Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39792
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 17 Aug 2023, 16:33

DDT/Naga Tuma,
የሆነ ማንነት ፈብርከህ ልትከበር እስከ ምትሞት እየታከት ነው ። ያንተ ቁጥር 1 ችግርና የውድቀትህ ምንጭ ይህ ነው ። መመሪያ እራሱ ቃላቱ ፋና እና ዲካ ላስተማረህ ግዕዝ አክብሮት ስጥ! አንድ ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ ካልቸር ይማራል ያ ምንም ማለት አይደለም ። ያን እስከ ካድክ እና በእረኛነትና ወራሪነት ባህሪህ እስከ ቀጠልቅ ድረስ አሁን ያለውን ጥላቻ ነው የምታመርተው!

እስቲ መጀመሪያ ቋንቋህ ከየት እንደ መጣ እወቅ?!

ሲቀጥል እነዚህ ምታያቸው ቋንቋቸውን ለውጠህ ግን ባህላቸው ተሸክመህ ያለሀው ክርስትናንን፣ እልልታን ያስተማሩህ፣ ሹሩባን ያስተማሩህ፣እንጊጫን ያስተማሩህ ፣ ኤሬቻን የሰጡህ አባቶችህ አያቶችህ የገላንና ያዬ ጉራጌዎች ናቸው ። ዛሬ ዘራችውን ልታጠፋ ትዳክራለህ !!!

ይህ የምታየው የፊቃቆ ለቀማና (የአክርማ ለቀማና) የአዳብና ባህል ከነገ ፍልሰታ ነሃሴ 15 ደመራ መትከያ ጀምሮ አዲስ አመትን (አክራሚ) አልፎ እሰከ መስቀል የሚከበረው የልጃገረዶችና ወጣቶች በዓል ነው ። ለሰጠንህ ካልቸር አመስግን !!!

ፊቃቆ ማለት አክርማ ሴቶች ልዩ ልዩ ስፌት የሚሰሩበት ስንደዶ ሳር ነው ። አንዲት ልጃገረድ ለጋብቻ ደርሳ የሴትነት ሙያ የምትማርበት ማለት ነው ። አዳብና ማለት አደይ አብና ማለት ነው። የአደይ አበባ መስጠት፣ መስጫ ባህል ሲሆን በንቁጣጣሽ ለጃገረዶች ከቤት ቤት የሚሰጡት አበባና እስከ መስቀል ድረስ በነጻ ለጨዋታ ወጥተው ከጎረምሶች ጋር በመጫወት በሎሚ የሚወጉበት ፍቅረኛ የሚመርጡበት ውድ የጉራጌ ወጣት ባህል ነው ።

እስቲ የገላን ልጃገረዶች ይህን ባህል እስካሁን ይዘውት እንደ ሆነ እናያለን ። አንተ ግ ን መጀምሪያ ታሪክን አትካድ፣ ሁለተኛ ይህን ሁሉ ባህል ያስተማሩህ ቅድመ አያቶችክን አትካድ! ችግርህ ያ ነው ከየት እንደ መጣህ እየካድ ወደፊት ለመሄድ መሞከርህ !

ፍቃቆ ማለት ይህ ነው!

Horus
Senior Member+
Posts: 39792
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 17 Aug 2023, 17:01

ያለፈው አመት አዳብና በአንድ መንደር (በዋጮ ገፈርሳ ሚካኤል) ። ገፈርሳ ፣ በሰባት ቤት ጀፎረ ለጋራ ጥቅም የተተወ የወል መሬት ማለት ነው ። በጉራጌኛ አረብኛም ግፈር፣ ጃፋር መተው ማለት ነው ። አዲሳባ አጠገብ ያለው ገፈርሳ የጥንት ጉራጌዎች የሰየሙት ጀፎረ ነበር!

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 13470
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by Noble Amhara » 17 Aug 2023, 17:07

በጎጃምና በጉራጌ መካከል ምዕራብ ሸዋ ነው።
Horus wrote:
17 Aug 2023, 17:01
ያለፈው አመት አዳብና በአንድ መንደር (በዋጮ ገፈርሳ ሚካኤል) ። ገፈርሳ ፣ በሰባት ቤት ጀፎረ ለጋራ ጥቅም የተተወ የወል መሬት ማለት ነው ። በጉራጌኛ አረብኛም ግፈር፣ ጃፋር መተው ማለት ነው ። አዲሳባ አጠገብ ያለው ገፈርሳ የጥንት ጉራጌዎች የሰየሙት ጀፎረ ነበር!

