Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5227
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 12 Jun 2026, 06:41
ከደማቁ የኤርትራ 35ኛ የነጻነት በዓል ማግስት እንሆ በጽምዶ 38 እና 39 ይዘት ዙርያ ዳግም ተገናኝተናል፡ የጽምዶንም ታሪክ መልክ መልኩን ለማስያዝ።
ጽምዶ 38 እና 39ን በጥቂቱ ገረፍ ገረፍ አድርገን ለማድመጥ እድሉን አግኝተን ነበር፡ ነጻ እይታችን እንሆ። ጽምዶ-38፡ የ35ኛ የነጻነት በዓላችንን ድምቀት በመግለጽ ትጀምራለች ብለን ገምተን ነበር። እንደጠበቅነው አልመጣችም። እንደተባለው ለ35ኛ የነጻነት በዓላችን ልዩ ድምቀት የሰጠ፡ የ15 ደቂቃዎች ደማቅ የርችት ተኩስ በቴሌቭዝን መስኮት ተመልክተን ነበር። አንዳንዶች እንደሚለት “ማሕበራዊ ፍትሕ እና ፍትሓዊ ተጠቃሚነት” ወዘት የሚል መርህ የሚከተለው የኤርትራ መንግስት፡ 15 ደቂቃ ሙሉ አስመራ ውስጥ ርችት ከመተኮስ፡ ለምን በ6ቱ የሃገሪቱ ዞባዎች ከፋፍሎ፡ የበዓሉን ድምቀት በመላዋ የሃገሪቱ ክፍሎች ይበልጥ አላንጸባረቀም የሚል ሃሳብ ማቅረብ፡ ለወደፊቱ ለሚደረጉት ተመሳሳይ ድግሶች ጠቃሚ እንደሚሆን በማሰብ ነው።
ጽምዶ 38 በጦቢያ ቅድመ-ምርጫ የተለቀቀ፡ “ጎሞቹ” በተባለ የጦቢያ ወታደራዊ ጀነራል ንግግር ዙርያ ያጠነጠነ መልእክት ይዟል። “ጎሞቹ” የተባለው “ተሾመ ገመቹ” ለማለት ይመስላል። ‘ምርኮኛ ጀነራል” የተባለው አንዴ “ጎሞቹ” ሌላ ግዜም “ወዲጎሞቹ” ተብሎ የተጠቀሰው ባለስልጣን ባገሩ ቴሌቭዥን፡ ጽምዶን በተመለከተ የ20 ደቂቃ ቃለምልልስ ከአንድ “ትግራዋይ ባንዳ” ጋዜጠኛ ጋር እንዳከናወነ ይገልጻል ኣወሉ። ይህን የ20 ደቂቃ ቃለ ምልልስ ለመግለጽ፡ ኣወል ከ25 ደቂቃዎች በላይ ትንታኔ ሲሰጥ፡ ከ25 ግዜ በላይ “ጎሞቹ” የሚለውን ቃል ሲያነሳም ተስተውሏል። ለእያንዳንዷ ደቂቃ ቢያንስ ቢያንስ ኣንድ “ጎሞቹ” መሆኑ ነው!
በ9ኛ ደቂቃው የጽምዶው አጋፋሪ የቦርትሱዳኑን ዝግጅት በተመለከተ በሚመስል መልኩ “ጽምዶ የአፍሪካ ቀንድ ምሑራንን ይዞ ከተፍ ብሏል” ቢልም እንኳ ከኤርትራ በኩል “ምሑራን” የተባሉት እነማን እንደሆኑ አልገለጸም። አወል “የጽምዶ አመራሮች ሁሉም ሲቪል ናቸው፡ ተቃዋሚዎች ደግሞ የጦር ጀነራሎች” ሲልም ተደምጧል፡ ከዚህ በፊት፡ በዚህ በዘመነ ድሮን፡ “ዙ-23 ነኝ” የሚለው አወሉ እንዲሁም የትግራዩ የጽምዶ-ሰው ብርሃነም ወታደር መሆናቸውን አስረግጠው ነግረውን እንደነበር እናስታውሳለን።
ኣወል በዚህ “ጎሞቹ” የሚለውን ቃል ኣለ ቅጥ ኣጋንኖ ባነገሰበት የጽምዶ ዝግጅቱ፡ “ዓቅመ-ቢስ ምላሱ ረዥም ነው!” የሚል ምሳሌ በመጠቀም፡ የጀነራሉንና የብልጽግኖችን ምላስ ማርዘም ለመከርከም ሞክሯል። ኣያይዞም ጀነራሉ “በሬና ቀበሮ ባንድላይ ሊጠመዱ አይችሉም!” ያሉትን ቃል በማንሳት “ሻዕብያና ሕወሓት ባንድላይ ሊጠምዱ አይችሉም” የሚል ትርጓሜ ሲሰጥ ተስተውሏል። ጀነራሉን ይጠይቅ የነበረውን ጋዜጠኛ ፍራቻ በማንበብ፡ የተረጋጋ መንፈስ አይነበብበትም በማለት ያብጠለጠለው የጽምዶ-አጋፋሪ፡ ጀነራሉ “ሕወሓትና ፋኖ በባህርያቸው ባንድላይ አይጠምዱም” ለማለት ፈልገው ሊሆን እንደሚችሉ ለመጠርጠር አልፈለገም። አወል በዚህ መልእኽቱ “የገጽታ ንባብ ኤክስፐርት” እንደሆነም ጠቁሞናል፡ በመሆኑም ጋዜጠኞቻችን ቃለምልልስ በሚያካሂዱበት ወቅት ገጽታቸው ላይም ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው ግሩም ትምህርት ሰጥቷል። ይሰማል የዓለም ጋዜጠኞች!
በ23ኛ ደቂቃ “ጀነራሉ ጽምዶ በሚያራግቡ አካላት ላይ እርምጃ እንወስዳለን” ማለታቸውን ተከትሎ፡ አወሉ የግሌ መልስ ነው በማለት “እስከ አሁን ታድያ ማን እጃችሁን ያዘው። ብልጽግና ዓቕም ደልባ፡ ጽምዶ በሚያካሂዱ የኤርትራ የኢትዮጵያ የትግራይና የሱዳን ህዝብ ላይ እርምጃ እወስዳለው ማለቷ ገራሚ ነው። ዓቅም ቢኖራት ኖሮ የአማራን ህዝብ በድሮን እያደባዩት እንዳለው ጽምዶ ላይም በሞከሩት ነበር።” ሲል ተደምጧል አያይዞም የግሌ መልስ ይሰመርበት በማለት “ወደ ትግራይ የምትተኮስ አንዲትም ትሁን ጥይት፡ ኤርትራ ላይ የጦርነት አዋጅ እንደማወጅ ነው የምንቆጥረው። ‘ጎመቹ’ ያኔ መሬት ላይ የት እንደምንጠብቅህ እወቅ!” በማለት በምላሱ ጉራ ቢጤ ሲቸበችብ ተስተውላሏ፡ ጢሙ ሽበት የወረረው “ስለ ፊዚካል ዲማርኬሽንና ድንበር አስፈላጊነት” አንዲትም ቃል የማይተነፍሰው አወሉ።
ቀጥሎም፡ “ጽምዶ አድማሱን አስፍቶ የኤርትራ የኢትዮጵያ የሱዳንንና የትግራይን ህዝብ አቅፏል” በማለቱ፡ ትውልዱ ከሽሬም ይመዘዛል እየተባለ የሚታማዉ ኤርትራዊው የጽምዶ አጋፋሪ አወል፡ ለሃገረ-ትግራይ እውቅና የሰጠ መስሏል። ደስ ይበልሽ ሃገረ ትግራይ በተለይም የትግራይ ህዝብ የትግል መዲናዋ ደደቢትና ሽሬ ደስ ይበላችሁ!
“ጽምዶ ብልጽግናን የናጠና ያናወጠ ናላቸውንም ያዞረ የህዝብ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው” ያለው አወል፡ “ይህን ሰላማዊ የህዝቦች እንቅስቃሴ ለመግታት የሚጥር ማንኛውንም ሃይል መሬቱ ላይ ያገናኘን ያኔ የምናደርገውን እናሳየዋለን” ሲል በሰላማዊ መንገድና በምላሱ ዝቷል።
ከዚህ ጉዳይ በመለስ፡ ጽምዶ 38 ስለ የጦቢያ ሃገራዊ ምርጫ ኢፍትሓዊነት ሳይታለም የተፈታ ሓቅ መሆኑን ሲደሰኩር ተደምጧል። ምርጫ የሚያካሂዱ አገራት፡ የዲሞክራሲ ሰርቲፊኬት ተቀብለው፡ ብድር ለመቀበል ራሳቸውን ሲያመቻቹ እንደሆነም ጠቁሟል። “ኢትዮጵያ በታሪኳ፡ ታሪክ የሚደግሙ እንጂ ታሪክ የሚፈጥሩ መሪዎችን አልታደለችም” ያለው የጽምዶው አጋፋሪ አወል፤ የዓዲኳላዋ የእታችን ልጅ አቶ መለስ ዓባይን ገድቦ ብርቅ ታሪክ እንደፈጠረ የዘነጋ መስሏል። የታሪክ በጎ በጎ ጎኑም አሁንም አሁንም ሊደገም እንደሚችል ያጤነ አልመሰለም ወዳጃችን አወሉ። የኢትዮጵያዉያን የዓድዋ ድል በሶማሊያ መደገሙንም የዘነጋ ይመስላል ብለንም ሓቁን አልገልጥለትም፡ የካራማራ ማለትም የምስራቁ ድል ምን እንደሆነ ሊያውቅ ስለማይችል! መደገም ያለበት ታሪክ መደገም፡ መፈጠር ያለበት ታሪክም መፈጠር እንዳለበትም አልገባውም።
በ35 ደቂቃም “ወንጀሉ ከባድ ስለሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣኑን ለቆ የሚኖርበት ቁመና የለውም” በማለትም የብልጥግናው ቁንጮ ላይ ተረማምዷል። ይህ አለም ዓቀፋዊ እውነት ፍንትው ብሎ የሚታየው ሰዉየው ዓሰብ መመኘቱና ካቅሙ በላይ ህልም ማለሙን ግምት ውስጥ ስናስገባ ነው!
የጽምዶው አጋፋሪ የጦቢያን መሪዎች ሲወቅስም፡ ኃይለስላሴን በወሎው ድርቅ ሲወቅስ፡ ደርጉንም ጦርነት ጦርነት በመጫወቱ ሲወቅስ፡ ይህን ፉርሽ አዙሪት ተከትሎም ብልጽግና “ዓሰብ ዓሰብ ባሕር ባሕር” መጫወቱን ገልጾ ሲወቅስ፡ የትግራይ የብልጽግና ምሰሶዎችን እነ ስታሊንን ሃይለ ደደቢትን ቢተውንና ጎደፋይን ላለማስቀዬም፡ የኤርትራ መሬትን ወርረው ለዘመናት የዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ አስተጓጉለው፡ በኤርትራ ህዝብ ዕድልና ሰላም ላይ ታሪክ የማይሽረው ጠባሳ የፈጸሙትን የወያኔዎችን የኢሓዴግ ስርዓትን ግን ሲወቅስና ሲነቅፍ አልታዘብነውም። የጽምዶው አጋፋሪ መርጦ አልቃሽነት ፍንትዉ ብሎ ታይቶናል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
በ45ኛ ደቂቃም የብልጥግናውን ወፈፌ መሪ “ራሱን እንደ የአምላክ መልክእክተኛና ነብይ ነው የሚቆጥረው” በማለት በብዙ የአፍሪካና የዓለም መሪዎች ላይ የሚታየውን ባህርይ ገልጿል። እራሱ የጽምዶው አጋፋሪ አወላችን የኛን ብረዚደንት ልብ ለማማለል ስማቸው አደናግሮት ነው መሰል “ነብይ” እያለ ሲያንቆለጻጽሳቸው በተለያዩ የጽምዶ ንግግሩ አድምጠን ነበር። ከመድኃኒታችንና ጌታችን ክርስቶስ በኋላ የነብያት ዘመን እስከነ አካቴው ማክተሙ አልገባውም። እርግጥ ነው የጽምዶው አጋፋሪ የብረዚደንታችንን አጥንታችውንም ቆጥሮ “ሓባ-አጽሙ” እያለም ሲጠቅሳቸውና ማሲንቆውን እየገዘገዘ አዚጥም አዚጥም ሲያስብላት ይደመጣል።
ጽምዶ 38 ሲጠቃለል፡ “ሻዕብያ ከብልጽግና ጋር ስውር ንግግር ያዟል” የሚል ዜና ውሸት መሆኑን፡ በኤርትራ በኩል ትግራይን የነጠለ ምንም ዓይነት ንግግር ከብጽልግና ጋር እንደማይካሄድ ቁልጭ አርጎ ገልጾ፡ የነ ሃይለ ደደቢትን ስጋት ለመቅረፍ በመሞከር፡ ድል ለሰፊው ሕዝብ በማለት ዝግጅቱን ቋጭቷል።
ጽምዶ 39
ፈጠን ብላ በጥድፊያ የወጣችው ጽምዶ 39 ደግሞ ትግራይ በብልጽግና ድሮን በተመታችበት ማግስት ብትቀርብም፡ ለሰላም ጥሪ ታቀርባለች፡ የትግራይን ህዝብ ለመታደግም ሞራላዊ ድጋፍ ታደርጋለች ብለን ብንጠብቅም፡ ስለ የጦቢያ “ምርጫ” ፉርሽነት በመተንተን፡ አንድ የምስራች ዜና አቅርባለች፡ ጽምዶ በኒውዮርክ በብራሰልስና በአዲስ አበባ በመንግስታት ጽሕፈት ቤቶች ውስጥ መግባቷም ተነግሯል።
የጽምዶው አጋፋሪ ያያ ሰይድ ልጅ አወል፡ ኢትዮጵያ ውስጥ “አሸባሪዎች” ቤተክርስትያኖችን እንዳቃጠሉ ገልጿል። ይህን እኩይ ድርጊት የፈጸሙት መንግስታዊ አሸባሪዎች ናቸው በማለትም ሃይማኖታዊ አሸባሪዎችን ነጻ ለማውጣት ቅኔ ሲቀኝም ተስተውሏል። የኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውስጥ ለውስጥ ቦተሊካዊ ንግግር ጀምሯል የሚል አሉባልታና የለየለት ውሸት መሆኑን ዳግም በመግለጽ፡ የአሜሪካ መንግስትን ግን ለዘመናት እናቀርበው የነበረ ሃሳብ ጋር በመስማማታቸው ከአሜሪካኖች ጋር ግንኙነታችን ከነበረው በተሻለ ደረጃ ላይ አለን በማለት ሲያትት አድምጠነዋል።
ቀጥሎም ኤርትራ በተባበሩት መንግስታት መድረክ፡ አንድ የሆነ ክፍል ውስጥ “ምክትል ብረሲደንት” ሆና መመረጧን በደስታ ስሜት የምስራች ነግሯል። እኛም “ፊዚካል ዲማርኼሽን ላይ የሚያደርስ ከሆነ ግሩም ዲብሎማሲያዊ ድል” ብለናል። ምንም እንኳ ኤርትራ እንደ ሃገር “ምክትል ብረሲደት” የሚለውን ቃል ብዙም የምትጠቀምበት ሃገር ባትሆንም፡ በተባበሩት መንግስታት መድረክ ይህን ሹመት መጎናጸፏን ለማወቅ አስችሎናል ጽምዶ 39። ለዚህ ድልም ለዕንቁዋ አምባሳደራችን ላያ-ሳርያም ልጅ ለወ/ሮ ሶፍያ ተስፋማርያም ምስጋና ሲያቀርብም አስተውለናል ያያ ሰይድ ልጅ።
በዚሁ የጽምዶ 39 ዲስኩርም፡ ከዚህ በፊት ጀነራል ፍሊጶስ ወልደዩሃንስ “የተቀኙለትን ቅኔ” አሁን ገና ያጣጣመ ሲመስል፡ “ጀነራላችን ወሬ አይወዱም ስራ እንጂ” በማለት ለመግለጽ መሞከሩ፡ ነገርና ቅኔ ከዓመት በኋላ የሚረዳው ዘገምተኛ ቢጤ መሆኑን ተገንዝበናል ወዳጃችን ያያ ሰይድ ልጅ። ጀነራሉ አስመራን ነጻ ባወጣው “ዛዛሚ ዅናት” በመባል በሚታወቀው፡ ከደቀምሓረ ጀምሮ የተደረገ የመጨረሻው ጦርነት ውስጥ የጦር መሪ ሆነው፡ የመገናኛ ሬዲዮናቸውን ይዘው፡ ጦር ይመሩ በነበሩበት ወቅት፡ ታጋይ ጋዜጠኞች ስለሁኔታው ጥያቄ ሲጠይቋቸው የሚያሳይ ታሪካዊ ተንቀሳቃሽ ምስል አቅርቧል። ያኔም የአሁኑ ጄነራል፡ ስንትና ስንት ወጣቶች ጦርነት ውስጥ ፊት ለፊት በሚተናነቁበትና፡ እሳቸውም ይህን ጦርነት እዬመሩ በነበሩበት ወቅት፡ “ለወሬ ግዜ የለንም” በሚል አኳኋን ከጋዜጠኛው ሲርቁ ተስተውለዋል። አዎን ያኔ ለወሬው ከድል በኋላ እንደርስበታለን ማለታቸው ነበር። አዎን “እንደ ጉንዳን በአንድ ዓላማ ተሰልፍው ጦርነት ውስጥ በመግባት፡ ጠላትን በማደባየት ፡ ህይወታቸውን በመሰዋት፡ ሃገር በመፍጠር ላይ ሁለንተናቸውን ለመሰዋት የተዘጋጁ ወጣቶችን በቅጡ የመምራት ድርብርብ ወታደራዊ ኃላፊነት ተጭኗቸው እያለ፡ ለወሬ ግዜው አልነበረም ለስራ እንጂ! አወልም ጭምር፡ እኒሁ ጀነራል ከሰራዊታቸው ጋር በግድብ ስራና ምረቃ ላይ በነበሩበት ወቅት ሊያናግራቸው አስቦ “ለወሬ ግዜ የለንም ለስራ እንጂ!” የሚል ቅልብጭብጭ ያለ ቅኔ ተቀኝተውለት እንደነበር ይታወሳል።
በዚሁ በጽምዶ 39፡ ወዳጃችን ያያ ሰይድ ልጅ አወሉ፡ ብረዚደንታችን ወደ ካይሮ ማቅናታቸውን ገልጾ በቀጣዩ ስራው፡ የግብጹን የሱዳኑንና የኛውን ብረዚደንት ፎቶ ከጽምዶ አባሎች ጎን እንደሚለጥፈው ገልጿል። እኛም ይህንን አስተውለን የግብጹ አልሲሲ ምን ስራ ቢበዛባቸው ነው ስልጣን ላይ ከወጡ ከሰኔ 2014 ጀምረው እስከ አሁን አንዴ ብቻ ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ፤ የኛው ብረዚደንት ግን 9 ግዜ በይፋ ወደ ካይሮ ያቀኑት ምስጢሩ ምንድን ነው ብለን ለማጥናት ሞክረናል። ብረሲደንታችን 3 ግዜ በግብጹ የአልሲሲ የንግስና ዕለት ማለትም ሰኔ 8 ካይሮ ውስጥ በመገኘት አጋርነታቸውን እስከመግለጥም ደርሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አልሲሲ፡ ኤርትራ ውስጥ ዩኒቨርሲቲ ሊሰራ ነው የሚል የመገናኛ ብዙሃን በሚባሉት ብዙሃንን ለማደናገር የተነዛ ወሬ በመስማታችን፡ ሰዉየው ባገሩ ከሰራቸው የትምህርት ተቋማት ይልቅ የሰራቸው መስጅዶች ይበዛሉ፡ ከ9ሽህ በላይ መስጅዶን ሰርቷል ወዘተ የሚል ሃተታ በማየታችን ገርሞን ፈገግ ብለናል። viewtopic.php?f=2&t=380519 ይህ ማለት ግን ከአልሲሲ ጋር የቀይ ባህርን የሰላም ጉዳይ በተናበበ መልኩ አናስኬደውም ማለት አለመሆኑ መታወቅ ይገባዋል። ለምን ቢባል ሁሉም ደንበሩንና ሃላፊነቱን አውቆ መጓዝ ስለሚገባው። እንደኛ እንደ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ነጻ እይታ፡ “ሓቀኛ ጽምዶ፡ በፊዚካል ዲማርኬሽን የተማከለ መሆን ይገባዋል” ምክንያቱም ጀግኖቻችን የተሰውት “ለዶብ ማለት ለድንበር” መከበር ስለሆነ!
አስቀድሞ አወል በጽምዶ 38 “ወደ ትግራይ የምትተኮስ አንዲትም ትሁን ጥይት፡ ኤርትራ ላይ የጦርነት አዋጅ እንደማወጅ ነው የምንቆጥረው። ‘ጎመቹ’ ያኔ መሬት ላይ የት እንደምንጠብቅህ እወቅ!” ብሎ በዛተው መሰረት፤ የመልስ ምት በሚመስል መልኩ፡ ትግራይ ውስጥ ሸራሮና ገማህሎ አካባቢ፡ የብልጽግና ድሮን ጉዳት ማድረሷን የሚገልጹ ዜናዎች በመስማታችን፡ ያገራችን ተቀኝዎች
አባኢሶሞ መሲሎም ዘራይ፡
አረሳሲኖም መሲሎም ዘራይ፡
ኪህረም ከሎ ስሒቆም ዳሕራይ! እንዲሉ
ውረድ እንውረድ ተባባሉና፡
አስደበደቡት አፋፍ ቆሙና!
የሚለው ዕድሜ ጠገብ ተረት ትዝ ብሎን፡ ትግራይ ውስጥ ሰለባ ለሆኑት ዜጎች መንግስተሰማይን ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ተመኝተናል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=308857&.
ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ ኤርትራዉያን ሃገር በመፍጠር የተሰዉ ጀግኖችን ይበልጥ የምንዘክርበት ወርሃ ሰነ በመግባታችን ይህችን ቅኝታችንን አካፍለናችኋል።
Meleket wrote: ↑08 Dec 2022, 08:34
ኣብ በሊሕ መላጸ
ተሰሪዖም ከም ጻጸ፡
ኣብ በሊሕ መላጸ፡
ብመስዋእቶም ...
ዘስገሩ ብጾቶም፡
ዘይርሳዕ ውዕለቶም፡
ንሳቶም ...
ኣብ በሊሕ መላጸ ሚልዮናት ዘስገሩ፡
በጃ እናሓለፉ ፍቕሮም ዘመስከሩ፡
ሃገር ዝፈጠሩ፡
“አናብስ ስዉኣት” ወትሩ ይዘከሩ።
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5227
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 12 Jun 2026, 08:49
እላይ ፎቶሾፕ የለጣጠፈችው እታለም ሕጸጿን ለማሳዬት ያህል ነው።
ሲጀመር Exorcist መስቀል እንዴት እንደሚይዝ ምንም ዕውቀቱ እንደሌላት፡ መስቀል አያያዟ በጣም እንዳስፎገረባት፤ ሲቀጥል በኣፏ ጽምዶ እያለች በፎቶሾፗ እንዴት በትግራይ እናቶች ላይ እንደምትሳለቅ፡ ይህም ነዉር እንደሆነ፡ የትግራይ እናት ማለት እነ አይተ ወልደኣብ ወልደማርያምንም ያፈራች መሆኗን፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች የጠቆምንበት ጽሑፍን ለማማዝ ያህል ነው። ገብተው እንዲጎበኙ ጋብዘንዎታል viewtopic.php?f=2&t=290749&start=60
Meleket wrote: ↑12 Jun 2026, 06:41
ከደማቁ የኤርትራ 35ኛ የነጻነት በዓል ማግስት እንሆ በጽምዶ 38 እና 39 ይዘት ዙርያ ዳግም ተገናኝተናል፡ የጽምዶንም ታሪክ መልክ መልኩን ለማስያዝ።
ጽምዶ 38 እና 39ን በጥቂቱ ገረፍ ገረፍ አድርገን ለማድመጥ እድሉን አግኝተን ነበር፡ ነጻ እይታችን እንሆ። ጽምዶ-38፡ የ35ኛ የነጻነት በዓላችንን ድምቀት በመግለጽ ትጀምራለች ብለን ገምተን ነበር። እንደጠበቅነው አልመጣችም። እንደተባለው ለ35ኛ የነጻነት በዓላችን ልዩ ድምቀት የሰጠ፡ የ15 ደቂቃዎች ደማቅ የርችት ተኩስ በቴሌቭዝን መስኮት ተመልክተን ነበር። አንዳንዶች እንደሚለት “ማሕበራዊ ፍትሕ እና ፍትሓዊ ተጠቃሚነት” ወዘት የሚል መርህ የሚከተለው የኤርትራ መንግስት፡ 15 ደቂቃ ሙሉ አስመራ ውስጥ ርችት ከመተኮስ፡ ለምን በ6ቱ የሃገሪቱ ዞባዎች ከፋፍሎ፡ የበዓሉን ድምቀት በመላዋ የሃገሪቱ ክፍሎች ይበልጥ አላንጸባረቀም የሚል ሃሳብ ማቅረብ፡ ለወደፊቱ ለሚደረጉት ተመሳሳይ ድግሶች ጠቃሚ እንደሚሆን በማሰብ ነው።
ጽምዶ 38 በጦቢያ ቅድመ-ምርጫ የተለቀቀ፡ “ጎሞቹ” በተባለ የጦቢያ ወታደራዊ ጀነራል ንግግር ዙርያ ያጠነጠነ መልእክት ይዟል። “ጎሞቹ” የተባለው “ተሾመ ገመቹ” ለማለት ይመስላል። ‘ምርኮኛ ጀነራል” የተባለው አንዴ “ጎሞቹ” ሌላ ግዜም “ወዲጎሞቹ” ተብሎ የተጠቀሰው ባለስልጣን ባገሩ ቴሌቭዥን፡ ጽምዶን በተመለከተ የ20 ደቂቃ ቃለምልልስ ከአንድ “ትግራዋይ ባንዳ” ጋዜጠኛ ጋር እንዳከናወነ ይገልጻል ኣወሉ። ይህን የ20 ደቂቃ ቃለ ምልልስ ለመግለጽ፡ ኣወል ከ25 ደቂቃዎች በላይ ትንታኔ ሲሰጥ፡ ከ25 ግዜ በላይ “ጎሞቹ” የሚለውን ቃል ሲያነሳም ተስተውሏል። ለእያንዳንዷ ደቂቃ ቢያንስ ቢያንስ ኣንድ “ጎሞቹ” መሆኑ ነው!
በ9ኛ ደቂቃው የጽምዶው አጋፋሪ የቦርትሱዳኑን ዝግጅት በተመለከተ በሚመስል መልኩ “ጽምዶ የአፍሪካ ቀንድ ምሑራንን ይዞ ከተፍ ብሏል” ቢልም እንኳ ከኤርትራ በኩል “ምሑራን” የተባሉት እነማን እንደሆኑ አልገለጸም። አወል “የጽምዶ አመራሮች ሁሉም ሲቪል ናቸው፡ ተቃዋሚዎች ደግሞ የጦር ጀነራሎች” ሲልም ተደምጧል፡ ከዚህ በፊት፡ በዚህ በዘመነ ድሮን፡ “ዙ-23 ነኝ” የሚለው አወሉ እንዲሁም የትግራዩ የጽምዶ-ሰው ብርሃነም ወታደር መሆናቸውን አስረግጠው ነግረውን እንደነበር እናስታውሳለን።
ኣወል በዚህ “ጎሞቹ” የሚለውን ቃል ኣለ ቅጥ ኣጋንኖ ባነገሰበት የጽምዶ ዝግጅቱ፡ “ዓቅመ-ቢስ ምላሱ ረዥም ነው!” የሚል ምሳሌ በመጠቀም፡ የጀነራሉንና የብልጽግኖችን ምላስ ማርዘም ለመከርከም ሞክሯል። ኣያይዞም ጀነራሉ “በሬና ቀበሮ ባንድላይ ሊጠመዱ አይችሉም!” ያሉትን ቃል በማንሳት “ሻዕብያና ሕወሓት ባንድላይ ሊጠምዱ አይችሉም” የሚል ትርጓሜ ሲሰጥ ተስተውሏል። ጀነራሉን ይጠይቅ የነበረውን ጋዜጠኛ ፍራቻ በማንበብ፡ የተረጋጋ መንፈስ አይነበብበትም በማለት ያብጠለጠለው የጽምዶ-አጋፋሪ፡ ጀነራሉ “ሕወሓትና ፋኖ በባህርያቸው ባንድላይ አይጠምዱም” ለማለት ፈልገው ሊሆን እንደሚችሉ ለመጠርጠር አልፈለገም። አወል በዚህ መልእኽቱ “የገጽታ ንባብ ኤክስፐርት” እንደሆነም ጠቁሞናል፡ በመሆኑም ጋዜጠኞቻችን ቃለምልልስ በሚያካሂዱበት ወቅት ገጽታቸው ላይም ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው ግሩም ትምህርት ሰጥቷል። ይሰማል የዓለም ጋዜጠኞች!
በ23ኛ ደቂቃ “ጀነራሉ ጽምዶ በሚያራግቡ አካላት ላይ እርምጃ እንወስዳለን” ማለታቸውን ተከትሎ፡ አወሉ የግሌ መልስ ነው በማለት “እስከ አሁን ታድያ ማን እጃችሁን ያዘው። ብልጽግና ዓቕም ደልባ፡ ጽምዶ በሚያካሂዱ የኤርትራ የኢትዮጵያ የትግራይና የሱዳን ህዝብ ላይ እርምጃ እወስዳለው ማለቷ ገራሚ ነው። ዓቅም ቢኖራት ኖሮ የአማራን ህዝብ በድሮን እያደባዩት እንዳለው ጽምዶ ላይም በሞከሩት ነበር።” ሲል ተደምጧል አያይዞም የግሌ መልስ ይሰመርበት በማለት “ወደ ትግራይ የምትተኮስ አንዲትም ትሁን ጥይት፡ ኤርትራ ላይ የጦርነት አዋጅ እንደማወጅ ነው የምንቆጥረው። ‘ጎመቹ’ ያኔ መሬት ላይ የት እንደምንጠብቅህ እወቅ!” በማለት በምላሱ ጉራ ቢጤ ሲቸበችብ ተስተውላሏ፡ ጢሙ ሽበት የወረረው “ስለ ፊዚካል ዲማርኬሽንና ድንበር አስፈላጊነት” አንዲትም ቃል የማይተነፍሰው አወሉ።
ቀጥሎም፡ “ጽምዶ አድማሱን አስፍቶ የኤርትራ የኢትዮጵያ የሱዳንንና የትግራይን ህዝብ አቅፏል” በማለቱ፡ ትውልዱ ከሽሬም ይመዘዛል እየተባለ የሚታማዉ ኤርትራዊው የጽምዶ አጋፋሪ አወል፡ ለሃገረ-ትግራይ እውቅና የሰጠ መስሏል። ደስ ይበልሽ ሃገረ ትግራይ በተለይም የትግራይ ህዝብ የትግል መዲናዋ ደደቢትና ሽሬ ደስ ይበላችሁ!
“ጽምዶ ብልጽግናን የናጠና ያናወጠ ናላቸውንም ያዞረ የህዝብ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው” ያለው አወል፡ “ይህን ሰላማዊ የህዝቦች እንቅስቃሴ ለመግታት የሚጥር ማንኛውንም ሃይል መሬቱ ላይ ያገናኘን ያኔ የምናደርገውን እናሳየዋለን” ሲል በሰላማዊ መንገድና በምላሱ ዝቷል።
ከዚህ ጉዳይ በመለስ፡ ጽምዶ 38 ስለ የጦቢያ ሃገራዊ ምርጫ ኢፍትሓዊነት ሳይታለም የተፈታ ሓቅ መሆኑን ሲደሰኩር ተደምጧል። ምርጫ የሚያካሂዱ አገራት፡ የዲሞክራሲ ሰርቲፊኬት ተቀብለው፡ ብድር ለመቀበል ራሳቸውን ሲያመቻቹ እንደሆነም ጠቁሟል። “ኢትዮጵያ በታሪኳ፡ ታሪክ የሚደግሙ እንጂ ታሪክ የሚፈጥሩ መሪዎችን አልታደለችም” ያለው የጽምዶው አጋፋሪ አወል፤ የዓዲኳላዋ የእታችን ልጅ አቶ መለስ ዓባይን ገድቦ ብርቅ ታሪክ እንደፈጠረ የዘነጋ መስሏል። የታሪክ በጎ በጎ ጎኑም አሁንም አሁንም ሊደገም እንደሚችል ያጤነ አልመሰለም ወዳጃችን አወሉ። የኢትዮጵያዉያን የዓድዋ ድል በሶማሊያ መደገሙንም የዘነጋ ይመስላል ብለንም ሓቁን አልገልጥለትም፡ የካራማራ ማለትም የምስራቁ ድል ምን እንደሆነ ሊያውቅ ስለማይችል! መደገም ያለበት ታሪክ መደገም፡ መፈጠር ያለበት ታሪክም መፈጠር እንዳለበትም አልገባውም።
በ35 ደቂቃም “ወንጀሉ ከባድ ስለሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣኑን ለቆ የሚኖርበት ቁመና የለውም” በማለትም የብልጥግናው ቁንጮ ላይ ተረማምዷል። ይህ አለም ዓቀፋዊ እውነት ፍንትው ብሎ የሚታየው ሰዉየው ዓሰብ መመኘቱና ካቅሙ በላይ ህልም ማለሙን ግምት ውስጥ ስናስገባ ነው!
የጽምዶው አጋፋሪ የጦቢያን መሪዎች ሲወቅስም፡ ኃይለስላሴን በወሎው ድርቅ ሲወቅስ፡ ደርጉንም ጦርነት ጦርነት በመጫወቱ ሲወቅስ፡ ይህን ፉርሽ አዙሪት ተከትሎም ብልጽግና “ዓሰብ ዓሰብ ባሕር ባሕር” መጫወቱን ገልጾ ሲወቅስ፡ የትግራይ የብልጽግና የጽምዶ ምሰሶዎችን እነ ስታሊንን ሃይለ ደደቢትን ቢተውንና ጎደፋይን ላለማስቀዬም፡ የኤርትራ መሬትን ወርረው ለዘመናት የዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ አስተጓጉለው፡ በኤርትራ ህዝብ ዕድልና ሰላም ላይ ታሪክ የማይሽረው ጠባሳ የፈጸሙትን የወያኔዎችን የኢሓዴግ ስርዓትን ግን ሲወቅስና ሲነቅፍ አልታዘብነውም። የጽምዶው አጋፋሪ መርጦ አልቃሽነት ፍንትዉ ብሎ ታይቶናል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
በ45ኛ ደቂቃም የብልጥግናውን ወፈፌ መሪ “ራሱን እንደ የአምላክ መልክእክተኛና ነብይ ነው የሚቆጥረው” በማለት በብዙ የአፍሪካና የዓለም መሪዎች ላይ የሚታየውን ባህርይ ገልጿል። እራሱ የጽምዶው አጋፋሪ አወላችን የኛን ብረዚደንት ልብ ለማማለል ስማቸው አደናግሮት ነው መሰል “ነብይ” እያለ ሲያንቆለጻጽሳቸው በተለያዩ የጽምዶ ንግግሩ አድምጠን ነበር። ከመድኃኒታችንና ጌታችን ክርስቶስ በኋላ የነብያት ዘመን እስከነ አካቴው ማክተሙ አልገባውም። እርግጥ ነው የጽምዶው አጋፋሪ የብረዚደንታችንን አጥንታችውንም ቆጥሮ “ሓባ-አጽሙ” እያለም ሲጠቅሳቸውና ማሲንቆውን እየገዘገዘ አዚጥም አዚጥም ሲያስብላት ይደመጣል።
ጽምዶ 38 ሲጠቃለል፡ “ሻዕብያ ከብልጽግና ጋር ስውር ንግግር ያዟል” የሚል ዜና ውሸት መሆኑን፡ በኤርትራ በኩል ትግራይን የነጠለ ምንም ዓይነት ንግግር ከብጽልግና ጋር እንደማይካሄድ ቁልጭ አርጎ ገልጾ፡ የነ ሃይለ ደደቢትን ስጋት ለመቅረፍ በመሞከር፡ ድል ለሰፊው ሕዝብ በማለት ዝግጅቱን ቋጭቷል።
ጽምዶ 39
ፈጠን ብላ በጥድፊያ የወጣችው ጽምዶ 39 ደግሞ ትግራይ በብልጽግና ድሮን በተመታችበት ማግስት ብትቀርብም፡ ለሰላም ጥሪ ታቀርባለች፡ የትግራይን ህዝብ ለመታደግም ሞራላዊ ድጋፍ ታደርጋለች ብለን ብንጠብቅም፡ ስለ የጦቢያ “ምርጫ” ፉርሽነት በመተንተን፡ አንድ የምስራች ዜና አቅርባለች፡ ጽምዶ በኒውዮርክ በብራሰልስና በአዲስ አበባ በመንግስታት ጽሕፈት ቤቶች ውስጥ መግባቷም ተነግሯል።
የጽምዶው አጋፋሪ ያያ ሰይድ ልጅ አወል፡ ኢትዮጵያ ውስጥ “አሸባሪዎች” ቤተክርስትያኖችን እንዳቃጠሉ ገልጿል። ይህን እኩይ ድርጊት የፈጸሙት መንግስታዊ አሸባሪዎች ናቸው በማለትም ሃይማኖታዊ አሸባሪዎችን ነጻ ለማውጣት ቅኔ ሲቀኝም ተስተውሏል። የኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውስጥ ለውስጥ ቦተሊካዊ ንግግር ጀምሯል የሚል አሉባልታና የለየለት ውሸት መሆኑን ዳግም በመግለጽ፡ የአሜሪካ መንግስትን ግን ለዘመናት እናቀርበው የነበረ ሃሳብ ጋር በመስማማታቸው ከአሜሪካኖች ጋር ግንኙነታችን ከነበረው በተሻለ ደረጃ ላይ አለን በማለት ሲያትት አድምጠነዋል።
ቀጥሎም ኤርትራ በተባበሩት መንግስታት መድረክ፡ አንድ የሆነ ክፍል ውስጥ “ምክትል ብረሲደንት” ሆና መመረጧን በደስታ ስሜት የምስራች ነግሯል። እኛም “ፊዚካል ዲማርኼሽን ላይ የሚያደርስ ከሆነ ግሩም ዲብሎማሲያዊ ድል” ብለናል። ምንም እንኳ ኤርትራ እንደ ሃገር “ምክትል ብረሲደት” የሚለውን ቃል ብዙም የምትጠቀምበት ሃገር ባትሆንም፡ በተባበሩት መንግስታት መድረክ ይህን ሹመት መጎናጸፏን ለማወቅ አስችሎናል ጽምዶ 39። ለዚህ ድልም ለዕንቁዋ አምባሳደራችን ላያ-ሳርያም ልጅ ለወ/ሮ ሶፍያ ተስፋማርያም ምስጋና ሲያቀርብም አስተውለናል ያያ ሰይድ ልጅ።
በዚሁ የጽምዶ 39 ዲስኩርም፡ ከዚህ በፊት ጀነራል ፍሊጶስ ወልደዩሃንስ “የተቀኙለትን ቅኔ” አሁን ገና ያጣጣመ ሲመስል፡ “ጀነራላችን ወሬ አይወዱም ስራ እንጂ” በማለት ለመግለጽ መሞከሩ፡ ነገርና ቅኔ ከዓመት በኋላ የሚረዳው ዘገምተኛ ቢጤ መሆኑን ተገንዝበናል ወዳጃችን ያያ ሰይድ ልጅ። ጀነራሉ አስመራን ነጻ ባወጣው “ዛዛሚ ዅናት” በመባል በሚታወቀው፡ ከደቀምሓረ ጀምሮ የተደረገ የመጨረሻው ጦርነት ውስጥ የጦር መሪ ሆነው፡ የመገናኛ ሬዲዮናቸውን ይዘው፡ ጦር ይመሩ በነበሩበት ወቅት፡ ታጋይ ጋዜጠኞች ስለሁኔታው ጥያቄ ሲጠይቋቸው የሚያሳይ ታሪካዊ ተንቀሳቃሽ ምስል አቅርቧል። ያኔም የአሁኑ ጄነራል፡ ስንትና ስንት ወጣቶች ጦርነት ውስጥ ፊት ለፊት በሚተናነቁበትና፡ እሳቸውም ይህን ጦርነት እዬመሩ በነበሩበት ወቅት፡ “ለወሬ ግዜ የለንም” በሚል አኳኋን ከጋዜጠኛው ሲርቁ ተስተውለዋል። አዎን ያኔ ለወሬው ከድል በኋላ እንደርስበታለን ማለታቸው ነበር። አዎን “እንደ ጉንዳን በአንድ ዓላማ ተሰልፍው ጦርነት ውስጥ በመግባት፡ ጠላትን በማደባየት ፡ ህይወታቸውን በመሰዋት፡ ሃገር በመፍጠር ላይ ሁለንተናቸውን ለመሰዋት የተዘጋጁ ወጣቶችን በቅጡ የመምራት ድርብርብ ወታደራዊ ኃላፊነት ተጭኗቸው እያለ፡ ለወሬ ግዜው አልነበረም ለስራ እንጂ! አወልም ጭምር፡ እኒሁ ጀነራል ከሰራዊታቸው ጋር በግድብ ስራና ምረቃ ላይ በነበሩበት ወቅት ሊያናግራቸው አስቦ “ለወሬ ግዜ የለንም ለስራ እንጂ!” የሚል ቅልብጭብጭ ያለ ቅኔ ተቀኝተውለት እንደነበር ይታወሳል።
በዚሁ በጽምዶ 39፡ ወዳጃችን ያያ ሰይድ ልጅ አወሉ፡ ብረዚደንታችን ወደ ካይሮ ማቅናታቸውን ገልጾ በቀጣዩ ስራው፡ የግብጹን የሱዳኑንና የኛውን ብረዚደንት ፎቶ ከጽምዶ አባሎች ጎን እንደሚለጥፈው ገልጿል። እኛም ይህንን አስተውለን የግብጹ አልሲሲ ምን ስራ ቢበዛባቸው ነው ስልጣን ላይ ከወጡ ከሰኔ 2014 ጀምረው እስከ አሁን አንዴ ብቻ ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ፤ የኛው ብረዚደንት ግን 9 ግዜ በይፋ ወደ ካይሮ ያቀኑት ምስጢሩ ምንድን ነው ብለን ለማጥናት ሞክረናል። ብረሲደንታችን 3 ግዜ በግብጹ የአልሲሲ የንግስና ዕለት ማለትም ሰኔ 8 ካይሮ ውስጥ በመገኘት አጋርነታቸውን እስከመግለጥም ደርሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አልሲሲ፡ ኤርትራ ውስጥ ዩኒቨርሲቲ ሊሰራ ነው የሚል የመገናኛ ብዙሃን በሚባሉት ብዙሃንን ለማደናገር የተነዛ ወሬ በመስማታችን፡ ሰዉየው ባገሩ ከሰራቸው የትምህርት ተቋማት ይልቅ የሰራቸው መስጅዶች ይበዛሉ፡ ከ9ሽህ በላይ መስጅዶን ሰርቷል ወዘተ የሚል ሃተታ በማየታችን ገርሞን ፈገግ ብለናል። viewtopic.php?f=2&t=380519 ይህ ማለት ግን ከአልሲሲ ጋር የቀይ ባህርን የሰላም ጉዳይ በተናበበ መልኩ አናስኬደውም ማለት አለመሆኑ መታወቅ ይገባዋል። ለምን ቢባል ሁሉም ደንበሩንና ሃላፊነቱን አውቆ መጓዝ ስለሚገባው። እንደኛ እንደ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ነጻ እይታ፡ “ሓቀኛ ጽምዶ፡ በፊዚካል ዲማርኬሽን የተማከለ መሆን ይገባዋል” ምክንያቱም ጀግኖቻችን የተሰውት “ለዶብ ማለት ለድንበር” መከበር ስለሆነ!
አስቀድሞ አወል በጽምዶ 38 “ወደ ትግራይ የምትተኮስ አንዲትም ትሁን ጥይት፡ ኤርትራ ላይ የጦርነት አዋጅ እንደማወጅ ነው የምንቆጥረው። ‘ጎመቹ’ ያኔ መሬት ላይ የት እንደምንጠብቅህ እወቅ!” ብሎ በዛተው መሰረት፤ የመልስ ምት በሚመስል መልኩ፡ ትግራይ ውስጥ ሸራሮና ገማህሎ አካባቢ፡ የብልጽግና ድሮን ጉዳት ማድረሷን የሚገልጹ ዜናዎች በመስማታችን፡ ያገራችን ተቀኝዎች
አባኢሶሞ መሲሎም ዘራይ፡
አረሳሲኖም መሲሎም ዘራይ፡
ኪህረም ከሎ ስሒቆም ዳሕራይ! እንዲሉ
ውረድ እንውረድ ተባባሉና፡
አስደበደቡት አፋፍ ቆሙና!
የሚለው ዕድሜ ጠገብ ተረት ትዝ ብሎን፡ ትግራይ ውስጥ ሰለባ ለሆኑት ዜጎች መንግስተሰማይን ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ተመኝተናል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=308857&.
ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ ኤርትራዉያን ሃገር በመፍጠር የተሰዉ ጀግኖችን ይበልጥ የምንዘክርበት ወርሃ ሰነ በመግባታችን ይህችን ቅኝታችንን አካፍለናችኋል።
Meleket wrote: ↑08 Dec 2022, 08:34
ኣብ በሊሕ መላጸ
ተሰሪዖም ከም ጻጸ፡
ኣብ በሊሕ መላጸ፡
ብመስዋእቶም ...
ዘስገሩ ብጾቶም፡
ዘይርሳዕ ውዕለቶም፡
ንሳቶም ...
ኣብ በሊሕ መላጸ ሚልዮናት ዘስገሩ፡
በጃ እናሓለፉ ፍቕሮም ዘመስከሩ፡
ሃገር ዝፈጠሩ፡
“አናብስ ስዉኣት” ወትሩ ይዘከሩ።
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5227
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 13 Jun 2026, 05:06
እንደሚታወሰው ባለፉት የጽምዶ ዝግጅቱ የጽምዶው አጋፋሪ አወሉ፡ የያኔውን ወታደር አብይ አሕመድ ዓሊ (የአሁኑን የኢትዮጵያ ጠቅላይን) መሆኑ ነው፡ በባድሜ አካባቢ በአንድ የጦርሰራዊቶች የሙዚቃ መድረክ መሃል ሲውረገረጉ አሳይቶን ነበር። ማን ያውቃል የወታደር ዝናሽን ልብ ለመስለብም ይሆናል ብለን ፈገግ ብለን ነበር።
እስቲ ዛሬ ደግሞ ለፈገግታ ያህል፡ የዛሬው የጽምዶ አጋፋሪ ኣወሉ፡ ምን ዓይነት ኰሜዲ ላይ ይተውን እንደነበር ፈገግ እያልን እንታዘበው። “ጭሎ” የመሰለው አወሉ ያኔ “ሓባ ዓጽሙ” ምናምን እያለ ኣይፎግርም ነበር! በወቅቱ ኤርትራ ውስጥ አሉ ከሚባሉት ጉምቱ ወጣት ኮሜዲያኖች መካከል ሓጎስ ወልደገብራኤል (ሱዚኒኖ) አንዱ እንደነበርም ይታወቃል! ተዝናኑ እስቲ! የጽምዶውን አጋፋሪ “ስንዝሮ” ያልነው በምን እንደሆነም ፍንትው ብሎ ይታያችዋል!
https://www.facebook.com/reel/1513953656773257
Please wait, video is loading...
ወርሃ ሰኔ በመሆኑም ሃገር ፈጣሪ ሰማእታቶቻችንንም እንዘክራለን።
Meleket wrote: ↑08 Dec 2022, 08:34
ኣብ በሊሕ መላጸ
ተሰሪዖም ከም ጻጸ፡
ኣብ በሊሕ መላጸ፡
ብመስዋእቶም ...
ዘስገሩ ብጾቶም፡
ዘይርሳዕ ውዕለቶም፡
ንሳቶም ...
ኣብ በሊሕ መላጸ ሚልዮናት ዘስገሩ፡
በጃ እናሓለፉ ፍቕሮም ዘመስከሩ፡
ሃገር ዝፈጠሩ፡
“አናብስ ስዉኣት” ወትሩ ይዘከሩ።
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5227
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 17 Jun 2026, 11:11
ኤርትራዉያን ሃገር የፈጠሩ ሰማእታቶቻችንን በምንዘክርበት በወርሓ ሰኔ፡ ከዚህ በፊት በፖርትሱዳን የተደረገው የጽምዶ ዝግጅት አካል የሆነው ሰሞኑን በቅርቡ የተሰራጨውን ከተለያዩ ተሳታፊዎች ጋር የተካሄደው ቃለመጠይቅን የያዘ “ጽምዶ 38 እና ሰፊ ቃለመጠይቅ” የሚል ርእስ ያለው የጽምዶ ዝግጅትን ለማድመጥ እድሉን አግኝተን ነበር። ጠቅላላው ይዘቱ ምን ይመስላል እንሆ። አንዳንድ ሃሳባችንን ደግሞ በነጻነት እናጋራችኋለን፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር!
አወል፡ ሲጀመር እነዚህ ጥቂት ጥያቄዎችን ለመመለስ በጋበዛችሁኝ መሰረት ተገኝቻለው በማለት፡ ጥያቄዎቹን አስቀድሞ ማንበቡን ጠቁሞናል ከጅምሩ። ምንም አልተዘጋጀሁም፡ አሁን ገና ከውጭ ሃገር መግባቴ ነው፡ ብዙ ድካም አለኝ፡ ግን ደህና የምችለውን እሞክራለው። በማለት ቃለመጠይቁን አስመራ ውስጥ እንዳደረገው ጠቁሞናል። ሌሎቹ ተጋባዥ እንግዶች “ኤሊቶች” ደግሞ ቃለመጠይቁን ቦርት ሱዳን ውስጥ እንዳካሄዱት ከውይይቱ መገንዘብ ይቻላል። በቀጥታ ወደ ዝርዝር ይዘቱ! ታሪክም እማደል እየከተብን ያለነው።
የፖርት ሱዳኑን ጽምዶ እንዴት አገኘሀው?
አወል ሰዒድ - የጽምዶው አጋፋሪ
አዳራሹ ውስጥ እንደተነገረው፡ ጽምዶ ወደ 3ኛ ደረጃ ከፍ ማለቱን ነው የሚያሳየው። “የኤሊት ጽምዶ” ነው። ጽምዶ ሲጀምር ከህዝብ መካከል የጦርነት የመጀመሪያው ቀጥተኛ ገፈት ቀማሽ በሆኑ አካላት ነው የጀመረው። ሩቅ ቦታ ሆነህ ስለ ጦርነት መገመት ብቻ ነው የምትችል፡ ግንባር ላይ ከሆንክ ግን ገፈት ቀማሽ ስለምትሆን የጦርነትን ጦስ በደንብ ነው የምታውቀው፡ ስለዚህ በነዚህ በገፈት ቀማሾች መጀመር መርጠናል። ሌላ ግዜ ከጽምዶ አባላት አስፈቅጀ ቦርቀቅና ሰፋ ያለ ትረካውን እነግራችኋለው፡ ለአሁን ግን ደረጃ በደረጃ እንዴት እንደተቀጣጠለ ልግለጽላችሁ። የሁለቱ ህዝቦች መንግስታት ቀይመስመሮችን ሳንጥስ ነገሩን ለመምራት ሞክረናል። [የድንበር ብይኑ መሬት ላይ በፊዚካል ዲማርኼሽን አማካኝነት ይቋጭ ማለትስ የመንግስታቱ ቀይ መስመር ነውን?] ይበልጥ እንድንታወቅ ጠላቶቻችን አብይ አህመድ ጭምር የጽምዶ አባል በመሆን ደግፈውናል። በኤርትራ ነጻነት በዓል ምክንያት አብይ አህመድን ላመሰግነው እወዳለው።
1100ኪሜ ባለው ስፍራ ጽምዶ አድርገን ወደ ሱዳን ተሸጋግረናል፡ ፖርት ሱዳን ላይ ጽምዶን ያካሄድነው በህዝብ ጥያቄ ነው አማራ ጋምቤላ ሱማሌና ሱዳን እንዲሳተፉ ለማስቻል ነው። ህዝብ ስለተባበረ ብልጽግናን ለጦርነት የሚሆን ስፍራ አሳጥቷታል። ቀስ በቀስ ጽምዶ በማደጉም፡ ኬላዎች መነሳት፡ ሰራዊት ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀስ፡ እስረኞች እንዲፈቱ ወዘተ ደግፏል። [ኤርትራ ውስጥ የነበሩ የትግራይ እስረኞች እንደተፈቱ ነግረሀን ነበር፡ ኤርትራዉያን ለዓመታት የተሰወሩ ወጣት ጋዜጠኞችና ጉምቱ ጉምቱ ሻዕብያዎችስ ለምን አልተፈቱም? እስቲ ፕሮ መሓመድ ሓሰን እንዲሁም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌንም ጠይቀህ መልሱን ንገረን] በኤርትራና በትግራይ በኩልም መሪዎች ድጋፋቸውን ለግሰውናል። ይህ የጽምዶ ሁለተኛው ደረጃ ነው። ሶስተኛው ደረጃ ደግሞ ይህን ስራችንን ለዓለም በሚገባው ቋንቋ መግለጽ ነው። እኛ ኦሮሞ እንዲህ ዓይነት ችግር እንደሚያሳልፍ አናውቅም ነበር፡ ምክንያቱም ኦፒዲኦ ኦሮሞ ስለሆነ የራሱን ህዝብ ይጨፈጭፋል ብለን አናስብም ነበር፡ የአማራም እንዲሁ። በኋላ ግን የተደበቀ ምስጢር መውጣት ጀመረ፡ በጽምዶ ምክንያት። [ከመከረኞቹ ነጮች በከፋና ባልተናነሰ ሁኔታ የውስጥ ጨቋኞች ህዝቦቻቸውን እንደሚጨቁኑ የማታውቅ ከሆንክ’ማ ምኑን ቦተሊካ ቻልከው አንልህም ያያ ሰይድ ልጅ!] ሱዳን ባለውለታችን ስለሆኑ ሱዳን ሆነን ጋምቤላን ኦሮሞን አማራን ሱማሌን ወዘተን ማግኘት ይቻላል ብለን፡ ሰዎች ጋብዘን አካሄድነው። ጽምዶ ውስጥ ችግራችንን አናወራም፡ እልፍ አእላፍ ችግር አሳልፈናል፡ ግን ስለ ችግራችን አናወራም። ይህን ይህን አሳልፈናል ወዘተ ካልን ጽምዶን እየነገድንበት ነው ማለት ነው።[ አወል - ጭሎ፡ ራስህ ይህን የዛሬውን ዝግጅትህን ስትጀምር እኮ፡ በጣም ደክሞኛል አሁን ገና ነው መግባቴ ግን ደህና ጥያቂያችሁን ልመልስ እሞክራለው ወዘተ እያልክ ሚዛንህን ከፍ ለማድረግ ቁመትህንም ለማርዘም ጥረሃል እኮ፡ ሁለንተናህን ለሃገር መስጠት ብርቅ ባልሆነባት በሰማእታት ምድር።]
ጽምዶ ማለት ሰላም እንሻለን የሚል መልእኽት ነው። የአካባቢያችን ዋንኛ ጠላት በአብይ የሚመራው ብልጽግና ነው። ከሱማሌ ከኤርትራና ከሱዳን ጋር እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ እየተናቆረ ያለው የአብይ ፓርቲ ብልጽግና ነው። [ከዚህ በፊት ኤርትራንም ከሁሉ ጎረቤቶቿ ጋር ተናቁራለች ብለው ይከሱን ነበር] አብይ ከነ ብልጽግና ባርቲው፡ እኛን እስርበእርስ ለማናቆር ያወጣውን እቅድ ነው ገና ወረቀት ላይ እያለ ያመከነው። እኛ ሰላም እንደምንሻ የሚሰማን ከሆነ ለዓለም ማኅበረሰብ ነው መንገር የምንፈልገው። ይህ ትልማችን በትግርኛ ጀምሮ በ9 የኤርትራ ብሄሮች ድጋፍ አግኝቶ፡ ትግራይ ውስጥም በ3 ብሔሮች ድጋፍ አግኝቷል [ትግራይ ውስጥ አማራና አገው በቁጥር ንጽጽር ከሳሆ (ኢሮብ) እና ኩናማ በላይ ናቸው፡ በነዚህስ ድጋፍ አግኝቷልን ብለብን አንጠይቅም።]የውክልና ጦርነት አፍሪካን ለዘመናት አድምቷል፡ አሁን ግን ይበቃል እያልን ነው። “ጽምዶ” የሚለውን ብራንድ አብይ በጌዲዮን ጢሞቲዎስ በኩል ዩኤን ጽህፈትቤት ውስጥ አስገብቶልናል፡ እኛ ግን “ጽምዶን” እንዴት አድርገን ዓለም ዓቀፋዊ መድረክ ውስጥ እናስገባዋለን ብለን እያሰብን ነበር። አብይ የጽምዶ አባል ነው የምንለው ለዚህ ነው። አንዳንድ ጊዜ ጠላት ያስፈልግሃል፡ ከሌለህም መፍጠርም ይገባሀል። ጠላት ስለነበረን ነው ይህን ሁሉ የተጓዝነው። የዓለም ማኅበረሰብን ለማሰማት፡ “ሎቢስት” መቅጠር አንችልም፡ ጽምዶ እንደሆን የድሆች ስራ ነው። ማንኛውም ሰላም ፈላጊ አካል ይህን ድማጻችንን እንዲያስተጋባልን ነው ፖርትሱዳን ውስጥ ያን ስብሰባ ያካሄደነው። ባሻችሁ ቋንቋ ለማኅበረሰብ አለም አሰሙልን፡ እኛ እዚህ ድረስ አምጥተነዋል ብለናቸዋል። ይህን እንዲከታተልልንም ከጽምዶ አካላት ዳንኤል ተክላይ የተባለ ሰው መርጠናል [ዳንኤል ተክላይ የተባለ አንድ ሃገር በሚል ስም የራሱ ንቅናቄ ከፍቶ የነበር፡ በውጭ ሃገር እየኖረ የኤርትራ መንግስትን በሃሳብ የሚሞግት የነበር፡ የኤርትራ ወጣት ድንበርና ልዑላዊነት ለማስከበር ግንባር ላይ ሲፋለም፡ የምዕራብ ቀምጣሌ ይገምጥ የነበረ፡ በጽምዶ አማካኝነት ኤርትራ የሄደ፡ አሁን EitreaNEXT.org የተባለ ድርጅት ስራአስፈጻሚ መሆኑ ነው፡ የዋርሳይን ጩኸት መቀማቱ ነው፡ በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ ይሉሃል ይህ ነው]፡ ይህ ሰው በእንግሊዝኛ እየሰራ ስለቆዬ እሱን መርጠነዋል። ማንኛውም ሰው ጽምዶ ይመለከተኛል የሚል ስሜት እንጂ የኔ የግሌ ነው ማለት አይቻልም፡ ጽምዶ የህዝብ ስለሆነ። እኔ ነኝ የጀመርኩት እኔ ነኝ ያካሄድኩት የሚል ጉዳይ ተረት ተረት ነው [ይህ አባባልህ የትግራዩን የጽምዶ አጋፋሪ የነበረ በብልጽግና ውርንጭሎች አማካኝነት የቦምብ ጥቃት የደረሰበት፡ የኋላኋላም በሕወሓት አላግባብ ታስሪያለው ያለውን፡ ብርሃነ ገብረግርግሽ (ልፍዓተይ ወይም ሰብ ዝሰኣነሰብ) ላይ ለመረማመድ አይመስልምን? የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል ይሉሃል ይህ ነው!] የጽምዶ 3ኛ ደረጃ ያልነው እነዚህ ኤሊቶችን ያሳተፈ ነው። እንችላለን የሚሉ አካላትን መድረክ ፍጠሩልን እንጂ ልናገኛችሁ እንሻለን የሚሉ አካላትን ደግሞ ጋብዘን መድረክ ፈጥረን ይህን ይመስላል የፖርት ሱዳኑ የጽምዶ ዝግጅት። [ይሁና የኤርትራው ኤሊት የጽምዶው አጋፋሪ ሆነ ማለት ነውን? በቃ የኤሊት ትርጉሙ እንዲህ ቀለለ ማለት ነው። ሙዚቃ ማቀናበርና ማሲንቆ መከርከር እኮ ለየቅል ነው። ኤሊቶች እንደ ሙዚቃ አቀናባሪዎች ሲታዩ፡ አጋፋሪዎች ደግሞ እንደ ማሲንቆ ገዝጋዥ ወይም ክራር ከራሪ ይቆጠራሉ።]
አንዳርጋቸው ጽጌ
ትላንት እዚህ ፖርትሱዳን ውስጥ ያደረግነው የጽምዶ ስብሰባ፡ ሃሳቡ ከመነጨበት የኤርትርና የትግራይ የድንበር ህዝቦች በላይ አልፎ ሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ህዝብ እንዲገነዘበው፡ በህዝብ የተጀመረ የሰላም ድምጽ መሆኑን፡ የእስካሁን የቀጠናችንን ችግር በአዲስ መልኩ ለመፍታት ሃሳብ ያመነጨ ስኬታማ ስብሰባ ነበር።
አብዱራሕማን ማህዲ
ግሩም ነው። ያፍሪካ ቀንድ ህዝቦች በጣም ለመቶዎች ዓመታት ሰቀቀን ውስጥ ናቸው። ኤሊቶች ነን ባዮች ለተራው ህዝብ ደንታ የሌላቸው ጦርነት እየጫሩ ስደተኛ ሲያመርቱ ኖረዋል። [ግሩም አገላለጽ ነው] ህዝብ ለህዝብ ሲወያይ ነው ለሰላምና ለልማት ዋንኛው መንገድ። ጥሩ ጅማሮ ነው፡ የአፍሪካ ህዝቦች መለያ ባህልና ባህርይም ነው፡ በጋራ መወያዬትና የጋራ መፍትሄ መሻት፡ አፍሪካውያን ይህ ነው ኑሯቸው። ተራው ህዝብ እርስ በእርስ መነጋገር ሲጀምር ነው ትክክለኛው ሰላም የሚመጣው። [ግሩም አገላለጽ ነው]
ፕሮ መሓመድ ሓሰን
የትላንትናው ዝግጅት የጽምዶ ውይይት፡ ሁለት አንጋፋ አርእስቶች ናቸው የተታዩት።[ምን እና ምን ናቸው የተታዩት?]
