Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Zmeselo
Senior Member+
Posts: 36747
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

Messages from ONLF and PP.

Post by Zmeselo » 17 Nov 2025, 17:08

The ONLF Central Committee has issued a new communiqué following its extraordinary meeting.
It addresses the worsening crisis in Ethiopia, violations of the 2018 peace agreement, repression of Somalis, and the new phase of national struggle.







PeePee, comminuqué:


Zmeselo
Senior Member+
Posts: 36747
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

Re: Messages from ONLF and PP.

Post by Zmeselo » 17 Nov 2025, 17:35

ወያኔዎች በብሄር ኮታ ጀነራል ያደረጓቸው አረመኔው ነፈስ በላ አብይ አህመድ በድጋሚ በማእረግ ያንበሸበሻቸው የወታደራዊ ሳይንስም፣ የፓለቲካም የዲፕሎማሲ ሳይንስም አካባቢ ያልደረሱ ደናቁርቶችን ይዞ ነው አሰብን እናስመልሳለን ብለው በየቀኑ የሚፎክሩት። ለመሆኑ አማራ ክልል በሁለት ሳምንት እንጨርሰዋለን ብለው የገቡበት፣ የዚህ ስውየ አልቆች የፎከሩበት ጦርነት ዛሬ ላይ የት ደርሶአል? የትግራይ ሁኔታ፣ በኦሮሞ ክልል የሚያካሄድው ጦርነት? ፣ የሀገሪቱ ሁለንተናዊ ቀውስ? ወዘተ.... በድጋሚ ለዚህ ስውየም ሆነ ለደናቁርት አለቆቹ የሚረዱት ጉዳዮች አይደሉም። ሀገርና ህዝብ ወደ ሌላ ገደል አፋፍ ይዘው ይነጉዳሉ።

ወገን ኢትዮጵያውያን፣ የፋሽስታዊውን አብይ አህመድ አገዛዝ ለማንበርከክ፣ ለማስገደድ ከትጥቅ ትግሉ ጎን ለጎን በከተሞች የህዝብ እምቢተኝነት አስፈላጊ ነው። ሁለቱ ጎን ለጎን መደረግ ይችላሉ። በሀገር ቤት ህዝቡ ልዩ የእምቢተኝነት ትግሎች እያደረገ ነው። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል አመራሮች አንዱ የሆነው አርበኛ ዘመነ ካሴ ህዝባዊ እምቢተኝነት በከተሞች መደረግ እንዳለባቸው ድጋፉን ሰጥቶአል። በዲያስፕራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጋራ ከቆሙ ለህዝባዊ እምቢተኝነቱ ትግሎችን በሰፊና ተከታታይ አለም አቀፍ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች፣ የኢኮኖሚ ቦይኮቶች፣ እንዲሁም አገዛዙ እኛ ከምንልከው የ ሃዋላ/የሬሚታንስ ገቢ እንዲደርቅ በማድረግና በሌሎችም ሰፊና ተከታታይ ዘመቻዎች በማድረግ የአመጽ ትግሉን እንዲሁም የህዝብ እምቢተኝነት ትግሉን ማገዝ ማጠናከር ይቻላል።

Zmeselo
Senior Member+
Posts: 36747
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

Re: Messages from ONLF and PP.

Post by Zmeselo » 17 Nov 2025, 17:52

📢 New Song Out Now! 🎧🔥

“The Notebook of Bacha - "ተጨፈጨፍን

Music based on Bacha’s own words from his interview about the Buré War - the truth, the leadership failures, the pain, and the lessons they never learned.



Zmeselo
Senior Member+
Posts: 36747
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

Re: Messages from ONLF and PP.

