ሰሞኑን አነጋጋሪው የችግራይ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና (ማትሪክ) ውጤት መለቀቁ ነበር። እነወያኔ ለትምህርት ሚኒስቴር በላኩት ደብዳቤ ችግራይ 9 ሺ ተማሪዎቹ ለፈተና ቀርበው ከ70% በላይ ማለፋቸውን ነው።
የሚገርመው 70% አልፈዋል ማለታቸው ነበር። እንዴት ነው 99.9% አልፈዋል አለማለታቸው ነው (እንደምናስታውሰው ሁሌም በ election ይሁን በምንም ችግራይ 99.9% አመጣሁ ማለት ስለምትወድ)
ሌላው አስገራሚው ነገር እንዴት ነው በመላው ችግራይ 9 ሺ ተማሪዎች ብቻ ለማትሪክ የቀረቡት? ችግራይ ከ214 በላይ high schools አላት ብለውናል ታዲያ እንዴት ቢሆን ነው 214 ትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ 9 ሺ ተማሪዎች ብቻ ለፈተና ያቀረቡት? ሌሎቹስ?
እንደሌላው ነገር ሁሉ የችግራይ ነገር የተምታታ ነው።
Re: እንዴት ሰነበትሽ አያልፍልሽ እምዬ ችግራይ ...
ብርሃኑ ነጋ ሲፈልግ ይሰጣል ሲፈልግ ይነሳል። ፈተናው እኮ ብርሃኑ ነጋ ነው እንጅ ትምህርት አይደለም። የእጅ መንሻ የይቅርታ ስጦታ ስለመሆኑ ትጠራጠራላችሁ እንዴ?
ማርክ በኪሱ ይዞ ወንበር ላይ የተቀመጠው ብርሃኑ ነጋ ይነፍጋል ይቸራል። እውነቱ ግን ትምህርት በኢትዮጵያ ሙቶ ከተቀበረ ከ33 አመታት በላይ ተቆጥረዋል። አሁን ደግሞ ብርሃኑ ኦነግ ተዝካሩን እያወጣ ነው። 1፡5 ሚልዮን ህዝብ ያለቀበት አገር ስለ ትምህርት ስኬትለማውራት መዳዳት መሳተዛዘኛ ይዞ ለቅሶ ቤት ድንኳን እንደመግባት ነው የሚቆጠረው። ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ።