Horus wrote: ↑14 Jan 2024, 16:12
ዲዲቲ፣
እኔ የነዚህ ባለግዜ ወራሪዎችን ሆያ ሆዬ አልከታተልም ። ሁሉም የስልጣና ገንዘብ ሩጫ ነው ። ጉራጌ መሬት የረገጠ የረጋ ሕዝብ ነው ። በዙሪያችን ያሉ ጉራጌ ኦሮሞ ክልሶች ሁሉ (ብዙ ናቸው ከግቤ ዳር እስከ አዋሽ እስከ ዝዋይ መቂ ጉራጌ ኦሮሞ ቅይጦች ናቸው ። በኅይለ ስላሴ ዘመን ሁሉም ጉራጌ ነን ይሉ ነበር ፤ ዛሬ ኦሮሞ ስልጣን ያዘ ሲባል ኦሮሞ ነን ብለዋል። ጉራጌ እንደዚህ ላለ የማነነት ነውጥ ክብር አይሰጥም ፣ ጉራጌ እንዲሆኑም አይለማመጥም ። ጉራጌ በመንግስት ድጋፍና ክራይ ሰብሳቢነት የሚኖር ሕዝብ ስላልሆነ !
አቢይ ደንዲን ያላሳየበት ምክኛት ምን እንደ ሆነ አላቅም ። ወንጪ ውስጥ እራሱ የሕዝቡ ብቸኛ መኖሪያ የሆነውን የእንሰት ተክል ማሳየት የጀመሩት አሁን ነው ። ያን ማድረግ ክልክል ነበር ። ያው ሁሉም ኬኛ የሚለው የካልቸር አልባ፣ የታሪክ አልባ ፣ ግንድ የሌለው ሰው በሽታ ነው። ስለዚህ ሕዝብቹ እራሳቸው ምን እንደሆኑ እስከ ሚጠይቁ ድረስ ሁሉም ያሻውን ማለት መፈብረክ ይችላል።
ሆረስ፥
ቀላል ጥያቄ። ኬኘ እና የኛ መሠረታቸዉ ኣንድ የሆነ ቃላት ኣይዴሉም?
ኬር እያልክ ኼረ ማወቅህን ወይም ኣለማወቅህን እስከዛሬ ኣላዉቅም።
ዳግማዊ ምኒልክን እያወደስክ መሪነታቸዉን በተቀበሉት እና ባልተቀበሉት ክርክር ዉስጥ ገብተህ ትከራከራለህ።
ለምን በዚህ ክርክር ዉስጥ ትገባለህ ኣልልም። ማለትም ኣልችልም። የእኔ ጥያቄ ዉዳሴህም ይሁን ወቀሳህ ሚዘናዊ ነዉ ወይ ነዉ።
የምትፈልገዉን ኣታዉቅም ተብለህ በኢትዮጵያ የዉስጥ ፖለትካ ዉስጥ በፖለትካ ኣዳሪነት የምትዋዥቅ ይመስላል።
ስህተት ከሆነ የሚከተለዉን ግምገማ እንደ ምሑርነትህ ገምግመህ ስህተት ነዉ ማለት ትችላላህ? ኣንተም ሚዘናዊ ያልሆነ የኣንዱ የኢትዮጵያ ጎሳ ኣወዳሽ፣ የሌሎች ጎሳዎች ወቃሽ ሳትሆን።
ስህተትን መልሶ መላልሶ ማንበብ ይሰለቻል። ስህተትን መልሶ መላልሶ ስህተት ነዉ ማለት ይሰለቻል። አዋቂን ስህተቱን ኣንዴ መንገር በቂ ነዉ።
ዳግማዊ ምኒልክ በአደዋ ዋዜማ ማዕከላዊነትን ያስፈፉ ግዜ ኣብረዉ የቆሙ እና የተቃወሙ የኢትዮጵያ ጎሳዎች ነበሩ። ኣብረዉ የቆሙም ሆነ የተቃወሙ ለምን ተቃወሙ ወይም ኣልተቃወሙም የሚል ክርክር እዚህ ኣላነሳም። ታሪክ ያበጥረዉ።
የእኔ ቀላል ጥያቄ የሸዋ ገበሬዎች እና የወለጋ ገበሬዎች ኣብረዉ መቆምም ሆነ መቃወም ኣንድ ሚዛን ላይ ሲደረግ ምን ልዩነት ነበረዉ ነዉ።
ለዚህች ቀላል ጥያቄ የተዛባ መልስን ነዉ የማነበዉ። አስተያየቱን ሳነብ ከልተሳሳትኩ ኦቦ ሌንጮ ለታ የተዛባ አስተታየት ከሚጽፉት ኣንዱ ነዉ። ኣብረዉ የቆሙትን የሸዋ ገበሬዎች ላይ ስሞታ ማሰማት ብቻ ሳይሆን ታሪካቸዉን ለማጉደፍ የለፋ እና የሚለፋ ይመስለኛል። የወለጋ ገበሬዎችም ከሸዋ ገበሬዎች ባልተናነሰ ሁኔታ በአድዋ ዋዜማ ከዳግማዊ ምንልክ ጋር ኣብረዉ የቆሙ ከሆነ ሁሉም በኣንድ ሚዛን ላይ ኣለማድረግ ስህተት ነዉ።