Horus
Senior Member+
Posts: 39792
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 17 Aug 2023, 17:26

ኖብል አማራ፣
በትክክል ጋፋት ወደ ደጋ ዳሞት ከመሻገሩ በፊትኮ የጋፋት እንደ ገብጣን ድምበርተኛ አገው ምድርኮ ፤ ዛሬ 7 ቤት ጭፈራ ውስጥ አገውኛ አለበት ። ወደ ምስራቅ ስትሄድ የሸዋ ኦሮሞ ባህል የምትለው ያለው ቢሾፍቱ ነው ። የጥንት ገላን በቃ ይህ ነው ። ሕዝቡ ባህሉን እንጆይ ማድረጉ ደስ ያላል ። እንደነ ዲዲቲ ያለ ከሃዲ ቀስ በቀ እውነቱን እያወቀ ይሄዳል !

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 13470
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by Noble Amhara » 17 Aug 2023, 17:32

Horus wrote:
17 Aug 2023, 17:26
ኖብል አማራ፣
በትክክል ጋፋት ወደ ደጋ ዳሞት ከመሻገሩ በፊትኮ የጋፋት እንደ ገብጣን ድምበርተኛ አገው ምድርኮ ፤ ዛሬ 7 ቤት ጭፈራ ውስጥ አገውኛ አለበት ። ወደ ምስራቅ ስትሄድ የሸዋ ኦሮሞ ባህል የምትለው ያለው ቢሾፍቱ ነው ። የጥንት ገላን በቃ ይህ ነው ። ሕዝቡ ባህሉን እንጆይ ማድረጉ ደስ ያላል ። እንደነ ዲዲቲ ያለ ከሃዲ ቀስ በቀ እውነቱን እያወቀ ይሄዳል !
Guraginya and Agawinya are very similar languages This leads us to believe Gaffat were actually Agaws of Shoua. Engicca/Engicha is Agaw Celebration

Naga Tuma
Member+
Posts: 6754
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by Naga Tuma » 17 Aug 2023, 18:36

Horus wrote:
17 Aug 2023, 16:33
ሲቀጥል እነዚህ ምታያቸው ቋንቋቸውን ለውጠህ ግን ባህላቸው ተሸክመህ ያለሀው ክርስትናንን፣ እልልታን ያስተማሩህ፣ ሹሩባን ያስተማሩህ፣እንጊጫን ያስተማሩህ ፣ ኤሬቻን የሰጡህ አባቶችህ አያቶችህ የገላንና ያዬ ጉራጌዎች ናቸው ። ዛሬ ዘራችውን ልታጠፋ ትዳክራለህ !!!
እኔ መሠረታችን እያልኩ ኣትካድ ትለኛለህ። DDT እና Naga Tuma ኣንድ ግለሰብ ትላለህ።

ኣንተ ከተሜ፣ እኔ እረኝነትን የማዉቅ ገጠሬ፣ መወያየት እንዴት እንቻልበት?

እኔ ወደ አስር ሺህ ዐመታት ፎቀቅ ላረግህ ነዉ የምጥረዉ። ክርስትና ስትለኝ አመርቲ እለሃለሁ። ፎቀቅ ካላልክ ኣታየዉም። ኣታዉቀዉም።

ስለዚህ እስቲ ወደ ገጠሩ ፎቀቅ ማለት ትችላልህ? ፈረስ መጋለብ ትችላለህ? ገርተህ ታዉቃለህ? ዱር/ድሮ አስር ሺህ ዐመታት በፊት የዱር ፈርስን ማላመድ የተጀመረበትን ግዜ ወይም ዱሪንግ ዘነጋህ?

