Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7461
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Naga Tuma » 09 Jun 2022, 19:51

Horus wrote:
02 May 2022, 13:54
ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ሕዝብ የገጠማቸው የእውቀትና ባህል ችግር እጅግ ግዙፍ ነው ። በዚህ አለም ላይ ተፈጥሮ ወይም ኔቸር የሚባል ነገር አለ። ይህ ሰው የሰራው፣ ሰው የፈጠረው አለም አይደለም። ነገር ግን የሰው ልጅ በዚህ የተፈጥሮ አለም ውስጥ ስለሚኖር የፍጥረትን ጸባይ ማወቅ ግድ ይለዋል ። ከተፈጥሮ ጋር በሰላምና በፍቅር መኖር አለበት ። ያ ካልሆነ ሰው እራሱ ይጠፋል።

ሁለተኛው አለም የሰው ልጅ እራሱ የፈጠረው ካልቸር ወይም ባህል ይባላል። ለምሳሌ መኪና፣ ሃይማኖት፣ ፖለቲካ፣ ዶሮ ወጥ እና ቀሚስ የሰው ስራዎች፣ የሰው ባህል፣ የሰው ካልቸር ናቸው። ሌላው ትልቁ እና አደገኛው ሰው ሰራሽ ነገር ሃሳብ ወይም እምነት ነው። ለምሳሌ አለምን (ኔቸርን) የፈጠረ እራሱ ፍጥረት ሳይሆን አላህ ነው፣ እግዚአብሄር ነው። ጎድ ነው። ጌታ ነው። ያዌ ነው፣ ቡድሃ ነው፣ ዋቃ ነው፣ ወዘተ የሚባሉት የሰው ሃሳቦች ናቸው ። እነዚህን ሃሳቦች የፈጠረው ሰው እራሱ ነው።

በአንድ ቃል እምነት ወይም ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ባህል ነው በቃ! የሰው ልጅን ውድቀት እያስከተለ ያለው የዘመናት ስህተት የሰው ልጅ ኔቸርና ካልቸርን ለያይቶ፣ አንዱ ካንዱ አቃርኖ፣ አንዱ ያንዱ ጠላት አድርጎ የሚደመድም ደደብ ሃሳብ መፍጠሩ ነው። ይህ ልክ እነ ዴካርት የሰው አካልና የሰው አይምሮ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፣ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው እንዳሉት ማለት ነው።

የሰው ልጅ አለምን አልፈጠረም። የሰው ልጅ እራሱ በተፈጥሮ የተፈጠረ ነገር እንጂ እራሱ ሕይወትን የፈጠረ ሃይል አይደለም። ካልቸር ወይም ባህል የሰው ልጅ ከፍጥረት የኮረጀው ሞዴል ነው ። ፈረስ አራት እግሮች ስላሉት ሰው አራት ጎማ ያለው መኪና ሰራ። የሰው ችሎታ ተፈጥሮን መኮረጅ ነው። የሰው ልጅ የተፈጥሮን አመክኞ ምን እንደ ሆነ አያውቅም። ፈረስ ለምን አራት እግር እንዳለው አያውቅም።

ስለ እምነትም፣ ስለሃይማኖት፣ ስለሌላ አለማዊ፣ ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና መለኮታዊ ነገሮች ሁሉ ያለው ግንዛቤ ተመሳሳይ ነው። በኮረጃቸው ነገሮች ያምናል። ያን እምነት ሃሳብ የለዋል። ያን እምነት ስለደጋገመው፣ ደጋግሞ ስላመነው እውቀት ይለዋል ። የሰው ልጅ በራሱ ካልቸር፣ በራሱ ባህል፣ በራሱ ሃሳብ ታስሮ ተቀፍድዶ በራሱ እስር ቤት ውስጥ የሚማቅቅ አሳዛኝ እንሰሳ፣ አሳዛኝ ፍጡር ነው ።

