Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11365
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"የዘመኑን ጀግና፣ ቢሞቀው ቢበርደው የማይጨንቀው ሀገርን ወጥሮ የያዛት ጠንካራ የብረት ምሰሶ" በዮሐንስ ቧያለው

Post by sarcasm » 10 Apr 2022, 19:16

እና አሁን ዮሐንስ ቧያለው ምን እያለ ነው? ከመጀመርያው ትክክል እንደነበር ከማስመሰል፣ መጀመርያ እራሴን ተሳስቼ እናንተን አሳስቻለሁኝና ይቅር በሉኝ ማለት አይኖርንበትም ?

የዘመኑን ጀግና ልንገርህ ..................‼️

እንደ አቶ ደመቀ መኮንን አስደናቂ መሪ የለም። ድጋፍ ሲበዛለት ጭብጨባው ሲደምቅለት አይኮራ ልታይ ልታይ አይል። የደጋፊ ድርቅ ሲመታው አይፈራ፤ ድጋፍ ለማግኘት ያላመነበትን ነገር የማይሰራ በራሱ ዛቢያ ላይ የሚሽከረከር መሪ ነው።

በነፈሰበት የማይነፍስ የተነሳውን ማዕበል የሚያናውጥ ሳይሆን በትግስት ወጀቡን ማዕበሉን ለማለፍ እና ሀገርን በስልት ለመምራት የተቀመጠ ፅኑ መሪ ደመቀ መኮንን ነው። የአቋም መንሸራተት፣ ድንፋታ፣ ዛቻ፣ ግልምጫ በገለጫው ቢሆን ኢትዮጵያ ብትንትኗ ይወጣ ነበር። አራት ኪሎ ቤተ መንግስትን በማንም ፋከራ ተናውጦ ሀገር እንዳይፈርስ አጥብቆ የያዘው ፅኑ ምስማር ደመቀ ብቻ ነው።

ጀግና መሪ መድረክ ላይ ወጥቶ በጭብጨባ ለመድመቅ ቃላት የሚደረድር አይደለም። ጀግና መሪ ድጋፍ ለማግኘት ለሀገር አደጋ የሚያስከትል ውሳኔ የሚወስን አይደለም። ጀግና መሪ በፈነዳ ጊዜ ህዝብ የሚያጠፋ የጥላቻ ፈንጅ የሚያጠምድ አይደለም።

ጀግና መሪ በጅቦች ጩኸት የማደነግጥ፣ በህዝብ ኩርፊያ ሳይፈራ፣ በህዝብ ድጋፍ ሳይኮራ ሀገርን ይጠቅማል ያለውን የፖለቲካ ፍልስፍና ነድፎ ብቻውንም ቢሆን ታግሎ ማሳዬት ነው። ደመቀ ደግሞ ይህን እያደረገው ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ለእኔ ትናንት የነበረ አሁንም ያለ ነገም የሚኖር ለሀገር መከታ የሆነ ታማኝ ዝምተኛ ጀግናዬ ነው። ቢሞቀው ቢበርደው የማይጨንቀው ሀገርን ወጥሮ የያዛት ጠንካራ የብረት ምሰሶ ጀግናህ ደመቀ ነው።
Please wait, video is loading...



Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: "የዘመኑን ጀግና፣ ቢሞቀው ቢበርደው የማይጨንቀው ሀገርን ወጥሮ የያዛት ጠንካራ የብረት ምሰሶ" በዮሐንስ ቧያለው

Post by Assegid S. » 11 Apr 2022, 07:48

ልክ ነው፤ እኔም እስማማለሁ! የሚበላውን ካገኘ ቢሞቀው ቢበርደው የማይጨንቀው ኣሳማ ብቻ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ኣማሮች እየታረዱ፣ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ አቅመ ደካሞችና ህፃናት ከመኖሪያ ቅያቸው እየተፈናቀሉ የማይጨንቀው፥ ኣማራን እንደ ካንሰር ቀስፎ የያዘ ጠንካራ የኦህዴድ ምሰሶ ደመቀ መኮንን ነው። ይህ ብቻም አይደለም፦ "ኣማራ መንገድ ዳር ተቀምጦ ሲለምን ማየት እፈለጋለሁ" ያለውን ፀረ-ኣማራ መሪ (ባህል ነውና "ነፍስ ይማር" ይባላል) ክፉ ህልሙን ሳይተገብር ቢያልፍም፥ በእግሩ ተተክቶ የጌታውን ምኞት ያሳካ ... የሙት ህወሃት ነፍስ አባት ደመቀ መኮንን ነው። ኣንተ ኣማራ፦ ቅኔው ገብቶህ ካልነቃህ ነገም አይቆምም ... "በኣብይ ተግባር - በደመቀ ጉዞ - በኣደም መንገድ" ይዞህ ሊነጉድ ቃል ገብቷል።



ሁሌም የሚገርመኝ የብኣዴን ባህሪ ግን ... ልክ እንደ Tower Bridge … ኣፋቸው የሚከፈተው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። እህል ሲጎርሱ እና ከስልጣን ሲነሱ።

Post Reply