1ኛ ለሱዳን ህዝብ አጋርነትን ለመግለጽ። በመካከላችን እየገቡ የሚበጠብጡ የውጭ ሃይሎች አሉ። ከቅርብም ከውጭም። ማንም የማንም ጠላት አይደለም። ከሱዳን ህዝብ ጋር አጋርነታችንን ለመግለጽ የተካሄደ ነው። [የምን መሸፋፈን ነው በጥባጭ ሃይሎች የተባሉት ለምን በስም አልተጠቀሱም?] 2ኛው ዓላማ ጽምዶ የሚለውን ፍልስፍና የኣፍሪካ ቀንድ ህዝብ በየቋንቋው እንዲወያይበት ነው። ጽምዶ ማለት በአንድ ላይ በህብረት እንስራ ማለት ነው። ግጭቶችም ቢኖሩ የምንፈታበት የራሳችን መድሃኒት መኖር አለበት የሚል ነው። ችግር የሚፈጥረው አካል፡ እንደገና ችግር ፈቺ መስሎ ዳግም ይመጣል። ሰላም አምጪ መስለህ በታታኝ መሆን ነው የነሱ ስራ። ለምን ሱማሌ አንድ አልሆነችም ታዲያ። እነሱ የሚሉትን የውሸት ሰላምን ትተን የራሳችን ሰላም እንፍጠር። ከባህር ማዶ መጥቶ ችግር የሚፈታ የለም። እነሱ ለራሳቸው ጥቅም ሲሆን የራሳቸው ጽምዶ አላቸው። የአለም ፖለቲካ በ1990 ሲለወጥ በ1992 “ማስትሪክት” የሚባል ፕሮግራም መጥቶ አውሮፓ ህብረትን ሲመሰርቱ የራሳቸውን ጽምዶ ፈጠሩ። እንዴት ፈጠሩት ሲባል፡ መጀመርያ አውሮፓ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጽምዶ ውስጥ መግባት አለባቸው አሉ። የታሪክ ካሪኩለማቸውንም ማስተካከል አለባቸው፡ ቀድመው ከዚህ በፊት ለወጣቶቻቸው ይግቷቸው የነበሩት የጦርነት ትምህርት ተሰርዞ በትብብር መንፈስ በዚህ ሁኔታ ነው የተፈጠረው። እያንዳንዱ ልጅና ወጣት ለአንድ አመት ሌላ ሃገር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትምህርት መማር ኣለበት ብለው “ኢራስሞስ” የሚባል ፕሮግራም ፈጠሩ። ኢራስሞስ ከዚህ በፊት የነበረ ሰላም ወዳድ ፈላስፋ ነው ብለው ነው የሚያምኑት። የራሳቸውን ጽምዶ ለወደፊት ትውልድ እያስተማሩ ነው። [ ታዲይ ምኑ ላይ ነው ሃጥያታቸው፡ አንተ እንደነሱ ማድረግ ስላልቻልክ እነሱን ማንቋሸሹ ምን ይሉታል? አፍሪካውያንን ሰነፎች ይሉናል ብለህም ነበር ከዚህ በፊት፡ ትክክል ናቸው ሰነፎች ባንሆን በየጎጡና በየሃይማኖቱ እየተቧደንን እንፋለስ ነበርን፡ ሱማሌ አንዷ የአፍሪካዉያን የስንፍና መገለጫ ናት? አይደለም እንዴ?] እኛ ደግሞ ሰው ነን። የራሳችን ጽምዶ መፍጠር አለብን፡ ይህ ጽምዶ ተባዝቶ ለቀጠናው ህዝቦች መዳረስ አለበት። እኛም ችግራችንን መፍታት እንችላለን፡ ከኛ ጋር አጋር መሆን የምትፈልጉ መንግስታትና ህዝቦች ጥሪያችን ይድረሳችሁ እላለው። እኛ ስንኩላን አይደለንም፡ እውሮች አይደለንም፡ ደንቆሮዎች አይደለንም፡ ጭንቅላት አለን፡ ባህል አለን፡ ሃይማኖት አለን፡ ዕድሜ ልካችን ስንኖር የነበርን ነን፡ ከዚያም አልፎ የሰው ልጅ የተፈጠረበት ስፍራ ነው የምንገኘው። የመጀመርያ ሰዎች እዚህ ነው የነበሩት፡ ስለዚህ እኔ በጣም ደስተኛ ነን። ይህ እንዲቀጥል እንፈልጋለን ወጣቶቻችን ጋር እንዲደርስም እንሻለን። ያፍሪካ ቀንድ ህዝቦችም ባንድ ላይ እንድንኖር እፈልጋለው። [ግሩም ትንታኔ ነው “ኤሊት” ተብለህ በስንኩላን በእውሮች መስማት በተሳናቸው ዜጎቻችን ስነልቦና ላይ መረማመድህ፡ አንተው ራስህ እያየህ የማታይ እየሰማህ የማትሰማ፡ የስደተኞች ሮሮ የማይሰማህ፡ የእስረኞችና የተሰወሩ ጋዜጠኞችና ቦለቲከኞች የቤተሰቦቻቸውም ድምጽ የማይሰማህ፡ የልማትና የህንጻ ስራዎች ፍላጎት ጥሪም የማይታይህ “የቦለቲካ ኣዝማሪ” ሆነህ እንዳይሆን ነፍስህን ፈትሽ ብሮፉርሸር መሓመድ።]
ንካዋ ኦሾላ
ጽምዶ አገር በቀል ግሩም ሃሳብ ነው መበረታታት ይገባዋል።
የጽምዶ እንቅስቃሴ አጀማመሩና ግስጋሴውን እንዴት ታየዋለህ?
አንዳርጋቸ ጽጌ
የጽምዶ ነገር በጣም የሚገርመው፡ ጀማሪዎቹ የኤርትራና የትግራይ የፖለቲካ ልሂቃን ወይም ወታደራዊ አዛዦች አይደለም የጀመሩት። ድንበር ላይ የሚኖሩ ህዝቦች ናቸው የጀመሩት። [አወል አቶ አንዳርጋቸው አንተን ሆነ ብርሃነ ገብረገርግሽን ኤሊቶች አይደላችሁም እያላችሁ ነውን?] ፖለቲከኞች ሰላም እንዲያመጡ የኛ አስተዋጽኦ ያስፈልጋል። እኛ ለእኛ ሰላም ካልቆምን ማንም ኣይቆምልንም ብለው ተራ የሚባለው ህዝብ ነው ጽምዶን የጀመረው። ከዚያ ጀምሮ ግን እየሰፋና እየተቀጣጠለ ከኤርትራና ትግራይ አልፎ በአማራ በኦሮሞ በከንባታ ወዘተ ኢትዮጵያ ውስጥም ተመሳሳይ ችግሮችን ይፈታል ብለን ነው የምናስበው። ከኤርትራና ኢትዮጵያ አልፎም በተመሳሳይ ችግር የሚናጡ ሃገሮች እንደ ሱዳንና ሱማሊያም ውስጥ ምስራቅ አፍሪካ በሙሉ መፍትሄ ያስገኛል ብለን ነው የምናምነው። ይህ ከሆነ ደግሞ የፖለቲካ መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ህዝቡ በትልቁ እጁን ያስገባበት የሰላምና መረጋጋት ሁኔታ በአፍሪካ ቀንድ ይፈጥራል ብየ አስባለው። ባጭር ግዜ ያመጣው እድገት ቀላል አይደለም በሂደት የአፍሪካ ቀንድ ትልቁ የሰላም ዋስትና ይሆናል ብዬ ነው የማስበው እኔ።[ በኤርትራና በቀይ ባህር አኳያ ያለው አመለካከትህንስ አስተካክለሃልን? በዚህ ረገድ ከብልጽግና ምንም ልዩነት አላየንብህም። https://mereja.com/forum/viewtopic.php? ... 5#p1534145]
አብዱራሕማን ማህዲ
ጽምዶ ከላይ ወደታች በተጽዕኖ የመጣ ሳይሆን ከታች ወደላይ ያደገ ሃገር በቀል የህዝብ ሰላማዊ ስራ በመሆኑ ስኬታማ ነው።
ንካዋ ኦሾላ
ተራው ህዝብ ፍላጎቱ አንድ ነው በመሆኑም ጽምዶ ማለቱ አይገርምም። ያፍሪካ ቀንድ ከሚንጣት ችግር መላቀቂያ አንዱ ፈውሷ ጽምዶ ነው።
በፖርት ሱዳን ጽምዶ ላይ የተካፈሉት ኣካላት የማን ወኪሎች ናቸው?
አወል
እኔ መቸም በአኝዋክ ቋንቋ አንዱን የጋምቤላ ሰው ላስረዳው አልችልም። አንድ መግባቢያ ቋንቋ ግን ያስፈልጋል። ሰላም ለምሳሌ ማንም ሰው ያውቃታል። በቀላሉ ለማንም ሰው ሰላምታ በማሳየት ልትገልጻት ትችላለህ። ገንዘብ ለመሰብሰብ በመገናኛ ብዙሃን ወሬ የሚያበዙ አካላት ሞልተዋል። ብልጽግና ውሾችን እንደሚልክብን አስቀድመን እናውቅ ነበር፡ በመሆኑም ይህን ለመፈወስ ነብሮችና አንበሶችን መልምለናል። የጽምዶ አባላት ብለን ፎቶግራፋቸውን የለጠፍነው ሰዎች አንዳንዶቹ ተሳዳቢዎችና መልካም ባህርይ የሌላቸው ሳይቀሩ አሉ። አንድም አለ ከኛም ከብልጽግናም ጋር የሚሰራ የነሱ ሰው፡ ባንድ ጭውውታችን “በብልጽግና እይታ አንዲት ውሸት 10 ሰዎችንም ማሞኘት ከቻለች” እንጠቀምባታለን የሚል ፈሊጥ ነው ያላቸው ብሎ ነግሮኝ ነበር። “ውሸትን እንደ መድፍ ነው የሚጠቀሙበት። [ውሸት የብዙ መንግስታት ቀንደኛ መሳሪያ መሆኑን አፍሪካውያን ጠንቅቀን እናውቃለን እኮ። አንዱ መሪ ተነስቶ ህገመንግስት እየቀረጽኩላችሁ ነው ሊልህ ይችላል፡ ቀርጾ ሳያስህ። እንዲያ ያሉ ያፍሪካ መሪዎች አታውቅምን አወል ያያ ሰይድ ልጅ]
አንዳንድ ሰዎች ክቡር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን “ማንን ወክለህ ነው ፖርት ሱዳን የሄድከው፡ አማራን ወክለህ ነውን?” ተብሎ ሲጠየቅ ሰምቸ ነበር፡ እሱም “ራሴን ነው የወከልኩት” ብሎ ነበር። እኛ ሰላም የሚለው ሃሳብ ደጋፊዎች ነን እንጂ፡ እኔም የኤርትራ ህዝብ ወኪል አይደለሁም።[ ታዲያ በምን ሂሳብ ነበር ብርሃነ ገብረገርግስን መረብ ወንዝ ድልድይ ላይ አንተም ህዝብህን እኔም ህዝቤን ይዘን እንገናኝ ትል የነበረው? እንዴ ለመልካም ነገርና ለሓቀኛ-ጽምዶ ከሆነ እኮ ህዝብ መወከል ነውር የለውም። እኛ የጠላነው “ፊዚካል ዲማርኬሽንን” ያላማከለ ጽምዶ ነው። ስጋታችን ውሎ አድሮ እንደ የስዑዲያ ጽምዶ እንደ የብሪቶሪያ ጽምዶ ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር። ] በጽምዶ ዝግጅት ሂደት ስህተቴ በሙሉ የኔ ነው፡ ውበቴ ግን የህዝብ ነው። ጽምዶ ውስጥ ያሉ ሁሉም ስህተቶች የኔ ናቸው፡ ሁሉም መልካም ጎኖች ደግሞ የህዝብ ነው። ይህን ሃላፊነት ይዘህ ነው ለመስዋእትነት የምትዘጋጅ።
ጽምዶ ውስጥ ዘር ማንዘር ጎጥ ሃይማኖትና ወገተኝነት ወዘተ የሚባል ፈሊጥ የለም፡ ስንጀምረው ደግሞ ይህንን ለመደምሰስ ብለን ነው የተነሳነው። [አወል ራስህ እኮ ነህ ኣምልኮተ ጣኦት ወይ ኣምልኮተሰብ ለማስፈን “ሓባ ኣጽሙ” እያልክ በሰማእታት ምድር አጥንት ቆጠራ የጀመርከው ወዳጃችን] አንዳርጋቸው ጽጌ አማራን አልወከለም ግን አማራ ነው። እኔ የኤርትራ ህዝብን አልወከልኩም ግን ኤርትራዊ ነኝ። እሳተፋለው የሚል ካለ ይምጣ ፡ ይህ ሸንጎ ወይ ካቢኔ ኣይደለም እሳተፋለው ያለ አካል ሁሉ ራሱን ወክሎ መምጣት ይችላል፡ በሩ ክፍት ነው። [ጎበዝ የሃገርህን ኤሊቶች ሳትጋብዝ፡ ከአፍሪካ ቀንድ “ኤሊቶች ጋር ለመነጋገር መሞከር ከንቱነት ነው። ያገርህን ልጆች፡ ካንተ ሃሳብ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ዜጎችህን “ትርፍራፊ በይዎች” እያልክ ነጋ ጠባ እየሰደብክ፡ ሌሎች “መጋበዝ” በሰማእታት ዓይን አያስከብርህም። ያገርህን ልጆች መጀመሪያ ጋብዝ! እርቅና ይቅርታን ከሃገርህ ልጆች ጋር ጀምረው መጀመርያ፡ ከዚያ በተረፈ መለፍለፍ ቦለቲካዊ አመንዝራነት ነው። ]
የቀጠናችን ችግር ምን መሆን አለበት?
አንዳርጋቸው ጽጌ
ጽምዶ መፍትሄ አለው ባይ ነኝ። በጋራ መስራት መፍትሄ ያመጣል የውጭ ጣልቃ ገብነት ማስቆም መቻል አለብን፡ አንዱ ሃገር ለጉልበተኛ ተላላኪ በመሆን አንዱን እያጠቃ የሚኖርበት አካሄድ መቆም አለበት።
አብዱራሕማን ማህዲ - ሱማሌ
ህዝቦች እርስበእርስ ሲወያዩ መግባባት ይፈጠራል እንላለን እኛ ሱማሌዎች። የችግር ገፈት ቀማሾች ህጻናትና እናቶች ናቸው። ጽምዶ እስከ ኡጋንዳና ኬንያ መስፋፋት ይገባዋል። ሱማሌዎች በሱማሌ በኬንያ በኢትዮጵያ በጅቡቲ እንኖራለን ጽምዶ ይበልጥ ያስፈልገናል።
ፕሮ መሓመድ ሓሰን - ሱማሌ
ቀጠናችን ሃብታም ህዝቡም የተዛመደ ነው። ጦርነት በረጅም እጅ ከውጭ ነው የሚመጣብን፡ የውስጥ ደላሎችም አሉ። ይህንን ለመቁረጥ ጽምዶ የሚባል አዲስ ፍልስፍና ፈጥረናል፡ መስፋፋት ደግሞ ይገባዋል። የአፍሪካ ቀንድ ዩኒቨርሲቲዎችና ቦለቲከኖች ይህንን ጽምዶ ለህዝባቸው ተደራሽ ማድረግ ይገባቸዋል እላለው። [ወዳጃችን ብሮፉርሸር መሃመድ፡ ኤርትራውያን ሆነው ከዓወል የተለየ አመለካከት ያላቸው ዜጎቻችንን ጽምዶ ለምን አትጋብዝም። ነው ወይስ “ጽምዶ” ከለር ብላይንድ ነው ወይም አንድ ድምጽና ቃና ብቻ ነው የሚሰማው? ሄ ሄ ኤርትራዉያን ዋዘኞች አንምሰልህ ቦለቲካዊ አዝማሪንና በማሲንቆ አያያዙ ነው ከማዶ የምናውቀው! ምን ለማለት ነው መጀመርያ በኤርትራውያን “ኤሊቶች” መካከል ውስጣዊ ጽምዶ እንዲፈጠር ጣሩ ለማለት ነው የጥምዶ - አጋፋሪዎች። ] የረዚም ግዜ ስራ ይጠይቃል፡ አወል ስዒድ መልካም ተግባር እያከናወነው ነው። እሱን የሚመስሉ ሰዎች እንዲፈጠሩ እንሻለን። ጽምዶ ማለት ሰላም ዲያሎግ ማለት ነው። ከታች ከዚያም በመለስተኛ ደረጃ ከዚይም ከፍ ብሎ በሃገሮች ደረጃ ጽምዶ መካሄድ ይገባዋል። ውጭ ያሉ የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ዲያስፖሮቻችንም ኤርትራውያን ኢትዮጵያዉያን ሱማሌዎች ሱዳኖች ጅቡቲዎች መካተት ይገባቸዋል። በሚገባቸው ቋንቋ የጽምዶን መልእኽት እናደርሳለን ባማርኛ በሶማሊኛ በዓረብኛ ወዘተ መድረስ አለበት። የቀጠናው የሰላምና የመረጋጋት ብሮግራም ነው። የራሳችን ፍልስፍና ነው ከማንም ሳንዋስ፡ [ሱማሌ እንኳ ራሷ ገና ሳትጣመድ እንዴት አድርጋ ነው ካፍሪካ ቀንድ ጋር የምትጣመደው? ኢትዮጵያም ገና ራሷ በውስጧ ሳትጣመድ እንዴት አድርጋ ነው ካፍሪካ ቀንድ ሃገሮች ጋር የምትጣመደው? ኤርትራም የተለያየ አመለካከት ካላቸው ልጆቿ ጋር በቅጡ ሳትጣመድ እንዴት አድርጋ ነው ከሱዳን ከኢትዮጵያና ከሱማሌ ጋር የምትጣመደው?] 3ኛ ደረጃ ደርሷል። ፖርትሱዳን ውስጥ ያደረግነው የምሁራንና የነቃው ክፍል ከህዝብ ጋር ሆኖ ስብሰባ ያካሄድነው ደስ ብሎኛል እንቀጥላለን። በብዙ ቋንቋም ኣባዝተን እናወጣለን ብዬ እመኛለው።
ንካዋ ኦሾላ
የቀጠናችን ችግር ከውጭ ሃብታችንን በሚፈልጉ አካላት የሚደገፍ ነው፡ ቦለቲከኞቻችን ደግሞ ለራሳቸው ጠባብ አጀንዳ ይደግፏል። ዲሞክራሲ መደገፍ ይገባዋል መሰረቱም ውስጣዊ ባህልና ወግ መሆን ይገባዋል። በጋራ መጓዝ ይገባናል።
የጽምዶ እንቅስቃሴ በቀጣይ የት ይደርሳል ብለህ ታስባለህ?