ኢትዮጵያዊያን የጎሳ እምነት፣ የሃይማኖት እምነት፣ የካልቸር እምነት ሁሉም ሰው ሰራሽ ባህሎች፣ ሰው ሰራሽ አርቲፋክቶች መሆናቸውን እስካልገባቸው ድረስ ከዚህ የአመጽ መከራ ሊላቀቁ አይችሉም። ምክንያቱም ካልቸር የአንድ ሰው ማንነት አይደለም። ካልቸር የአንድ ሰው ምንነት አይደለም ። ባህል ወይም ካልቸር የሰው ተግባር፣ የሰው ስራ፣ የሰው ስነምግባር ነው እንጂ የሰው ምንነት አይደለም። ሰው ምንድን ነው? ሲባል መልሱ ሰው ተፈጥሮ የሰራው እንሰሳ ነው ። የሚያስብ እንሰሳ ነው ። ካልቸር፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ፖለቲካ፣ ዘፈን፣ ሃሳብ ምንድን ነው? ሲባል መልሱ የሰው ስራ፣ የሰው ተግባር፣ የሰው ቢሄቪየር ነው ።

ታዲያ ኢትዮጵያዊያን እራሳቸው በሰሩት እምነት፣ እራሳቸው ባመኑት እምነት፣ እራሳቸው በፈጠሩት ባህል እርስ በርሳቸው ሲተላለቁ፣ ሲሰቃዩ፣ ሲሰደዱ፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲያለቅሱ ከማየት የበለጠ ምን የሚያሳዝን፣ ምን የሚያሳፍር ነገር አለ? አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን በሁለት ሰው ሰራሽ ባህል ተከፋፍለው እንዲህ ሲፋጁ ማየት የሰዎች የማሰብ ችሎታ ዝቅጠት ብቻ ሳይሆን እራሱ የባህሉ፣ የእምነቱ፣ የሃይማኖቱ ደካማነትን ያሳያል። ኢትዮጵያዊያን ከዚህ የጭለማ እምነት ወጥተው ወደ ብርሃን ሃይማኖት ካልገቡ የነገ ሕይወታቸው የመከራ ዘመን እንደ ሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው!
ሆረስ፥

ይህን ጥልቅ ማስተዋል እና ትንታኔ ኣንብቤ ሳስታዉስ ሰነበትኩ። ኣሁን ፈልጌ ኣገኘሁት።

የሰዉ ልጅ የፈጠረዉን ቆም ብሎ ማስተዋል የነበረዉን ያስታዉሳል፣ ወደ ፊት ያሳያል።

እኔ ስለዚህ ርዕስ በቂ ትምህርት እና ዕዉቀት የለኝም። ለማወቅ ጥረት ማድረጉ ኣብሮኝ ሰንብቷል። የእኔ የኢትዮጵያ ህዳሴ የሰነበተ ደወል ስለዚህ መሰረታዊ ርዕስ ነዉ።

የእድሜ ባለፀጋ ለመባል የበቃሁ ይመስለኛል። ባህልም የእድሜ ባለፀጋ ነዉ መባል የሚችል ይመስለኛል። ከዚህ ኣንፃር የኢትዮጵያ ባህል ትልቅ የእድሜ ባለፀጋ ነዉ መባል የሚቻል ይመስለኛል። ይህ በብዙሃን ኣልተስተዋለም ማለት ከሌሎች ኣንፃር ሲታይ ፀጋዉ ብዙ ጉድለት ኣለዉ ማለት የሚቻል ኣይመስለኝም።

ትልቁ ጉድለት የምለዉ በብዙሃን ኣለመስተዋሉ ነዉ። በ1983 (እ ኢ ኣ) ኣከባቢ የማስታዉሰዉ ኣንድ የኦቦ ሌንጮ ለታ የቭኦኤ ቃለ መጠይቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ሆኖ ነዉ እንጂ በዛን ወቅት ኢትዮጵያ ዉስጥ የበዛ እልቂት ሊከሰት ይችል ነበር የሚል ኣይነት ነበር።

የህዝቡ ባህል ግዝፈት ከነፃ እንዉጣ ማስተማር የገዘፈ የነበረ ሆኖ ይሁን?