እስቲ ፈረሶች በግዕዝ የሚለዩበትን ንገረኝ። መጋለ፣ ዳማ፣ ቦረ፣ ቡሎ፣ ኦዶልቸ፣ ሻሾ ማለት ትችላለህ? እስቲ የምታዉቀዉ ግዕዝ ዉስጥ ፈልጋቸዉ እና ሻሾ እንዴት ሻይን እንደሆነ ንገረን። ፈቀቅ ያረገሃል።

ከቻልኩ ለወደፊት እንደ ቭትሩቭያን ማን ለማስቀርጸዉ ቃላት ሶስት ልጨምር።

ሶምበ/ሳምባ፣
ሞረ/ማራ፣
ጮመ/ጮማ፣

Horus
Senior Member+
Posts: 39792
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 17 Aug 2023, 21:47

Noble Amhara wrote:
17 Aug 2023, 17:32
Horus wrote:
17 Aug 2023, 17:26
ኖብል አማራ፣
በትክክል ጋፋት ወደ ደጋ ዳሞት ከመሻገሩ በፊትኮ የጋፋት እንደ ገብጣን ድምበርተኛ አገው ምድርኮ ፤ ዛሬ 7 ቤት ጭፈራ ውስጥ አገውኛ አለበት ። ወደ ምስራቅ ስትሄድ የሸዋ ኦሮሞ ባህል የምትለው ያለው ቢሾፍቱ ነው ። የጥንት ገላን በቃ ይህ ነው ። ሕዝቡ ባህሉን እንጆይ ማድረጉ ደስ ያላል ። እንደነ ዲዲቲ ያለ ከሃዲ ቀስ በቀ እውነቱን እያወቀ ይሄዳል !
Guraginya and Agawinya are very similar languages This leads us to believe Gaffat were actually Agaws of Shoua. Engicca/Engicha is Agaw Celebration

ኖብል አማራ፣
አገውኛ ቋንቋ የሴም ቋንቋ አይደለም ። አገውኛ ከአማርኛ፣ ትግርኛና ጉራጌኛ የሚያመሳስለው ሰዋስዉ ብቻ ነው ። ማለትም ሌሎችች የሴም ቋንቋዎን ዲዲቲ በላ ጨጨብሳ ሲሉ (ሳብጀክት ፣ቨርብ ኦብጀክት) ። የኢትዮጵያ ሴም ቋንቋዎች ዲዲቲ ጨጨብሳ በላ ይላሉ (ሳብጀጅክት ፣ ኦብጀክት፣ ቨርብ) ። ጋፋትኛ ቋንቋ ሀርት ዝ በሚባል ሊንጉዊስት ተጠንቶ 8ኛው የኢትዮሴሚቲክ ቋንቋ ነውኮ ። (ትግረ፣ ትግርኛ፣ አማርኛ፣ አርጎቤ፣ ሃረሬ፣ ጉራጌ፣ ጋፋት፣ ግዕዝ) ። አንተ እንኳን ሊስት በደረከው የቃላት ሊስት አንድም ጋፋትና አገው ተምሳሳይ ቃላት አላገኘንም ።

Horus
Senior Member+
Posts: 39792
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 17 Aug 2023, 22:10

Naga Tuma wrote:
17 Aug 2023, 18:36
Horus wrote:
17 Aug 2023, 16:33
ሲቀጥል እነዚህ ምታያቸው ቋንቋቸውን ለውጠህ ግን ባህላቸው ተሸክመህ ያለሀው ክርስትናንን፣ እልልታን ያስተማሩህ፣ ሹሩባን ያስተማሩህ፣እንጊጫን ያስተማሩህ ፣ ኤሬቻን የሰጡህ አባቶችህ አያቶችህ የገላንና ያዬ ጉራጌዎች ናቸው ። ዛሬ ዘራችውን ልታጠፋ ትዳክራለህ !!!
እኔ መሠረታችን እያልኩ ኣትካድ ትለኛለህ። DDT እና Naga Tuma ኣንድ ግለሰብ ትላለህ።

ኣንተ ከተሜ፣ እኔ እረኝነትን የማዉቅ ገጠሬ፣ መወያየት እንዴት እንቻልበት?

እኔ ወደ አስር ሺህ ዐመታት ፎቀቅ ላረግህ ነዉ የምጥረዉ። ክርስትና ስትለኝ አመርቲ እለሃለሁ። ፎቀቅ ካላልክ ኣታየዉም። ኣታዉቀዉም።

ስለዚህ እስቲ ወደ ገጠሩ ፎቀቅ ማለት ትችላልህ? ፈረስ መጋለብ ትችላለህ? ገርተህ ታዉቃለህ? ዱር/ድሮ አስር ሺህ ዐመታት በፊት የዱር ፈርስን ማላመድ የተጀመረበትን ግዜ ወይም ዱሪንግ ዘነጋህ?

