ካልተሳሳትኩ አቶ ኣንዳርጋቸዉ ኢትዮጵያዊያን ነፃነት ነፃነት ማለትን ያበዙበት ግዜ ነዉ ትግል የጀመረዉ።
በእኔ ግምት በዚህ ግዜ ኢትዮጵያ ከዛ ነፃነት ነፃነት ኣዙሪት ወጥታለች።
ሌላ ግምቴ በዚህ ግዜ ኢትዮጵያን ይዟት ያለዉ የዚህ የሰዉ ጎሳ፣ የዛ የሰዉ ጎሳ ኣዙሪት ነዉ።
ከዚህም ኣዙሪት የምያወጣት ዕዉቀት ነዉ።
በኣጋጣሚ እዚህ ፎረም ላይ አቶ ኣንዳርጋቸዉ ኣንድ ስለ ጎሳ የሰጠ ማብራርያ ከሰማሁዋቸዉ ሁሉ የላቀ ነዉ። እኔ እንደገባኝ ነዉ እሱ ያብራራዉ።
አማርኛ ተናጋሪ፣ ኦሮምኛ ተናጋሪ፣ ትግርኛ ተናጋሪ፣ ጉራግኛ ተናጋሪ፣ ወዘተ ኢትዮጵያዊ ስንል ያለምክንያት ኣይዴለም።
ዕዉቀት ይህን ኣበጥሮ ስያብራራ ሁላችንም የተለያዩ የኢርዮጵያ ቋንቋዎችን መናገር የምንችል ኢትዮጵያዊዎች እንሆናለን።
በዕዉቀት መስክ እርግማንም ሆነ ተዓምር ትርጉም ዬላቸዉም።
ስህተት እርግማን ኣይዴለም። በዕዉቀት ይታረማል። የሙሴን ስህተት ስግመንድ ፍሪዩድ ኣርሞታል። ከሶስት ሺህ ዓመታት በኋላ።
ኣንድ ስህተትን ኣንድ ሺህ ግዜ ደጋጎም ከመናገር ኣንድ እዉነትን ኣንዴ መናገር ይበልጣል።
ጠቃሚ ሊሆኑ የምችሉ ሁለት የማልረሳቸዉ የስራ ልምዶች ኣሉኝ።
ኣንዱ ከእንግሊዛዊ ጋር ነዉ። ስህተትን ኣንድ በኣንድ እንዴት እንደምያበጥር ያዉቃል። ስህተት ቢቀመጡበት በኖ እንደማይጠፋ ያዉቃል። በእኔ ግምት ለእራሱ ገቢ ጥቅም ስህተት ላይ እንዴት እንደምያዘግም ያዉቃል። ኣንድ ግዜ ስብሰባ ዉስጥ ሌሎች ያላጤኑት ስህተት እንዲታረም እኔ ስናገር እሱ ወደ እኔ ዞሮ ዓይኖቹ የአዉሬ ዓይኖች መስለዉ ኣዩኝ። የሰዉ ዓይኖች እንደዛ ሲሆኑ ከዛ በፊት ኣይቼ ኣላዉቅም። ካዛ በኋላም ኣይቼ ኣላዉቅም።
ይህ ስህተትን ማረም ምን ያህል ቁልፍ እንደሆነ ምሳሌ እንዲሆን ነዉ።
ሁለተኛዉ መሠረቱ የቻይና ሰዉ ነዉ። ሲናገር ቃላት ከአፉ እስኪወጡ ያስጠብቃል። መጀመርያ ላይ የመናገር ድክመት ይመስለኝ ነበር። ቆይቼ ያስተዋልኩኝ ስህተት ከአፉ እንዳይወጣ የሚጠነቀቅ መሆኑን ነዉ።
ስህተት ከአፍ ሳይወጣ ተጠንቅቆ መናገር ችሎታን የት እንደተማረ ኣላዉቅም።
የእኛ የኢትቶጵያዊያን አነጋገር በኣብዛኛዉ ባህላዊ ነዉ። እዉነት ነዉ ብለን የምንገምተዉን እዉነት እንደሆነ እንናገራለን። ለዚህም ነዉ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ይህ እርግማን ነዉ፣ ይህ ተዓምር ነዉ ማለት በቀላሉ የሚመጣላቸዉ።
የቻይና ቋንቋን ባላዉቅም ቻይናዎች እርስ በእርሳችዉ ሲነጋገሩ ስሰማ የእነሱም ባህላዊ ይመስለኛል። በፍጥነት ይነጋገራሉ።
ስህተት ከአፍ ሳይወጣ በፍጥነት መናገር ትልቅ ችሎታ ነዉ። ፍጥነት ዉስጥ ስህተቶች የሚወረወሩ ከሆነ ስህተት እየበዛ ይሄዳል።
አላማችን ስህተትን እየቀነሱ መሄድ ሲሆን ኣዙሪት ዉስጥ ኣንገባም። ካለንበት ኣዙሪት እንወጣለን እንጂ።
ብዙ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ለማዳመጥ ግዜ ያጥረኛል። ሲሳይ አጌና ካጋጠመኝ እና ግዜ ካለኝ ሳዳምጠዉ ስህተት ከአፉ ሳይወጣ ኣስቦ የመናገር ትልቅ ዝንባሌ ያለዉ ይመስለኛል።
የዛ አይነት ዝንባሌ እየለመለመ ሲሄድ ከኣዙሪት ያላቅቀነል።
በመጨረሻም ብዙዎቻችን ኢጎ ወይም ከማን ኣንሼ የምያጠቃን ይመስለኛል። ከማን ኣንሼን ዉልቅ ኣድርገን ከማን በልጬን ጥልቅ ብናደርግ ስርዓትን ከሁላችንም በላይ ማድረግን የበለጠ እየተለማመድን እንሄዳለን። ኣዙሪት ዉስጥ ኣንገባም። ኣዙሪት ዉስጥ ካለን ስርዓት ከዛ ዉስጥ ያወጣናል።
ይህ ለወቀሳ ሳይሆን ጥቅም ያለዉ ከሆነ ያለኝን ሀሳብ እና ልምድ ለማካፈል ነዉ።