Page 1 of 1

መቅደላና ሄግ - ድርብርብ ታሪክ ያስተናገደችው ታሪካዊቷ “አብሪል 13”

Posted: 13 Apr 2026, 07:51
by Meleket
Meleket wrote:
15 Apr 2025, 03:57
በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ኮሚሽኑ ከ23 ዓመታት በፊት ያስተላለፈው ብይንን በተመለከተ ያፍሪካ ቀንድ የመገናኛ ብዙሃን በዝምታ ማለፋቸውን ታዝበናል። ቢሆንም ግን ብይኑ የተላለፈባት ታሪካዊቷን ቀን “ኣብሪል 13” በተመለከተ፡ በሌላ ታሪካዊ ፍጻሜ በግጥምም ስትዘከር ኣስተውለናል፡ ዝርዝሩን ኣያይዘናል “ዝክረ ኣብሪል 13 1868 ወመቅደላ!”
Meleket wrote:
15 Apr 2025, 03:00
ታሪካዊዋን "ኣብሪል 13" ፍጻሜ በግጥም ለማስታወስና ለመዝናናትና ለማዝናናት ያህል ነው!

ከህንድ ተነስቶ ገሰገሰ እንግሊዝ፣
ከዙላ ተነስቶ ገሰገሰ እንግሊዝ፣
በሰንዓፈ አድርጎ ገሰገሰ እንግሊዝ፣
ያጤ ቴዎድሮስን መንግሥት ሊገዘግዝ፣
እዬተላላከው የትግራዩ በዝብዝ!


ቴዎድሮስን ሊያጋድም ናፕዬር ገሰገሰ፡
ትግራይና ወሎን እያደፈረሰ፡
"የጦቢያን ሰራዊት" እዬገረሰሰ፡
የቋረኛውን ትዕቢት እያስተነፈሰ፡
መቅደላ ኣናቱ ላይ እንግሊዝ ነገሰ፡
ጦብያ ምን ትያለሽ መንግስትሽ ፈረሰ።


ቢያውቀውማ ኖሮ ቀይባህርን ቴዎድሮስ፡
ዙላ ላይ ነበረ እንግሊዝ ሚቃወስ፡
ባህሩ ዳር ነበር ናፒዬር ሚደመሰስ።

ቀይባህርን ቴዎድሮስ ቢያውቀውማ ኖሮ፡
ናፒየርና ጭፍራውን ባህሩ ውስጥ ነካክሮ፡
በደመሰሳቸው በክንዱ ደካክሮ።

ኣያውቀውም ነበር ቴዎድሮስ ቀይ ባህርን፡
ከጥንት ከጠዋቱ የኛ የሆነውን።


"ዝክረ ኣብሪል 13 1868 ወመቅደላ" ተጣፈ በእኛ በኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
Meleket wrote:
14 Apr 2025, 11:22
ታሪካዊቷ “ኣብሪል 13” ተዘክራ ውላለች - ከ157 ኣመታት በፊት መቅደላ ላይ ኣጤ ቴዎድሮስና እንግሊዞች ተርመስምሰው ነበር።
Battle of Magdala
Sir Robert Napier’s capture, on 13th April 1868, of the Fortress of Magdala, stronghold of the Emperor Theodore III of Abyssinia

Assault on the Kukitber Gate at the Battle of Magdala on 13th April 1868 in the Abyssinian War


ይህቺ ታሪካዊት ዕለት የኤርትራና ኢትዮጵያ የደንብር ብይን ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ የተወሰነባት ዕለትም ነች!
ሲጠቃለል የሄጉን ብያኔ በፊዚካል ዲማርኬሽን መሬት ላይ በተግባር ስጋ ማልበስ፡ ሁነኛው የኤርትራና ኢትዮጵያ የድንበር ኣዋሳኝ ህዝቦች የሰላም ዋስትና ነው ብለናል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ከቀደምት ኣያቶቻችን በወረስነው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር!