Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42927
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Horus » 15 Apr 2022, 01:17

ይህ የእኔ እይታ ነው ። ለምንድን ነው የሪጂሙ ድጋፍ መሰረት የብልጽግና ፓርቲ ሳይሆን ሚሊተሪውና ሴኩሪቲው ሆነዋል ያልኩት?

ዛሬ ለጄኔራል መኮንኖች የሰጠው ስልጠና ብዙ ነገሮችን ያዘለ ነው ።

የመጀመሪያው አቢይ ስለ ሲቪል ሚሊታሪ ግንኙነት ያቀረበው ሞዴል ነው ። በአንድ አገር መንግስት ተዋቀር ውስጥ የሲቪሉ ፖለቲካ ክንፍና የሚሊታሪው ክንፍ ያላቸው ትስስር እና ስልጣን አከፋፈል የሚወስንበት ሞዴል አለ (በፖለቲካ ቲኦሪ ውስጥ)። ሶስቱን አቢይ ጠቅሷቸዋል ።

አንዱ ሞዴል ሚሊታሪው ፍጹም ፕሮፌሽናል ተቋም ስለሆነ የአባላቱ ምልመላና ስብጥር ውስጥ የፖለቲካ (የጎሳ) ስሌት አያገባውም የሚል ነው።

ሌላው ሞዴል ሚሊታሪው ልክ እንደ ብልጽግና ፓርቲ በጎሳ ስሌት መሰረት በማዋቀር ሚሊታሪው የፓርቲው መሳሪያ የሚያደርግ ሞዴል ነው ። አቢይ እነዚህን ሁለት ሞዴል ይቃወማል።

ሶስተኛው ሞዴል አሁን ያለው ያቢይ ሞዴል እሱ ፕሉራሊስት ሞዴል ይለዋል። በዚህ ሞዴል መሰረት የሚሊታሪው ምልመላ ተዋጽኦ የጎሳ ውክልና ታሳቢ ያደረገ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ከብልጽግና ነጻ የሆነ፣ የብልጽግና ታዛዥ ያልሆነ ሚቲታሪ ነው እይተገነባ ያለው ።

ይህ ትልቅ ትልቅ ቁም ነገር ነው።

አቢይ በብልጽግና ፓርቲ ላይ እምነት ቢኖረው ኖሮ፣ ያቢይ ስልጣን መሰረት ብልጽግና ቢሆን ኖሮ አርሚው ለፓለቲካው ፓርቲ ታዛዥና ሚሊታሪው ለፖለቲካ እንዲገዛ ያደርግ ነበር። ያ ያልሆነበት ምክኛት የጎሳ ካድሬዎች በጎሳ ተከፋፍለው መንግስት ማቆም አይደለም፣ መንግስት መምራት የማይችል የጎሳ ጥርቃሞ እንደሆነ አቢይ ያምናል። ስለሆነም ሌቦች ነው የሚላቸው። ከዚህ በታች ባለው ቪዲዮ ውስጥ አቢይ በግልጽ ብልጽግና በምንም አይነት ወደ ሚሊታሪው እንዳይደርሱ ሲል ጀነራሎቹን ትዕዛዝ ይሰጣል።

የዚህ ሁሉ ውጤት ምን እንደ ሚሆን መገመት ይቻላል።

አንደኛ ከዚህ በኋላ የአቢይ ስልጣን መሰረት የሚሆነው ሚሊታሪው እንጂ የኦሮሞ ወይም የአማራ ጎሳ ካድሬዎች አይሆኑም። ይህ ብቻ አይደለም። የትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ ወይም ሌላ የጎሳ ጦር ተነስቶ አቢይን ለማውረድ ቢሞክር በፌዴራል ሚሊታሪው ይመታል።

በሌላ በኩል ሚሊታሪው እራሱ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ እንዳያስብ ሚሊታሪው በጎሳ ስሌት ስለቆመ መፈንቅል ማድረግ የሚችል አንድነት ሊኖረው አይችልም ።

ስለዚህ በእኔ እምነት የሚሊታሪው ተጽዕኖ እያደገ ይመጣል፤ የአቢይ ዋና ደጋፊ ሃይል ሚሊታሪው ከሆነ የክልሎችና የብልጽኛ ተጽዕኖ እየቀነሰ ይሄዳል ። ለዚህ ነው አቢይ እራሱ ብልጽግና የሌቦች ድርጅት ነው የሚለው።

ከዚህ መደምደሚያ የሚነሳው አዲስ ጥያቄ አቢይ አህመድ በሚሊታሪው ተደግፎ ወደ አምባገነን መሪነት ያዘምም ይሆን ወይ የሚለው ነው?

Last edited by Horus on 15 Apr 2022, 02:32, edited 3 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42927
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Horus » 15 Apr 2022, 01:53

Actually, Abiy Ahmed's assertion that there are only three models of civil-military relations in existence is inaccurate. There are four types of civil-military relations in the present world. They are called ....
(1) Societal model
(2) Organizational Model
(3) Corporatist Model
(4) Personalist Model

The Societal model of a military is where the structure and composition of the military resembles that of the society. The military reflects the class and ethnic structures of the society. This is the model Abiy chose to use. But this kind of military composition is open to persistent politicization of the military. In other words, there is no guarantee that Abiy's new military would stay out of Ethiopian ethnic politics.

The organizational model is what known as professional military such as the US military

Corporatist military model is what we see in Sudan and Egypt to some degree. Corporatist military like a corporation has its own interest and its behavior driven by its interests including owning its own business etc.

Personalist military model is to be found in some African countries where the military is identified with a particular individual general or commander and the military behaves as if it is a private army of the influential general.

Each of these civil-military relational models are associated with their own types of political regime and particular type of military coup. For example, the recent Coup in Mali was a societal model military coup. The Derg coup was a classic societal military coup.

For example, if Abiy uses a military coup to get rid of PP party and decide to rule by decree, it would a combination of Societal and Organizational military coup. I will not go into its description.
Last edited by Horus on 15 Apr 2022, 02:40, edited 1 time in total.


Horus
Senior Member+
Posts: 42927
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Horus » 15 Apr 2022, 02:34

TGAA wrote:
15 Apr 2022, 02:30
You are creating a dichotomy where it doesn't exist.
How?

Right
Member
Posts: 4866
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Right » 15 Apr 2022, 05:10

Full of crap.
First of all, Abiye created PP but no body else. In his own world Abiye a narcissist self imitates Col. Menigstu (worker party) & Melese Z(EPDRF) and try to present himself as a smarter version by creating an ethnically composed version of EPDRF 2 AKA pP party.
On its inception, although PP members were loyalists and die hard supporters due to his weak and incompetent leadership he lost his own baby.
And now on the military. Through out its history Ethiopia never had such a weak and disorganized military. The Northern part of Ethiopia is still occupied by Sudan. Imagine if any of past Ethiopian leaders allowing this to happen. And then his incompetent Generals can’t even win a civil war against a TPLF. TPLF still control party of Afar and Amhara land. And it is preparing for a major offensive in the coming rainy season. I am talking about ENDF, since Ethiopia has several independent military organized at the killing level.
If you can’t control a political party of your own creation how can you control an incompetent and useless group of military leaders. Just like the general public, soldiers don’t respect weak and incompetent leaders. Just ask members of ENDF from soldiers, low ranking officers to high ranking officers what they think of about “Field Marshall” Berhanu Jula’s appt and the first thing you will get is sarcastic laugh. The military is not a good place to be a political refugee for a leader like Abiye. Remember at the beginning we said to Abiye abolish the killil special force. The Oromo Special force is already out of control. And guess what it is now closer to OLF and TPLF than Abiye.
Abiye has no a clue on what he is doing.
Man, you are embarrassingly bending for this man because he appointed a couple of opportunistic Guraghies.

Abere
Senior Member
Posts: 15501
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Abere » 15 Apr 2022, 10:10

The Ethiopian Defense Force (ENDF) reputation and competence is destroyed by PP-OLF. It is an ethnic based force as TPLF's era. ENDF is a liablity to the country. It is wasting the resource, asset and patriotic support. It is good for nothing. I really really feel bad for those soldiers who lost their lives in the spirit of defending their country. Had the resource ENDF been wasting used by comptent, committed, transparent militray leadership and political leaders, the country would have been free exactly in 2020. If the ill-armed, volunteer, own funded Afar forces and Fano are fearsome for TPLF how on earth is ENDF seen as coward by ragtga TPLF. As of now, TPLF is only scared of Fano and Afar people. TPLF is a rat that does not walk into areas where the cats are around. Abiy Ahmed talks alot but I don't think people even listent to speech. I stopped watching any video of him unles someone writes short paragrahs of what he said. The country needs a result based leader, people want result not talks. If he wanted to make the militraty courages, professional, de-ethnicized, patriotic, Why did not he do that. The last time we learnt about ENDF is firing at civilians, retreat and allow TPLF loot, kill people and livestock.


Horus
Senior Member+
Posts: 42927
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Horus » 15 Apr 2022, 13:41

Right & Union
የምትባሉ የፖለቲካ መሃይም የኢ አር ቦዘኔዎች ሙሉ ቀን አቢይና ጉራጌን በመስደብ ያ የታመመ ሳይኮሎጂህን ታስታግስ እንደሆን እንጂ ተው ፖለቲካ የረባ ሃሳብ እንኳ አንጎልህ ውስጥ የለም! ፋንዲያ ሁሉ!! በል ተንጫረር :lol: :lol:

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Za-Ilmaknun » 15 Apr 2022, 13:58

It is so painful to watch or hear whatever this man says. However, one thing that has come to be clear is that TPLF/OLF would rather fight against ENDF than Fano or Afar warriors. This has been proven by the recent interviews of the farmers in the conflict zones. TPLF militia only goes to fight where ENDF is at and run away where they are confronted by Fano.

I feel bad for the regular army members but the high ranking military officials are incompetent and always ready to sell their country to whoever is the highest bidder, not to mention their ethnically induced political militarism as demonstrated in Metekel, Ataye and many many other places. I am not sure how this force would be the last line of defense for whatever this man has in mind. We all need to remember how TPLF came close to Arat Killo a few months ago and how they were forced to retreat. He didn't even trust his troops but called on other forces to do the job of beating back the TPLF invaders.

The PM always says things when new realities are on the horizon and he does the opposite when he thinks that the storm is subsiding. He has no principle, no loyalty and no courage. Afar is shouldering the country's fight while the PM is roaming around farms and dictating how his subjects should learn to eat banana and avocado. Whatever he does is what he thinks would serve prolong his delusion. He is immune to the pain and the sufferings of the country but quick to pay his condolences when some tragedy hits somewhere outside of the country.

As it stands now, the military is the Oromo version of what it was under TPLF leadership. 90% of the military and polices forces leadership are from one ethnic group. I am not sure what mirrors the party structure in the military if this ain't.

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Za-Ilmaknun » 15 Apr 2022, 14:12

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ለመከላከያ መኮነኖች የተናገሩት ሐሳብ ።
ባህርዳር ። ሚያዚያ 07/2014/ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካድሬ እያጠፋ መከላከያ ዋጋ መክፈል የለበትም ብለዋል። ታጣቂዎችም ትጥቅ ይፈታሉ ብለዋል።
መረጃውን በዝርዝር እንመልከተው

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ህዝብ የሚፈልገውን በመናገር ኢትዮጵያዊዉ ሙሴ፣ አሻጋሪያችን፣ አንድ ጤነኛ መሪ መቶ ሚሊየን እብዶችን እየመራ የሚሉ ውዳሴዎች አግኝተዋል።

አስረን አናጣራም፣ አጣርተን እናስራለን። ኢትዮጲያዊ በየትም ቦታ ይኖራል። ኢትዮጵያ ጭቆና በቃት በሚሉ የስልጣን መባቻ ንግግራቸው ብዙዎችን አስጨብጭበዋል።

በትናንትናው ዕለትም የመከላከያ መኮነኖችን ሰብስበው መቶ ከመቶ በሁለት ዓመት ውስጥ ስንዴ ለራሳችን ተርፈን ወደ ውጭ እንልካለን ሲሉ ነግረዋቸዋል። የመከላከያ ጀኔራሎችን ስለግብርና ምርት እቅድ መናገሩ የቱን ያህል አስፈላጊ ነው የሚለውን እንተወዉና፣ ኢትዮጵያ በየዓመቱ ወደ 80 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ከውጭ ታስገባለች። ወደ 50 ቢሊየን ብርም በስንዴ ብቻ ወጭ ይደረጋል። ይሄ ሁሉ ባለበት ለስንዴ ራስን መቻል መናገራቸው ቢያስጨበጭብ ችግር አልነበረውም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2012 ዓም በሸህ ሁሴን አላሙዲ የተገነባው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ በአዲስ አበባ ሲመረቅ ከሁለት ዓመት በሗላ ስንዴ ከውጭ አናስገባም ብለው ነበር። ሁለት ዓመቱ ሲደርስ እንደገና ከሁለት ዓመት በሗላ ስንዴ ወደ ውጭ እንልክ ካልሆነ በስተቀር ወደ ውስጥ አናስገባም አሉ።

የዓለም የምግብ ምግብ ፕሮግራም ሰሞነኛ ትንታኔው ኢትዮጵያ በስንዴ እጦት ርሃብ ከሚያስተናግዱ ሀገራት ተርታ ትቀመጣለች የሚል ነው። ኢትዮጵያ 30 ከመቶ ስንዴ የምታመጣው ከዮክሬን ነበር። ዮክሬን ጦርነት ውስጥ ስትገባ የስንዴ አቅርቦት ጠፋ። በጠቅላይሚኒስትሩ ዕቅድ ቢሆን ዘንድሮ በስንዴ ራሳችን እንችል ነበር። ነገሩ በስንዴ ራሳችን ስለመቻሉ ይቆየንና ፣ ስንዴ አምራች አርሶአደሮች የአፈር ማዳበሪያ ያገኙት 40 ከመቶ አይሆኑም። ያም በተጋነነ ዋጋ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ አበባ ከመትከል፣ ቤተመንግስት ከማደስ እና ሌሎች አብረቅራቂ ነገሮችን ከማሳየት ውጭ የግብርና ቴክኖሎጂ፣ የመስኖ ግድብ፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት፣ ሰላምን አስጠብቆ ትርፍ ምርት ስለማምረት የሰሩት ስራ አይታይም። ይሄ ካልሆነ ደግሞ በምግብ ራስን መቻል በምኞት እና በጓሮ ተክል በመትከል አይረጋገጥም።

ሌላው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት መሰረታዊ ጉዳይ የሀገር መከላከያ የብልፅግና ወይም በጥቅሉ የፓርቲ እስረኛ መሆን እንደሌለበት ነው። የሀገር መከላከያ የሀገር የመጨረሻው ምሽግ እና ውግንናውም ለሀገር እንጂ ለፓርቲ መሆን የለበትም ብለዋል። በብሄር ቋጥሮ ውስጥ በመግባት ከሀገር ዝቅ ማለት ለመከላላከያ አይመጥንም ያሉ ሲሆን፣ መከላከያ ለካድሬ መላላክ የለበትም ብለዋል። ካድሬ ባጠፋው መከላከያ ለማስተካከል ዋጋ ይከፍላልም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ካድሬነትን አጣጥለው መከላከያን አወድሰዋል። በ2012 ዓም ለብልፅግና ፓርቲ ማደራጃ ገንዘብ በሸራቴን አዲስ ሲሰበሰብ የተማረ ኢኮኖሚ ፕሮፌሰር ቤት ወይም መኪና የለውም። እናንተ ግን ባለሀብቶች ሳትማሩ ሀብታም ሆናችሗል። ከተማረ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ያልተማረ ሀብታም ለሀገር የተሻለ ስለመሆኑ ተናግረው ነበር። ጠቅላይሚኒስትር አብይ እንደ መድረኩ ሁኔታ እንጂ መርህ የተከተለ እና ቀጣይነት ያለው ንግግር ሲያደርጉ ብዙ አይስተዋሉም።

በብሄር መሸጎጥ ልክ አይደለም ቢሉም ብልፅግና በተለይም የኦሮሞ ብሌፅግና ህወሃትን ለመተካት መሮጡ የአደባባይ ሀቅ ነው። ብሄርተኛነት በብልፅግና ውስጥ ባይኖር አዲስአበባ በሙያው ፣ በህዝብ ተቀባይነቱ እና የከተማ የመምራት ልምድ ባለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትመራ ነበር። በብልፅግና ውስጥ ብሄርተኝነት ባይኖር የኦሮሞ ብልፅግና የአማራ ብልፅግናን ተቃርኖ መግለጫ አያወጣም ነቀር። የብልፅግና ሊቀመንበር ደግሞ አብይ አህመድ ናቸው። የማይግባቡ የፓርቲ ቅርንጫፎች መሪ ሆነው ከብሄር ቋጠሮ እንውጣ ብለው መምከራቸው ከራሳቸው ሁኔታ፣ ከብልፅግና መንግስት ፖለቲካዊ አረዳድ ጋር አብሮ የማይሄድ ነው። በመሰረታዊነት ግን የጠቅላይሚኒስቴር ሀሳብ በተግባር ቢመነዘር ጥሩ ነበር። ነገርግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩትን ሲሆኑት በብዛት አይታዮም።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለመከላከያ መኮንንኖች ትጥቅ እናስወርዳለን ሲሉም ተናግረዋል። በአን

Right
Member
Posts: 4866
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Right » 15 Apr 2022, 14:15

Horus,
You must be burning inside to come out said and what you said to the two people you claimed to ignore.

For you political maturity is to blabbering garbage that may help Ataturk gain support.

“Abiye tempting to abandon his own brain child PP and seek a shelter at the disorganized ENDF”.
And you are a matured political analyst? Denkeem.

Misraq
Senior Member
Posts: 17878
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Misraq » 15 Apr 2022, 15:16

Summarizing the FOTO addicted imposters' presentation with two points...

1- You, the military leaders are part of the larger society hence don't listen the people's grievance because if you do, you will be tempted to attempt a coup d'etat on me to remove me from power.

2- Soon, I will relace each and everyone of you with loyal Oromos just like the way TPLF made 98% top military brass Tegaru to run the affair for 27 years."


Union

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Union » 15 Apr 2022, 15:20

Right, I was just about to say that. He keeps saying he is some deep political analyst but his political predictions in the past have all been wrong. According to him Birhanu was supposed to be a PM by now. Now we know he is saying that because Birhanu is a Gurage, period!!. Birhanu is now rejected by Ethiopians so horus claims to LOVE Abiy now. We will see how far he will LOVE abiy. With his bogus writing above he is trying to save Abiy. haha


Right wrote:
15 Apr 2022, 14:15
Horus,
You must be burning inside to come out said and what you said to the two people you claimed to ignore.

For you political maturity is to blabbering garbage that may help Ataturk gain support.

“Abiye tempting to abandon his own brain child PP and seek a shelter at the disorganized ENDF”.
And you are a matured political analyst? Denkeem.

Abere
Senior Member
Posts: 15501
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Abere » 15 Apr 2022, 20:26

ሆረስ፤

ዐብይ አህመድ ተስፋ የቆረጠው በእኔ በሦስት ወይም አራት ምክንያት ይመስለኛል።

1) በኦነግ ወይም ኦሮሙማ -ብልጽግና:-
እነኝህ ተረኞች ዐብይ ከሚጓዝበት ፍጥነት በላይ በመሄዳቸው ለተቃውሞ እና አለመሳካት አስተዋጽዖ አድርገዋል።

2) በትህነግ-ወያኔ:-
ወያኔን ለመታደግ ዐብይ ያልወጣው ተራራ ያልቧጠጠው ገደል የለም። ያን ሁሉ ዕልቂት ፈጽመው የጥሞና ጊዜ ሰጣቸው አማራ እያወደሙ ትግሬ ሲያርስ ይክረም አማራ እና አፋር ሲራብ ለትግሬ ስንደ እና ዘይት ሲጭን፤ ወያኔ የሚፈልገውን ሁሉ እያደረግ አልበቃም በማለት ለዐብይ አልተባበሩትም። ከጊዜ ወደ ጊዜ አዳዲስ ክልል እያዋለደ፤የጎሳ ክልል የበላይ ጠባቂ ሁኖ እያለ አሃዳዊ እያሉ ያሳጡታል።
3) በእራሱ
ዐብይ እራሱ አብላጫውን ድርሻ ይይዛል። አንድ ሰው ስንት ጊዜ እንድሳሳት እድል ይሰጠዋል? መሪ ሁኖ ብዙ ዕድል ይሰጠው ማለት አስቸጋሪ ነው።
ያን ሁሉ ሰራዊት እና ሰው መስዋዕት አድርጎ ከመቀሌ በአንድ ጀንበር መውጣት፥ ከታዋቂው ነፍስ አጥፊ ስብሃት ነጋ በነጻ ከእስር መለቀቅ። ድብቅ የሴራ ስምምነት በአፋር እና አማራ ጀርባ ከትህነግ ጋር እስከ ማድረግ ወዘተ። የስብዕና መርህ ችግር ይታይበታል ባይ ነኝ።

እና

4ኛ) በውታፍ ነቃይ ጋዜጠኞች፥ደጋፊዎች :-

መደገፍ በሚገባበት እየደገፉ መንቀፍ እና መምክር በሚያስፈልግበት ጉዳይ ደግሞ ጠ/ሚሩን በዚህ ረገድ እንደመርዳት እንደ ፈጣሪ እየካቡ ስህተት በስህተት እንድሆን ቀላል ድርሻ አላበረከቱም። ስንቱን ዘርዘሮ ይጨረሳል - ስንኮመኩም የከረምነው በዚህ 4 አመታት ከጦርነት እስከ ልማቱ በሙሉ ውሸት ነበር። አይነጋም መስሏት አሁን እያየነው ነው - ውሸቱ አልቆ ምን ይዋሽ፡፣

ቁም ነገሩ፡ አሁን ምን ቢያደረግ ሁኔታዎች ይስተካከላሉ ነው።

- ብልጽግና የሚባል ድርጅት ሙሉ በሙሉ መፍረስ ያለበት አይመስልህም?
- የጎሳ ክልል እና ኢ-ህገ መንግስቱ በዐዋጅ ይሁን በሌላ መንገድ ቢታገድስ?
- መከላከያ በአዲስ መልክ እና በአድስ አመራር ቢደራጅ እንድሁም አሁን በግንባር የሚዋደቁትን ህዝባዊ ሃይል በመርዳት ትህነግን መደምሰስ
- ከትህነግ-እና ሼኔ ከሚባለው ምግሼ ኦነግ-ብልጽግና የሚደረገ ግንኙነት ለህዝብ ቢታወቅስ?

እኔ በበኩሌ መንግስት ሽባ ሁኗል። መንግስት ደግሞ አገሪቱ አሻንጉሊት እንኳን ቢሆን ያስፈልጋታል - ረጅም ዱላ ባይመቱበት ያስፈራሩበታል ይባላል አይደል። አሁን ብዙዎች የሽግግር ወዘተ ይላሉ ግን ደግሞ ምንም ዓይነት ብቁ እና ታማኝ ሰው የለም እነ መራራ ፥ልደቱ፤ታምራት ላይኔ - በቃ አርቲ ቡርቲ ሰው ነው። እንድሁ ግርግሩን ተጠቅሞ የስቃዩን ዙር ማብዛት ነው። እንደት አይነት ወታደራዊ መንግስት ቢሆን ይሻላል? የዲሞክራሲውን ነገር እኔ ለጊዜው ይቆየን ባይነኝ። ዲሞክራሲ የሚባልም ነገር ውሸት ነው። ቢያንስ ሰላም የሚያሰፍን አመራር ያስፈልጋል። የጎሳ አማራሮች ሁሉም እንደ መኪና ማይሌጃቸውን ጨርሰዋል - ለዚህ ነው የሚንጫጩት አልሆንላችው ብሎ።

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by sun » 15 Apr 2022, 20:39

Abere wrote:
15 Apr 2022, 20:26
ሆረስ፤

ዐብይ አህመድ ተስፋ የቆረጠው በእኔ በሦስት ወይም አራት ምክንያት ይመስለኛል።

1) በኦነግ ወይም ኦሮሙማ -ብልጽግና:-
እነኝህ ተረኞች ዐብይ ከሚጓዝበት ፍጥነት በላይ በመሄዳቸው ለተቃውሞ እና አለመሳካት አስተዋጽዖ አድርገዋል።

2) በትህነግ-ወያኔ:-
ወያኔን ለመታደግ ዐብይ ያልወጣው ተራራ ያልቧጠጠው ገደል የለም። ያን ሁሉ ዕልቂት ፈጽመው የጥሞና ጊዜ ሰጣቸው አማራ እያወደሙ ትግሬ ሲያርስ ይክረም አማራ እና አፋር ሲራብ ለትግሬ ስንደ እና ዘይት ሲጭን፤ ወያኔ የሚፈልገውን ሁሉ እያደረግ አልበቃም በማለት ለዐብይ አልተባበሩትም። ከጊዜ ወደ ጊዜ አዳዲስ ክልል እያዋለደ፤የጎሳ ክልል የበላይ ጠባቂ ሁኖ እያለ አሃዳዊ እያሉ ያሳጡታል።
3) በእራሱ
ዐብይ እራሱ አብላጫውን ድርሻ ይይዛል። አንድ ሰው ስንት ጊዜ እንድሳሳት እድል ይሰጠዋል? መሪ ሁኖ ብዙ ዕድል ይሰጠው ማለት አስቸጋሪ ነው።
ያን ሁሉ ሰራዊት እና ሰው መስዋዕት አድርጎ ከመቀሌ በአንድ ጀንበር መውጣት፥ ከታዋቂው ነፍስ አጥፊ ስብሃት ነጋ በነጻ ከእስር መለቀቅ። ድብቅ የሴራ ስምምነት በአፋር እና አማራ ጀርባ ከትህነግ ጋር እስከ ማድረግ ወዘተ። የስብዕና መርህ ችግር ይታይበታል ባይ ነኝ።

እና

4ኛ) በውታፍ ነቃይ ጋዜጠኞች፥ደጋፊዎች :-

መደገፍ በሚገባበት እየደገፉ መንቀፍ እና መምክር በሚያስፈልግበት ጉዳይ ደግሞ ጠ/ሚሩን በዚህ ረገድ እንደመርዳት እንደ ፈጣሪ እየካቡ ስህተት በስህተት እንድሆን ቀላል ድርሻ አላበረከቱም። ስንቱን ዘርዘሮ ይጨረሳል - ስንኮመኩም የከረምነው በዚህ 4 አመታት ከጦርነት እስከ ልማቱ በሙሉ ውሸት ነበር። አይነጋም መስሏት አሁን እያየነው ነው - ውሸቱ አልቆ ምን ይዋሽ፡፣

ቁም ነገሩ፡ አሁን ምን ቢያደረግ ሁኔታዎች ይስተካከላሉ ነው።

- ብልጽግና የሚባል ድርጅት ሙሉ በሙሉ መፍረስ ያለበት አይመስልህም?
- የጎሳ ክልል እና ኢ-ህገ መንግስቱ በዐዋጅ ይሁን በሌላ መንገድ ቢታገድስ?
- መከላከያ በአዲስ መልክ እና በአድስ አመራር ቢደራጅ እንድሁም አሁን በግንባር የሚዋደቁትን ህዝባዊ ሃይል በመርዳት ትህነግን መደምሰስ
- ከትህነግ-እና ሼኔ ከሚባለው ምግሼ ኦነግ-ብልጽግና የሚደረገ ግንኙነት ለህዝብ ቢታወቅስ?

እኔ በበኩሌ መንግስት ሽባ ሁኗል። መንግስት ደግሞ አገሪቱ አሻንጉሊት እንኳን ቢሆን ያስፈልጋታል - ረጅም ዱላ ባይመቱበት ያስፈራሩበታል ይባላል አይደል። አሁን ብዙዎች የሽግግር ወዘተ ይላሉ ግን ደግሞ ምንም ዓይነት ብቁ እና ታማኝ ሰው የለም እነ መራራ ፥ልደቱ፤ታምራት ላይኔ - በቃ አርቲ ቡርቲ ሰው ነው። እንድሁ ግርግሩን ተጠቅሞ የስቃዩን ዙር ማብዛት ነው። እንደት አይነት ወታደራዊ መንግስት ቢሆን ይሻላል? የዲሞክራሲውን ነገር እኔ ለጊዜው ይቆየን ባይነኝ። ዲሞክራሲ የሚባልም ነገር ውሸት ነው። ቢያንስ ሰላም የሚያሰፍን አመራር ያስፈልጋል። የጎሳ አማራሮች ሁሉም እንደ መኪና ማይሌጃቸውን ጨርሰዋል - ለዚህ ነው የሚንጫጩት አልሆንላችው ብሎ።
Pathological liar Abere the Mad Bere, just get the hard kicks to your greasy behind and then get out of here instead of boring us to death.


