Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42902
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በጎሳ ፖለቲካ የተፈጠረው የኢትዮጵያ መከራ በጎሳ ፖለቲካ አይወገድም

Post by Horus » 08 Mar 2022, 22:29

ፓርቲያችሁን አይደለም ሂአአዴግ፣ አይደለም ብልጽግና ማህበረ መላዕክት ልትሉት ትችላላችሁ፤
የዚህ ኮሚቴ የዚያ ኮሚሽሽ፣ የዚህ ፓርላማ የዚያ ምክክር በሉት፤
ሺ ግዜ የኦሮትግሬ፣ የኦሮማራ፣ ያማራትግሬ ምናምን ሚዛን ቢቀመር ቢፈርስ፣
በየአመቱ አዲስ ቲኦሪ ቢደመር ቢቀነስ ቢሰበክ ቢከለስ፤

ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ ዜጋዎች የራሳቸውን ሰንደቅ አላማ መያዝ እስካልቻሉ ድረስ፤
ሕዝቦች በዘር ክልል እስር ቤት ታጉረው የጎሳ ከበርቴና የጎሳ ባለመሬት ባላባት እንደ መስፍን በልዩ ሃይል አፍኖ መግዛት እስከ ቀጠለ ድረስ፤
የትግሬ ባንዳዎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የጠፈጠፉት ሕገ ጎሳና የጎሳ ፓርላማ ጸንቶ ኢትዮጵያዊያን ንጹህ ዉሃና ዘይት እንዳያገኙ እስከ ተደረገ ድረስ።
ባንድ ቃል ይህ ቆሻሻ የጎሳ ስርዓት መለወጥ፣ ማፍረስ እስካልተጀመረ ድረስ ሁሉ ያሻውን ሊዘባርቅ ይችላል።

ግን መንግስት የሚባል ነገርም አይረጋም፣ ሰላም የሚባል ነገርም አይኖርም፣ እድገት የሚባል ነገርም የኢትዮጵያ እድገት ሳይሆን የመሬት ባላባት የሆነው የጎሳ ከበርቴና በጉቦና በሌብነት የሚከብረው የጎሳ የቢሮ ከበርቴ ብልጭልጭ ማዘናጊያ ሆኖ ይቀራል ።

በመንግስት ላይ ትችት፣ ነቀፋ ወይም ቅዋሜ አለኝ የሚሉ ሁሉ በኢትዮጵያ ኢጎሳዊ ሰርዓት እንዲመጣ እስካልሰሩ ድረስ እራሳቸው የችግሩ አካል እንጂ የመፍትሄ አካል አይደሉም! አይሆኑም!

የጎሳ ፖለቲካ ገና ሁሉንም ይደመሳሳል! :idea:

Abere
Senior Member
Posts: 15490
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በጎሳ ፖለቲካ የተፈጠረው የኢትዮጵያ መከራ በጎሳ ፖለቲካ አይወገድም

Post by Abere » 09 Mar 2022, 18:33

የጎሳ ፓለቲካ እና የአገር ፀረ- አለመረጋጋት የሆኑት ትህነግ እና ኦነግ -ብልጽግና እስካልጠፉ ድረስ ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ አገር ሰላም ማስበ ከንቱ ህልም ነው። የጎሳ ወረርሽኝ ተሸካሚ ፈረሶች እነኝህ ሁለቱ ናቸው - እነኝህ ብቻ ናቸው ቢባል ስህተት አይመስለኝም። ታዲያ እንደት ነው እነዚህን ማፍረስ የሚቻለው ነው ዋናው ጥያቄው? የአገሪቱን መሳርያ በመንግስትነት ታጥቀዋል፤ የአገሪቱን ገንዘብ በመንግስትነት በባንክ እና በኩባንያ ያንቀሳቅሳሉ፥ ሲፈልጋቸው ዐዋጅ አውጥተው የፈለጉንት ያስራሉ ፥ የፈታሉ። ኦነግ-ብልጽግና ዋና የጎሳ ጭራቅ ንጉስ ነው ። አያ ሰባት ቀንዶ የሆነው 7ኛው ንጉስ እኮ ስለ አገር ሳይሆን ስለ ጎሳ ነው ደፋ ቀና የሚለው። አዎን፥ በቲዎሪ (ንድፈ-ሃሳብ) ደረጃ ጎሳኝነት ጸረ-ሰብዐዊ ነው፤ ጸረ-ህዝብ እና ጸረ-አገር ነው። ግን ይህ አይነት መንግስት ነው ኢትዮጵያ ያላት። ምን አይነት ድርጅት እና መቸ ነው ኢትዮጵያን ከዚህ 7ኛው የጎሳ ጭራቅ ወይም ከሊጥ ደፊ የትግሬ ነጻ አውጭ ነኝ ባይ ሊገላግላት የሚችለው? ከግድግዳው ላይ ካለው ትልቁ ምስል ላይ ብናተኩር ውጤት ይኖራል። የሰማይ ስባሪ የሚያህሉ ሁለት የጎሳ ጭራቆች አሉ። እነርሱም ትህነግ ወያኔ እና ኦነግ (ኦደፓ-ኦነግ) ናቸው። እነኝህ ሲጠፉ ያለምንም ጥርጥር የጎሳ ፓለቲካ አብሮ ይጠፋል። እነርሱ የሚያስወሩትን ወሬ እና ፕርፓጋንዳ መጣል አለብን። ለእኛ የሚነግሩን እራሳቸውን የሚያስፈራቸውን እንጅ አገር እና ህዝብ የሚጠቅመውን አይደለም። 7ኛው ጭራቅን ለማመን የሚነግርህ ተቃራኒ ማድረግ ብቻ ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 42902
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በጎሳ ፖለቲካ የተፈጠረው የኢትዮጵያ መከራ በጎሳ ፖለቲካ አይወገድም