Post by Zmeselo » 17 Nov 2025, 21:32



የጂንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ለመገናኛ ብዙሀን መረጃ መስጠታቸውን ተከትሎ ከሀላፊነታቸው ተነሱ

By: wazemaradio

https://wazemaradio.com/%e1%8b%a8%e1%8c ... %e1%88%98/

Nov 17, 2025



ዋዜማ- የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር በአካባቢው ስለተከሰተው “የሔሞሬጂክ ፊቨር” እንደሆነ በተገመተው ተላላፊ በሽታ ሰዎች መሞታቸውን ገልፀው ለመገናኛ ብዙሀን መረጃ መስጠታቸውን ተከትሎ ከሀላፊነታቸው ተነሱ።

ዋዜማ ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮና ከሆስፒታሉ ምንጮች እንደሰማችው የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ቢንያም አስራት ለአንድ አለማቀፍ ሚዲያ “የሔሞሬጂክ ፊቨር” እንደሆነ በተገመተው በሽታ ሳቢያ ሀኪሞችን ጨምሮ ሰዎች መሞታቸውን ገልፀው መረጃ በመስጠታቸው ከሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ምስጢሩ ሐምደኪ በተጻፈ ደብዳቤ ከሕዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ተነግሯቸዋል።

ዳይሬክተሩ ከሃላፊነት ከመነሳታቸው በፊት ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ከታከሙት አራት በሽተኞች አንዱ በህይወት እንዳለ እና የተሻለ የሚባል የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ሁለት የሆስፒታላቸው የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ እስካሁን ስድስት ሰዎች ተመሳሳይ ምልክቶችን በማሳየት ህይወታቸው ማለፉን ለዶቸ ቨለ ራዲዮ በይፋ ገልፀው ነበር።

የበሽታው ክስተትና ምንነት ዓለማቀፍ ትኩረት የሳበ ሲሆን የዓለም የጤና ድርጅትም ከመንግስት ጋር በመቀናጀት አስቸኳይ የመስክ ቡድን ወደ ስፍራው ልኳል።

የጤና ሚኒስቴር እስከአሁን ድረስ ስምንት ሰዎች በበሽታው የተጠረጠሩ መሆኑን ባወጣው መግለጫ ይፋ ያደረገ ሲሆን ስለ ሞቱ ሰዎች ያለው ነገር የለም።

ዶክተር ቢንያም አስራት በበሽታው ሞት መመዝገቡን ይፋ ካደረጉ በኋላ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ የቅርብ የስራ ባልደረቦቻቸው ነግረውናል።

ዶ/ር ቢንያም በሆስፒታሉ ውስጥ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አስራር በማስተዋወቅና የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከል በማስገንባት ለአገልግሎት ለማብቃት በዝግጅት ላይ እንደነበሩ ባልደረቦቻቸ ይናገራሉ።

ሆስፒታሉን በበላይነት የሚያስተዳድርው የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በጉዳይ ላይ አስተያየት እንዳለው ብንጠይቅም ሀላፊዎቹ ምላሽ መስጠት እንደማይፈልጉ ነግረውናል።

የጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጂንካ ከተማ
ትክክለኛ ምንነቱ ገና በመጣራት ላይ ያለ እና “የሔሞሬጂክ ፊቨር” በሽታ እንደሆነ የተገመተ በሽታ መከሰቱን
ሕዳር 3 በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀው ነበር።

የዓለም ጤና ድርጅት፣ የበሽታውን ምንነት ለማወቅ ለሚደረጉ ምርመራዎች እና በሽታውን ለመቆጣጠር ለሚደረጉ ጥረቶች 11 አባላት ያሉት የአስቸኳይ ድጋፍ ሰጪ ቡድን እና የሕክምና መሳሪያዎችን ወደ አካባቢው መላኩን እንዲሁም ለዚሁ ጥረት የሚውል 300 ሺሕ ዶላር መመደቡን አስታውቋል።


_____________



What's does this "በሕይወት ያለ ሰው የለም", actually mean?


Zmeselo
Senior Member+
Posts: 36747
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

Re: Messages from ONLF and PP.

Post by Zmeselo » 18 Nov 2025, 11:00

በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ሁሉቆ ቀበሌ ላይ በማርበርግ ቫይረስ በሽታ እንደተጠቁ የተጠረጠሩ 13 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ሚድያችን አረጋገጠ

"የአካባቢው አመራሮች መረጃውን ካወጣችሁ ተጠያዊ ትሆናላችሁ ብሎ ፀጥ አስብሎናል። አሁን ላይ በአካባቢው የመንግስት ወታደሮች ተሰማርተው ማንም እንዳይወጣ ተከልክሏል"- የአካባቢው የጤና ባለሙያች

Post Reply