አንዳርጋቸው ጽጌ
ይሰፋል ብዬ ነው የማስበው፡ ምክንያቱም ሁሉም ቦታ ያሉ ህዝቦች ተመሳሳይ ፍላጎት ስላላቸው። የኤርትራ የትግራይ የአማራ የኦሮሞ እናቶች የሚፈልጉት፡ ልጆቻቸው አድገው በስነስርዓት ተምረው ልጅ ወልደው የልጅልጆችን አይተው ለወግ ለማእረግ እንዲደርሱ እንጂ እንዲዋጉ አይደለም። ከሰላምና መረጋጋት ሌላ የሚፈልጉት ሌላ ነገር የለም። መሰረታዊ የትምህርት የጤና መብትን ብቻ ነው የሚጠይቁት። ሌላ የተወሳሰብ ጥያቄ የላቸውም። የሰላምም የጋራ ብልጽግናም የውጭ ጣልቃ ገብነትንም መከላከያ ትልቁ ዋስትና ጽምዶ ላይ የተመሰረተ የለውጥ ፍልስፍና ነው።
አብዱራሕማን ማህዲ
እንደኔ አመለካከት ይህ እንቅስቃሴ ባፍሪካቀንድ ሃገሮች ውስጥ ተፈላጊም አስፈላጊም ነው፡ መስፋፋት ይገባዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ በሱማሌና ኦሮሞ መካከል፡ በትግራይና አማራ፡ በኣማራና በኦሮሞ፡ በአፋርና ሱማሌ መካከል ፡ በኤርትራና በኢትዮጵያ ደንበር፡ በሱዳንና በኢትዮጵያ አዋሳኝ ደንበሮች ወዘተ ጽምዶ መስፋፋት ይገባዋል።
ፕሮ መሓመድ ሓሰን
በትንሽ ጀምሮ ኢሊቶች ላይ ደርሷል፡ አባዝተን በሰፊው እንቀጥለዋለን እንገፋበታለን። ስኬታማ ስብሰባ ነው እንገፋበታለን። [የሌሎቹን ባናውቅም፡ የኤርትራ “ኤሊቶች” እነማን መሆናቸው ነው? ዘርዘር ተደርጎ ቢገለጥልን።]
ንካዋ ኦሾላ
በኢትዮጵያ ኤርትራ ወሰን የሚኖሩ ህዝቦች እነሱ ባልሰሩት ችግር ምክንያት ሲጎሳቆሉ ኖረዋል፡ አሁን መፍትሄው እዛው በቅሏል በህዝቦች። ጽምዶ በኣፍሪካቀንድ እንዲሁም በአህጉር ደረጃ ሊገፋበት ይገባል። አህጉሩ በመጥፎ አመራርና ከተጠያቂነት ውጭ በሆነ አመራር ምክንያት ችግር ውስጥ የተናጠ አህጉር ነው። [ግሩም እይታ ነው]በመሆኑም ጽምዶ ለአህጉሩም ፈውስ ሊሆን ይችላል።
በቀጣይ የጽምዶ ስራ ህዝብ ምን መጠበቅ ይገባዋል?
አወል
ምን እንዳናገረኝ አላውቅም፡ ብርሃነ ልፍዓተይን አንድቀን አንተ ህዝብህን እኔም ህዝቤን ይዘን እንገናኛለን ብየው ነበር። [የኤርትራ ወኪል ሆነህ ነበር ማለት ነውን? እላይ ራስክ ካቀረብከው ሃሳብ ጋር አይጣረስምን?] እንደዚያ ተሳክቶ በማየቴ ደስ ይለኛል። መልካም መመኘት ቅዱስ መጸሓፍት እንደሚሉት “ተመኙ እሰጣችኋለው” ነው የሚለው ፈጣሪ። ተመኝተንም ሰጥቶናል፡ በመሆኑም ፈጣሪ የጽምዶ ኣባል ነው ረቢ ኣልእዓለሚን የጽምዶ ኣባል ነው፡ ምክንያቱም ጽምዶ የሰላም ሄደት ነው። የተመኘነውን ሁሉ እየተገበረልን ነው። [አወል፡ ፈጣሪ እኮ ወንድማማቾች በሰላም ሲኖሩ እንዴት መልካም ነው ብሎም እኮ ይገልጽልናል፡ አንተ ግን በዋነኝነት ወንድሞችህን “ፍርፋሪ ለቃሚዎች” እያልክ ስም በማጠልሸት፡ ካንተ የተለየ ስሜትና ሃሳብ ያላቸውን የወንድሞችህን ድምጽ ከመስማት ተቆጥበህ፡ ከጎረቤቶቻችን ጋር ነው መሞዳመድ የያዝከው፡ አይደለም እንዴ? ታዲያ የማይሳሳተውና የማያሳስተው ፈጣሪ ይህን “የመርጦ አልቃሽነት” ድርጊትህን እንዴት ያየዋል ብለህስ ታስባለህ?] ጽምዶ የህዝብ ነው። ህዝብ አወል አትምጣ ካለኝ እኔ አልመጣም ጽምዶ ግን ይቀጥላል። በዛላምበሳ አካባቢ ሁለት ቦታ ላይ ዳግም ጽምዶን ቀጥለውበታል፡ ለኔ አልነገሩኝም። ጠላቶቻችን ላይ ነውጥ እንደፈጠረ ለማወቅ የብልጽግና ሰዎችን ቃለመጠይቅ መስማት በቂ ነው። እነዚህ ውሾች እንደሚጮሁ ስላወቅን አንበሶችን አሰማርተንባቸው እየመለሱላቸው ነው። [የምታመልከው ፈጣሪ በአርአያው የፈጠራቸውን ሰዎች ነውን ውሾች እያልካቸው ያለሀው፡ እንዲህም አድርጎ የለ “ 'የነቃ' ኤሊት”!]
ለህዝብ የሚተላለፍ መልእክት ካለ?
አንዳርጋቸው ጽጌ
በተለያዩ ወቅቶች ስለ ጽምዶ ምንነት የተሰጡ ማብራሪያዎችና መግለጫዎች ቃለመጠይቆች የተሰሩ ቪዲዮዎች አሉ፡ ህዝብ የነዚህን ቪዲዮዎች ይዘት እንዲመረምርምና እንዲረዳ፡ ተረድቶም ለዚህ ቅዱስ ሃሳብ ህዝብ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አደርጋለው።
አብዱራሕማን ማህዲ
ለአፍሪካ ቀንድ መንግስታት መልእክት አለኝ። አፍሪካ ቀንድ በተለያዩ ሃገሮች የተዋቀረ ነው። አፍሪካ ቀንድ ሃብታም ነው፡ ብዙ ውሃ ብዙ ወርቅና ሚንራሎች አሉት። ለአፍሪካ ተርፎ ለሌላ የሚሆን ሃብት አለን። አፍሪካ ከአራት ብትከፈል ያፍሪካቀንድ ወይም ምስራቅ ኣፍሪካ፡ ከሌሎች ከሰሜን ደቡብ ምዕራብ የተሻለ ሃብትም አለው። አፍሪካ ቀንድ ከገዢዎች በወረሰው ግጭት ምክንያት ሁሌም ግጭት ውስጥ የሚኖር ክፍል ነው። የውሸት ዳርድንበሮችን ጨምሮ ህዝብ ሊወያይባቸው ይገባል። [ሄ ሄ የውሸት ዳርድንበር ብሎ ነገር የለም። የሁላችን ሃገሮች የቀኝ ገዚዎች የቅርምት ውጤት ናቸው። ያን ድንበር ማክበር ደግሞ ዓለምአቀፋዊ ህግ መሆኑን መዘንጋት አይገባንም።] አንዱን ደፍጥጠህ በሌላው ላይ መኖር አይቻልም። መንግስታት ሌሎች መንግስታትን፡ ህዝቦችም ጎረቤት ህዝቦችን ማክበርና መከባበር አለብን። የህዝብ ልዕልና የትም ቢሆን የትም መከበር አለበት። አውሮፓ ብትሄድ ድንበር ብሎ ነገር የለም። ከለንደን ወደ ፊንላንድ ልትሄድ ብትፈልግ ማንም ወረቀት ብሎ አይጠይቅህም። በሰላም ደግሞ ይኖራሉ በሰላም ይናገዳሉ፡ ሃብት ይከፋፈላሉ ወዘተ። ታዲያ እኛ ኣፍሪካውያን ለምን እንደዚያ አናደርግም? ፓስፖርት ዶክመንት ወዘተ ብለን የምንጨናነቀው ለምንድን ነው? ግጭቶቻችንን ካስወገድን በባህርያዊ መንገድ ለሚሊዮኖች ዓመታት በሰላም እንኖር እንደነበርነው ሆነን መኖር እንችላለን። ከሱማሌ ወደ ኤርትራ ብትሄድ በመልክህ ማንም ሊለይህ አይችልም። ሱማሌ በል፡ ሱዳን በል፡ ኤርትራዊ በል፡ ኢትዮጵያዊ በል፡ ወዘተ እኛ አንድ ህዝብ ነን። የምንኖርበት ስፍራ መልክዓምድር ስለወሰነው ብቻ ነው የተለያዩ ቋንቋዎች የምንናገረው እንጂ በመሰረቱ አንድ ህዝብ ነን። በመሆኑም ለመላው ለአፍሪካ ቀንድ ሕዝብ ማለት የምንፈልገው እስቲ በጨዋ ደንብ እንወያይ እንነጋገር፡ ለመንግሥታቱም የምንለው ማንም አካል የህዝብን መብት መደፍጠጥ አይችልም። ህዝባችሁን በጨዋ ደንብና በህግ የማታስተዳድሩና መብቱን የማታከብሩ ከሆናችሁ፡ መንግሥታት ተብላችሁ ልትጠሩ አትችሉም፡ መንግሥታትም አደላችሁም። የህዝባችሁ ረሃብ እርዛት ሕመም የማይሰማችሁ ከሆናችሁ መንግሥታት አደላችሁም መንግሥታት ተብላችሁ ልትጠሩም አትበቁም። ጎረቤቶቻችሁን የማታከብሩ ከሆናችሁ፡ ለገዛ ህዝባችሁ ነው ችግር የምታመጡበት። ምክንያቱም እያንዳንዱ ተግባር ተመሳሳይ ተጻራሪ ተግባርም ስላለው፡ ይህ የኑሮ ህግንና የሕይወት ህግ ነው። ከሰደብከኝ እሰድህባለው። ወንድሜ ነህ ካልኩህ አንተም ወንድሜ ትለኛለህ። በመሆኑም የግጭት አፈታት አመለካከታችንን ማስተካከል ያስፈልገናል። በወንድማማችነት በጋራና በመተሰሰብ መኖር ይቻላል፡ ይህ ነው ለአፍሪካ ቀንድ ሆነ ለአፍሪካ ሃገሮች ህዝቦች መልእክቴ። እኛ ሶማሌ እንደመሆናችን መጠን ብዙ እንግልትና ስቃይ አለብን፡ በአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦች ስቃይም ስቃያችን ነው። ወንድምህ ተርቦ እያለ አንተ በጥጋብ ምድሪቱን ካስቸገርክ፡ ነገ ተነገ ወዲያ ራሱ ወንድምህ ይገድልሃል። በመሆኑም ጎረቤትህን ደፍጥጠህ እኔ በልጽጌያለው አድጊያለው ማለት አይቻልም። ጥሪያችን ለወንድማማችነት ለትብብርና ለሰላማዊ ግንኙነትና ተግባቦት ነው። [ ግሩምና በሳል ቦለቲካዊ ወገንተኝነት የማይታይበት አገላለጽ ነው!]
በመቀጠል ዓብዱራህማኑ እና ንካዋ ኦሾላ ከ 56 ደቂቅ በኋላ በአረብኛና በአኝዋክ ቋንቋዎች ስለ ጽምዶ ያላቸውን አመለካከት አስነክተውታል።
ፕሮ መሓመድ ሓሰን - ሱማሌ
በመጨረሻ የምናገረው፡ ጽምዶ የጮሌና የአጭበርባሪ የፖለቲካ አክሮባት አይደለም። [ግዜ ደጉ ምንነቱን ያሳየናል] ጽምዶ በመሬት ላይ ህዝብንና ህዝቦችን የሚያስተቃቅፍ፡ ችግራቸውንም ወደላይ የሚያመጣ፡ የነሱንም አመለካከትና ችግሮቻቸውንና የመፍትሄ ሃሳቦቻቸውንም ወደፊት የሚያመጣ ነው። [የኤርትራና የኢትዮጵያ ድንበር በፊዚካል ዲማርኼሽን ይቋጭ የሚል የህዝብ ክፍል ድምጽስ አይሰማምን። “ንዶብ እንዲዩ ተከፊሉ ጅግና!” ሲባልስ አልሰሙምን። ታዲያ ይህንን ያላማከለ “ጽምዶ” የጮሌዎችና የቦለቲካ አጭበርባሪዎች እጅ የለበትም ይላሉን? ብሮፉርሸር! viewtopic.php?f=2&t=308857&. ] ስለዚህም ነው ህዝቦቹ ትላንትና በነበረው ስብሰባ፡ እናቶች አባቶች አያቶች ጉልማሳ የተለያዩ ቋንቋ የሚናገሩ፡ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋ የሚያወሩ ኦሮሞ ሶማሌዎች ቢንሻንጉል ጋምቤላ እነዚህ ሁሉ ማይተዋወቁ ክፍሎችም በዚህ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል። የጽምዶ የፍልስፍና አመለካከትንም በደንብ የተረዱ ስለሆኑ፡ እነሱም በየአካባቢያቸው ሄደው ይህን መሰል ኮንፈረንስ ማዘጋጀታቸው አይቀርም። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሊፈታ የሚችለው በቀጠና ደረጃም ሊፈታ የሚችለው፡ ይሄ አወል ሰዒድ በየቦታው ሂዶ ጽምዶ ብሎ የሚናገረው፡ በሽታውን ሊፈውስ የሚችል አዲስ መድኃኒት ነው እላለው። [አዲሱ መድኃኒት መልካም ነበር፡ ግን “የፊዚካል ዲማርኼሽን ትግባሬ” የሚባል ቅመም ጎድሎታል፡ በመሆኑም ተፈላጊውን ፈውስ በማምጣት ረገድ ችግር አለው] እናንተም ወጣቶቹ ልትቀጥሉበት እንሻለን፡ እኔና ጓደኞቸም ስንመለስ ጽምዶን በአረብኛ በፈረንሳይ በኔዘርላንድ በስፓኒሽ እናደርሳለን። እኛ ቆማጦች አይደለንም የአእምሮ ቁምጥና የለንም ችግሮቻችንን መፍታት እንችላለን። ይሄንን ችግራችንን እንድንፈታ የሚፈልግ ክፍል ካለ ተባበሩን አግዙን። እኛ ይሄ ክራቫት ያጠለቀ በአውሮፕላን የሚሽከረከር በየሆቴል ላይ የሚዘፍነው የውሸት ጽምዶን፡ እውነተኛ ጸባዩን ነው ማሳየት የምንፈልገው። በመጨረሻ በጣም አመሰግናችኋለው። [ግሩም ትንታኔ ነው። ቁምጥና ምናምን እያሉ በበሽተኞች ስነልቦና ምሳሌ መስጠት የአእምሮና የአስተሳሰብ ህመም ምልክት ነው። አርሙት። በአውሮፕላን የሚሽከረከር ክራቫት ያጠለቀውን ይሁን ያላጠለቀውን፡ “ፊዚካል ዲማርኼሽን ትግባሬን” ገሸሽ ያደረገን የሸፈጥ ጽምዶም እውነተኛ ጸባዩን ማሳየት ደግሞ የኛ ሃላፊነት ነው፡ ምክንያቱም ድንበር ላይ የተሰውትና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የተሰውት የሰማእታቶቻን አደራም ስለሆነ። viewtopic.php?f=2&t=360645]
በመጨረሻ የምታስተላለፈው መልእክት
አወል