Post by Horus » 09 Mar 2022, 20:26

Abere wrote:
09 Mar 2022, 18:33
የጎሳ ፓለቲካ እና የአገር ፀረ- አለመረጋጋት የሆኑት ትህነግ እና ኦነግ -ብልጽግና እስካልጠፉ ድረስ ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ አገር ሰላም ማስበ ከንቱ ህልም ነው። የጎሳ ወረርሽኝ ተሸካሚ ፈረሶች እነኝህ ሁለቱ ናቸው - እነኝህ ብቻ ናቸው ቢባል ስህተት አይመስለኝም።
አበረ፣
የጎሳ ፖለቲካ ተሸካሚዎች ትህነግና ኦነግ ብቻ አይደሉም፤ በኢትዮጵያ ዜግነት ሳይሆን በራሱ ዘውግ የተደራጀው ሁሉ ካማራ እስከ ደቡብ፣ ካፋር እስከ ሱማሊ ያለው ሁሉ የዘር ፖለቲካ ተሸካሚ ነው ። የዘር መደራጀት እምቢ ብለው በዜግነት መታገል ካልተጀመረ ስልጣን ላይ ያሉትን የኦሮሞ ሆነ የትግሬ ያማራ ሆነ የሲዳማ የዘር ነጋዴዎችን የሚነካ ነገር አይመጣም! በዘር ተገራጅቶ እነሱን መቃወም ከንቱ ግዜ ማባከን ነው!

Abere
Senior Member
Posts: 15490
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በጎሳ ፖለቲካ የተፈጠረው የኢትዮጵያ መከራ በጎሳ ፖለቲካ አይወገድም

Post by Abere » 10 Mar 2022, 10:40

የጎሳ ፓለቲካ የኦነግ እና የወያኔ ስሪቶች እንጅ ሌላ ማንም አልፈጠራቸውም። ትህነግ እና ኦነግ ሲጠፉ ሙሉ ለሙሉ የጎሳ ዛር ይጠፋል። አሁን የሚያፍቅ የጎሳ ስሜት ሙሉ በሙሉ ይጠፋል። ሁሉን አይነት እንቅስቃሴ የጎሳ ባህርይ የተሰጠው ከተንኮለኛ የኦነግ-አደፓ እና ትህነግ ፕሮፓጋንዳ ነው። ይህ ማለት ለአገር የሚጠቅመውን በማጥፋት ጎጅ የሆነው እንድንሰራፋ ማድረግ ማለት ነው። ይህ ደግሞ የተሳሳተ እርምጃ እና ግንዛቤ የዋህ የሆነው ህዝብ እንድይዝ የማድረግ የውዥንብር ድርጊት ነው። የስንዴውን ማሳ አረም ለማረም ስንዴውን በመንቀል የእንክርዳዱ ቡቃያ በመተው እንድያድግ ማድረግ እንደማለት ነው። ኦነግ እና ትህነግ ብቻ ናቸው ስትራቴጅክ የኢትዮጵያ ጠላቶች - መደምሰስ ወይም መጥፋት አለባቸው። በርዕዮተ አለም ላይ የተመረኮዘ የዜግነት ፓለቲካ ጠቃሚ መሆኑ ግልጽ ነው። ግን በፍጹም አሁን ያሊመጣ አይችልም። ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ ነው ኢትዮጵያ ያልተረጋጋች በሁለት ጠንቀኞች ኦነግ እና ትህነግ የምትታመስ አገር ነች - እነሱም ይህ እንዳይኖር ማንኛውንም ሃይል ይጠቀማሉ። ስለዚህ አገሪቱ ሌላ አብዮት ውስጥ መግባቷ አይቀርም ባይ ነኝ። የዜጋ ፓለቲካ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሳካል ማለት በሬ ወተት ይሰጣል ብሎ መሞኘት ነው።

