው፤ አማራና ደቡብ በዜጋ መንግስት ላይ ውይይት መጀመር ግድ ይላቸዋል !!

Post by Horus » 29 Jan 2020, 00:04

ያልኮልና የድራግ ሱስ እንደ ማለት ነው። ለ30 አመት በትግሬ ስር ያለሰራውና የቀን ጅቦች መሳሪያ የነበረው አሁን አዲስ ጠርሙስ ውስጥ ስለገባ አዲስ መንግስት ሊሆን ከቶም አይችልም ። ኢትዮጵያ ከትግሬ ቀውስ ወደ ኦሮሞ ቀውስ ነው የተሸጋገረችው ።

አሁን አማራ ዝም ብሎ ከንቱ መግለጫ ማዥጎድዱን ትቶት ፣ ይህን የድንቁርን ህሳቤ የሆነውን ጎሳ ፌዴሬሽንን በማፍረስ መቆሚያ ያለው የዜጎች ፌዴራል መንግስት ከሚፈልጉት ጋር አዝቸኳይ ወይይት መጀመር ግድ ይለዋል።

በቃ የጎሳ ድራማ መድረሻውን ፣ ፍጻሜውን መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ አይቶታል ። ከዚህ የትም ፈቀቅ አይልም ። የሚቀጥለው አገር አቀፍ የርስ በርስ ጦርነት ነው።

የጎሳ ፌዴሬሽን ሞቶ በእሬሳው መከርፋት ነው አገሪቷ እየታመሰች ያልቸው።


Last edited by Horus on 29 Jan 2020, 01:26, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 40031
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ፌዴሬሽን የሚባለው ተረት እየፈራረሰ ነው፤ አማራና ደቡብ በዜጋ መንግስት ላይ ውይይት መጀመር ግድ ይላቸዋል !!

Post by Horus » 29 Jan 2020, 01:14

የጎሳ መንግስት የመፍረሱና በፍጹም የማይሰራ ሞዴል ለመሆኑ ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

አንድ የመንግስት ድርጅት ቢያንስ የሚከተሉትን 4 ወይም 5 አምስት ፋይዳኦች አሉት

አንድ ፤ ያገር አንድነት፣ ያገር መረጋጋት፣ ያገር ጉልበት ማረጋገጥ። በዚህ ግብ ላይ የጎሳ መንንግስት የ3ቱም ተቃራኒ ነው። ያገር አንድነት አፍርሷል። ያገር መረጋጋት (ሰላም) አፍርሷል። አግሪቷን ፈጽሞ አድክሟል ።

ሁለት፣ አንድ መንግስት የህዝቦችን መብት፣ ፍትህ ፣ ዴምክራሳዊ ህይላቸውን ማረጋጥ አለበት ። የጎሳ መንግስት የጥቂት የጎሳ ባልስልጣኖች መድለቢያ መስረቂያ እንጂ ህዝቡ እውነተኛ ዴሞክራሲ፣ ነጻነት፣ ፍትህ ሚባል የለውም ። ዜጋ ሁሉ ይጎሳ ፍፈፋ ባሪያ ሆኖዋል ።

ሶስት፤ ትልቁ የኢትዮጵያ ቅውስ የብልጽግ ና፣ ትምህርት ፣ የጤና መኖር ነው ። ዛሬ እጅግ እጅግ ግዙፉ 110 ምሊዮን ህዝብ ጥያቄ ድህነት፣ ት/ቤቶች የጎሳ መጋደያ ሜላ መሆንና በሽታ የተንሰራፋበት አገር መሆኑ ነው። በኢትዮጵያ 25 ሚሊዮን ህዝብ ያይምሮ እመምተኛ ነው ። ሌላው ቤቱ ይቁጠረው ። የኮሌጅ ምሩቅ የስራ ማመልከቻ በእንግሊዝኛ መሙላት አይችልም።

አራት ፣ አንድ መንግስት የፈጠራ ባህል፣ ከባቢ አክባሪ ባህል ፣ ፈሪሃ ፈጣሪ ያለው ህዝብ የሚያለማ ባህል መገንባት ግዲታው ነው ። ግ ን የጎሳ ፌዴሬሽን በዚህ ሁሉ ወድቋል።

ስለዚህ ለምንድን ነው ጥቂት የጎሳ ፖለቲካ ሰዎች ሙጭጭ ብለው የያዙት? መስረቂያ፣ ባለ ተራ ሆነው መዘርፊያ፣ ሌሎችን መጨቆኛ መሳሪያ ስለሚሹ ነው ።

Post Reply