ከወራት በፊት ድፌንድዘትሩዝ (ማን እንደሆነ ኣላዉቅም) እዚህ ፎረም ላይ ተደራጁ የሞል ምክር ጽፎ ሳየዉ ከኢትዮጵያ ህዝብ በላይ የተደራጃ ኣለ ወይ ብዬ ዝም ኣልኩኝ። ምክንያቱም ህዝባችን በባህል እንደ ቤተሰብ፣ በሃይማኖት፣ በጎሳ፣ በነገድ፣ በደቦ ጭምር የተደራጀ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ። ስለዚህ እጥረቱ መደራጀቱ ላይ ነዉ ወይስ ዉጤት ማምጣቱ ላይ ነዉ ብዬ ራሴን ጠይቄ ዝም ኣልኩኝ።

ከዓመታት በፊት ከኣንድ ጓደኛዬ ጋር የሃይማኖት ዉይይት ጀመርን። አንድ ቅጽበታዊ ቃላቶቼን ኣልረሳቸዉም። እንካፓስቴቲ ስ ጎዸ ኣልኩኝ። እንካፓስቴት ያደርገሃል ማለት ነዉ። እኔም ኢቶንግልሽ እናገራለሁ። ሆሌ ባይሆንም። I remember it as one of my spontaneous outbursts. The strong reaction I got was that the complexity of human biology can not be explained without leaving it to God. I stand to be corrected if I misheard or misunderstood that strong reaction to my spontaneous outburst.

ከዛ ከዓመታት በሁዋል ልያጫዉተኝ ጠይቆ ብቅ ያለ እንግዳ ስለ እግዝኣብሔር መንግስት በዉስጥህ መሆን ስንኝ ልያስተምረኝ ዳዳ። ኣዉቀዉ ስለነበረ መለስኩለት። ከዛም የኣዉሮፓ ትራንስፎርሜሽን እና እድገት የመጣዉ ያንን ከተገነዘቡ በሁዋላ ነዉ የሚለዉን ሊጨምርልኝም ዳዳ። ያም ኣንብቤ ኣስተዉዬ የነበረ ነዉ።

ማስተዋል ብቻ ሳይሆን ስለርዕሱ እዛም እዚህም ስቀባጥር ሰንብቻለሁ። ካልዘነጋሁ ስለ ኢትዮጵያ አጀንዳ የተለያየ ጊዜ እዚህ ፎረም ላይ ስታስተምር ስለዚህ ርዕስ ኣንስቻለሁ። ኣሁን ኣንስቼ ነበር ለማለት ሳይሆን የርዕሱ ቁምነገርነት የበለጠ እንዲስተዋል ተጨማሪ ከሆነ ብዬ ነዉ።

ስለዚህ ርዕስ ኣንድ ቁልፍ ግንዛቤ ነዉ ብዬ የማስበዉ ዋቅን ኡማ ዸ የሚል ነዉ። ትርጉሙም ዋቃ ተፈጥሮ ነዉ ማለት ነዉ። የማክበር እና መስገድ ልዩነት ማስተዋልም ይህንን ቀልፍ ግንዛቤ ከማስተዋል የሚመጣ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ። እስከዛሬ ነበርሽ እንዴ የሚሉ ለዚህ ኣይኖቻቸዉን መጀመርያ ከከፈቱ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42981
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 09 Jun 2022, 23:45

ናጋ ቱማ፣
እኔ ስለ ኢትዮጵያ አጀንዳ ሃሳቤን ስሰጥ ደጋግሜ የምላቸው ነጥቦች አይለወጡም ። ኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልጋቸው ፈጣሪ (ክሪኤቲቭ)፣ ኢኮሎጂካል እና መንፈሳዊ ካልቸር ነው። ይህንኑ ነው ደጋግሜ የምለው ። ለዚህ ምክኛት አለኝ። ካልቸር የራሳችህን የሰዎች ስራ ነው ብያለሁ ። ያ ማለት ደሞ ካልቸር ሃሳብም ሆነ ቁሳቁስ ይዘቱ የሰዎች ክህሎት፣ ችሎታ ወይም ብልሃት ነው። ካልቸር የኑሮ ዘዴ ነው ። ስለዚህ ብልሃት ክሪኤቲቭ ካልሆነ ያረጃል፣ ከጥቅም ውጭ ይሆናል ።