እስቲ ፈረሶች በግዕዝ የሚለዩበትን ንገረኝ። መጋለ፣ ዳማ፣ ቦረ፣ ቡሎ፣ ኦዶልቸ፣ ሻሾ ማለት ትችላለህ? እስቲ የምታዉቀዉ ግዕዝ ዉስጥ ፈልጋቸዉ እና ሻሾ እንዴት ሻይን እንደሆነ ንገረን። ፈቀቅ ያረገሃል።

ከቻልኩ ለወደፊት እንደ ቭትሩቭያን ማን ለማስቀርጸዉ ቃላት ሶስት ልጨምር።

ሶምበ/ሳምባ፣
ሞረ/ማራ፣
ጮመ/ጮማ፣
ናጋ
የፈረሱን እርሳው። ተክለጻዲክ መኩሪያ አለ የሚባል ሶርስ ጣሊይን በመኖር ባለም ላይ ስለኢትዮጵያ የተጻፈ ጥናት አድረገው ኦሮሞ (በያኔ ጋላ) ሸዋ ከደረሰ በኋል ፈረስ መጠቀም ከጉራጌ ተማረ ይላሉ ። ኦሮሞ (ጋላ) ሸዋ እስከ ሚደርስ ፈረስ የመጠቀም ባህል አልነበረውም ።

ፈርስ (ፋርዳ) የፋሪስ ቃል ሲሆን ፈረስ ማለት ቃሉ እራሱ ከፋር የመጣ እንሰሳ ማለት ነው። ሳታጠና አትናገር ብዬ ነበር ።

ዛሬ ፈረስ ከተማርክ በኋላ የምትጠቀማቸው ቃላት ጉራጌኛ ናቸው ። ጉግስ ጉራጌኛ ነው ። ዛሬ ትጉሙን አልነግርህም ። ባንተ ልሳን ጉግስ ካለ ነገረን ። ሶምሶማ ጉራጌኛ ነው። ስግሪያ ግዕዝም ጉራጌኛ አማርኛም ነው ። እኔ ባስር አመቴ ደርማ የተገዛልኝ የፈርሰ ካልቸር ባላገር ነኝ። ደርማ ምን ማለት ነው? ልድገመው ስታጠና አትናገር ። ባካባቢህ ጉራጌዎች ካሉ ቋንቋ ያልረሱ ጉገት ወይም ጉግ ምን ማለት ነው በላቸው?

ከዚያ በተረፈ በአፋን ኦሮሞ ውስጥ የውሰት ቃላቶች እንዳሉ ማጥናት ያንተ ፈንታ ። አንድ ኦሮሞ ጓደኛዬ እንደ ነገረኝ ከሆነ እራት ማለት ኧርባታወይም ኢርባታ ይባላ አለኝ ። ይህም ማለት እራት ለማለት የተውሶ ቃል ምትጠቀመው ! እራት (ኧርባት) በጉራጌኛ ምዕራብ (የጸሃይ መግባት) ጋር የመጣ ከጸሃይ ኧርብ (መጥለቅ) በኋላ የሚበላ ማለት ነው። ቃላት መዋስ በአለም ሕዝብ ዘንድ ምንም ክፋት የለውም ። ግ ን አንድ ካልቸር ከሌላ ካቸር የተዋሳቸውን ነገሮች በክብር ይናገራል ። አንተ ይህን ማድረግ አትችልም ። ለመማር፣ ለማወቅ ስለማትገልግ ።

ብርቱካን የሚባለው ፍሬ ፖርቱጋሎች ይዘውት ስለመጡ ልክ ፈርስ ፋርስ እንደ ሚለው ዛሬ ብርቱካን የምንለው ፍሬ ፖርቹጋል ማለት ነው ። እስቲ አንተም የኔ ምትላቸውን ቃላት ከየት እንደ መጡ ተመራመር ።

እውቀት ብርሃን ነው ከዉሸትም፣ ከስህተትም ከሃፍረትም ይጠብቅሃል !

በተረፈ ውሾቻን ብልዩ ልዩ ስም እንደ ምንጠራ ሁሉ ፈረሶቻን ብሾ፣ ቡሎ፣ ነብሴ የተፈለገ ስም የሰጣቸዋል ፣ አንተ ምን ያክል ናያኢቭ አላዋቂ እንደ ሆንክ ገባኝ ። እየዚያ የፈረስ ፔት ስሞች ዉሻህን ቦቢ እንደ ማለት እንደ ሆነ እንኳ አታቅም! ያሳፍራል !