ለኤርትራዉያን ይሁን ለትግራይ ሰዎች እባካችሁን ዝምብለን መናቆር አይገባንም። ጽምዶ አንዲትም እንከንና ተንኮል ክፋትም የለበትም። [ጽምዶ አንድ ትልቅ እንከን አለው፡ እሱም “የፊዚካል ዲማርኼሽን ትግባሬን” ገሸሽ በማድረግ፡ አላስፈላጊ ቁርሾ ላይ ሊዳርግ የሚችል ቁስል ሳይፈውስ በመነሳቱ፡ ዘለቄታዊ የሰላም ዋስትና ሊሆን ስለማይችል። እስቲ አሁን “በፊዚካል ዲማርኬሽን ትግባሬ የኤርትራና ኢትዮጵያ የድንበር ውዝግብን መቋጨት ለጽምዶ ምን እንቅፋት ስለሆነ ነው፡ ጽምዶ ጉዳዩን አድበስብሳ ለማለፍ የምትጥረው?] ምንም ዓይነት የምናተርፍበት ነገርም የለውም። ስትራቴጂክ ነው፡ ማንኛውም ህዝብ ሰላም ያስፈልገዋል ነው እያልን ያለነው። ትላንት ምን ላይ ነበርን የሚለው ጉዳይ እዚህ ላይ ግምት ውስጥ አይገባም። ትላትን እዋጋ ነበርና ዘለዓለም እየተዋጋሁ እኖራለው የሚል ሙግትና እኔን ሊያስገድድ የሚችል ሕጋዊ አንቀጽ የለም። አወልና ናስሮቪች ተጣልታችሁ ነበርና ምርኩዝ እስክትይዙ ድረስ ተዋጉ የሚል ህግ የለም። ይቅርታ እንባባላለን እንካካሳለን በዚህም ይቋጫል። ማን ነው እየተዋጉ ለዘለዓለም ይኑሩ ብሎ የሚለን። ስለሆነም እኛ ራሳችን መጪውን ኑሯችንን ህይወታችንንና ታሪካችንን መጻፍ ኣለብን ነው እያልን ያለነው። በመሆኑም መልእክታችን አንዳንድ ሰዎች ለጥቅም ወይም ለክፋት ወይም በቅን ልቦናም ሊሆን ይችላል ጽምዶን የምትተናኮሉ፡ ግንባር ላይ ያሉ ህዝቦችን ተመልከቱ። ታሪክ ደግሞ እየመዘገበው ይሄዳል። ስለሆነም የታሪክ አተላ አንሁን፡ መልካም ስላልሆነ የሚል መልእክት አለን። [ጽምዶን ለፊዚካል ዲማርኼሽን ትግባሬ ባለማትጋቷ ከታሪክ ተጠያቂነት ልታመልጥ አትችልም፡ አካሄዷን ካላስተካከለች viewtopic.php?f=2&t=308857&. ]
ሌላው መልእክቴ አንዳንድ የማህበራዊ ብዙሃን ተገልጋዮች፡ ከዚህ ቪዲዮዎችን የሚልኩ ኤርትራዉያን ይሁኑ ሌሎች ሰዎች፡ አገርህን በሚመለከት መጥፎ ገጽታ ስላስተጋባህ፡ ጀግንነት የሚመስላቸው አሉ። ይህ ጀግና አያደርግህም። ጀግና የሚያስብልህ እናትህ ገጽታዋ ፉንጋ ልትሆን ትችላለች፡ ሸውራራም ልትሆን ትችላለች፡ ቀውስም ልትሆን ትችላለች፡ ዱዳ ወይ እውር ወይም ስንኩል ልትሆን ትችላለች፡ የናትህን እንከን ሚዲያ ላይ መዘክዘክ ጀግና አስያብልህም። ስለ ሃገርህም እንዲሁ። ከእናት በኋላ ሃገር ነው የምትመለከትህ፡ ከናትህ ማህጸን ከወጣህ በኋላ ወደ ሃገርህ ነው የምትገባው። ከቤት ወደ ቤት ማለት ነው። ሃገሩን ሲያራክስ የሚውል ሰው ሰነፍ ነው ተሳክቶለትም አያውቅም። ስርዓት ሌላ ነገር ነው፡ ፖሊሲም ሌላ ነገር ነው የአመለካከት ሆነ የአስተሳሰብ ልዩነት ሊኖር ይችላል። [ግሩም አገላለጽ ነው፡ ቦተሊካ ውስጥ ግን “ተጽእኖ ፈጣሪ አካላት ወይም ፕረዠር ግሩፕ” የሚባሉ አሉኮ፡ መስተካከል የሚገባው ነገር እንዲስተካከል እንከንን የሚያወጡ። የፖሊሲ ስህተት እንዲታረም መሆኑ ነው። እንዲያ ካልሆነ ግን ተጠያቂነትም ከሌለ ሃገር ሃገር አትሆንም የግለሰቦች የግል ኩባንያ እንጂ! ይህ እንዳይሆን መታረም የሚገባው ነገር ይፋ ቢሆን ቅር ሊለን አይገባም። ስድብ ግን የአስተሳሰብ ደካማነት መግለጫ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። አንተው ራስህ ነህ የሃገርህን ልጆች “ፍርፋሪ ለቃሚዎች” በማለት ስትሳደብ የምትውለው አይደለም እንዴ? የጽምዶ ኤሊቶች ጭምር ሊመሰክሩት ይችላሉ ይህን ሃቅ።] ቀኑን ሙሉ ሃገርህን እየሰደቡ የሚኖሩ አሉ። እዚህ ውስጥም ኣሉ ሳያውቁ እንዲህ የሚያደርጉ ‘አርቲስቶች’። ምን ያረጋሉ መሰለህ የሆነ ዝግጅት አደረግን ብለው፡ አንዳንድ ቦታ ሂደው ተንቀሳቃሽ ምስል ይቀርጻሉ፡ ታዲያ ምን ዓይነት ጥበብን የማጣጣም ህዋስ እንዳላቸው አይገባኝም፡ እጅግ በጣም መጥፎ የሆነ የፈራረሰና ክፉ ገጽታን የሚያስተጋባ ስፍራ ሄደው ዝግጅታቸውን ይሰራሉ። ይህ ስንፍናችንን የሚያሳይ ነገር ብዙም ባንጠቀምበት መልካም ነው። አንድ ሓቅ ግን ኣለ። አልተመቸንም፡ ርቦንም እያለ ጥርሳችንን ነክሰን እንሄድ ነበር። ተርበናል ወይ ከተባለ አዎ ተርበናል። ስለተራብን ግን ሃገራችንን አልሸጥንም። ኤርትራ አትሸጥም አትለወጥም። [እርግጥ ነው ሰማእታቶቻችን ሃገር የፈጠሩት ሃገር ለመሸጥ አይደለም።] ትክክለኛው የልዑላዊነት ትርጉም ኤርትራ ነች። ሻዕብያ በህይወት እያለ የኤርትራን ሁሉ ጠላቶቿ ማስወገድ አለበት። ይህ ማሕላው ነው። ሃላፊነትም ነው። የኤርትራን ሊብሬቶም (ካርታ) ሊያስረክበን ይገባል፡ ሁሉንም ጠላቶቿን ማስወገድም ይገባዋል፡ በቀረችው ነጠብጣም ደሙ ማለት ነው። ይህ ነው ማህላው። ይህን ለማድረግም ሰንደል ጫማውን ሳይቀይር እያየነው ነው። [ጎበዝ የኤርትራ ካርታ ስእል ላይ ብቻ ሳይሆን ምድሩም ላይ 146 የጋራ ፈርጦቻችንን በማመላከት ችካሎችን አድርጎ ቁልጭ አድርጎ ያስረክብ ነው እያልን ያለነው እኛም] ኤርትራ ውስጥ ጣልቃ ገብነት የለም፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ኤርትራ ውስጥ ቦታ የላቸውም፡ የምንመገበው ምግብ የራሳችን የምንጠጣው ውሃም የራሳችን ነው። የራሳችን ሰላም የራሳችን ኦክስጅን ነው ተቆጣጥረነው ያለው። [ተው ተው ቢያንስ ቢያንስ ኦክስጅኑን ለፈጣሪ ስጠው እንጂ!] የሚበከል ሆነ የሚበክል ቆሻሻ የለንም። [የሚበክል ቆሻሻ ኣለን የሚሉ አካላት አሉ፡ በየበዓሉ የሚታረዱ የከብትና የእንስሳ ቆዳ በየቦታው እየተጣለ ብከላ ያስከትላል፡ መታረም አለበት፡ አይደለም እንዴ? ለምን ይዋሻል!] ሃገራችን ሆዳችንና አላማችን ንጹህ ሆኖ ነው 35ኛ ዓመት የነጻነት በዓላችን ላይ የደረስነው። ሻዕብያ እንደወላጅ ያለችውን እየቆጠበ ነው አሁን ያለንበት ሰላማዊ መድረክ ላይ ያደረሰን። በመሆኑም ኤርትራን ልጆቿ ያንጿታል፡[ በትጥቅ ትግሉ ወቅትም ኤርትራን ልጆቿ ያንጿታል እየተባለ ይዘመር ነበር፡ ግሩም ትንቢት ነው። አሁን ግን ለምንድን ነው የህንጻ ስራ በይፋና በቅጡ የማይጀመረው። ኤርትራውያን የስራ ተቋራጮች ምን ሆነው ነው በአፍሪካ ሃገሮች ብዙ ስራ ሲሰሩ፡ ሃገራቸው ውስጥ የህንጻ ስራ ሲሰሩ የማይታዩት።] በቀለምና በብልጭልጭ ነገር አትመኑ አይዟችሁ። ተቃርበናል፡ ድንቅድቅ ጨለማ ካለ ንጋትም ኣለ ማለት ነው። አመሰግናለው። አሁን ደክሜያለው። ጎደና ሓርነት ላይ ያለውን ውበት ቀርጻችሁ አሳዩዋቸው - አስላ ላቪስታ። [አሁን ግዜው ኤርትራ ሃገር ፈጣሪ ሰማእታቶቿን የምታከብርበት ወቅት በመሆኑ ይህን ጋብዘናል እኛም መልካም መልካሙን የምንመኘው ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።]
ወርሃ ሰኔ በመሆኑም ሃገር ፈጣሪ ሰማእታቶቻችንንም እንዘክራለን።
Meleket wrote: ↑08 Dec 2022, 08:34
ኣብ በሊሕ መላጸ
ተሰሪዖም ከም ጻጸ፡
ኣብ በሊሕ መላጸ፡
ብመስዋእቶም ...
ዘስገሩ ብጾቶም፡
ዘይርሳዕ ውዕለቶም፡
ንሳቶም ...
ኣብ በሊሕ መላጸ ሚልዮናት ዘስገሩ፡
በጃ እናሓለፉ ፍቕሮም ዘመስከሩ፡
ሃገር ዝፈጠሩ፡
“አናብስ ስዉኣት” ወትሩ ይዘከሩ።
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5227
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 26 Jun 2026, 11:23
ጽምዶ 41- እዛ ፕሮስ መዘከርታ ንዝሓለፉ ሰማእታት ኤርትራ ትኹነለይ። 20 ሰነ ማለት ዝኽርኻን ሕድርኻን ምሕዳስ ማለት ስለዝዀነ ቢሉ ጀሚሩ’ሎ አወል። [ኣብ ዝሓለፈ ኣብ ቅድሚ ሓወልቲ ኣዅሱም ሽጉጥ ኣብ ኢድኻ ሒዝኻ ርኢናካ ነቢርና፡ ኣብቲ ስርሒት ንዝሓለፉ ሰማእታት ዘኺርካዮም’ዶ? ንወለዶምን ኣሕዋቶምን ኣጸናኒዕኻ’ዶ? ሕቶ ንሕልናኻ ገዲፍና፡ ኣብ ትሕዝቶ ጽምዶ 41 ዛሎና ናጻ ርእይቶና ክነካፍል ኢና ንሕና ኤርትራዉያን ደያኑ ማእከልን መስመርን በቲ ልሙድ ኤርትራዊ ጭዉነት ሓበንን ፍናንን።]
ኣወል ብዛዕባ ኣሰያይማ ተጋደልትና ዘሎኻ ጊጉይን ዝንቡዕን ርእይቶ ንምፍዋስ ክንፍትን፡ ንሕና ኤርትራዉያን ብሓፈሻ ከምዡይ ንብል፡ “ምእንቲ ሕዝቢ ኤርትራ ንዝተቃለሰ ተጋዳላይ ንብሎ፤ ቅድሚ ናጽነት ኤርትራ አብ ቃልሲ ንዝተሰለፈ ‘ይከኣሎ’ ንብሎ፤ ድሕሪ ናጽነት ካብ ይከኣሎ ይወርስ ንዘሎ “ዋርሳይ” ንብሎ። ይከኣሎ ወለዲ ምስ ይከኣሎ ደቆም ብሓባር ዝተቃለሱሉ እዋን ኔሩ፤ ዋርሳይ ወለዲ ምስ ዋርሳይ ደቆም ብሓባር እንተወፈሩ’ዉን ኣይገርመናን፤ ታሪኽ ኢዩ ዚውረስን ዚድገምን ዛሎ።” ምእንቲ ምኽባር ልዑላዉነት “ብሕጂ ንዝመጹን ዝወፍሩን ወለዶ መን ስም የውጽኣሎም፡ መን’ከ ይበሎም፧” ንዚብል ሕቶካ፤ “ዘርከበ የውጽኣሎም፡ ሕዝቢ ዝረዓሞ ስም ድማ “ስሞም ወይ ሳጓኦም ይኸውን። እንተደልዮም ባዕሎም የውጽኡ፡ እንተደሊዮም ካብ ወለዶም ማለት ካብ ‘ይከኣሎ’ ወይ ‘ዋርሳይ’ ወይ ‘መንደላይ’ ስም የውጽኡሎም። ንስኻ እንተወሊድካ፡ ባዕልካ ወይ ሰበይትካ ወይ ኣቦታትካ ወይ ኣቦሓጎታትካ ወይ ደቅኻ፡ ወይ መቕርብኻ፡ ወይ ጎረባብትካ፡ ነቲ ናትካ ውላድ ስም ወይ ሳጓ ከውጽኡ ተኽእሎ ኣሎ። ነዚ ከም ውሁብ ውሰዶ። ኣብዚ ጉዳይ ኣስማት ተጋደልትና ድማ ሕዝቢ ዝረዓሞ ዓብሊሉ ይወጽእን ይዝውተርን። ናይ ግድን ሚኒስትሪ ምክልካል ስም ከውጽእ ኣይዀነን። እቲ ሚኒስትሪውን ናይ ህዝቢ ክንዲ ዝዀነ ህዝቢ ንዝረዓሞ አስማት ዕሽሽ ኣይብልን ኢዩ። ሕዝቢ ንዝረዓሞ ስም ክትሓኽኽ ምፍታን ወይም ምእማም “ሱሳ” ኣላታ፡ ጊጉይ ኢዩ።
ንስዉእ ተጋዳላይ ኢሳያስ ጸጋይ ጠቂሽካ፡ ብዛዕባ “ዋርሳይ” እትብል ቃል ክትገልጽ፡ “ኢሳያስ ጸጋይ ዚበሃል ንፉዕ ኤርትራዊ አርቲስት ዘምጻኣ ስያሜ” ቢልካ፡ ስዉእ ጅግና ኢሳያስ ጸጋይ ስሙይ ስነጥበባዊ ጥራሕ ኣይኰነን፤ እንታይ ደኣ፡ ኣንጊሑ ምእንቲ ናጽነት ኤርትራ ዝወፈረ፡ ንሰብ ብረት ብቋንቁኦም ብብረት ዝመለሰ፡ ኣብ ጐድኒ ስዉኣት ተረጋሪጉ ዝሰንከለ፡ ብብርዑ ‘ለሚን ለሚነይ እናበለን እናገጠመን’ ንብዙሓት ናብ ሰውራ ዘሰለፈ፡ መዳርግቲ ኣልቦ ዕንወት ኣብ ልዕሊ መግዛዕቲ ዘስዓበ፡ ናጽነት ዘግሓደ ጅግና ወዲ ኤርትራ ኢዩ። ታሪኽ መዚኑ ድማ ኣብ ወቅቱን ሰዓቱን፡ ጉልባብ ጊጉይ ከይዲ መራሕቲ ሕወሓት ንመንእሰይ ወለዶ ኤርትራ ዝመሃረ’ኡ። ስዉእ ኢሳይያስ ጸጋይ ንበለጸይናታት ሰብ ሽረን ዓድዋን ንሰብ ዓዲግራትን መቐለን ንሰብ ተምቤንን ሓውዜንን ንሰብ ትግራይን ወዘተን ብሓፈሻ፡ መስፋሕፋሒ ቍንቝኝኦም ብምክሻሕ፡ ከምዙይ ገቢሩ በቲ ልሙድ ኤርትራዊ ጭዉነት ሓበንን ፍናንን፡ ነቱይ ሓቂ ዝዳሕድሖ፡ ገለ ካብ ግጥምታቱ እስከ ክንዝክር ክንፍትን፦
ዋርሳይ እዞም ሰባት ግን መን ኢዮም፧
ኣብ ድቃስ ሓሊሞም፡
ኣብ ጸድፊ ዘሊሎም፡
ዓባይ ትግራይ ደልዮም፡
ዋርሳይ ኣባሽመል ኣሎኹ እንዶ ኢልካዮም!
መንዮም ከምዛ ጋሻ ዚዅሕዅሑ፧
መንዮም ክሳብ ዓንቐር ዚምኽሑ፧
ዛንታ ኪኾነካ ዋልታ ኤረ፡
ቃታ ኣየጽረዩን ክሳብ ሽረ፡
ሓቂ ክደግመልካ ውላድ ሳዋ፡
ተምሃሮ ኢዮም ኔሮም ክሳብ ሸዋ።
ብንመልኾ ቋንቋ ተዛሪቦም፡
30 ዓመታት ኣዘንጊዖም፡
ደጀኖም እንዲና መፈጠሮም፡
ዕጥቆም ኔርና ብረቶም ዝናሮም፡
ኣየ ጋዶ ሓያላት ኢና ኢሎም፡
ከምዛ ዘይንፈልጦም ውሻጠኦም።
ሕልምን ጋሕድን ክልተ ኣርእስትታ’ዩሞ፡
ሕልሚ ክነሳሲ - ኣይጥዕመናን’ዩ!
ነዛ ርስቲ እንዲና ተፈጢርና፡
ንዶብ እንዲዩ ተከፊሉ ጅግና።. . .
ብመሬት ዓደቦ የሎን ዋዛ፡
ዋርሳይ ራዛ ናይ ኣያካ ሓዛ።
ንመሬቱ መሪር ዋጋ ዝከፈለ፡
ብፍቕሪ መሬቱ ዝነድድ ክቡር ህዝቢ፡
ሞሳ እምበር ብድዐ ኣይጻማኡን’ዩ!