ሌላው ነጥብ ካልቸር ስነ ምግባር ነው፤ ማለትም የተግባር ስነ ስርዓት ነው። የተግባር ሳይንስ ነው ። ኢኮሎጂካል ኤቲክስ ወይም ኢኮሎጂካል ስነ ምግባር ማለት የሰው ልጅ ስለራሱ ድህንነት ብቻ ሳይሆን ስለ እንሰሶች፣ እጸዋት፣ አፈር፣ ዉሃ ፣ አየር፣ ሁሉ ድህንነት ባህሪውን ማሰልጠን አለበት ። በዩኒቨርስ ውስጥ ሁሉ ነገር ሕይወት አለው፣ ሁሉ ነገር ከሁሉ ነገር ጋራ የተጋመደ መሆኑን ማመንና በዚያ መሰረት ምግባሩን ማሰልጠን ማለት ነው።

ይህን አይነት ኢኮሎጂካል ኤቲክስ ወይም the ethics of well-being of all የሚለው ሞራል ፊሎሶፊ ሄዶ ከመንፈሳዊነት ጋር አንድ ይሆናል ። መንፈሳዊነት በአንድ ሃይማኖት ከማመን በላይ ነው። በአንድ ፈጣሪ ከማመን በላይ ነው ። ምናልባትም የሰው ልጅ ሊደርስበት የሚችለው ንቃተ ስሜት ወይም ኮንሺየስነስ ጥግ ነው ። ለምሳሌ ስንት ሰው ነው እንሰሳዎች ሁሉ ልክ እንደ ሰው ስሜት (ፊሊንግ) እንዳላቸወና ልክ እንደ ሰው ህመም (ፔይን) እንደ ሚሰማቸው የሚያውቅ፣ የሚያስብ ? ስንት ሰው ነው እጸዋት ህይወት እንዳላቸው የሚያውቅና የሚያስብ?

ስለዚህ እኔ ስለ ካልቸር ሳወራ ስለነዚህ 3 ግዙፍ ነገሮች ማለት ፈጠራ፣ ኢኮሎጂና መንፈሳዊነት ነው ። ይህን የምጽፈው በኢትዮጵያ አጀንዳ ስር ነው። የኢትዮጵያ አላማ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ፐርፐዝ ምንድን ነው? ለሚለው አጀንዳ አንዱ ምላሼ ነው ።

በዚህ ሃረግ መጀመሪያ ያለው ሃሳቤ እምነትና ካልቸራችንን የተቸሁበት ነው ። የሰው ምጀመሪያ ነጻ ፍጡር ነው ። የሰው ልጅ ዋጋ የሚተመነው በነጻነቱ ልክ ነው ። ስለሆነም እራሳቸው ለፈጠሩት እምነት፣ ሃይማኖት፣ ማለትም ካልቸር ባሪያ ሆነው እርስ በርስ የሚተላለቁ ሕዝቦች በመሰረቱ የአብርሆት ደረጃ ያልደረሱ ናቸው ነው የምለው። ነጻ ሕዝብ ሳይሆኑ የምነታቸው ባሪያ ናቸው ነው የምለው ።

ካልቸር ማለት ኮምፒተንስ ወይም ክህሎት ወይም ዘዴ ማለት ነው ። ክህሎት የሰው መሳሪያ አገልጋይ እንጂ ሰውን እንደ ባሪያ የሚገዛ ሃይል አይደለም፣ መሆን የለበትም። ስለዚህ ስለ አንድ ሃይማኖት፣ እምነት፣ ባህል፣ ወግ ወዘተ ስናወራ፣ ስናሞግስ ወይም ስንተች ያ ባህል፣ ያ እምነት ምን ፋይዳ አለው? ምን ያደርጋል? ምን ቫልዩ ይጨምራል ብለን ካልመዘነው በጭለማ ውስጥ ጥንቆላ በመከተል የምንኖር ደንቆሮች ነን ማለት ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42981
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 10 Jun 2022, 01:02

የኢትዮጵያ አጀንዳ ምንድን ነው?
በእኔ እምነት የኢትዮጵያ አላማ ...

