እንደዛሬም ስቄ አላውቅም
ፕሮፌሰር ተብዬው ጻድቁ ኢዮብ ትክክለኛው ስሙ ኢትዮብ (ኢትዮጵያ ) ነበር ይላሉ።
በመቀጠልም..........
- "...በኢትዮጵያ በተከታታይ እየተከሰተ የሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ በሚቀጥሉት አስር አመታት ምስራቅ አፍሪካን ለሁለት ከፍሎ ኢትዮጵያን በሁለት በኩል የውቅያኖስ ባለቤት ያደርጋታል። የመሬት መንቀጥቀጥና እሱን ተከትሎ በሚከሰተው ንዝረት ደግሞ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኘው አትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ የቀድሞ መጠሪያው “የኢትዮጵያ ውቅያኖስ ” ተቀይሮ እናያለን።"
"...በአሜሪካ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ እና የአውሎ ነፋስ አደጋዎች የቅጣት ነው። በኢትዮጵያ ግን ለምርቃት ነው።"
"...የዛሬ አስራ ሁለት ሺህ አመታት አከባቢ አሁን ካለነው ስልጣኔ የበለጠ የሰለጠንን ነበርን። በዛን ጊዜ አውሮፕላን፣ ድሮን፣ ሮኬት፣ የጨረር መሳሪያ (Laser Weapons)፣ ሲነማ፣ ፍሪጅ፣ ወዘተ ነበረን።🛸
"...አፋር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሳለች። አፍሪስካውያን እያለ ይጠራቸዋል። አፍሪካ የሚለው ስምም አፋር ከሚለው የመጣ ነው። የአሰብ እውነተኛ ስሙ ተርሴስ ነው። የቅዱስ ኢዮብ ልጆች ፣ አስር ወንዶች ከነሚስቶቻቸው ኢትዮጵያ ጋር መጥተው ከአፋሮች ነው የተደበለላለቁት። ኢትዮጵያን የመጡበት ምክንያት ደግሞ ኢዮብ (ኢትዮብ ) ኢትዮጵያ ከሚለው ስም የመጣ ስለሆነ ነው።
ሊበሏት የፈለጉ አሞራ ጅግራ ይሏታል ይመስላል ነገሩ። ቂቂቂቂቂቂቂቂ









