በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል!
Posted: 09 Nov 2021, 04:49
ኣዪ ኢትዮጵያ ፓትሪያርኩ ሙፍቲዉና ካርዲናሉ የት ሄደው ነው ኦቦሳንጆ መንግሥትንና “ኣማጺያኑን” ሚያሸማግሉት፧?
እኒህ ሶስት ሰዎች እድሉ ልክ እንደ ኦቦሳንጆ ቢመቻችላቸው፡ ኢትዮጵያዊ እውነታን በመጋፈጥና በማፍረጥረጥ፡ ዘለቄታዊ መፍትሔን ይዘው እንደሚያሸማግሉ ሚሊዮኖች ያምናሉ።
ከዚህ በፊት በነዚህ ኣካላት እርቁ ተሞክሮ ነበር የሚሉ ሰዎች ኣይጠፉም፡ እርቅ ለማምጣት ደከመኝ ሰለቸኝ ማለት አይገባም። ኦቦሳንጆም ቢሆኑ ባንዴ ችግሩን ኣይፈቱትም ሶስቴ አራቴ መመላለሳቸው አይቀርም!
ላበሾች የሚያምርባቸው በራሳቸው የሃይማኖት አባቶች አማካኝነት ችግራቸውን ቢፈቱ ነው። ያለ አንዳች ‘ሪሞርኬ’ ለነዚህ ሶስት የሃይማኖት አባቶች እድሉን ቢሰጡ ኢትዮጵያዊ ውበት ያለው ፈውስ ከውስጥ ማግኘት በቻላችሁ ነበር፡ ብለን ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እንመክራለን። ኦቦሳንጆ ደግሞ እነ ሚኒልክ ሳልሳዊ እንዳሉት ኣገራቸው ሄደው የቦኮሃራምን ቀውስ ይፈቱ ዘንድ “የቤት ሥራ” ይሰጣቸው! ኣይሆንም በነዚህ ሶስት አካላት ኣንሸማገልም የሚል ኣካልም “ባዕድ ኣምላኺ” መሆኑን ለሰፊዉ የጦቢያ ህዝብ በገዛ ድርጊቱ ይመሰክራል።
ሰላምና ፍቅር ለታላቋ ስጦቢያ!