ሁሉንም በኣንድ ሚዛን ላይ ኣድርጌ ወይ ተመሳሳይ ነበሩ ወይም የዚህኛዉ አከባቢካዛኛዉ አከባቢ በመተባበርም ይሁን በመቃወም ልዩነት ነበራቸዉ ብሎ በግልጽ ማሳመን ከቻለ ከእኔ የማንበብ ችሎታ ማነስ ነዉ ብዬ ይቅርታ እጠይቃለሁ።
ትግልን በወጣትነት ዕድሜዉ ጀምሮ የኢትዮጵያ የዉስጥ ዉጥንቅጥ ዘመን የተረፈ ነዉ። በዛ ዘመን ትግል ሽርሽር እንዳልነበረ እገምታለሁ።
ቢሆንም ስህተት ላይ ስህተት ላለመጨመር ጋዜጠኛዋ ቤቲ ይህቺን ቀለል ጥያቄ ልትጠይቀዉ ትችላለች።
እኔ የማነበዉ ስህተት እና ትዝብት መሠረት የሚከተለዉ ግምገማ ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ምኒልክ ማለት የተጀመረዉ መሃል ኢትዮጵያ ሳይሆን ሰሜን ኢትዮጵያ ነዉ።
ክርስትና መቀበል እና ያልተቀበለዉን መዝለፍ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ የተጀመረ ኣልነበረም። የሮሙ ካቶሊኮች ያልተቀበሉትን ያራሳቸዉን ሕዝብ ፓጋን እያሉ ሲዘልፉ ኖረዋል።
ዳግማዊ ምኒልክ በታሪክ አጭር በሚባል ግዜ ዉስጥ ነዉ በአድዋ ዋዜማ ሃገርን የበለጠ ኣደራጅተዉ ያዘጋጁት።
እ አ አ በ1896 ዋራሪን ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ኣሸንፈዉ በሰባት አጭር ዓመታት ዉስጥ ነበር እዚህ ኣሜሪካ በሰዉ ልጅ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ አይሮፕላን ከመሬት ተነስቶ ሰሜን ካሮላይና ዉስጥ ድያብሎስን ግደል ጋራዎች በተባሉ ዙርያ የተሽከረከረዉ።
ኣይሮፕላን ለመጀመርያ ግዜ እዚህ ኣሜሪካ ዉስጥ ተሽከርክሮ ስድስት አጭር ዓመታት ሳይሞላ ነዉ የአሜሪካ የዲፕሎማሲ ልኡክ አዲስ አበባ የገባዉ።
ይህን ታሪክ እኔ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ነዉ ያነበብክኝ። ይህን ሁሉ ሳናዉቅ እኔን ጨምሮ ዳግማዊ ምኒልክን በተለያየ ደረጃ ወቅሰናል።
ስንቶቻችን የአሜሪካ ኤምባሲ የደረስን ይህን ሁሉ ታሪክ ኣዉቀን ኣይመስለኝም።
ከወጣትነቴ ጀምሮ የሰላሌዉ ራስ ጎበና፣ የወንጪዉ ፊታዉራሪ ሀብተግዮርጊስ፣ የነቀምቴዉ ደጃዝማች ኩምሳ ሞሮዳ፣ የደምቢ ዶሎዉ ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ፣ የቤኒሻንጉል ንጉስ ሸጎሌ በተመሳሳይ ሁኔታ የተከበሩ የሃገር አመር አካሎች ነበሩ።
የኣሁን ጥያቄዬ በምን ምክንያት ነዉ ራስ ጎበና እና ደጃዝማች ኩምሳ ሞሮዳ ኣንድ ሚዛን ላይ የማይቀመጡት? በምን ሚዛን ነዉ ፊታዉራሪ ሀብተግዮርጊስ እና ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ ኣንድ ሚዛን ላይ ያማይቀመጡት?
ዳግማዊ ምኒልክ በአደዋ ዋዜማ ሃገርን ስያደራጁ በነበራቸዉ መተባበር ወይም መቃወም ልዩነት ነዉ?
የቋንቋ እና የሀይማኖት ተፅእኖ መቀበል እና ኣለመቀበል ችሎታ ተመዝኖ ነዉ?