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by sun » 17 Aug 2023, 22:31

Horus wrote:
05 Aug 2023, 16:26
ፋኖ የሚለው ቃል በግእዝ፣ በላቲን፣ በግሪክ፣ በሳንስክሪት (ሂንዲ) ምንም ሳይለወጥ በድምጽም በትርጉምም አንድ የሆነ እጅግ ትንታዊና ግዙፍ ቃል ነው ።

ቃሉ የተወለደው በጥንታዊት ግብጽ ነው ። ዛሬ ‘ፋ’ የተባለው የቃሉ መጀምሪያ ክፍል ግብጾች ባ፣ ወይም ፓ፣ ወይም ፋ ይበሉት አይበሉት በውል አይታወቅም ።

በእኔ ግምት ‘ባ’ ይባል ነበር ባይ ነኝ። ይህም ያልኩት የፋ ተዛማጅ ግእዝ ቃል ቦ (ሆነ፣ ታየ፣ ተከሰተ) ስለሆነ ነው።

የግብጽ ትርጉሙ ግን ይታወቃል ። በራ፣ ታየ፣ ተገለጸ ማለት ነው። ይህ ዛሬም ያለው ትርጉሙ ነው ።

ፋኖ የሚለው ቃል ሁለተኛ ክፍል ‘ኖ ‘፣ ነ ፣ የሚለው ቃል ነው ።

ይህ ድምጽ በጥንታዊ ግብጽ ‘ረ ‘ ነበር ። ወደ ጥንታዊ ሴም ቋንቋ ሲለወጥ ‘ለ’ ሆነ ። በግእዝና አማርኛ ‘ነ ‘ ሆነ።

የግብጾች ‘ረ’ ብርሃን ወይም ጸሃይ ማለት ነው ። የሴማዊያን ‘ለ’ ብርሃን’ ማለት ነው ።

የብርሃን አምላክ ስም ‘ኧል‘ ‘ኤል‘ ኤላ፣ ኤሎሄ፣ ወዘተ ከዚያ ቃል የተቀዱ ናቸው ።

ስለዚህ ፈና፣ ፋና፣ ፌኖ፣ ፊና፣ ፋኖ ማለት ፏ ያለ ብርሃን፣ ፋ ያለ የበራ ብርሃን ፣ በብርሃን መገለጽ ማለት ሲሆን የቀሩት ልዩ ልዩ አጠቃቀሞቹ እንደ ሚከተለው ነው።

ፋኖ (ቅጽል) መሪ ብርሃን፣ አመልካች፣ ጠቋሚ፣ አቅጣጫ የሚያሳይ ማለትም ቀዳሚ ማለት ሲሆን ባንድ ቃል ግምባር ቀደም መሪ ማለት ነው ።

ፈነው ተገለጸ ብሩህ ሆነ ማለት ነው ።

ፍኖት መንገድ፣ አቅጣጫ ፣ አመልካች ማለት ነው ። ለምሳሌ ፍኖተ ሰላም፣ ፍኖተ ብርሃን፣ ፍኖተ ሰማይ ..

ፋና የወደፊት ጉዞ የሚያሳይ ሲሆን ሌሎች ፋና ወጊ ይሉታል

ሌሎችም ብዙ የኢትዮፒክ ዝርያዎች አሉት ።

በግሪክና ላቲን ፌኖማ መገለጽ፣ አፒራንስ ማለት ሲሆን ፌኖሜና ባይምሮ ውስት የሚታይ ማለት ነው ።

ፌኖሜኖሎጂ የሚባለው የፍልስፍና መስክ በዚያ የተሰየመ ነው ። ሪያሊቲ የሚታወቀው ባይምሮ ውስጥ በሚገለጽ ምስል ነው የሚለው ፍልስፍና ።

ኤፒፋኒ ወይም ጥምቀት እግዚአብሄር ለሰው ወይም ለሰው አይምሮ የተገለጸበት ማለት ነው ።

በአጭሩ በዚህ እጅግ ጥልቅና ጥንታዊ ቃል ነው በቅጽል ፎርሙ ፋኖ ብሎ አማራ የነጻነት ትግል ግምባር ቀደም ጦረኞችን የሰየመው ።

ድል ላማራ! ድል ለኢትዮጵያ!!!

