Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6028
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Naga Tuma » 26 Mar 2025, 17:48

ይህ ጥያቄ ለረጅም ግዜ ከእኔ ጋር ሰንብቷል።

ቀላል መልሱ ተናግሮ የማሳመን ችሎታ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ጠለቅ ስንል ነዉ መልሱ ከባድ የሚሆነዉ።

አንደበተ ርቱዕነት ባህሉ የሆነ ማህበረሰብ ሊኖር ይችላል?

መልሱ ኣዎ ከሆነ እንደዚህ ዐይነት ባህል ማካበት የሚቻለዉ እንዴት ነዉ? እንደዚህ ዐይነት ባህልን ማካበት ምን ያህል ዘመናትን ይወስዳል?

የኢትዮጵያን ስልጣኔ በጥልቅ እናዉቃለን የምትሉ ኢትዮጵያዊያን እስቲ ይህቺን አጭር ጥያቄ በትክክል መልሱ።

Horus
Senior Member+
Posts: 35629
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Horus » 26 Mar 2025, 21:06

Naga Tuma wrote:
26 Mar 2025, 17:48
ይህ ጥያቄ ለረጅም ግዜ ከእኔ ጋር ሰንብቷል።

ቀላል መልሱ ተናግሮ የማሳመን ችሎታ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ጠለቅ ስንል ነዉ መልሱ ከባድ የሚሆነዉ።

አንደበተ ርቱዕነት ባህሉ የሆነ ማህበረሰብ ሊኖር ይችላል?

መልሱ ኣዎ ከሆነ እንደዚህ ዐይነት ባህል ማካበት የሚቻለዉ እንዴት ነዉ? እንደዚህ ዐይነት ባህልን ማካበት ምን ያህል ዘመናትን ይወስዳል?

የኢትዮጵያን ስልጣኔ በጥልቅ እናዉቃለን የምትሉ ኢትዮጵያዊያን እስቲ ይህቺን አጭር ጥያቄ በትክክል መልሱ።
አንደበተ ርቱዕ ማለት ተናግሮ የሚያሳምን ማለት አይደለም ፤ አንደበተ እውነት ፣ እውነት ተናጋሪ genuine, authentic, truth speaker ማለት ነው። ለምሳሌ በግርዝና ሴራ (ጉርዝ ሽማግሌ) የሚተዳደሩት ጉራጌዎች በጎርደና፣ ጆካ፣ ጉርዳ የሚገዙት ሕዝቦች አንደበተ ርቱዕ በሆኑት ሽማግሎች (ባሊቆች) ቃል ነው የሚገዙት ምክኛቱም እነዚህ ባሊቆች አቀተኘ ስለሆኑ ። አቀተኘ አቅ (ሃቅ) ተናጋሪ ፣ አቅ ፈራጅ ማለት ነው። በፖለቲካ የሚገዙ ሕዝቦች ባብዛኛው በውሸት ነው የሚገዙትና የሚዳኙት ። አንድ ሰው ቃሉ ለምስክርነት ይበቃል ከተባለ አንደበተ ር ቱ ዕ ነው ። አንድ ቀን እንኳ ሲዋሽ የተገኘ ሰው በጉራጌ ባህል ለምስክርነት አይበቃል።

Abere
Senior Member
Posts: 13629
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Abere » 26 Mar 2025, 21:56

Naga Tuma
ጥያቄህን ሆረስ የመለሰልህ ይመስለኛል። ቀለል ባለ አማርኛ - ርቱዕ ማለት ቀጥ ያለ ትክክል ማለት ነው። ለምሳሌ አንድን ጽሁፍ ለማስተካከል እና ለማረም አርታዒ ይፈለጋል። ግድፈት ወይም ስህትተትን ማረም እንደ ማለት።

ፍትህ ወይም ርትዕ እንፈልጋለን ይባላል። ወይም አንድ ሰው በፍርድ ቤት ተከራክሮ ጉዳዩን [ረታ] ይባላል። ረታ (ረ'ተ'ዓ0 ማለት ሀቅኝነቱን አረጋገጠ ማለት።

