Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4606
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራ እና የኢትዮጵያ 146ቱ የጋራ ፈርጦች!

Post by Meleket » 04 Jun 2025, 11:39

Meleket wrote:
09 Nov 2022, 10:35
የኤርትራ እና የኢትዮጵያ 146ቱ የጋራ ፈርጦች! - የ146ቱ ካምፖች ወግ!

ጐበዝ እነዚህ 146 የጋራ ፈርጦቻችን ከነ 'ኮኦርዲኔታቸው' በማያሻማ መልኩ “ይግባኝ በማይባልበት” ፍርድ ተወስነው፡ ቁልጭ ብለው ትግባሬን እየጠበቁ የተቀመጡ ናቸው።

https://legal.un.org/riaa/cases/vol_XXVI/771-799.pdf

ታድያ ሃገራችን ኤርትራና ጐረቤቷ ኢትዮጵያ በሰላም ይኖሩ ዘንድ፡ እንዲህ ቢደረግ ምን ይመስላችኋል?

1.) በ146ቱ ነጥቦች፡ በያንዳንዷ ስፍራ የጋራ ወታደራዊ ካምፕ በመገንባት የደንበር ጸጥታ አስከባሪ ሃይል ማስፈር።

2.) በ146ቱ ካምፖች የሚኖሩት የሁለቱ ሃገራት የሰራዊት ብዛት 80 ከኢትዮጵያ (ሁሉን ኢትዮጵያዊ ብሄር ብሄረሰቦች የወከለ እንዲሆን ማለትም ኣልተወከልኩም የሚል ኢትዮጵያዊ ብሄር እንዳይኖር ማለት ነው።) ኤርትራም በበኩሏ ከ80 ያልበለጡ የሰራዊቷ ኣባሎችን በነፍስወከፍ 146ቱ ካምፖች ውስጥ እንድታስቀምጥ ማድረግ።

3.) ይህም ማለት 146*80 = እያንዳንዷ ሃገር ቢያንስ ቢያንስ 11,680 በወታደራዊ ዲሲፕሊን የተመሰከረላቸውን የሰራዊት አባሎቿን ለድንበር ጥበቃ እንድታሰማራ ማድረግ። ይህ የሁለቱ ሃገራት መንግስታት የሰራዊት ክፍል፡ ፈጣን በሆነ ዘመናዊ የመገናኛ መሳርያዎች የታጠቀ ማድረግ። [ስለ ወጪው አትጨነቁ፡ የሁለቱ ሃገራት ህዝብ ሊሸፍነው ይችላል፤ የሁለቱ ሃገራት ህዝብ በረባ ባልረባው ከመናቆር፡ ገንዘብ አዋጥቶ ሰላሙን ማስጠበቅ ይቀለዋል!]

4.) የሁለቱም ሃገሮች የአየር ሃይል፡ ሃገሮቹ ዬተስማሙባቸውን ያህል የአሰሳና ዳሰሳ ሂሊኮፕተሮችና ድሮኖች ለዚሁ ድንበር ጸጥታ መመደብ። [በሂሊኮፕተርና በድሮን ከመጨፋጨፍ ይሄ ሳይሻል ኣይቀርም ትላላችሁን?]

5.) በዚህ መሰረት፡ በድንበር አካባቢ ምናልባት ሊፈጥር የሚችልን ግጭት በግዜ ማጤንና ፈጣን ፈውስ በመሻት እልባት ላይ ማድረስ።

በዚህ መልኩ “ፊዚካል ዲማርኬሽኑን” ብንጀምረው የሁለቱ አጎራባች ሃገሮች ህዝቦች ዘለቄታዊ ሰላምና እፎይታን ለማግኘትና ለማጣጣም አይችሉም ትላላችሁን? እስከ መቼ ድረስ እርስ በእርስ ማናቆር ጐበዝ!

ለዛሬ 146 የጋራ ፈርጦቻችንን እዚህ ተመልከቷቸው!ከገጽ 786-794 ወይም ከ ገጽ 17-25 ቁልጭ ብለው አሉላችሁ።



ጐበዝ "ፊዚካል ዲማርኼሽኑ" በዚህ ሃሳብ አኳያ ቢተገበር ምን ይመስላችኋል? እስቲ የሚጐድለውን አጉድላችሁ፡ የሚጨመረውን ጨምራችሁ ሃሳባችሁን አክሉበትና ወደ ትግባሬ እናምራ። የየሃገሮቻችን ቦተሊከኞቻችንን እንዲህ አድርገን 'ጭራውን መያዝ' የፈሩትን ነገር በማደፋፈር እናግዛቸው እንጂ ጐበዝ! አይመስላችሁም። "ፊዚካል ዲማርኼሽን ይቻላል!"

ተጻፈ፡ በኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 4606
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራ እና የኢትዮጵያ 146ቱ የጋራ ፈርጦች!