Horus wrote:
09 Mar 2022, 20:26
አበረ፣
የጎሳ ፖለቲካ ተሸካሚዎች ትህነግና ኦነግ ብቻ አይደሉም፤ በኢትዮጵያ ዜግነት ሳይሆን በራሱ ዘውግ የተደራጀው ሁሉ ካማራ እስከ ደቡብ፣ ካፋር እስከ ሱማሊ ያለው ሁሉ የዘር ፖለቲካ ተሸካሚ ነው ። የዘር መደራጀት እምቢ ብለው በዜግነት መታገል ካልተጀመረ ስልጣን ላይ ያሉትን የኦሮሞ ሆነ የትግሬ ያማራ ሆነ የሲዳማ የዘር ነጋዴዎችን የሚነካ ነገር አይመጣም! በዘር ተገራጅቶ እነሱን መቃወም ከንቱ ግዜ ማባከን ነው!

Horus
Senior Member+
Posts: 42902
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በጎሳ ፖለቲካ የተፈጠረው የኢትዮጵያ መከራ በጎሳ ፖለቲካ አይወገድም

Post by Horus » 10 Mar 2022, 14:41

Abere wrote:
10 Mar 2022, 10:40
የጎሳ ፓለቲካ የኦነግ እና የወያኔ ስሪቶች እንጅ ሌላ ማንም አልፈጠራቸውም። ትህነግ እና ኦነግ ሲጠፉ ሙሉ ለሙሉ የጎሳ ዛር ይጠፋል። አሁን የሚያፍቅ የጎሳ ስሜት ሙሉ በሙሉ ይጠፋል። ሁሉን አይነት እንቅስቃሴ የጎሳ ባህርይ የተሰጠው ከተንኮለኛ የኦነግ-አደፓ እና ትህነግ ፕሮፓጋንዳ ነው። ይህ ማለት ለአገር የሚጠቅመውን በማጥፋት ጎጅ የሆነው እንድንሰራፋ ማድረግ ማለት ነው። ይህ ደግሞ የተሳሳተ እርምጃ እና ግንዛቤ የዋህ የሆነው ህዝብ እንድይዝ የማድረግ የውዥንብር ድርጊት ነው። የስንዴውን ማሳ አረም ለማረም ስንዴውን በመንቀል የእንክርዳዱ ቡቃያ በመተው እንድያድግ ማድረግ እንደማለት ነው። ኦነግ እና ትህነግ ብቻ ናቸው ስትራቴጅክ የኢትዮጵያ ጠላቶች - መደምሰስ ወይም መጥፋት አለባቸው። በርዕዮተ አለም ላይ የተመረኮዘ የዜግነት ፓለቲካ ጠቃሚ መሆኑ ግልጽ ነው። ግን በፍጹም አሁን ያሊመጣ አይችልም። ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ ነው ኢትዮጵያ ያልተረጋጋች በሁለት ጠንቀኞች ኦነግ እና ትህነግ የምትታመስ አገር ነች - እነሱም ይህ እንዳይኖር ማንኛውንም ሃይል ይጠቀማሉ። ስለዚህ አገሪቱ ሌላ አብዮት ውስጥ መግባቷ አይቀርም ባይ ነኝ። የዜጋ ፓለቲካ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሳካል ማለት በሬ ወተት ይሰጣል ብሎ መሞኘት ነው።

Horus wrote:
09 Mar 2022, 20:26
አበረ፣
የጎሳ ፖለቲካ ተሸካሚዎች ትህነግና ኦነግ ብቻ አይደሉም፤ በኢትዮጵያ ዜግነት ሳይሆን በራሱ ዘውግ የተደራጀው ሁሉ ካማራ እስከ ደቡብ፣ ካፋር እስከ ሱማሊ ያለው ሁሉ የዘር ፖለቲካ ተሸካሚ ነው ። የዘር መደራጀት እምቢ ብለው በዜግነት መታገል ካልተጀመረ ስልጣን ላይ ያሉትን የኦሮሞ ሆነ የትግሬ ያማራ ሆነ የሲዳማ የዘር ነጋዴዎችን የሚነካ ነገር አይመጣም! በዘር ተገራጅቶ እነሱን መቃወም ከንቱ ግዜ ማባከን ነው!
አበረ
አንዴ ልድገመው፤ በጎሳ የመጣው የኢትዮጵያ መከራ በሌላ ጎሳ ትግል አይጠፋም! ትግሬ በኦሮሞ ቢተካ፣ ኦሮሞ ባማራ ቢተካ ቴዲ አፍሮ ጨርሶታል! አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ የተባለው ነው! ሰላም!

Post Reply