ኣብ ዘመነ “ጽምዶ” ስለዛሎና፡ እዚኣ ብርቂ ግጥሚ ዝኸዘነቶ፡ ነቲ እዋኑን ኩነቱን እትገልጽ ታሪካዊ ትሕዝቶ ዲዩ ምሕኻኽ ተደልዩ! ሄሄ ንስታሊንን ሃይለ ደደቢትን ጎደፋይን ወዲ ቢተውን ወዘተ ክተሓጉስ፡ ‘ንመራሕትኹም ዛሕዚሕናልኩም’፣ ‘እዛ ወዓግ ማለሊት’ ወዘተ እናበልካ ንዝተዛረብካዮ ዘረባ ኪተልዝብ፡ ንዓና ንኤርትራዉያን ታሪኹም ረስዑ ዲኻ ትብል ዛሎኻ፧ ወዳጀ “ተጋዳላይ አወል” ኣይዘረባን’ኡ። ክነሕጽሮ ናብ ካልእና መታን ክንሳገር፡ ኣብ ኣሰያይማ ዛሎኻ ርድኢት ክነመዓራርየልካ። ንናጽነት ዝወፈረ ተጋዳላይናን ህዝባዊ ሰራዊትናን “ይከኣሎ” ንብሎ፤ ንምዕቃብ ልዑላዊነት ንዝወፈረ 2ይ ወለዶ ተጋዳላይና “ዋርሳይ” ንብሎ፡ ምስ ብልጽግና ወፊሩ ንጃንዳ ማሌሊት ንዝቐጽኤ 3ይ ወለዶ ንኡስ ተጋዳላይና “መንደላይ” ንብሎ። ናይ ሕጂ ተጻማዶ ወየንቲ’ኳ “ጀኖሳይደር፡ አራዊት ሰራዊት ኤርትራ” ኢዮም ዚብልዎ ዝነበሩ። ን4ይ ዲዩ 5ይ ወለዶ ተጋዳላይና ድማ ሽም ከምዘይንስእነሉ ንፈልጥ። ኩሉ ሽምና ድማ ሓወልትና ኢዩ። ዋርሳይ ኮነ መንደላይ ተጋደልቲ ኣይኮኑን ዝበለ ኤርትራዊ የሎን። ገድሊን ተጋዳላይ ዚብል ሽምን አብ እዋን ብረታዊ ቃልሲ ጥራይ ዝተፈጥረ ኣይኮነን፡ ቀደም ብጥንቲ ዝነበረን ሕጂ ዛሎን፡ ብሕጂዉን ንዝንተእለት ዚነብር ኢዩ’ሞ “ተጋዳላይ” ዚብል ሽም ከይጠፍእ ክንዲ ቕንጣብ ስክፍታ የብልናን። ታሪኽ ኣይምሕርን ኢዩ፡ ከምታ ዘላታ ኢና ድማ ንንኡስ ወለዶ ነውርሶ፤ እቲ ምንታይ ታሪኽ ገድሊ ንጹሕ ሕዝቢ ንምሕኻኽ ምፍታንን ንምሕኻኽ ምእማምን ወንጀል ስለዝዀነ፡ ሕድሪ ስዉእ ምጥላም’ዉን ስለዝዀነ።
ክነጠቃልሎ፡ ንስኻ “ወሪሰ ሕልፍን ትርፍን እጋደል አሎኹ” ቢልካ ትሓስብ ኣሎኻ፡ ገሊኡ ድማ ብሕጂ እናወረሰን ሕልፍን ትርፍን ንምግዳል እናጸዓረ ከምዝርከብ ክትኣምን ይግባእ። ተጋዳላይ ንዚብል ሽም ግቡእ ትንታኔ ክትህብ ምፍታንካ ግሩም ኢዩ። “ተጋዳላይ ንእትብል ቃል ከምዘላታ ንውሉድ ወለዶ ነሰጋግራ” ቢልካ እዚ ማለት ንውረሳን ነወራርሳን ማለት ኢዩ። ከምቲ ዝበልካዮ፡ “ፕረዚደንት ካብቶም ኣቀዲሞም ዝነበሩ ወሪሱ ድሕሪኡ ተጋዲሉ” ኢልካ፡ እዚ መግለጺ ጌጋ ርድኢትካ ኢዩ፡ እቲ ሓቂ ከምኡ ኣይዀነን፤ እንታይ ደኣ “ከም ሰቡ እናወረሰ ተጋዲሉ፡ እናተጋደለ ድማ ወሪሱን የውርስን ኣሎ።” ኢዩ እቲ ቅኑዕ ንባብ፡ መክንያቱ ሕድሪ ጥራሕ ኣይኮነን ዚውረስ፡ እናተጋደልካ ካብ ብጮትካን ህዝብካን ብግብሪ እትወርሶ ክብርታት ገድሊ ብዙሕ ስለዝዀነ።
አወል ክሳብ ሕጂ ነቶም ንማንታ ህንጻታት ኣማሪካ ብምዕናዉ፡ 3ሽሕ ሰላማዉያን ሰባት ኣብ ቅጽበት ዓይኒ ንዝቐዘፉ ግብረሽበራዉያን “ተቃለስቲ’ ብማለት ተጋደልቲ ዚብል ማዕረግ ንዝሓብካዮ ጊጉይ ብህሎኻ፡ ብዕሊ ተጋግዬ ኣይበልካን። ተጋዳላይ ጌጋኡ ንኪእርም ነግፈረግ አይብልን። ቕኑዕ ተጋዳላይ ተጋግዬ፡ ጌጋ መዓልቲ ውዒለ ቢሉ “ይቕሬታ” ኢዩ ዚሓትት። ንስኻ ንግብረሽበራዉያን ተቃለስቲ ቢልካ ህዝቢ ኣጋጊጋ ኣሎኻ፡ ይቕሬታ ሕተት፡ ቅንዕና ዝወረሰ ተጋዳላይ መታን ክንብለካ ንሕና ኤርትራዉያን ደያኑ ማእከልን መስመርን። ብዛዕባ ሃገራዊ ኣገልግሎት ዛሎኻ ርድኢትዉን ዳግም መርምሮ። ህዝብን ሃገርን ምግልጋል ክቡር ዕዮ ኢዩ። ከምዚ ኣይኮንኩን ከምዚ ኢየ ምባል ትርጉም የብሉን። ጥራሕ ግቡእ ግልጋሎት ሃብ። ሓንቲ ዛንታ ንአንፊና ፈይ ከነብለልካ፡ ቀደም ብግዜ መግዛእቲ፡ ሓደ ካቶሊካዊ ካህን ናብ ከረን ይገሹ ነቢሮም፡ ኣብ ኬላ አብ ተፍትሽ፡ ጥራዉዝቶም ወተሃደራት ደርጊ እንተፈተሽዎ “ገድሊ፡ ምግዳል፡” ወዘተ ዚብል ቃላት ምስ ረኸቡሎም፡ ወንበዴ ቢሎም ከከላብትዎም ፈቲኖም ክሳብ ቕኑዕ ትርጉም እቲ ቃል ብዕሊ ዝርድኡ። መንፈሳዊ ገድሊ ኮነ ማኅበረሰባዊ ገድሊ ንህዝቢ ምብርካት፡ ኩልትንናካ ንአገልግሎት ህዝቢ ምዉፋይ ዜስምዕ ኣካል ክቡር ገድሊ ህዝብታት ኢዩ።
ወርሓቱ ወርሓ ሰነ ኢዩ፡ “ኤርትራ ሃገረ ተጋደልቲ” ጥራይ ካብ ምባል “ኤርትራ ሃገረ ወረስቲ፡ ሃገረ ተጋደልቲ፡ ሃገረ ሰማእታት ኢያ። 20 ሰነ ድማ ንኣኦም ዝተወፈዬት መዓልቲ ዝኽሪ ሰማእታት ኤርትራ ኢያ።” ምባል ይምረጽ።
ኣብ መበል 11 ደቂቅ ናብ ጉዳይ ጽምዶ ንስገር ብቋንቋ ጐረባብትና። “ቡና ይፈላ፡ ልጆችን ሰብስብ ጐረቤቶችንም ጥራ ስለ ጽምዶ እናውራ” በሚለው አባባሉ የሚታወቀው አወል ሰይድ፡ በ 11ኛ ደቂቃ አንድ ስነምግባራዊ ያልሆነ የካርቱን ስእል አቅርቧል። ህዝብ ፊት እንዲህ ባለጌ የሆነ ካርቱን ማቅረብ ነዉር ነው። አንገት ላይ የተንጠለጠለ የሚጎትት ክራባት ባለበት ስፍራ እንደዚያ ኣይነት ካርቱን ለህዝብ መዘርጋት ግብረገብነት አይደለም፡ ኤርትራዊ ጭዋነትንም አያመለክትም፡ የአስተዳደግ ክፍተትንም ያመለክታል።
ከዚያ በተረፈ “የአብይ ጉድፍ አጣቢዎች” ሬድዋንና ጌታቸው አልጀዚራ ላይ በዘረጉት ጽሑፍ ዙርያ “ጽምዷዊ” መልስ ሰጥቷል። ከዚያ በፊት ግን ጋዜጠኛው መሳይ መኮንን ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፡ “ሰሜንኞች በጽምዶ ጥላ ስር እየመጡብህ ነው” በማለት ከሌላው ህዝብ ጋር ለማጋጨት ብልጽግና ጅጅጋ ላይ ባደረገው የባለስልጣናቶቹ ስብሰባ የሚሄድበትን ስንኩል መንገድ አስመልክቶ በጠየቃቸው መሰረት፡ “ጽምዶ ሰላምን ከወታደራዊና ፖለቲካውያን ልሒቓን ኣውጥቶ ህዝብ እጅ ውስጥ ማስገባት የሚል ሰላማዊ ፍልስፍና ነው። ሰላም የሚጸናው በባለስልጣናት ሳይሆን በተራው ህዝብ መተሳሰር ነው የሚል እምነት ስላለኝ ፖርት ሱዳን በመሄድ ተቀላቅያለው። ብልጽግና ቀሺም ስለሆነ፡ ግፍ ያልፈጸመባት የኢትዮጵያ ስፍራ አትገኝም። እነኝህ ግፍ የተፈጸመባቸው ህዝቦች ደግሞ አንድ ቀን ይጣመዳሉ የሚል ስሌት አልነበረውም። ጌታቸው ራሱ “የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ዱባይ ድረስ ልኮ ከኤርትራ ጋር ተጣመድ ከፋኖም ጋር የምንጣመድበትን መንገድ ፈልግ ብሎኝ ነበር ያለ ሰው ነው።” አሁን እኛ ከኤርትራ ጋር ብንጣመድ ማለቃቀስ በፍጹም አያምርበትም። ሕወሓትን በጥቂት ቀናት ውስጥ ከኤርትራ ጋር ተጣምዶ ለጦርነት እየመጣብን ነው ብሎ እያለቃቀሰ ይከሳል፡ ራሱ ብልጽግና ግን አስቀድሞ ህወሓት ላይ በሸራሮ የድሮን ጥቃት አድርሷል። ፈርተውና ተንቦቅቡቀው ስላሉ፡ የሚያደርጉትን አያውቁም፡ ገና ብዙ ይለፈልፋሉ። እንቆረጥማችኋላን እናቀልጣችኋላን የሚለው አባባል ፍራቻቸውን ብቻ ነው የሚገልጠው።” ሲሉ መልሰዋል።
አወል 29ኛ ደቂቃ ላይ “ጦርነት የለም፡ ጉራና ፕሮፓጋንዳ ግን መልኩን ቀያይሮ ይኖራል” ብየ ነበር የሚል አባባሉን ካለፉ ፕሮሶቹ ጠቅሷል። እኛም “አዎን ኤርትራ ውስጥ “ጦርነት” ኣይኖርም፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ፋኖ እየተዋጋ ነው፡ ህወሓትም በግዳጅም ጭምር ሰራዊት እየመለመለ ነው ሲባል ሰምተናል ግን ይህ ምን ያመላክታል አንለውም።
መሳይ መኮንን ከጽምዶው ምርኮኛና ዳንሰኛ ፕሮፌሰር መሓመድ ሓሰን ጋር ባደረገው ቃለምልልስም፡ “ፖርትሱዳን ለምን ሄድክ” ባለው መሰረት፡ እኔ ራሴን ወክየ ተጋብዤ ነው የሄድኩት፡ ጋባዤም ኤርትራዊ ብሎገር አወል ሰይድ ነው። በጽምዶ ህዝብ ለህዝብ አገናኝቶ፡ ብዙ መልካም ነገሮች ሲደረጉ አይቻለው። ከአንድ በሬ ይልቅ በሁለት በሬ ጥሩ ማረስ ይቻላል የሚል ፍልስፍና ነው። ብዙ ሃገሮች ከዚህ በፊት በተለያየ መልክና ስም ተግብረውታል። ተጋብዘን ነው የሄድነው። “3ኛ ደረጃ ላይ አድርሼዋለው፡ ከዚህ በኋላ ያለው የናንተ ስራ ነው” ብሎ አስረክቦናል። “ህዝቡ ኣይደለም ተነስቶ የተገዳደለው፡ ፖለቲካዊ ኢሊቱ ነው ተከፋፍሎ ይህን ሁሉ ውድመት ያደረሰው፡ ስለዚህ ህዝብ ከህዝብ ጋር መታረቅ አለበት። ሰፊ ሰላም የሚያሰፍን ትልቅ ፍልስፍና ነው። ” ብሏል የጽምዶው ምርኮኛ ብሮፉርሸር። [እኛም ይህ ምን ማለት ነው? የህዝብ ለህዝብማ ምንም ችግር የለበትም እኮ ብለህናል፡ መታረቅ ያለበት ቦለቲካዊ ኤሊቱ ነው ማለት ብቻ ነበር ከፕሮፉርሸር የሚጠበቀው ብለናል] ብሮፌሰሩ ቀጥለው “ጽምዶ ማለት በሰላም መኖር ማለት ነው። እኛ ለልጆቻችን ጦርነት አናወርስም፡ በጦርነትም የሚፈጁበት ምንም ምክንያት የለም ማለት ነው። አፍሪካ ቀንድ ከጦርነት ባሻገር ወደ አዲስ የሰላም መድረኽ መግባት አለባት፡ በኛው መላ ማለት ነው። ሊከፋፍሉንና ጣልቃ ሊገቡብን የሚያስቡ አካላት ቢታቀቡ መልካም ነው።” ሲሉ ተደምጠዋል።
ቀጥለውም “ለምሳሌ የቬትናሞችን ጽምዶ እንመልከት፡ ቬትናም በ1880 በፈረንሳዮች ቅኝ ስር ሲገቡ፡ በሃይል ብዙ ቬትናማውያንን ወደ ካቶሊክ ሃይማኖት ቀየረች።” ብለዋል [ ድረገጾችን ስንፈትሽ ግን ፈረንሳይ በቬትናም በሃይል የካቶሊክን እምነት እንዳላስፋፋች በሰፊው ይገልጻል።] አናሳውን ብሄርም የግዛቷ አገልጋይ አድርጋ አቋቋመችው፡ እርስ በእርስ ጦርነት ለመፍጠርም ተጠቀመችበት። ህዝቡ በሳል አመራር እንደ ሆቺሚኒ ሲያገኝ ግን ጽምዶ ፈጥሮ ብዙ ታሪክ ሰራ። “ህዝቤን አወሃህጄ ለውጭ ጠላት ፋታ ሳልሰጥ ካልታገልኩ ምን ፋይዳ አለው” በማለት ሆቺሚኒ ብርቱ ትግል አድርገው ተሳክቶላቸዋል።
የሚገርምህ 1954 አሜሪካ በዴን ቤንፉ ፈረንሳዮችን እንዳሸነፉ ተመሳሳይ ፖሊሲ ነው የተጠቀሙት። አንዲት ታክቲክ ግን ጨመሩ። ሰሜን ቬትናም ውስጥ 4 ሚልየን ካቶሊካዉያን ነበሩ፡ እነዚህን በመኪና በኣንቶኖቭና በአውሮፕላን ጭነው ወደ ደቡብ ቬትናም ወስደው ካቶሊካዊ መንግስት መሰረቱ። [ድረ ገጾች ግን እንደሚነግሩን Operation Passage to Freedom በተባለው የአሜሪካኖች እርዳታ፡ ለ300 ቀናት በተከፈተው ድንበር፡ 600 – 800 ሽህ ቬትናማውያን ካቶሊኮች፡ ኮሚኒስቱን ስርኣት ጥለው ወደ ደቡብ ቬትናም ሲያቀኑ ሌሎች 600 ሽሕ ደግሞ እዛው ኮሚኒስቱ ደቡብ ቬትናም ውስጥ እንደቆዩ ነው። 4 ሚልየኑ ብሮፌሰር ያጋነኑት ቁጥር ሳይሆን አይቀርም] ስለዚህ በሰሜንና ደቡብ ቬትናም መካከል በካቶሊካዉያንና ካቶሊካዉያን ባልሆኑ ቬትናሞች መካከል የ1ሽ ዓመታት ጥል ዘሩ ማለት ነው። መጨረሻ ይህንን እንዳሸነፉ ጀነራል ዚያብ ህዝቡን ሲያነጋግሩ “አሸናፊና ተሸናፊ የለም ሁላችን ቬትናሞች ነን፡ ከፋፍሎን የነበረውን ሃይል አሸንፈናል ስለዚህ ሀ ብለን በአዲስ ጽምዶ አዲስ ካሪክለም በመቅረጽ እንጓዝ በማለት ተጓዙ፡ አሁን ቬትናም ትልቅ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ደርሳለች [ድረገጾች ደግሞ የቬትናም የእድገቷ ምክንያት ይህ ነው ይሉናል Vietnam's rapid economic rise is primarily driven by export-led industrialization, massive Foreign Direct Investment (FDI), and heavy integration into global trade networks. A strategic geographic location and a young, highly-educated workforce further position it as a major global manufacturing hub.] ይህን መሰሉን አደጋ ከሩቅ የማያይ አመራር ካለ ሁሌም አደጋ ላይ ነን።[ግሩም አገላለጽ ነው እኛም ለዚህም ነው የአገር ውስጥ እርቅና ጽምዶ ይቅደም የምንለው]
ሩዋንዳ አንድ ቋንቋ የሚናገሩ ቱትሲና ሁቱ በውጭ ሃይሎች ምክንያት ተከፋፍለው እርስበእርስ ተጨፋጨፉ አንድ ሚልየን ሰው በ3 ወራት ውስጥ ሞቱ። እናንተ ናችሁ ያጋደላችሁን በገዛ ራሳችን ችግራችንን እንፈታለን ብለው ሩዋንዳን አረጋግተዋታል።[እኛም፦ እንዲህ ሲሆንም እማደል “ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” የሚባለው፡ አፍሪካውያን በችግር ከመማር ይልቅ ከችግሩ በፊት እንዲያ ባለማሰባችን ምዕራብ ሆነ ምስራቅን መኮነን ስህተት ነው የምንለው።] እኛ የቤት ስራችንን መስራት ይገባናል፡ የቀጠናችንን ሆነ የየሃገሮቻችንን ችግር መፍታት ያለብን ራሳችን ነን። “ጽምዶ ማለት በመጀመሪያ ደረጃ ታጋዩ ከጎረቤቶቹ ከዛም ከራሱ ህዝብ ጋር መታረቅ ኣለበት።” ሲሉም ተደምጠዋል [አዘባርቀውታል፡ መቅደም የሚገባውን አላስቀደሙም ብሮፌሰሩ] አልጀሪያም የገዛ ራሷ ጽምዶ ነበራት። ከፈረንሳይ ጎን ሆነው የተዋጉ አልጀራውያን ነበሩ፡ በኋላ ሸሽተው ወደ ፈረንሳይ የሄዱ፡ አልጀርያ ውስጥ የቀሩም ነበሩ። እንዲህ አይነቱን አስተምረህ አንቅተህ ልትጠቀምበት ካልቻልክ ዘመንህን ሙሉ በውጊያና በመገዳደል ነው የምታሳልፈው። እኛ ጦርነት እንዲስፋፋ አንሻም፡ ስለዚህ ጽምዶ መድሃኒት ነው። ሲሉ ተደምጠዋል ብሮፌሰሩ [እኛም፦ እንዴ መድሃኒቱ ግሩም ነው። በተሳካ ሁኔታ 100% ውጤታማ እንዲሆን ብዙ ቀመም ይጎድለዋል፡ 1) ጽምዶ ከየሃገራቱ ሊቃውንት ጋር መመካከር ይገባዋል 2) ሃገራቱ አህጉራዊ ድንበርን ማክበርና መሬት ላይ መመላከት የሚገባቸው ምልክቶችም መገንባት ያስፈልጋል አላስፈላጊ ቁርሾ መፍጠሪያ ክብሪቶች እንዳይሆኑ። ነው እያልን ያለነው።]
አቶ አንዳርጋቸው በ41ኛ ደቂቃ እንዲህ ይላል፦ የኤርትራ መንግስት እንዴት እንደሚሰራ ኣውቃለው። ጽምዶ የሚለውን እንቅስቃሴ ነጻ ለቀውታል። ከፈቃዳቸው ውጪ ሊሆን ኣይችልም። [እኛም፦ NoMore የሚል አንድ እርስዎም የነበሩበትን ያልተሳካ እንቅስቃሴን አስታወሱን እኮ ኦቦ ኣንዳርጋቸው ብለናል] የትግራይና የአማራ ገበሬ ፍላጎቱ 100% አንድ አይነት ነው። [እኛም፦ ማንኛውም ገበሬ ፍላጎቱ አንድ አይነት ነው። መሬቱን በቅጡ ማረስ ዝናብ እንዲዘንብለት መጸለይ፡ ምርቱን መሰብሰብና ሸጦ ኑሮውን መግፋት። ሌላው የጦርነት ቡራከረዩ “ነቅተናል” የሚሉ አካላት ተንኮል ውጤት ነው። ብለናል።]