Horus
Senior Member+
Posts: 42927
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Horus » 15 Apr 2022, 22:07

አቶ አበረ፣
ከሁለት ንኡስ ነገሮች በተቀር ባልከው ሁሉ እስማማለሁ። የማልስማማው አቢይ ከትግሬ መውጣልት አልነበረበትም በሚለው አልስማማም። በአለም ታሪክ ጥርነት መጀመርና ወደ ጦርነት መግባት በጣም ቀላል ነው፤ ግን ጦርነትን ማቆምና ከጦርነት መውጣት በጣም በጣም ከባድ ነገር ነው። አርቆ የሚያስብ ጦር ለጦርነቱ ግልጽ የሆነ ለከት የተበጀለት አላማ ሚሽን ይዞ ገብቶ፣ ያገኘውን ውጤት ምንም ይሁን ምን ይዞ መውጣት አለበት ። የጦርነት አላማ ፖለቲካ ስለሆነ ዲስፕሊን ይጠይቃል፣ በንዴት አይመራም። ስለዚህ አቢይ ከትግሬ መቀመቅ መውጣቱ ትክክል ነበር ብዬ አምናለሁ ።

ሌላው ሚዲያ ለአቢይ በማጨብጨባቸው እንዴት እሱን ተስፋ እንደ ሚያስቆርጡት ግልጽ አይደለሁ ።

በተረፈው ባልከው እስማማለሁ፤ ግን አበረ አንድ ነገር ልንገርህ ።

አቢይ አህመድ የኦሮሞ ተገንጣይ ሆኖ እነኦነኛ ሸኔን አስተባብሮ የኦርሙማ ነጻነት አቀንቃኝ ሆኖ ልክ እንደ ትግሬዎቹ መሆን ቢፈልግ ማንም የሚገታው አልነበረም፣ ዛሬም ከነሸኔ ጋር ሆኖ የኦሮሞ መንግስት ነጻ ሚያወጣ ማድረግ የሚችለው ነገር ነው ። አቢይን አለቅጥ የሚቃወሙት ሁሉ ይህን ክሬዲት አይሰጡትም። ያ ግዙፍ ስህተት ነው ። አቢይና መለስን ማመሳሰል ታሪካዊ ስህተት ነው ።

አቢይ የዜጋ ፖለቲከኛ አይደለም። አቢይ ከኢህአዴግ የተወለደ የብሄር ብሄር ሰብ ፖለቲከኛ ነው። ምን ያህል የኦሮሞ የበላይነት ማስፈን ይፈልጋል የሚባለው በፋክት ላይ ቆመን መከራከር ያለብን ነገር ነው። ከነሺመልስና ሌሎቹ ጋራ ያላቸው ፍትጊያ ያ ይመስለኛል ። የነሱ ድጋፍ መሰረት ኦሮሞ ስለሆነ ሺመልስ ደጋግሞ የሚለው አንዴ በጃችን የገባችው ስልጣን በፍጹም ከማንም አንጋራም ነው የሚለው ። አቢይ በዚህ 100% አይሳማማም።

ስለዚህ ከአቢይ የዜጋ ፖለቲካ መፍትሄ መጠበቅ ትርፉ ንዴት ነው ። ኢትዮጵያ በዜጋ ሰርዓት የምንል ያንን እምንፈጥር እኛ ነው እንጂ አቢይ አይሰጠንም። አቢይ ደጋግሞ ብሏል የሱ አማለካከት የጎሳና የዜጋ ፖለቲካ ሊጣጣሙ ይችላሉ የሚል ነው። ምንም ነገር ማድረግ ያልተቻለውም ጎሰኘትና የኢትዮጵያ ዜገኘት ስለማይጣጣሙ ነው ።

ይህ በጎሳና በዜጋ መሃል ያለው ገመድ ጉተታ ነው ብልጽግናን እያፈረሰው ያለው ። አቢይ በጎሳ ተረኛነት ከነሱ ጋር ቢቆም ይህ ሁሉ የብልጽኛ መንጋ ሌባ ከኋላው ይቆሙ ነበር ። ከትግሬ ተገንጣዮች አንስተህ እስከ ሱማሌ ክልል ያለው ፍትጊያ ያ ነው ።

አቢይ አንድ የሚያውቀው ነገር አለ፣ እሱም ትግሬዎች የጠፈጠፉትን የጎሳ ቂጣ ይዞ የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ እንደ ማይቀጥል በደምብ ገብቶታል። ለዚህ ነው ኢትዮጵያ አፍቃሪ የሆነ ሚሊታሪ ገምብቶ የስልጣኑ መሰረት ወደዚያ ያዞረው ።

ስለሽግግር ፋንዲያዎች ያልከው እጅግ ትክክል ነው ። ኢትዮጵያ ምንግዜም መንግስት ትፈልጋለች ። አሁን ልብ ካልክ ይህ ሁሉ ጸረ አቢይ መንጋ አንዳቸውም የኢትዮጵያ አጀንዳ የላቸውም፤ ፍላጎታቸው አቢይ ቀውስ ውስጥ ግብቶ ማየት ብቻ ነው ። ባብዛኛው የትግሬና የኦሮሞ ተገንጣዮች የንዴት መግለጫ ነው ። ልብ ብለህ ተከታተል አንዳቸውም አቢይ ወርዶ እንተካ ነው የሚሉት እንጂ የጎሳው ሲስተም እንዴት በዜጋ ሲተም መተካት እንዳለበት ቤሳ ሳንቲም ሃሳብ የላቸውም።

አንተም እንዳልከው የዜጋው ካምፕ ድጋፍ ለማጣት እራሱ አቢይ ነው ተጠያቂው ፤ ስብሃትን መፍታቱ ካካ ነው! ዜጎች ታሪካዊ ሰንደቅ አትያዙ የሱ ጠብ ያለሽ በዳቦ ነው ። ከዚያ በተረፈ የክልል ልዩ ሃይሎች በሙሉ ወደ ወደ ኢትዮጵያ ሰራዊት መካተት አለባቸው ወይ መፍረስ አለባቸው ። ባንድ አገር 10 የተለያዩ ሚሊታሪ ሃይሎች ሊኖሩ ፍጹም ክልክል ነው። ስለዚህ እነዚህ በየክልሉ የወጠጡ የዎርሎርድ ጦሮች ወይ በውድ ይፈርሳሉ ወይም በፌዴራል ጦር ይመታሉ ማለት ነው።

ስለዚህ በእኔ ግምት አቢይ ስልጣን ላይ መቆየት ከፈለገ ቁርጥ ያሉ እርምጃዎች እንዲወስድ ይገደዳል ብዪ አምናለሁ ። ዞሮ ዞሮ በመላ ኢትዮጵያ አቢይን በሃይል ማውረድ የሚችል ፌዴራል ጦሩ ካልሆነ በስተቀር (ያንንም እጠራጠራለሁ) ሌላ ሃይል የለም ። የምትሰማው ሁሉ የሶሺያ ሚዲያ ጫጫታ ነው ። ግን በርግጠኝነት የጎሳው እምቧይ ካብ ፍርክርኩ እየወጣ ነው ። ስልጣን አቢይና ሚሊታሪው ዙሪያ እየተከማቸ ነው!!!

