የዘመኑን ጀግና ልንገርህ ..................
እንደ አቶ ደመቀ መኮንን አስደናቂ መሪ የለም። ድጋፍ ሲበዛለት ጭብጨባው ሲደምቅለት አይኮራ ልታይ ልታይ አይል። የደጋፊ ድርቅ ሲመታው አይፈራ፤ ድጋፍ ለማግኘት ያላመነበትን ነገር የማይሰራ በራሱ ዛቢያ ላይ የሚሽከረከር መሪ ነው።
በነፈሰበት የማይነፍስ የተነሳውን ማዕበል የሚያናውጥ ሳይሆን በትግስት ወጀቡን ማዕበሉን ለማለፍ እና ሀገርን በስልት ለመምራት የተቀመጠ ፅኑ መሪ ደመቀ መኮንን ነው። የአቋም መንሸራተት፣ ድንፋታ፣ ዛቻ፣ ግልምጫ በገለጫው ቢሆን ኢትዮጵያ ብትንትኗ ይወጣ ነበር። አራት ኪሎ ቤተ መንግስትን በማንም ፋከራ ተናውጦ ሀገር እንዳይፈርስ አጥብቆ የያዘው ፅኑ ምስማር ደመቀ ብቻ ነው።
ጀግና መሪ መድረክ ላይ ወጥቶ በጭብጨባ ለመድመቅ ቃላት የሚደረድር አይደለም። ጀግና መሪ ድጋፍ ለማግኘት ለሀገር አደጋ የሚያስከትል ውሳኔ የሚወስን አይደለም። ጀግና መሪ በፈነዳ ጊዜ ህዝብ የሚያጠፋ የጥላቻ ፈንጅ የሚያጠምድ አይደለም።
ጀግና መሪ በጅቦች ጩኸት የማደነግጥ፣ በህዝብ ኩርፊያ ሳይፈራ፣ በህዝብ ድጋፍ ሳይኮራ ሀገርን ይጠቅማል ያለውን የፖለቲካ ፍልስፍና ነድፎ ብቻውንም ቢሆን ታግሎ ማሳዬት ነው። ደመቀ ደግሞ ይህን እያደረገው ነው።
አቶ ደመቀ መኮንን ለእኔ ትናንት የነበረ አሁንም ያለ ነገም የሚኖር ለሀገር መከታ የሆነ ታማኝ ዝምተኛ ጀግናዬ ነው። ቢሞቀው ቢበርደው የማይጨንቀው ሀገርን ወጥሮ የያዛት ጠንካራ የብረት ምሰሶ ጀግናህ ደመቀ ነው።
Please wait, video is loading...

