***{{{BREAKING NEWS}}}***Etdf-Asf Have Cut Weldia-Meqelle Road & Going 2Wards Mersa((MEQELLE IS NEXT))!!! WEEY GUUD !!!
Posted: 11 Dec 2021, 12:01
==========================================================================================================
Natnael Mekonnen
t0i26m1uoi334g8asahuf65 ·
ሰበር ዜና
#Ethiopia : በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ዋናውን የወልድያ መቀሌ ጎዳና ቆርጦታል

===========================================================================================================
Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
21tt8tgi38m48g6a ·
ሰበር ዜና
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ዋናውን የወልድያ መቀሌ ጎዳና ቆርጦታል፡፡
***************************
( ኢ ፕ ድ)
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በአሸባሪው ወራሪ ላይ በሰነዘሩት ክንደ ብርቱ ማጥቃት፣ በምሥራቅ ግንባር ስትራቴጂያዊ የሆኑትንና ወራሪው በፍጻሜ ዋዜማ ላይ መሆኑን የሚያሳዩትን የዞብል ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርጆ፣ ፎኪሳ እና ቦረን ከተሞችን ተቆጣጥሯል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን በመቆጣጠር የወልድያ መቀሌ ዋናውን አውራ ጎዳና በመቁረጥ ጠላት መውጫ አጥቶ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ግንባር የድሬ ሮቃና የሶዶማ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከተሞችና ተራሮች በመቆጣጠር ጥምር ጦሩ ወደ ሐራ ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል፡፡
በውጫሌ ግንባር ደግሞ የአምባሰል ከፍተኛ ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ የሮቢትና የጎልቦን፣ በወረባቦ ወረዳ የሚሌ ኮትቻን፣ በሐብሩ ወረዳ የኮልቦን፣ የመርካታና የፋጂን አካባቢዎችን በመቆጣጣር ወደ መርሳ ከተማ እየገሠገሠ ነው፡፡
በእነዚህ ግንባሮች በተደረገው ኦፕሬሽን በአሸባሪው የጠላት ኃይል ላይ በተሠነዘረበት ማጥቃት ጠላት ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆኗል፡፡ የወገን የመካናይዝድ ኃይልና ንሥሮቹ የአየር ኃይሉ በጥምረት ባካሄዱት ኦፕሬሽን የጠላት ኃይል ምንም ዓይነት ተሸከርካሪ እና ከባድ መሣሪያዎችን ይዞ እንዳይንቀሳቀስ ስላደረጉት፣ ጠላት በየአቅጣጫው ጥሎ ለመፈርጥጥ ተገድዷል፡፡
ለበርካታ ቀናት ያከማቻቸውን ቁስለኞችንም ጥሎ ፈርጥጧል፡፡ የዘረፈውን ንብረትም በየቦታው እያዝረከረከ እግሬ አውጪኝ በማለት ላይ ይገኛል፡፡ ጠላት ዋናው የቆቦ ወልድያ መንገድ ስለተዘጋበት በድንብርብር በጋሸና ላሊበላ በኩል ለማምለጥ ከፍተኛ ትንቅንቅ ቢያደርግም በወገን ጥምር ጦር እንደ ቅጠል ከመርገፍ አልተረፈም፡፡
በወረራ ውስጥ የቆየው ኅብረተሰብ በከፍተኛ ወኔና ጀግንነት በመነሣሣት ከወገን ጦር ጋር ተባብሮ በመሰለፍ አኩሪ ተጋድሎ ፈጽሟል፡፡ አሁንም ክንደ ብርቱውን የወገን ጥምር ጦር መቋቋም አቅቶት በየጢሻው የተበተነውን የአሸባሪውን ጀሌ፣ የየአካባቢው ሕዝብ በመማረክ፣ እምቢ ያለውንም በመደምሰስ የጀግንነት ተግባሩን እንዲፈጽም መንግሥት ጥሪ ያቀርባል፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለኢፕድ በላከው በዚሁ መረጃ "ነጻነታችንን የምናረጋግጠው በተባበረ ክንዳችን ነው!" ሲል ገልጾአል። See less