የብልጽግና ፓርቲ አይፈርስም ፣ ያ አቢይ የሚገዛበት መሳሪያ ቢሮክራሲ ስለሆነ ። ፒፒ ተጠጋኞ ለብዙ አመታት ይቀጥላል ። የዜጋ ፖለቲካው ካምፕ ጠንክሮ ስልጣም ላይ ቢወጣ እንኳን የጎሳው ክንፍ ለብዙ ብዙ አመት ይኖራል ። የእኔ ሃሳብ አዲስ ሰርዓት ስንፈጥር የጎሳው ፓርላማ የራሱ የታችኛው ፓርላማ ቆሞለት በቋንቋ፣ ባህል፣ ማናምን ላይ ውክልና ኖሮት ከብሄራዊ ፖለቲካ ቢወጣ ምርጫዬ ። ሌሎች በአዋጅና በህገ መንግስት ማሻሻያ የሚፈርሱት የሚታደሱት የትኞቹ ናቸው የሚለው የሚነግረን መጪው ዲያሎግና ድርድር ይሆናል ።

Right
Member
Posts: 4866
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Right » 15 Apr 2022, 23:52

Union,
He thinks that he can get away with this treacherous conning.
This is not a peanut market.
Abiye who came to power with a lot of hope is really an extension of the woyannie regime.
For 4 long years the nation is in crisis and all he does is add more fuel to the fire by holding and promoting ethnic federalism.
He talks sweet but he delivers shi$$t.

Believe me the Guraghies and PP alliance against Ethiopia will not last.

Union

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Union » 16 Apr 2022, 00:07

Right,
He does not care if Abiy's PP is an extension of woyane regime as long as birhanu nega aka biramtu nega holds some fake goverment position handed to him by abiy.
And he does not care for his religion either. Abiy is slaughtering Orthodox Christians while they were celebrating the manifestation of their God. After all this crimes Abiy has done this full of crap suggests abiy just needs some correction and advices. Haha
Again, such people would do anything for money and power, forget God, they care less.

Right wrote:
15 Apr 2022, 23:52
Union,
He thinks that he can get away with this treacherous conning.
This is not a peanut market.
Abiye who came to power with a lot of hope is really an extension of the woyannie regime.
For 4 long years the nation is in crisis and all he does is add more fuel to the fire by holding and promoting ethnic federalism.
He talks sweet but he delivers shi$$t.

Believe me the Guraghies and PP alliance against Ethiopia will not last.

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by TGAA » 16 Apr 2022, 00:09

