Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

ባስመዘገበው ዕድገት የተገረሙ በርካታ የውጭ መንግሥታትንና ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ‹‹ምን አግኝታችኋል? ነዳጅ አገኛችሁ ወይ?›› የሚሉ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ ማድረጉን:-ዓብይ አህመድ

Post by Za-Ilmaknun » 04 Nov 2024, 12:53

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ባስመዘገበው ዕድገት የተገረሙ በርካታ የውጭ መንግሥታትንና ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ‹‹ምን አግኝታችኋል? ነዳጅ አገኛችሁ ወይ?›› የሚሉ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

-8 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል
-በግጭት ምክንያት 5,568 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል
-በአማራ ክልል ድርቅ 85 ሺሕ የቤት እንስሳት ሞተዋል


የምክር ቤቱ አባላት ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከልም የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን፣ እየተንሰራፋ ይገኛል ያሉትን ብልሹ አሠራርና የኮንትሮባንድ ንግድን፣ የሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያና የኑሮ ድጎማን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና በኢንቨስትመንት ላይ የሚታዩ ማነቆዎችን የተመለከቱ ይገኙባቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ መንግሥታቸው ባለፉት ስድስት ዓመታት ባካሄደው አገራዊ ሪፎርም ያልተዳሰሰ ዘርፍ አለመኖሩን፣ በዚህም የተገኘው ውጤት ከ2017 ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮጵያ እንደ አገር ማንሰራራት የምትጀምርበት ዓመት እንደሚሆን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተጠናቀቀው 2016 ዓ.ም. 8.1 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም ደረጃ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ ጥቂት አገሮች ተርታ ያሠለፈና በርካታ አገሮችም ዕውቅና የሰጡት እንደሆነ አስታውቀዋል።

በዚህም የተነሳ፣ ‹‹ከብዙ አገሮች ጋር በምናደርገው ግንኙነት የተገኘውን ዕድገት ለማመን የተቸገሩ፣ ምን አግኝታችኋል? ነዳጅ አገኛችሁ ወይ? የሚል ጥያቄ የሚያነሱ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት አሉ፤›› ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ ‹‹ሪፎርሞቻችንን ጨርሰን አሁን ማንሰራራት የምንጀምርበትና በታሪካችን ዓይተን የማናውቃቸው ውጤቶችን እያየን ትውልድን ወደ ማፅናት ሥራ የምናሸጋግርበት ዘመን መጀመሪያ ይሆናል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡ :lol: :mrgreen:

https://www.ethiopianreporter.com/135062/

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12902
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ባስመዘገበው ዕድገት የተገረሙ በርካታ የውጭ መንግሥታትንና ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ‹‹ምን አግኝታችኋል? ነዳጅ አገኛችሁ ወይ?›› የሚሉ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ ማድረጉን:-ዓብይ አህመድ

Post by DefendTheTruth » 04 Nov 2024, 14:58

የግድ ማዕድን ወይም ነዳጅ ማግኘት የለብህም፣ ትልቅ የዕድገት እምርታ ማስመዝገብ ለማቻል። ብዙ ምርት ማግኘት ወሳኝ ሆኖ ሳላ፣ ትልቅ ኢኖቬሽን መጠቀም ና ምርታማነትን ማሳዳግ፣ እንደዚያዉ ለትልቅ እምርታ ያበቀሃል፣ እንደ ፋንዶ ና አንዳንድ የአማራ ፖለቲከኞች ዝም ብሎ copy&paste መጠቀምን እንደ ትልቅ አድርጎ ከልተቆጠረ። ማስረጃ ትፈልጋለህ?



We are really tired to lecture you again and again that there will be some people who will go hungry, no matter how much economic growth a country may achieve. There are people still going to bed empty stomach in the USA, the world's largest economy.

Go figure out why!



Post Reply