ሆረስ ዐይነ ብርሃን
https://www.dw.com/en/haiti-un-says-gan ... a-65073970

Naga Tuma
Member+
Posts: 6754
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by Naga Tuma » 18 Aug 2023, 14:52

Horus wrote:
17 Aug 2023, 22:10
Naga Tuma wrote:
17 Aug 2023, 18:36
Horus wrote:
17 Aug 2023, 16:33
ሲቀጥል እነዚህ ምታያቸው ቋንቋቸውን ለውጠህ ግን ባህላቸው ተሸክመህ ያለሀው ክርስትናንን፣ እልልታን ያስተማሩህ፣ ሹሩባን ያስተማሩህ፣እንጊጫን ያስተማሩህ ፣ ኤሬቻን የሰጡህ አባቶችህ አያቶችህ የገላንና ያዬ ጉራጌዎች ናቸው ። ዛሬ ዘራችውን ልታጠፋ ትዳክራለህ !!!
እኔ መሠረታችን እያልኩ ኣትካድ ትለኛለህ። DDT እና Naga Tuma ኣንድ ግለሰብ ትላለህ።

ኣንተ ከተሜ፣ እኔ እረኝነትን የማዉቅ ገጠሬ፣ መወያየት እንዴት እንቻልበት?

እኔ ወደ አስር ሺህ ዐመታት ፎቀቅ ላረግህ ነዉ የምጥረዉ። ክርስትና ስትለኝ አመርቲ እለሃለሁ። ፎቀቅ ካላልክ ኣታየዉም። ኣታዉቀዉም።

ስለዚህ እስቲ ወደ ገጠሩ ፎቀቅ ማለት ትችላልህ? ፈረስ መጋለብ ትችላለህ? ገርተህ ታዉቃለህ? ዱር/ድሮ አስር ሺህ ዐመታት በፊት የዱር ፈርስን ማላመድ የተጀመረበትን ግዜ ወይም ዱሪንግ ዘነጋህ?

እስቲ ፈረሶች በግዕዝ የሚለዩበትን ንገረኝ። መጋለ፣ ዳማ፣ ቦረ፣ ቡሎ፣ ኦዶልቸ፣ ሻሾ ማለት ትችላለህ? እስቲ የምታዉቀዉ ግዕዝ ዉስጥ ፈልጋቸዉ እና ሻሾ እንዴት ሻይን እንደሆነ ንገረን። ፈቀቅ ያረገሃል።

ከቻልኩ ለወደፊት እንደ ቭትሩቭያን ማን ለማስቀርጸዉ ቃላት ሶስት ልጨምር።

ሶምበ/ሳምባ፣
ሞረ/ማራ፣
ጮመ/ጮማ፣
ናጋ
የፈረሱን እርሳው። ተክለጻዲክ መኩሪያ አለ የሚባል ሶርስ ጣሊይን በመኖር ባለም ላይ ስለኢትዮጵያ የተጻፈ ጥናት አድረገው ኦሮሞ (በያኔ ጋላ) ሸዋ ከደረሰ በኋል ፈረስ መጠቀም ከጉራጌ ተማረ ይላሉ ። ኦሮሞ (ጋላ) ሸዋ እስከ ሚደርስ ፈረስ የመጠቀም ባህል አልነበረውም ።

ፈርስ (ፋርዳ) የፋሪስ ቃል ሲሆን ፈረስ ማለት ቃሉ እራሱ ከፋር የመጣ እንሰሳ ማለት ነው። ሳታጠና አትናገር ብዬ ነበር ።

ዛሬ ፈረስ ከተማርክ በኋላ የምትጠቀማቸው ቃላት ጉራጌኛ ናቸው ። ጉግስ ጉራጌኛ ነው ። ዛሬ ትጉሙን አልነግርህም ። ባንተ ልሳን ጉግስ ካለ ነገረን ። ሶምሶማ ጉራጌኛ ነው። ስግሪያ ግዕዝም ጉራጌኛ አማርኛም ነው ። እኔ ባስር አመቴ ደርማ የተገዛልኝ የፈርሰ ካልቸር ባላገር ነኝ። ደርማ ምን ማለት ነው? ልድገመው ስታጠና አትናገር ። ባካባቢህ ጉራጌዎች ካሉ ቋንቋ ያልረሱ ጉገት ወይም ጉግ ምን ማለት ነው በላቸው?