ሆረስ፦ እኔ አብይ ያደረገው የወታደራዊ ሞዴል ትንተና ላይ ብዙ የሚለው የለኝም ምክንያቱም የተለያዩ ሞድሎችን በቲዎሪ ደረጃ (entertain ) የምናደርገው ተግባራዊነቱንና ለችግሩ መፍትሄ ማቅረብ መቻሉን በመገምገም ነው፤ ሞዴሎችን የምናያችው ለ ‘ivory tower ‘ abstraction ሳይሆን ያሉብንን የህብረተሰባዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን መፍታት ይረዱናል ወይ የሚለውን መልስ እስከሰጡን ድረስ ብቻ ነው ፡፡
ሀሳብህን መሰረት ያደረክባቸው ሁለት ግምቶች ችግር አለባቸው
አንደኛ አብይ በአፉ አውጥቶ እኔ ሪፎርም ላደርግ እንጂ ልቀይር አልመጣሁም ብሎ ፍለፊት ተናግሯል ፤ ብልጽግናም የእርሱ ፈጠራ ነው ፤ ሲነሳ የተጀመረበት አላማና አሁን ያለበት ቦታ ደግሞ አራምባ ና ቆቦ ነው ፤
የሞጋሳ ፖለቲካ ነው ዋና ችግር እየሆነ ያለው ፤ ያለውንም የወያኔ ሲስተም ሊጠብቁና ሊያስፋፉ የሚፈልጉት ኦሮሞ ይቅደምን ያነገቡ ናቸው ;
እርግጠኛ አይደለሁም ምን ያህል የአብይን ንግግሮች በተልይ ፎርማል ያልሆኑ ንግግሮቹን በደንብ ከሰማህው ልቡ የት እናድለ ማወቅ ቀላል ነው፤ በአንድ ወቅት ስለህብረብሄር ፓሪቲዎች ሲናገር ፤ “ቀረብ ብለህ ስታያቸው ያንድ ብሄር ፓርቲዎች ናቸው ብሎ ሲናገር ሰምቼዋለሁ፤ በዚህ ላይ የፖለቲካው መሰረት የሆነው የኦሮምያ ፖለቲካ ቀርብ ብለህ ሰታየው የአብይ የኢትዮጵያ ዝማሬ ቅዝምዝም ወዲህ ፍየል ወደዚያ ነው ስለዚህ ብልጽግና ያለውን ችግር “sequester” አድርጎ ወታደሩ ላይ የሚንጠለጠልበት መገድ ቢኖርም እንኳን ሀብረተሰቡ በጎሳ ፖለቲካ እየተፈረካከስ ወታደሩ ለብቻው የኢትዮጵያዊነት ደሴት ሊሆን የሚችልበት መንገድ ሊኖር አይችልም ፡ ትልቁ የአብይ ስራ መሆን የነበረበት ኢትዮጵያዊነትን በብልጽገና ውስጥ ማስረጽ ቢችል ነበር ፤ ምክንያቱም ያንን ቢያደርግ በተመሳሳይ ሁኔት ወታደሩንም ዲሞክራቲክ የሆነ ነገር ግን የሲቬሉን አስተዳደር የሚያከብር ብሄራዊ ጦር ማድረግ ይችል ነበር፡፡ አሁን ግን ጉሰኞች በተለይም እርሱ የመጣበት የኦሮም ብልጽግና ፓርቲና ሊሎች ጸረ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ተዋንያን የወያኔ ኮፒ ፖለቲካ እየተጫወቱ ወታደሩን ወደብሄራችሁ ዝቅ አትብሎ ምክር መምከር “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ “ የሚለውን ነው አባባል ነው የሚገልጸው፡፡ አንተም በአንዱ መልስህ ላይ እንዳየሁት እራሱ ምንም እንኳን እንደሌሎቹ ጥግ የደረስ ጉሰኝነት ባያሳይም በዚያም አብይ የብሄር ፖለቲካ ተጫዋች መሆኑን አምነሀል ፤ ይህንን አባባልሀን እንኳን ብናየው እርሱ የብሄራዊ ፖለቲካ አማላኝ ሆኖ ፤ ብልጽግናም በተመሳሳይ ሁኔታ የጎሰኛ ፓለቲከኞች ከሆነ እንዴት አድርጎ የኢትዮጵያን ሰራዊት ከጎሰኝነት አውጥቶ የኢትዮጵያ ተከላካይ በተጨማሪም ለአብይ አስተማማኝ ምርኩዝ እንደሚሆን ግራ አጋቢ ነው ፤ ለዚህም ነው ልዩነት በሌለበት ልዩነት ትፈጥራልህ ያልክህ፤ እውነት አሁን ካልበት “quagmire “ ኢትዮጵያንም ቢሆን እራሱንም ነጻ ማውጣት የሚችለው እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ፊደራሊዝምን ብልጽግና ውስጥ ማስገባትና ማስረጽ ሲችል ነው ፡፡ እንደዚህ አይነት እርምጃ ቢወስድ አብዛኛውን ብልጽግናን እንዲሁም ወታደሩን በአንድ ግዜ ከጎኑ ማሰለፍ ይችላል ፤ ይህንን ለማድረግ ደግም ጉሳዊ ፓሪዎችን ቦታ መንሳት የለበትም ፤ ምክንያቱም አብዛኛ የተማረው ህብረተሰብ ተቀባይነት ስሌላቸው ፤ ነገር ግን አብይ እራሱ እንደዚ አይነት ጠንካራ ኢትዮጵያዊነት የሚፈራ ነው የሚመስለኝ ፤ ለዚህ ደግሞ እንደ ማስረጃ ማቅረብ የሚቻለው ፤ ህብረ ብሄራዊ ኢትዮጵያዊነት በሀገም ሆነ በኢንተርናሽናል መድረክ ተቀጣጥሎ ሲመጣ የወሰዳቸው እርምጃዎች ማስረጃዎች ናቸው ፤ ለዚህም ነው ቀዝቃዛ ውሀ ለማፍሰስ እነስብሀትን የወያኔ ወንጀለኞችን “ እግዚያብሄ ጠይቆኝ ብሎ የለቀቃችው። አሁን አብይን እያሳሰበው ያለው የአማራ ብልጽግናዎች ፊት ማዞርና ከወያኔ ጦርነት ማለቅ በኋላ የአማራ ሀይል መፈርጠም ነው፤ ለዚህ ነው አሁን ብሄራዊውን ጦር ከአማራ ለሚመጣ ግፊት መጠቀምያ ለማድረግ ነው ይህ ሁሉ ዲስኮራ፡፡ ያም ግን በጣም ችግር ያለበት ነው፤ የትግራይን ጦር ሳያስፈታ የአማራን ጦር ማስፈታት ስለማይችል ነው፤ አብይ ወታደሮችን ስለኢትዮጵያዊነት ከማስተማር እንዲሁም የጎሳ ፖለቲካ ያሳንሳችኋል ብሎ ከመደስኮር ያንን ፖለቲካ እራሱ በተግባር እያሳየ ተከተሉኝ ማለት ይችል ነበር ፤ ከአፍ ዝመራ በስትቀር አብይ የጎሳ ፖለቲካን አዘዋሪ ነው ፤ ጭልጥ ብሎ የዘር ፖልቲካን ቢሽከም ድጋፉ ኦሮሞ ጋር ብቻ ስለሚቀር ነው ዝመራውን የቀጠለው፡፡

Horus wrote:
15 Apr 2022, 02:30
You are creating a dichotomy where it doesn't exist.
How?
[/quote]

Horus
Senior Member+
Posts: 42927
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ተስፋ ቆርጧል፤ የመንግስቱን ድጋፍ መሰረት ወደ ሚሊታሪው አዙሯል!

Post by Horus » 16 Apr 2022, 00:49

Please wait, video is loading...
TGAA
በብዙ ነገሮች ላይ ያለህ የራስህን ህሳቤና እምነት መዘርዘርህ ጥሩ ነው ። እኔ ደግሜ ልጠይቅህ፤ ስለአቢይ አህመድ መንግስትም ሆነ ስለጎሳ ስርዓት ሁለቱ የተነሳሁባቸው የተሳሳቱ አሰምሽኖች (እምነቶች) እስቲ በአንድ አረፍተ ነገር አንድ ሁለት ብለህ አስቀምጣቸው? ልብ በል አንተ የራስክን መሰልኝ ሳይሆን ከእኔ የወጡ ሃሳቦች ወይም እምነቶች? ከዚያም ጭብጥ በሆነ ነጥብ ላይ እንመላለሳለን።

Post Reply