ኦቦ ዳጬ ልጁን ጎበና ሲል ኦቦ ለታ የሮሙ ካቶሊክ ኣማጺ ልጅ ሃይማኖትን ከአድዋ በኋላ ተቀብሎ ነዉ ልጆቹን ዮሓንስ እና ኣብረሃም ያለዉ።
ባህል ቢባል ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እ ኢ አ በ1964 ነዉ ቦረና ድረስ ሄዶ ለካ ኣንተ ነህ ብሎ የኢትዮጵያ ታሪክ ሆሊ ግሬይል መባል የሚችልን ያስቀመጠዉ።
ትግል ቢባል ሌንጮ ለታ በወጣትነቱ የትግል ሜዳ ሄዶ የራሱን ወታደሮች መምራት የቻለ ይመስለኛል።
ቀድሜ ቆርጬ ነዉ የትግል ሜዳ የደረስኩኝ እንዳይል ኣንድ ግዜ የሰማሁኝ አፈ ታሪክ እዉነት ከሆነ እራሱን ደመቅሳ ያለዉ በዾ ደቻሳ ከባሮ ቱምሳ ጋር የነበረዉ ጸብ በዾ ቆርጠን ወደ ትግል ሜዳ እንሂድ ሲል ባሮ እምቢ ብሎ ቀርቶ የከተማ ዉስጥ ትግል ሲጠነክር ተከትሎ ደርሶ ልምራችሁ ሲል ትላንት እምቢ ብለህ ቀርተህ ዛሬ ተከትለህ መጥተህ ልምራ ትላለህ ወይ ነዉ። ካልተሳሳትኩ ሌንጮ ከባሮ ጋር ተከትሎ የደረሰ ነዉ።
የራሱን ወታደሮች ለመምራት በቂ ግዜ ኣልነበረኝም እንዳይል ደጃዝማች ገረሱ ዹኪ፣ ጃገማ ኬሎ የጣልያን ወረራ ግዜ ከነበራቸዉ ግዜ የበለጠ ነበረዉ። እነሱ በዛ ግዜ የነበራቸዉን ገድል እና የሌንጮ ለታን የትግል ሜዳ ገድሎችን ማወዳደር ያስቸግረኛል። ስለማለዉቅ።
እ አ አ በ1991 የሎንደን ኮንፍረንስ ብዛት ያላቸዉን ጎሳዎች እወክላለሁ ብሎ በቁጥር የምያንሱትን ጎሳዎች የወከሉት የእሳያስ እና መለስ ታናሽ ሆኖ ነዉ የተገኘዉ።
ምናልባትም ዳግማዊ ምንልክን እየኮነነ ቀዳማዊ ምኒልክን የልኮነኑት ታናሽ ታጋይ ሆኖ ይሆናል እዛ የተገኘዉ።
በዛ ስብሰባ ላይ እዛም እዚህም ከኢትዮጵያ ነፃነት ነፃነት ነፃነት ሲባል ኣብሬ የኢትዮጵያ መንግስት ዉስጥ ሰርቼ ነበረ ካለዉ ኢትዮጵያን ወክሎ ከተገኘዉ ተስፋዬ ድንቃ ጋር ነዉ የተገናኘዉ።
ኣንዱ በእንግሊዘኛ መናገርን ሳያመነታ ሌላዉ በኣማርኛ መናገርን ሰያመነታ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ። ከእንግሊዘኛ እና ኣማርኛ ለአፋን ኦሮሞ የቱ ይቀርባል ቢባል ያለምንም ጥርጥር ኣማርኛ ነዉ።
ቢሆንም በእንግሊዘኛ መናገር እና መጻፍ በኣማርኛ ከመናገር እና መጻፍ የቀናበት ዘመንም ነበር።
ኣንዳንዴ የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ናደዉ ደርሶ ይደረምሳልን ሰምቶ ከደርግ በኋላ ወደ ከተማ ተመልሶ ከእሱ በፊት የነበረዉን የራሴ ሕዝብ የሚለዉን ታሪክ መደርመስ ገባ ወይ ብዬ እራሴን እጠይለሁ።
ከኣድዋ ማግስት ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ የዉስጥ የዉጥንቅጥ ዘመን ብዙ ስህተት ተሰርቷል። በኣጼ ሀይለስላሴ ግዜ ኢትዮጵያ ትቅደምን የወረሰዉ ደርግ የሃገር አመራር ልምድ በኣንድ ቀን እንዲዳሽቅ አድርጎ ቡቃያ ኣእምሮች ተሰዉተዋል።
ኢትዮጵያ ትቅደም ከተባለ በኋላ እዛም እዚህም ነፃነት ማለት በዝቶ ነበር። ካዛም ኢትዮጵያ በእኩልነት ትነሳ እየተሰማ ነዉ።
ይህ ሁሉ ትግል ሽርሽር እንዳልሆነ እየታወቀ ነዉ።
ቢሆንም በአድዋ ዋዜማ ከዳግማዊ ምኒልክ ጋር መተባበርም ሆነ ኣለመተባበር ሚዘናዊ ካልሆነ ምንድነዉ? ድንቁርና፣ መሃይምነት፣ ወይስ በሽታ?
ድንቁርና ቢቀመጡበት በኖ ኣይጠፋም።
የታሪክም ሆነ የወደፊት ሚዘናዊነት ለምን ይዛባል?