Horus the Gurage Calls for a Christian Crusade on Somalia
Posted: 02 Jul 2024, 21:27
This is very interesting. I was for a while researching the motives of this man. Goes to show a strong crusader element. Somalia and Muslims need to know this INFO. A Jihad to liberate the Muslim people of Ethiopia should be considered.
His topic was titled አዲሱ የኦቶማን ኢምፓየር ፤ አቢይ አህመድ የአጼ ልብነ ድንግልን ድክመት እንዳይደግም
Re: አዲሱ የኦቶማን ኢምፓየር ፤ አቢይ አህመድ የአጼ ልብነ ድንግልን ድክመት እንዳይደግም
His topic was titled አዲሱ የኦቶማን ኢምፓየር ፤ አቢይ አህመድ የአጼ ልብነ ድንግልን ድክመት እንዳይደግም
Re: አዲሱ የኦቶማን ኢምፓየር ፤ አቢይ አህመድ የአጼ ልብነ ድንግልን ድክመት እንዳይደግም
Horus wrote: ↑02 Jul 2024, 13:39የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የ1520ዎቹ አገራችን አይደለችም። 17 አመታት በፈጀው የኦቶማን ኢምፓየር ፕሮክሲ የግራኝ ወረራ ግራኝ የተሸነፈው በመጀመሪያው የባደቄ (የሞጆ) ወንዝ ጦርነት ብቻ ነው። ያሸነፉትም ቀስተኞቹ አመያዎች ናቸው ። ከዚያ በኋላ የብርቱካን (የፖርቹጋል) ክርስቲያን ጦር እርዳታ እስከ መጣ ድረስ ግራኝ ቤተ ክርስቲያን እና በጻሕፍቷን አቃጥሎ ለ1000 አመታት ያከማቸችውን የወርቅ መስቀሎች ከመላ ኢትዮጵያ ለ17 አመት ዘረፈ ። ታሪክ በውል እንደ ዘገበው ልብነ ድንግል እጅግ ደካማ ንጉስ ነበር።
ዛሬ ቱርክ በተመሳሳይ በመላ አፍሪካ ተስፋፍታ አዲሱን ኦቶማን ኢምፓየር ለመገምባት አምርራ እየሰራች ነው ። ባፍሪካ ውስጥ ሱማሊያ የተባልቸው ፍርስራሽ አገር የቱርክ ቅኝ ግዛት ነች ቢባል ማጋነን አይሆንም ። ቱርክ የፖለቲካ ጥቅም የላትም ። የቱርክ አላማ ሃብትና ሃብት ብቻ ነው ። ይህን ለማሳካት የምትጠቀመው ደሞ ፖለቲካ ወይም ዲፕሎማሲ አይደለም፣ የጦር ኃይል ነው ።
አሁን ላይ ባፍሪካ ቀንድ ተፋጠው ያሉት የአረብ ኤምሬቶች ባንድ በኩልና ቱርክና ቀጥር በሌላ በኩል ነው። ቱርክ የሶማሊያን ወደቦች ይዛ የኢትዮጵያን ንግድ መቆጣጠር ነው አላማዋ። ኢምሬት የበርበራ ወደብ ይዘው ከወዲሁ 30% የኢትዮጵያ ንግድ ተቆጣጥረዋል ። ኢምሬት ኢትዮጵያ በነሱ ላይ ጥገኛ እንድትሆን ነው የሚፈልጉት ። ቱርክ በነሱ ላይ ጥገኛ እንድንሆን ነው የሚፈልጉት ።
በእኔ እምነት ኢትዮጵያ የባህር ኃይል እንዳይኖራት ከሚፈልጉት አገሮች ቁጥር አንዷ ቱርክ ነች ። አቢይም ሆነ አጽቀ ስላሴ በምንም አይነት ቱርክን ማመን፣ የቱርክን ምክር መስማት የለባቸውም።
ሶማሌላንድ በውድም ሆነ በግድ ፤ በኢትዮጵያ ታወቀችም አልታወቀች ነጻ አገር መሆኑዋ ሳይታለም የተፈታ ነው ። ዞሮ ዞሮ ቱርክም ከሱማሌላንድ ሬፑብሊክ ጋር ውል ፈጥራ የነሱን ባህር ለመቆጣጠር መሥራቷ አይቀሬ ነው ። ስለዚህ የኢትዮጵያ ፍኖተ ተግባር መሆን ያለበት የሚከተለው ነው ።
እሺ ካሉ ከቱርክ ጋር የባህር ኃይላችንን በመገንባቱ ፓርትነር ሆነው የሶማሌላንንም ነጻነት እንዲደግፉ ማድረግ ። ይህ ለ4ቱም አገሮች ሶማሊያ፣ ሶማሌላ አገር፣ ኢትዮጵያና ቱርክ ዊን ዊን ፖሊሲ ነው ። በዚህ የማይመቻት አረብ ኢሚሬት ቢሆንም ኢሚሬት ወታደራዊ ኃይል የላቸውም ፤ እንዲያም ከቱርክ ጋርም ያላቸው ዝምድና በጣም እያደገ ስለሆነ የኢምሬት ትቅምም ማስገባት ይቻላል።
ይህ ካልሆነና አቢይና አጽቀ ስላሴ በቱርክ ተታልለው ከሱማሌላንድ ውል ወደ ኋላ ካፈገፈጉ ኢትዮጵያ ወደ ፊት በፍጹም የባህር ኃይል አይኖራትም ፣ ቤዝ አይኖራትም። ሶማሌላንድ የጦር ቤዝ የሰጠችን በአንድና አንድ ጥቅም ብቻ ነው ፤ የአገርነት እውቅና ለማግኘት ።
ስለሆነም ቱርኮች ኤም ኦ ዩውን እንዲዘገይ ፣ እንዲደናቀፍና ፣ እንዲከስም ካደረጉ ሶማሌላንድ አንድም በኢትዮጵያ ያላት እምነት ያከትማል ፤ ሌላም አዲስ አገር እውቅና ከሰጣት በኋላ በፍጹም የጦር ቤዝ ለኢትዮጵያ አትሰጥም ! ስለዚህ እነአጽቀ ስላሴ ከፍተኛ በቱርክ የመታለል አደጋ ላይ ይገኛሉ።
ይልቁንም ኢትዮጵያ በጀመረችው ድፍረት ቀጥላበት የሶማሌላንድ ውልን ባስቸኳይ መፈረምና ከዚያ በኋላ የዲፕሎማሲ ጨዋታ ማጧጧፍ ነው ያለባት ። ለምን ቢባል ...
ነገ ኢትዮጵያ በሉዋያ ጦር ሰፈር ብታቆም ቱርክ የመታደር ኃይል አምጥቶ መላ ሱማሌን የመጠበቅ አላማም ፍላጎትም የለውም ። ዞሮ ዞሮ ከአል ሻባብና አይሲስ ጋር የማያባራ ጦርነት ውስጥ እንደ ሚገባ ስለሚያውቅና ደሞም ከኢትዮጵያ ጋር ተቆራርጦ ባፍሪካም ያለውን ተጽኖ ማጣት ስለማይፈልግ ቱርክ በጭራሽ የራሱን ቬትናም ባፍሪካ ቀንድ እንዲኖረው አይፈልግም ። የቱርክ ፍላጎት ገንዘብ ነው።፣
የኢትዮጵያ እድል ግን አሁን ክሪቲካል ነጥብ ላይ ይገኛል።
(ስለ ታይፕ ግድፈት ይቅርታ)