ቀጥሎም ጋዜጠኛ ጸዳለ ለማና ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳን ኣንስቶ ጽምዶ አንዳንድ ሃሳቦችን ኣካፍሏል።[ እኛ እያልን ያለነው ደግሞ ኤርትራዉያን ጋዜጠኞችንና ኤርትራዉያን ፕሮፌሰሮችን እንደነ ጸዳለ፡ ህዝቅኤል፡ መሓመድ፡ አንዳርጋቸው ወዘተ የመሳሰሉትን የተለያየ አመለካከት ያላቸው ‘ልሒቃንን’ መቼ ነው የምታስተዋውቁን ነው። ስንት ምሁራን በየሃገራቷ ያላት ኤርትራ በጽምዶ ዙርያ ያንዱንም አመለካከት እስካሁን አላሰማችሁንም እኮ።]
አወል በ45ኛ ደቂቃ ላይ ሁለት ተፋላሚዎችና የጦርነት ነጋሪ ጎሳሚዎች ሬድዋንና ጌታቸው አሁን ላይ ተጣምረው ደብዳቤ ጽፈዋል ይላል። [እሱና የትግራይ የጽምዶ አባላትም እኮ ይፋለሙና ላንቃቸው እስኪበጠስ የጦርነት ነጋሪት ይጎስሙ እንደነበረ ረስቷል አወሉ። በዚህ አኳያ የጽምዶ አጋፋሪዎች ከሬድዋንና ጌታቸው በምንም አትለዩም። ሚዛኑ እናንተንም ይመለከታል ለማለት ነው።] ፕሪቶሪያ ማለት በማይክል ሃመር ተጽፎ፡ ፈርሙት ተብለው ጠረጼዛ ስር የተወረወረ ጽሑፍ ነው ብላሉ አወሉ።[ እኛም፦ ተዉ ተዉ ህዝብ የመከረበትንና ፕሮፌሰር በረኸት የተሳተፉበትን ህገመንግስታችንን እንዳታስታውሰን ብለን አናስቀውም።] “ያልተተገበረና የማይተገበር የፕሪቶሪያ ውልን መቆስቆስ” . . . ሲልም ተደምጧል የጽምዶው አጋፋሪ፡ [ተው ተው ሃገራዊ ቅዋም እና ፊዚካል ዲማርኬሽንም እኮ አልተተገበሩም። አይደለም እንዴ? ረቢና ስዉኣት ያዩሃል ለህሊናህ ፍረድ። ብለናል] የትግራይ ህዝብ አሁን የተሸረበበትን ሴራ አውቆ ትግራይን ትግሬ ለማድረግና “የተወረረ መሬቱን ለማስመለስ” መቀነቱን አስሯል ይላል አወል።[ በጦርነት አይሁን ብቻ እንጂ ትግራይን ትግሬ ያድርጋት፡ ምስኪን የትግራይ ህዝብ እየተገፈፈ ነው የሚለው ዜና በጣም ያስጠላል። አንድ ብዙዎችን በፈቃዱ የከፈለ ህዝብ ተገዶ ጦርነት ውስጥ እንዲሳተፍ ሲኮነን ያሳዝናል። በእርግጥ እውነተኛ ጽምዶ ለዚህ ኣይነቱ የጦርነት ድግስ ጥሩ ሰላማዊ መልስ ባልጠፋው የነበረ የሃሳብ በነጻነት መንሸራሸር ቢኖር ኖሮ።]
በ47ኛ ደቂቃ፡ የብልጽና መንግስት የጽምዶ አጋፋሪዎች ፖርት ሱዳን ውስጥ ከሁሉም ለሰላምና ለእኩልነት የሚጥሩ ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቻችን ጋር ስንገኛ ግዜ ጨርቁን ጥሎ አብዷል ብሏል። [እኛም ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሄር አላት፡ ታዲያ የስንት ብሄር ተወካዮች ናቸው ቦርትሱዳን ላይ የተሳተፉት ብለን ጥያቄ አልጠየቅነውም።]
“እኔና ከመረብ ወንዝ ባሻገር ያሉ የትግራይ ወንድሞቸ ጋር ጽምዶን ወጥረን የያዝነው ሰላም ስለሚያሰፍን ነው።” ለሚለው አወል [እኛም “ዋርሳይ እዞም ሰባት ግን መን እዮም . . . ንዶብ እንዲዩ ተከፊሉ ጅግና!” የሚለውን ኤርትራዊ ታሪካዊ ሙዚቃ እያጣጣምን፡ “ፊዚካል ዲማርኬሽን” የሚል ነገር ዘነጋህ እንጂ ሃሳብህ መልካም ነበር ብለነናል።]
የፕሪቶሪያ ስምምነት ጌታቸውን ከትግራይ በረሃዎች ሬድዋንን ደግሞ ከኣዲስ አበባ ፕሪቶሪያ ወስዶ ያገናኘ እንጂ ለትግራይ ህዝብ የፈየደው ምንም ነገር የለም ሲልም ተደምጧል። [እንዴ ምን ማለትህ ነው፡ የፈየደው ነገር አለ እንጂ! ከፕሪቶሪያው ውል በኋላ እኮ የጥይትና የመድፍ የመትረየስና የላውንቸር የታንክና የድሮን የሚግም ጭምር ድምጽ፡ አሁን አሁን ጀምሮ ካልሆነ በስተቀር እኮ በጣም ቀንሷል። በግዙፉም ሞትና የአካል ጉዳትም ቀንሷል። አይደለም እንዴ!] የገዛ ህዝቡን ያሰቃየ ስርዓት በቱልቱላዎች በኩል የሰላም ሃዋርያ መስሎ ሊታይ መሞከሩ አስቂኝ ነው። ሲልም ተደምጧል አወል [ እዚህ ላይስ “ወመዓሰላማ” እያልን በአባባሉ 100% ተስማምተናል]
ወደ ዲፕሎማሲው ስንቀጥል፡ ብዙ ሳንንዛዛ ካይሮ፣ ሳውዲያና ሱዳን እንዲሁም ሱማሌ ኤርትራን ያጠቃለለ ኪዳን ተመስርቷል። ኤርትራን መንካት አይቻልም፡ ኤርትራን ነካህ ማለት ኤርትራ ከመሰረተችው ወታደራዊ ኪዳን ጋር ትፋለማለህ ማለት ነው። ኪዳኑን ነካህ ማለት ነው። ሲል ተደምጧል አወል። [እኛም፦ ታዲያ እንደ እድሜ ጠገቡ NATO፡ ቀይባሕርን የሚመለከት Red Sea States Treaty Organization (RSSTO ወይ RASO) የተባለው ኪዳን ተመስርቷል አትለንምን? “ስም ዘዘርከበ እንተውጽኣ እንታይ ጸገም ኣለዎ፡ ህዝቢን መንግስታትን እንተኣአሚኖምሉ ይርዕም፡ ቢልና ክነስሕቐካ እምበይ።”] ኤርትራ በጥበብ በህግና በልዑላዊነት ከሚያምኑ የቀጠናችን ሃገራት ጋር ሆና፡ ቀጠናችንን ከሚያውክ የውጭ ሃይል ሆነ ተላላኪ ሃይል ጋር በዲፕሎማሲ እየተፋለመች፡ ብርቱ የደህንነት ሃይል እንያነጸች መሆኗል ገልጦ፡ አያይዞም ይህን እውን ለማድረግ እድሜና ቦለቲካዊ ተሞክሮ ጠገቡ የኤርትራው ፕረዚደንት ካይሮም ሱማሌም ሳውዲያም እየኔዱ ካርታ መጫወቻ ቦለቲካዊ ካርዶችን እየተጠቀሙባቸው ነው ሲልም ተደምጧል። [እኛም፦ ግሩም ቦለቲካዊ ጆኬር ሆነዋላ ብለን አላሳቅነውም አወልን፡ በዩክሬን ልዑላዊነት ጉዳይ የቀጠናችን ሃገራትን አቋምም አላስታወስነውም ምክንያቱም RSSTO ወይ RASO ከNATO ጋር እንዳይጣላ በማሰብ!]
52ኛ ደቂቃ እንዲህ ብሎናል፡ ግብጽ በትጥቅ ትግል ወቅት ባለውለታችን ነበረች። አንድ ጓዴ ጽፎ የላከልኝን እንዳለች ላንብብላችሁ “ጫታሙ ብርሃኑ ጁላ ግብጽና ኤርትራ በ1960ዎቹ ነው ጽምዶ የጀመሩት ብሎ ነበር። ኤርትራና ግብጽ ግን በ1875-78 የራስ ወልደሚካኤል ልጅ መስፍን ወልደሚካኤል ፖለቲካዊ ሳይንስ ተምሮ ወደ ሃገሩ ተመልሶ ፡ ከአባቱ ጎን በመቆም ጦርነት ውስጥ ተሰልፎ ተዋግቷል፡ ስለዚህ በ1960 ሳይሆን 1875 ነው ግብጽና ኤርትራ ጽምዶ የተጀመረው። ግብጽ ለኤርትራ ነጻነት በመጀርያ ደረጃ ዕውቅና ከሰጡት ሃገራት ትመደባለች። ምንም ዓይነት የታሪክ ቁርሾም የለንም ከግብጽ ጋር ሲልም ተደምጧል የመጣለትን እንደወረደ ሳያላምጥ የሚውጠው አወል። ታሪክን መርመር” ሲል ተደምጧል [እኛም፦ ታሪክ ስንመረምር ከ1865-1885 ለጣልያን አስረክባ እስከወጣችበት ግዜ ድረስ፡ በቱርኮች ይሁንታ ግብጽ ምጽዋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥራ፡ በስዊዝ ተወላጁ በዋርነር ሙዚንገር አስተዳደር ስር ታስተዳድራት ነበር፡ ምጽዋን። ወደ ኤርትራው ደጋማ ክፍል ቀስ በቀስ መውጣት ስታልም፡ ያኔ ግብጽ በኬዲቭ እስማኤል ነበር እየተመራች እስከ ሱማሌ ድረስ ለመስፋፋት ጥረት ታደርግ የነበረችው። ታዲያ እየተንፏቀቀች ወደ ደጋማው ክፍል መስፋፋት ስትጀምር በህዳር 16 1875 ዓ.ም ጐዳጉዲ ጉንደት ከሃበሻ ጦር ጋር በተደረገው ጦርነት፡ ከ3ሽህ የግብጽ ሰራዊት ጥቂቶች ብቻ በህይወት ሲተርፉ፡ 2200 መሳርያና 16 መድፍ ተማርካለች። ያኔ ደጃዝማች ወልደሚካኤል ሰለሞን ከትግራዩ አጤ ዮሃንስ ጋር ጥምዶ ገብተው በሃበሻ ጦር ስር ነበሩ። ታዲያ ብርቱ ሽንፈትን የተጎነጩት ግብጾች 15ሽህ ሰራዊት አሰልፈው መሓመድ ራቲቭ ፓሻን መሪ አድርገው፡ ጀነራል ዊ.ዊ. ሎሪን የተባለ አሜሪካዊ መርሰነሪ፡ ዊልያም ማክዳይና ፓርለስ ፊልድ በተባሉ ኮሎኔሎችንም እየተመሩ፡ በጠቅላላው 18 ኮሎኔሎች የተሳተፉበት ዳግም ጦርነት በጉራዕ ገጠሙ። ታዲያ ታህሳስ 5 1875 ዓ.ም የግብጹ ንጉስ እስማኤል ለጠቅላይ ምኒስትራቸው ለራቲቭ ፓሻ፡ “ጉንደት ላይ ጉድ ያደረገንን ያበሻ ጦር መሪ አጤ ዮሃንስን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተህ አስፈላጊ ከሆነ ዓድዋ ድረስ ዘልቀህ ደምስሰው” የሚል መመሪያ ሰጡ። ከ15-29ሽህ የሚገመተው የግብጽ ጦር ከምጽዋ ተነስቶ በአስመራ በኩል ተጉዞ ጉራዕ ሲደርስ፡ ዳግም ሂሳቡን አገኘ። ሄሄ ያገራችን ጀግኖች የዋዛ ኣይደሉም፡ “ብዙ ከሚነገርለት ከዓድዋው ጦርነት የላቀ ድል ነበር የተጎናጸፉት ያበሻ ጥምር ሰራዊት በጉራዑ ድል” ይላሉ ኤርትራዊው ኢትዮጵያዊውም ጭምር ተመራማሪው ያገራችን ሰው ዶ/ር ተወልደ ትኩእ።
በጉንደቱ ጦርነት ከሓበሻ ሰራዊት ጎን ጀብዱ የፈጸሙት ደጃች ወልደሚካኤል ሰሎሞን የኋላ ኋላ ከቱርክ ጋር በመጣመድ፡ በጉራዑ ጦርነት አሰላለፍ ቀይረው ከግብጽ ጎን በመሰለፋቸው፡ ግብጾች የ"ራስነት" ማዕረግ፡ ለልጆቻቸው ደግሞ የደጃዝማችነት ማዕረግ ሰጧቸው። በፈረንጆች አቆጣጠር ከማርች 7-10 1876ዓ.ም በተካሄደው የጉራዕ ጦርነት ግብጾች ሲሸነፉ፡ ራስ ወደሚካኤል ራስነታቸውን ይዘው ከግብጾች ጋር ወደ ጊንዳዕ ሸሹ ይላል ዮሃንስ ኮልሚዲን። እኛ ሚመስለን የነበረ ራስ ወልደሚካኤል ራስ ባይሩን በመግደላቸው ራስ የተባሉ ነው፤ ነገር ግን በግብጽ ራስ ተብለው ተሸንፈው ጊንዳዕ ከሄዱ በኋላ፡ ከተወሰነ ግዜ በኋላ ራስ ባይሩኡ የሓማሴን አስተዳዳሪ ለመሆን በቋመጠበት ወቅት ነበር አስመራ ላይ ራስ ባይራኡን ያሸነፉትና የገደሉት፡ ታሪኩን መልክ መልኩን ለማስያዝ ያህል ነው።]
ኣወል ሲያጠቃልል፦ "ኤርትራ በዲብሎማሲ ተመሳሳይ አመለካከት ካላቸው የቀይባህር ሃገራት ጋር በመጥመድ የውጭ ሃይሎችን እና ተስፋፊ እርምጃቸውን አምክናለች። ሱዳንንም ሆነ ሱማሌንም ሃገራዊ ልዑላዊነታቸው እንዳይደፈር የበኩሏን ገንቢ ሚና ተጫውታለች። ብረዚደንታችን ከግብጽ ጋር በተነጋገረ በሳልስቱ የግብጽ መሪ ወደ ኣሜሪካ ሄደ፡ ብረዚደንታችን ከሳውዲ ጋር እንደተነጋገረ የሳውዲ መሪ ወደ አሜሪካ ሄደ። ትራምፕ በናይል ዙርያ ግብጽን የሚደግፍ ንግግር አድርጓል። “የሰው ባህር የምትመኚ ብልጽግና ወዮልሽ!” እያለ ነው። "ብሏል።. [እኛ ደግሞ ከኤርትራውያን ወንድሞችህና እህቶችህ ጋር ለመጣመድስ ምን ጥረት አድርገሃል ብለን አንዲት ጥያቄ ጠይቀነዋል። እነ ብሮፌሰር መሓመድም እኩዮቻቸው ማለት ኤርትራውያን ብሮፌሰሮች እና፡ ኤርትራዉያን የቦለቲካል ሳይንስ ምሁራን በሌሉበት ከኤርትራ ጋር ጥምዶ እየሰራን ነው ማለት ፡ እንደ ምሁር መጠን ሊያሳስባቸው ሊያሳፍራቸውም ይገባል።]
ባለቀ ሰዓት በጽምዶ 41፡ የቀይባህር ወደቦች የሽኩቻ ወደቦች ከሚሆኑ ይልቅ፡ የቀጠናውን ኢኮኖሚ የሚቀይሩ የልማት በሮች ይሆናሉ፤ በቀጣይ ጊዜያት ዓሰብና ምጽዋ ላይ ብቻ ሳይሆን ማርሳ ፋጥማ ላይ ምን እንደሚሰራ ለማየት ዓይኖቻችንን ከፍተን መጠበቅ ብቻ ነው የሚገባን ያለው አወል፡ [ልክ ህዝባችን ለዓመታት የመከረበትና የዘከረበት ህገ መንግስቱ ይተገበራል ወይም ብዙዎች የተሰውበት ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ድንበር “ፊዚካሊ ዲማርኬት” ይደረጋል ብለን አይናችንን አፍጥጠን እንደጠበቅነው ማለትህ ነውን አላልነውም፡ ገራሚውን የጽምዶ አጋፋሪ]
አቅሙን የማያውቀው አወል፡ እንደ የኢራኑ ጢማም መሪ፡ እስራኤልን ከብልጽግናና ከኤሚሬት እኩል አቋምሽን ካላስተካከልሽ ትጠረጊያለሽ በማለት ሲወርፍም ተደምጧል። እስራኤል በወባ በሽታ ክፉኛ ተጠቅተው የነበሩትን ብረዚደንታችንን ነፍስ አዘርታ፡ ለወግ ለማዕረግ እንዲበቁ ያደረገች ባለውለታችን መሆኗን ዘንግቷል ብለን አላሳቅነውም።
ሲደመድም፡ ቀጣዩ ጥምዶ ሱማሌያ አልም ካይሮ ወይም ኣሜሪካ ይሆናል ብሎናል። ወደ አሜሪካ ሲያቀና መቼም የ9/11 ሰለባዎች ሃውልት ላይ የህሊና ጸሎት ያደርስ ይሆናል ብለን እንገምታለን። ያኔ እንገናኝ ብሏል የጥምዶው አጋፋሪ። እኛም "ወመዓሰላማ" ብለን አገባደናል ጽምዶ 41ን።
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5227
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 29 Jun 2026, 11:09
እንደ ጠቢቡ ሰለሞን “ትዕቢት ውድቀትን ትቀድማለች” እያሉ፡ በግድና በፈጣጤ “ተጋዳላይ” በሉኝ የሚለውን ኣወልን እየኮረኮሙት ነው ኤርትራዉያን ወጣቶች! እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞችም፡ ታሪኩን መልክ መልኩን ለማስያዝ እየሞከርን ነው፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር!
Please wait, video is loading...
Please wait, video is loading...
እኛም ወርሃ ሰኔ በመሆኑ፡ ሃገር ፈጣሪ ሰማእታቶቻችንን እንዘክራለን።
Meleket wrote: ↑08 Dec 2022, 08:34
ኣብ በሊሕ መላጸ
ተሰሪዖም ከም ጻጸ፡
ኣብ በሊሕ መላጸ፡
ብመስዋእቶም ...
ዘስገሩ ብጾቶም፡
ዘይርሳዕ ውዕለቶም፡
ንሳቶም ...
ኣብ በሊሕ መላጸ ሚልዮናት ዘስገሩ፡
በጃ እናሓለፉ ፍቕሮም ዘመስከሩ፡
ሃገር ዝፈጠሩ፡
“አናብስ ስዉኣት” ወትሩ ይዘከሩ።
እላይ ለአወል ግሩምና ኣጥጋቢ መልስ በመስጠት ልክልኩን እዬነገሩት ያሉትን ወጣቶች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር ማመስገንም እንወዳለን!
“ንፉዓት፡ ጀጋኑ፡ ወረስቲ ሕድሪን፡ ዓቐብቲ ታሪኽ ኤርትራን” ቢልና እውን ደጋጊምና በስም ስዉኣትን ህልዋትን ጭዋታት ደቂ ኤርትራ ብሓፈሻ ከነተባብዖም ንደሊ! ኤርትራዉያን ወጣቶች በሙሉ፡ የነ የጽምዶዉ ምርኮኛ ብሮፉርሸር መሓመድን የቦለቲካ የማሲንቆ ጨዋታና ዳንስን በጥሞና እየተከታተሉ እንደሆነም ግልጽ ምልክት ነው። የተለያየ ድምጽ ያላቸውን የኤርትራዉያን ወጣቶችንና ምሁራንን ድምጽ ያላካተተ “ጽምዶ”፡ በትዕቢት ተወጥሮ ኤርትራዉያንን “በላዕቲ ውዳቕ” እያለ የሚሰድብ “ጽምዶ”፤ “ፊዚካል ዲማርኬሽንን”ም ችላ ብሎና አድበስብሶ የሚጓዝ “ጽምዶ”፡ በኤርትራዉያን በጎሪጥ እንደሚታይ ምስክር መጥራት ኣያስፈልግም። በመሆኑም የጽምዶ አካላት ጽምዶ ይሳካና የታለመለትን ግብ ይመታ ዘንድ፡ እንደ ባንድ ወቅት ያስተጋባ እንደነበረው NoMore የተባለው ሰሞንኛ እንቅስቃሴ አውላላ ሜዳ ላይ እንዳይቀር፡ እነዚህን እዉነታዎች ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ በኤርትራዊ ጭዋነት ብንጠይቅ ቅር ሊላቸው አይገባም።