Page 1 of 1
ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!
Posted: 04 Jan 2025, 13:34
by Horus
ትፈነዳለች! ትንቀጠቀጣለች! እስከስታ ትረግዳለች! አዳዲስ ወንዞችን፣ ተራሮችን ትወልዳለች! አሮጌውን ሰባብራ አዲሶቹን ታመጣለች! ፍጥረት እጹብ ድንቅ! ኢትዮጵያዊያንም እንዲያከብሯት እንዲፈሯት ታስተምራለች!! ይህ ትውልድ እድለኛ ነን! መሬት ፍጥረት ስንት ሚሊዮን አመት በፊት የሰራችውን መልሳ እያሳየችን ነው!! በኃያሏ ምድር ፊት የሰው ልጅ አቅም ኢምንት እንደ ሆነም ዘላለማዊ ዊዝደም እየሰጠችን ነው !! አግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃት
Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!
Posted: 04 Jan 2025, 13:42
by Abere
ቀን በበቅሎ ሌት በቆሎ የአዲስ አበባ ነገር የግሪምቢጥ። ፒያሳ በባዶው ውሃ ሲባክን ሲንቦጫራቅ ሲያይ አምሽቶ ማታ ቤት ሲገባ ሽንት ቤት የሚያጸዳበት (የሚያወርድበት) ውሃ አጥቶ ቤቱ ሲገማው ያድራል። የመታጠቢያ እና የመጸዳጃ ቤቱ ድርቆ የበሽታ ቋት የሚጠጣ ውሃ እጥረት በሽበሽ። ቅድሚያ የግል ንጽህና
Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!
Posted: 04 Jan 2025, 14:07
by Selam/
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ከምድራዊ ንዋይ አንቋላጮች፣ ከጣዖት አምላኪ ጭልፊቶች፣ ከግብዝ አረማውያኖች፣ ከስድ-አደግ ባለጌዎች፣ ከድሃ-ጠል ካድሬዎች፣ ከሆዳም ጎጠኞች፣ ከልበ-ደንዳና ጨካኞችና ከገዳዮች ይጠብቃት። የመዳን ክንፉን በተበደሉት፣ በተቸገሩትና በተጎዱት ላይ ይዘርጋ።
Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!
Posted: 04 Jan 2025, 14:12
by Horus
Abere wrote: ↑04 Jan 2025, 13:42
ቀን በበቅሎ ሌት በቆሎ የአዲስ አበባ ነገር የግሪምቢጥ። ፒያሳ በባዶው ውሃ ሲባክን ሲንቦጫራቅ ሲያይ አምሽቶ ማታ ቤት ሲገባ ሽንት ቤት የሚያጸዳበት (የሚያወርድበት) ውሃ አጥቶ ቤቱ ሲገማው ያድራል። የመታጠቢያ እና የመጸዳጃ ቤቱ ድርቆ የበሽታ ቋት የሚጠጣ ውሃ እጥረት በሽበሽ። ቅድሚያ የግል ንጽህና
አው ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው! አበሻ በአፉ ጤፍ ይቆላል ይባል የለ?!!
Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!
Posted: 04 Jan 2025, 14:18
by Abere
የብልጽግናው ካህናት በፏፏቴው ዳርቻ ሲታዩ አንድ ነገር አስታወሰኝ። በዚህ በሰሜን አሜሪካ በርካታ ቤተክርስቲያን በብልጽግና ቀሳውስት እየተወረሩ ነው የሚል በርካታ ቅሬታ ስለሰማሁ። በኮንዶምንየም፤በአፓርትመንት፤ወዘተ ጥቅማጥቅም የተገዙ በዲያስፓራ የተላኩትን ምዕምን እገሌ እኮ ብልጽግና ቄስ ነው የሚል ሃሜት ይሰማል። የiPhone እና iPad ቄሶችም ይሏቸዋል - Addis Ababa የብልጽግናው ሲኖዶስ የሚልካቸው ( በስራ ላይ ታጠናላችሁ) የተባሉ ናቸው ይባላል
Selam/ wrote: ↑04 Jan 2025, 14:07
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ከምድራዊ ንዋይ አንቋላጮች፣ ከጣዖት አምላኪ ጭልፊቶች፣ ከግብዝ አረማውያኖች፣ ከስድ-አደግ ባለጌዎች፣ ከድሃ-ጠል ካድሬዎች፣ ከሆዳም ጎጠኞች፣ ከልበ-ደንዳና ጨካኞችና ከገዳዮች ይጠብቃት። የመዳን ክንፉን በተበደሉት፣ በተቸገሩትና በተጎዱት ላይ ይዘርጋ።
Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!
Posted: 04 Jan 2025, 14:38
by Selam/