ወያኔ በወላይታ ብጥብጥ ለማስነሳት ገንዘብ አስታጥቆ የላካቸው ንብረት ሲያቃጥሉ!!!!
Posted: 21 Dec 2019, 11:17
የዎላይታ ብሔር በክልል እንደራጅ ጥያቄ ከተጀመበረት ጊዜ አንስቶ ፍፁም ሠለማዊ በሆነ መንገድ እየተጠየቀ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ጥያቄውም በዚህ ሁሉ አግባብ ግን ምላሽ ሳያገኝ በክልል ምክር ቤት ለአንድ ዓመት ሙሉ መቆየቱ ያስቆጣቸው የተለያዩ ማህበራዊ መሠረቶችም የተለያዩ ዜዴዎችን በመጠቀም ጥያቄያቸውን በሠለማዊ መንግድ እያስተጋቡ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ አካላት ግን ጥያቄውን ከሠላማዊ መንገድ እንዲያፈናግጥና አቅጣጫ እንዲስት ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ እነደሆነ ተደርሶቤታል፡፡
በተለይ በቀን 09/04/2012 ዓ፣ም ወደ ማታ አካባቢ በዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተፈፀመው እኩይ ተግባር ፍፁም ኢ- ሠላማዊ በመሆኑ ይወገዛል፡፡
የዎብን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ታደሰ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤትን በእሳት ለማቀጠል የተሞከረው ሙከራ በጽ/ቤቱ ሠራተኞች፤ በፀጥታ አካላትና በአካባቢው በሚገኙ ማህበረሰብ አካላት ባደረጉት ርብርብ በቁጥጥር ማዋል ተችሏል፡፡
ተግባሩን የፈፀመውም አቶ አንዱዓለም ታደሰ ሲሆን እጅ ከፍንጅ ተይዞ በህግ ቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ ከዚህ ውጭ ከጉዳዩ ጋር ተያይዘው በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚነዙ መረጃጃዎችም ከእውነት የራቁ መሆኑን ህብረተሰቡ በማወቅ የማህበራዊ ሚዲያውን በተገቢውና የመረጃው ተገቢነትን አውቆ እንዲጠቀም ተጠይቋል፡፡ ይህ ስልት ሠለማዊ ትግል ባለመሆኑ ሁሉም ሰው ሊያወግዜው እንደሚገባና በየአካባቢያችንም ጥያቄውን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ለመቀየር የሚንቀሳቀስ አካላትን ለህግ በማቅረብ ህብረተሰቡ ለከተማው ሠላምና ፀጥታ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡
***
ምንጭ:- የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ህዝብ ግንኙነት ዩኒት ታህሳስ 2012