የአቢይ አህመድ አሊ የፈረስ ስም፡ አባ ደምር ብዬዋለሁ! ሆረስ ዘ ኢትዮጵያ ነኝ!
Posted: 29 Jan 2026, 23:10
አቢይ አህመድ አሊ ወደፊት በታሪክ ሚዛል ላይ ምን መስሎ ፣ ማንን መስሎ ይወጣል በሚለው ጉዳይ ላይ ሁለት ነገሮችን ብዬ ነበር።
አንዱ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ በማዘመን ርዕይ የተመሰረተ ሆኖ ጠ/ሚ አቢይ አህመድ አሊ አሁን በያዘው ቀጥሎ ኢትዮጵያ በሁሉም መልኳ አዘምኖና የብሄራዊ አንድነትና ሁሉም የሚገዛው ኢትዮጵያዊነት ሳይኮሎጂ እንዲሰፍን ካደረገ የኢትዮጵያ አታቱርክ ይሆናል ብዬ ነበር። የቱርኩ ከማል አታቱርክ የሚታወቀው የዘመናዊት ቱርክ አባት ተብሎ ስለሆነ!
ከዚህ ብዙ ባልራቀ እይታ ግብጾች አቢይ አህመድ አሊ የቱርኩ ኤርዶጋን ወይም የሊቢያው ቃዳፊ ይመስላል ብለዋል።
ሁለተኛው ያልኩት ነገር አቢይ አህመድ አሊ አሁን በያዘው ቀጥሎ አገሪቱን ገንብቶና አዘምኖ በተለይም ኢትዮጵያን ወደ ታሪካዊ የቀይ ባህር አገርነቷ ከፍ ካደረጋ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከአጼ ምኒልክ ዳግማዊ ቀጥሎ የሚቆም የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ በታሪክ ይመዘገባል ።
እነዚህ ሁለት እይታና ትንበያዎቼ አሁምን እጸናባቸዋለሁ!
ዛሬ የማነሳው ሶስተኛ ጉዳይ የአቢይ አህመድ አሊ የፈረስ ስም ማን ይባል የሚለው ነው። ሰውዬው የሚያምንበት፣ የሚመራበትና ተደጋጋሚ መጻሕፍት የጻበበት ንድፈ ሃሳብ መደመር ይለዋል! ከዚህ የሰውዬው ፍልስፍናና ማስተዳደሪያ ሞዴሉ በመነሳት የፈርሱን ስም አባ ደምር ብዬዋለሁ !
ሆረስ ዐይነ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ
ጃኗሪ 29 ቀን 2026 ዓም