(1) ብሄራዊ አንደንቷ የጸና፣ የተረጋጋች፣ ጠንካላ አገር መሆን፤
(2) ዴሚክራሳዊ፣ ነጻና፣ ፍትሃዊ ማህበረ ሰብ መሆን፤
(3) የበለጸገ፣ የተማረ፣ ጤናው የተጠበቀ ሕዝብ መሆን፤
(4) የሚፈጥር፣ ኢኮሎጂያዊና መንፈሳዊ ካልቸር መገንባት።
በቃ ይህ ነው የኢትዮጵያ ፋይዳ!

Horus
Senior Member+
Posts: 42981
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 10 Jun 2022, 03:03

ካልቸር የሌለው ሕዝብ ሃይማኖት የለውም ።

Abere
Senior Member
Posts: 15518
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Abere » 10 Jun 2022, 11:07

ሆረስ፤

እነኝህን ዐበይት ጉዳዮች የሚያውጅ መቅድም ያለው ህገ-መንግስት አገሪቷ አላት ዎይ የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው። የመመሪያ መጽሀፍ ወይም Manual የሌለው ፎርጅድ መኪና እንደ መንዳት ነው - አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ። መኪናው አንድ ቦታ ቀጥ ሲል ዋይ! እባካችሁ ግፉ! ግፉ! ልክ ዐብይ አህመድ ወያኔ ደብረብርሃን ብቅ ስትል ፋኖ እብካህ ያለ የሌለህን ይዘህ ይችን ወያኔን እርዱኝ በደቦ ይልሃል። ወያኔ ስትባረር ደግሞ ምን እና ወደት እንደሚሄድ አያውቅም - ህግ የለውም፥ መመሪያ ራዕይ የለውም። እንደ ምሳሌ ማንሳቴ ነው።

መመኘት መልካም ነው ግን ምኞት ደግሞ ከተጨባጩ ሁኔታ ጋር ሲሄድ መልካም ነው። የኢትዮጵያ ዕጣ በእነኝህ ነገሮች ላይ መቶ በመቶ የተወሰነ ነው። ሀ) የጎሳ የክልል በረት(ጋጥ) መፈራረስ 2) በትህነግ እና ኦነግ ልክ ተቀዶ የተሰፋው የዴዴቢት ኢ-ህገ መንግስት ሲሰረዝ ነው፡

ይህን ለማድረግ የተዘጋጀ መሪ በሌለበት ቅን ምኞት ብቻውን የሚሆን አይደለም። ባዶ ተስፋ ይሆናል። እንደ እኔ የኢትዮጵያ ችግር የመሪ ችግር ብቻ ነው። ቆራጥ፥ አስታዋይ፤ብልህ፥ መደሎ ዐልባ፥ የመምራት ሞገስ እና ቅቡልነት ያለው፥ የመርህ ሰው፤ አገሩን ከነፍሱ በላይ የሚያፈቅር መሪ ያስፈልጋትል። ይህ አይነት መሪ እንደ እድል ሁኖ ከእምዬ ዐጼ ምኒልክ በኋል አልተወለደም። ዐብይ አህመድ ሙሴ አሻጋሪያችን ሲሉት፤ ለዐድዋ ክብረ በዓል እምዬን ምኒልክን እኔ እበልጠዋለሁ ብሎ የእርሱን ፎቶግራፍ አስውድሮ መስቀል አደባባይ የህዝብ መሳቂያ ሲሆን ዋለ። በዛን ዕለት ግን ብዙ ንጹሃን በኦነግ ይታረዱ እና ይጨፈጨፉ ነበር።



Horus wrote:
10 Jun 2022, 01:02
የኢትዮጵያ አጀንዳ ምንድን ነው?
በእኔ እምነት የኢትዮጵያ አላማ ...

(1) ብሄራዊ አንደንቷ የጸና፣ የተረጋጋች፣ ጠንካላ አገር መሆን፤
(2) ዴሚክራሳዊ፣ ነጻና፣ ፍትሃዊ ማህበረ ሰብ መሆን፤
(3) የበለጸገ፣ የተማረ፣ ጤናው የተጠበቀ ሕዝብ መሆን፤
(4) የሚፈጥር፣ ኢኮሎጂያዊና መንፈሳዊ ካልቸር መገንባት።
በቃ ይህ ነው የኢትዮጵያ ፋይዳ!