Post by Meleket » 11 Jun 2025, 04:23

ኣብ "ጽምዶ 5.1" ጋዜጠይና ስታሊን ምስ ኣወል ስዒድ ‘ስንዝሮ’ ዝገበሮ ቃለምልልስ ሰሚዕናዮ። ስታሊን ንመራሕቲ ኤርትራ ንጀነራል ፍሊጶስ ንሚኒስተር ዬማነ ካብ ህግደፍ’ ውን ንሓጐስን ንዬማነን “ዶብ ጠርርዎ” ከምዝበሎም ኣጻዕድዩ ነጊሩና። ግርም ገበርካ። ሓቀይና “ጽምዶ” ንፊዚካል ዲማርኬሽን ብቀዳምነት ዚሰርዕ ኪኸውን ይግብኦ ኢዩ። ንብረዚደንት ኢሳይያስ’ከ ብዛዕባ እዚ ጉዳይ ተቢዕኻ ሓቲትካ ‘ዶ፧ እንተ ዓወል ስዒድ፡ ኣብ ሞንጎ ቨርቺዋል ዲማርኬሽንን ፊዚካል ዲማርኬሽንን ዘሎ ፍልልይ ዚርድኦ ኣይመስልን። ተተግቢሩ ኢዩ ቢሉ ኪካትዓኻ ፈቲኑ ነቢሩ፡ ምስኪናይ!

ትግባረ “ፊዚካል ዲማርኼሽን” ግን ንመን ኢዩ ዚጐድእ? ዚረኣይን ዚድሕሰስን ምልክት ዶብ፡ ብመሰረት ብይን ሄግ ኣብ 146 ነቁጣታት ምትካል ንመን ይጐድእ? መን ይህሰ? ሰብ ፍሉይ ረብሓታት (ሰ.ፍ.ረ.) ጥራሕ ኢዮም በዚ ተግባር ዚጉድኡ፡ ዕንቕፋት እዉን ዚዀኑ ዚብል ኢዩ መትከል ኤርትራውያን ደያኑ ማእከልን መስመርን! ንዝበለጸ ትንታነ በዡይ ዕለት ንዝቀረበ ርእይቶና ኣብዡይ ንበቡ። viewtopic.php?f=2&t=310610&p=1562890#p1562890

እንተ ልባዊ ድሌት ሃልዩ ግን መዳውብቲ ሰራዊት፡ መዳውብቲ ህዝብታት ኮፒ ናይ ብይን ሄግ ዓቲሮም ፊዚካል ዲማርኬሽን ንምግባር ጂፒኤስ ጥራይ ኢዩ ዘድልዮም። ህዝብታትና ባዕሎም ንፊዚካል ዲማርኬሽን ብጭውነትን ሰላማዊ መንፈስን ተግቢሮም ዓለም ከዛርቡ ይኽእሉ ኢዮም፡ ቦተሊከኛታት ድማ ነዚ ቅዱስ ተግባር ከተባብዑ እምበር ከይኮልፉ ንምዕዶም፡ በቲ ልሙድ ኤርትራዊ ጭዉነት ሓበንን ፍናንን።

Meleket
Member
Posts: 4606
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራ እና የኢትዮጵያ 146ቱ የጋራ ፈርጦች!

Post by Meleket » 05 Jul 2025, 03:20

Meleket wrote:
05 Jul 2025, 02:56
Meleket wrote:
27 Jun 2025, 04:50
አንት ብልጽግና እንዲሁም ወይን፡
ምን ያጣላናል በሄጉ ብይን?

ይልቅ እንትጋ ለጋራ ፍቅር፡
ችካል ቸክለን ሰላም እንኑር!

ይብቃ መናቆር እንዲያው ለከንቱ፡
ትብብር ይንገስ ይመር ውጤቱ፡
መማር ይበጃል ከባለፉቱ! :mrgreen:
viewtopic.php?f=2&t=308857

viewtopic.php?f=2&t=364184

Zmeselo wrote:
04 Jul 2025, 11:27
Mr. Secretary,

On this 4th of July—America’s Day of independence and sovereign dignity—we urge you to reject Ethiopia’s desperate letter of distortion. Eritrea has honored international law, respected borders, and pursued peace. Ethiopia, meanwhile, defies the EEBC ruling, occupies sovereign Eritrean land, and fuels proxy wars while blaming others. This manipulative appeal is not a cry for peace—it’s a plea for cover.

As America celebrates liberty, truth, and restraint, we ask you to stand on principle: truth first, law first, peace first, sovereignty first—Fourth for Marco.

Eritrea seeks no war, no interference—only mutual respect. Ethiopia’s regime can not be allowed to drag the region into another needless conflict through false victimhood.

With respect.
@TheNation1993


The, "daddy pls help" letter. 👇

Ridiculous people!



የኢትዮጵያ ሆኑ የኤርትራ የሃይማኖት ኣባቶች፡ የሃገር ሽማግሌዎች፡ ምሁራን ወዘተ መሪዎቻቸውን “ፊዚካል ዲማርኬሽን” ኣሁኑኑ በማለት ለሰላም መትጋት ይጠበቅባቸዋል። የሁለቱ ሃገራት ፖለቲከኞችም ከጥቂት ዓመታት በፊት ፍቅር በፍቅር ነን “ፍቅር ያሸንፋል” እያሉ ህዝቡን ሲያዘፍኑና ምድሪቱን ቀውጢ ሲያስደርጉ የነበሩ፡ ኣሁን ለመወነጃጀል መቀዳደም ኣይገባቸውም! ኣሳፋሪ ተግባርም ነው። ስንታረቅ ኣብራችሁን ደንሱ፡ ስንጣላ ደግሞ ተቧቀሱልን ሊባል ኣይገባውም የሁለቱ ሃገራት ምስኪን ህዝብ። በመሆኑም የሁለቱ ሃገራት ቦተሊከኞች በጨዋ ደንብ የኣልጀርሱን ስምምነትና የሄጉን ብይን በመተግበር ለቀጠናው ዘለቄታዊ ሰላም እንዲተጉ ደግመን ደጋግመን እናሳስባለን እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር!

Post Reply