በዚህ ዘመን ግን አንደበተ ርቱዕ ማለት ቱልቱላ ወሬ ውሸትም ቢሆን ተውሮ የሚሰራ ሊሆን ይችላል። ከአድርባይነት በመነጨ ምክንያት በአነጋገር ስህተትን እንደ እውነት ያሽሞነሙናል። It is called Political correctness. አፈ-ቅቤ ይባላል

Horus
Senior Member+
Posts: 35629
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Horus » 26 Mar 2025, 22:33

Abere wrote:
26 Mar 2025, 21:56
Naga Tuma
ጥያቄህን ሆረስ የመለሰልህ ይመስለኛል። ቀለል ባለ አማርኛ - ርቱዕ ማለት ቀጥ ያለ ትክክል ማለት ነው። ለምሳሌ አንድን ጽሁፍ ለማስተካከል እና ለማረም አርታዒ ይፈለጋል። ግድፈት ወይም ስህትተትን ማረም እንደ ማለት።

ፍትህ ወይም ርትዕ እንፈልጋለን ይባላል። ወይም አንድ ሰው በፍርድ ቤት ተከራክሮ ጉዳዩን [ረታ] ይባላል። ረታ (ረ'ተ'ዓ0 ማለት ሀቅኝነቱን አረጋገጠ ማለት።

በዚህ ዘመን ግን አንደበተ ርቱዕ ማለት ቱልቱላ ወሬ ውሸትም ቢሆን ተውሮ የሚሰራ ሊሆን ይችላል። ከአድርባይነት በመነጨ ምክንያት በአነጋገር ስህተትን እንደ እውነት ያሽሞነሙናል። It is called Political correctness. አፈ-ቅቤ ይባላል
አበረ፣
በትክክል፤ ቴክኒካል ሆንክ አትበለኝና ይህ ቃል ሳንስክሪት (በሂንዱ ቅዱስ ቋንቋ ወይን የህንዶች ግዕዝ) ተመሳሳይ ነው ። እነሱ ዕ አይከቱበትም 'ርት' ሲሉት በላቲን 'ራይት' (rith) ሲሆን ዛሬ right የሚባለው እንግሊዝኛ ነው ። Yes, justice & truth ፍትህና ርትዕ ይሏል። ሃቅ እንደ ወረደ ካረብኛው አንድ ነው። ለምሳሌ እምርታ ቆንጆ ቃል ነው ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6028
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Naga Tuma » 27 Mar 2025, 05:19

ሆረስ እና አበረ፥

ረታ በሚለዉ ቃል ተስማማን። እዉነት ሆነ ትክክል የሚረታ ነዉ።

ካልተሳሳትኩ አንደበት ስለ አነጋገር ነዉ። ስለ መርታት ችሎታ ነዉ። ስለ አነጋገር ዘዴ ነዉ።

ልጅ ሆኜ አከ ቦረናት ዱቢ ቤከ ሲባል ሰምቻለሁ።

እንደ ቦረና ሰዉ አነጋገር ይችላል ማለት ነዉ።

ከበርካታ ዓመታት በፊት የሚከተለዉ ቪድዮ ኣጋጥሞኝ ሰማሁት።

ሎሬት ፀጋዬ በአንደበተ ርቱዕነቱ ያስደነቀኝ ሰዉ ነዉ ያለዉን ስትሰሙ ምን ማለቱ ነዉ የገባችሁ?

እዚህ ዉስጥ ስለ ወል፣ ዉል (will) ያብራራል።

Abere
Senior Member
Posts: 13629
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Abere » 27 Mar 2025, 10:35

Naga Tuma,
I think you used the Poet Laureate, Tsegaye G/Medhin, in out of context. I am not sure poetic facts are in symmetry with broader facts, in history, geography, anthropology, etc. Poetry echoes more of rhetoric to rhythm with feeling of audience.
Establishing fact requires validating many historical findings and research.

Post Reply