ከዚያ በተረፈ በአፋን ኦሮሞ ውስጥ የውሰት ቃላቶች እንዳሉ ማጥናት ያንተ ፈንታ ። አንድ ኦሮሞ ጓደኛዬ እንደ ነገረኝ ከሆነ እራት ማለት ኧርባታወይም ኢርባታ ይባላ አለኝ ። ይህም ማለት እራት ለማለት የተውሶ ቃል ምትጠቀመው ! እራት (ኧርባት) በጉራጌኛ ምዕራብ (የጸሃይ መግባት) ጋር የመጣ ከጸሃይ ኧርብ (መጥለቅ) በኋላ የሚበላ ማለት ነው። ቃላት መዋስ በአለም ሕዝብ ዘንድ ምንም ክፋት የለውም ። ግ ን አንድ ካልቸር ከሌላ ካቸር የተዋሳቸውን ነገሮች በክብር ይናገራል ። አንተ ይህን ማድረግ አትችልም ። ለመማር፣ ለማወቅ ስለማትገልግ ።

ብርቱካን የሚባለው ፍሬ ፖርቱጋሎች ይዘውት ስለመጡ ልክ ፈርስ ፋርስ እንደ ሚለው ዛሬ ብርቱካን የምንለው ፍሬ ፖርቹጋል ማለት ነው ። እስቲ አንተም የኔ ምትላቸውን ቃላት ከየት እንደ መጡ ተመራመር ።

እውቀት ብርሃን ነው ከዉሸትም፣ ከስህተትም ከሃፍረትም ይጠብቅሃል !

በተረፈ ውሾቻን ብልዩ ልዩ ስም እንደ ምንጠራ ሁሉ ፈረሶቻን ብሾ፣ ቡሎ፣ ነብሴ የተፈለገ ስም የሰጣቸዋል ፣ አንተ ምን ያክል ናያኢቭ አላዋቂ እንደ ሆንክ ገባኝ ። እየዚያ የፈረስ ፔት ስሞች ዉሻህን ቦቢ እንደ ማለት እንደ ሆነ እንኳ አታቅም! ያሳፍራል !
ኣዉቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት ኣይሰማም ኣሉ?

የአስር ሺህ ዐመታት የኢትዮጵያ ታሪክ ጻፍ እና ኣስተምረኝ ኣልኩህ። ኣዉቃለሁ ስለምትል። ኣልጻፍክም።

የቦረና እና የግዕዝ ዲክሽናሪ ይዘጋጅ እና እንማማር ኣልኩኝ። ደግ ነዉ ማለትህን ኣልሰማሁም ወይም ኣላነበብኩም።

ጉራግኛ ተማሩ፣ ካልተማራችሁ እንደዉሾች ኣትጩሁ ትላላህ። ጉራግኛ ተናጋሪ ነኝ ያለዉ ዶክተር ሃይሌ የመጣነዉ ጉርኣ ከሚባል የኤርትራ ክፍል ነበር ማለቱን ኣስታዉሳለሁ። እዉነት ከሆነ ጉርኣ ኢትዮጵያ ዉስጥ የነበረች ደሴት ኣልነበረችም። ኢትዮጵያዊያን ሌሎች አከባቢም ይኖሩ ነበር። ከዛ ቅርብ ግዜ በፊት ጀምሮ።

ኣንተ መቼ ነዉ በማታዉቀዉ ማፈር የምትጀምረዉ? ባማታዉቀዉ ኣንጠልጥዬህ እንደ ጥቢ ጥቢ ላረግህ ምኞት ዬለኝም። ምኞቴ የበለጠ እወቅ ነዉ። ከቻልክ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6754
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Post by Naga Tuma » 18 Aug 2023, 15:00

Horus wrote:
17 Aug 2023, 21:47
አገውኛ ቋንቋ የሴም ቋንቋ አይደለም ። አገውኛ ከአማርኛ፣ ትግርኛና ጉራጌኛ የሚያመሳስለው ሰዋስዉ ብቻ ነው ።
ፕሮፌሰር ዶናልድ ኤን ለቪን ይህን እንደ ኣንድ ማስረጃ በማስቀመጥ ነዉ ኣማርኛ ሴሜታይዝድ ነዉ ያለዉ። ኣንተ ከማንነት ትግል ዉስጥ መዉጣት ኣስቸገረህ። ይህን የምያክል ማስረጃ የምታዉቃቸዉ ቋንቋዎች ዉስጥ እያየህ።

Post Reply