Horus
Senior Member+
Posts: 42981
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 10 Jun 2022, 11:22

"የኢትዮጵያ ዕጣ በእነኝህ ነገሮች ላይ መቶ በመቶ የተወሰነ ነው። ሀ) የጎሳ የክልል በረት(ጋጥ) መፈራረስ 2) በትህነግ እና ኦነግ ልክ ተቀዶ የተሰፋው የዴዴቢት ኢ-ህገ መንግስት ሲሰረዝ ነው፡" ትክክል።

ግን መፍትሄውና መሪነቱ ካንተና እኔ ይጀምራል። እኔና አንተ ይህን ስራ እንዲሰሩ የቀጠርናቸው ሰዎች የሉም። እኔና አንተ ቁጭ ብለን ማንንም የመውቀስ የሞራል መብት የለንም። የማንፈልገውን ስርዓት መለወጥ የራሳችን ግዴታ ነው ። ግን ልብ አድርግ፤ መሪ ስትሆን አንተ የምትፈልገው አይደለም የሚሆነው፤ ተቅላላው ማህበረሰብ የሚፈልገውን እንጂ።

Abere
Senior Member
Posts: 15518
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Abere » 10 Jun 2022, 11:41

ስለ ኢትዮጵያ እኮ ብዙዎች መስዋዕትነት በአሁኑ ሰዐት እየከፈሉ ነው። በእውነት ለእውነት የቆሙ ታፍነው እየታሰሩ ነው - እጃቸውን አጣምረው አልተቀመጡም። ገሚሶች ከጎጠኛ መንግስት ጋር ቃታ እየተማዘዙ ነው። ሌላው ዜጋ እኔም አነተም ቢሆን የተለየ ለውጥ አታመጣም። ምክንያቱም የመጣውን ለውጥ ህዝብ አስበልቶ ያጣውን ነው ለማስመለስ እየታገለ ነው ያለው። የዚህ አይነት ትግል ከሆነ አዎን ሁላችንም ድርሻችንን መወጣ አለብን።

ለውጥ እንድመጣ የቀጠርናቸው የሉም። 27 አመት ህዝብ ታግሎ ለውጥ አመጣ፤ ለውጡን እንድመራ ህዝብ ዐደራ ሰጠው - ኦሮሙማ ዐብይ አህመድ። ቁማር በላው። አሁን ቁማርተኛ በአደራ አጉዳይነት ወንጀለኛ ነው አይደለም?

በአንድ አገር ውስጥ ሁሉም ዜጋ የሚፈልገውን የሚያደርግ መሪ የለም- አይኖርምም። አንድ መሪ ግን የሁሉም ህዝብ መሪ ነው - መድሎ እና መገለል በቡድን ይሁን በግለሰቦች ላይ አይፈጽምም። ችግሩ ግን የኢትዮጵያ መሪ የአንድ ጎሳ ጥቅም አስከባሪ ነኝ - ያንን ለማስከበር ሌላውን መግዛት አለብኝ ነው -በማደናገርም ይሁን በማሳመን ( confuse and convince) ያካልሆነ በጦርነት በመውረር።
Horus wrote:
10 Jun 2022, 11:22
"የኢትዮጵያ ዕጣ በእነኝህ ነገሮች ላይ መቶ በመቶ የተወሰነ ነው። ሀ) የጎሳ የክልል በረት(ጋጥ) መፈራረስ 2) በትህነግ እና ኦነግ ልክ ተቀዶ የተሰፋው የዴዴቢት ኢ-ህገ መንግስት ሲሰረዝ ነው፡" ትክክል።

ግን መፍትሄውና መሪነቱ ካንተና እኔ ይጀምራል። እኔና አንተ ይህን ስራ እንዲሰሩ የቀጠርናቸው ሰዎች የሉም። እኔና አንተ ቁጭ ብለን ማንንም የመውቀስ የሞራል መብት የለንም። የማንፈልገውን ስርዓት መለወጥ የራሳችን ግዴታ ነው ። ግን ልብ አድርግ፤ መሪ ስትሆን አንተ የምትፈልገው አይደለም የሚሆነው፤ ተቅላላው ማህበረሰብ የሚፈልገውን እንጂ።

Post Reply