
ትናንት በEmail የደረሰኝን (በእንግሊዝኛ ተጽፎ ወደ አማርኛ የተረጎምሁትን) ያልተጣራ አደገኛ መረጃ ስሜታዊ ሆኜ ወይም ደንግጬ ለጥቂት ሰአታት Post አድርጌው እንደነበር ይታወቃል።
እውነት ለመናገር ይበልጥ የተጎዳሁት እኔው ነኝ። ዞረም ቀረ Post ያደረግሁትን ደብዳቤ ወዲያውኑ ደምስሼዋለሁ።
ኦሮሞ ወዳጆቼ "Gadaa Gabra'ab እንዴት እንዲህ በፍጥነት ስሜታዊ ሆነ?" የሚል ጥያቄ ሲያነሱ - ሲጻፉ ውለዋል። "በለጸግህ እንዴ?" ብለው እኔን ከአብይ ጋር በማያያዝ ያላገጡብኝ ኦሮሞችም አሉ።
ከ"የቡርቃ ዝምታ" መታተም ጀምሮ ለ23 አመታት ከኦሮሞ ህዝብ ትግል ጋር የሚያውቁኝ አድናቂዎቼ የነበሩ ኦሮሞዎች ጭምር 180 ዲግሪ ተጠምዝዘው ሲያጠቁኝ አይቼ እንደተሳቀቅሁ አልደብቅም።
ርግጥ ነው፣ የዘመኑ ፋሽን እንዲያ ነው። ያም ሆኖ ኦቦ አዲሱ አረጋ በዚህ ፋሽን መሰረት ሲያጠቃኝ ከማንም ቀድሞ ፊትለፊት ወጥቶ ለኔ የተጋፈጠው ጃዋር መሃመድ ነበር። "ነባር ወዳጅህን ስለመጠበቅ" እንዲሁም "አዲስ ወዳጅ ለማፍራት ነባር ወዳጅህን መግደል እንደማይገባ" ህብረተሰብን ያስተማረው ጃዋር ነበር።
ስለኔ ማወራት ፈልጌ አይደለም። ርእሰ ጉዳዬ ስለ ጽናት ነው። ስለ እውነት ነው። "ገበሬው ማረሻውን ተክሎ ካልያዘ በሬዎቹ ይወዛወዛሉ።" የሚል አባባል አለ። እና እኔ በጭፍን የኦሮሞ መሪዎችን እንዳሞግስ ብቻ የምትጠብቁ ኦሮሞዎች ካላችሁ አልተግባባንም። እንደ አንድ የኦሮሞ ዜጋ ነጻ ነኝ። በሞጋሳ ባህል ያገኘሁትን ኦሮሞነት እንደ ጃኬት ከኔ ትከሻ ላይ የመግፈፍ መብት ያለው ኦሮሞ የለም። የምጽፈው ለኦሮሞ መራራ ቢሆን እንኩዋ መቃወም እና መሞገት እንጂ ሌላ አይቻልም። የማከበረው ኦቦ ዳውድ ኢብሳን እንኩዋ በጽሁፍ አፈር ድሜ ባበላው ለማንበብ ተዘጋጁ። ምክንያቱም ኦሮሙማ ይህን ይፈቅዳል። እኔ የማውቀው ኦሮሞነት እና ኦሮሙማ ከሙሉ ነጻነት ጋር ነው። "ኦሮሞ ኢትዮጵያን የሚመራበት ዘመን ከመጣ ተአምራዊ ዴሞክራሲ ያሳየናል" እያልኩ በስሜት ስጽፍ የኖርኩትም ለፕሮፓጋንዳ አልነበረም። የልቤን ነው።
አንድ ተጨማሪ እውነት ላንሳ!?
ትናንት Post ስላደረግሁት መረጃ መረዳት የምትችሉት ደብዳቤውን ማን እንደላከልኝ ብታውቁ ነበር። ዳሩ ግን ማንም ይሁን ማን ምንጊዜም ለወዳጆቼ ታማኝ መሆን ስላለብኝ ደብዳቤውን የላከልኝ ኦሮሞ ማን እንደሆነ ልነግራችሁ አልችልም። በርግጠኛነት የምነግራችሁ ገለልተኛ እና የተከበረ መሆኑን ብቻ ነው። ይህ ማለት ግን አይሳሳትም ማለት አይደለም። ተሳስቶ አሳስቶኝ ሊሆን ይችላል። ስሙን ብነግራችሁ ምናልባት እንደኔው ችግር ውስጥ ወይም የህሊና እስርቤት ውስጥ ልትገቡ በቻላችሁ። የሚሻለው እንደ ጥላሁን ገሰሰ አባባል "ሆድ ይፍጀው"፣ "ጊዜ ይፍጀው" ብሎ ሁሉን ለጊዜ መተው ነው።
ይችን አጋጣሚ በመጠቀም በእኔ ላይ ስም የማጠልሸት ስራ የጀመራችሁ "አዲሱ አረጋዎች" ሆይ! ይመቻችሁ!!
https://www.facebook.com/photo.php?fbid ... =3&theater