ከወራቶች በፊት የሀይማኖት አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደጦር ግንባር ለመዝመት ወስነው ነበር።
በጦርነቱ ወቅት የኢትዮጵያ አምላክ በሚል የዳቦ ስም ፈጣሪን ወገንተኛና የእነሱ አሃዳዊ ፖለቲካ ጉዳይ አስፈፃሚና ጠበቃ ለማድረግ የቻሉትን ሁሉ እንዳደረጉ መረሳት የለበትም።
ትምቢቱም ፤ እውነቱም ፤ እምነቱም ፤ ሀይሉም ፤ የእነሱ ብቻ እንደሆነ ከመፅሀፉም ከሀይማኖትም ከታሪክም ሲያመሳክሩ ... የእነሱን ቅዱስነት የሌላውን ዲያቢሎስነት ሲስሉና ሲገልፁ ጦርነቱን በመንፈሳዊ ፤ በመለኮታዊ ፤ በተአምራት አውድ ሲተነትኑ ሲያቀጣጥሉ እንደነበር መታወቅ አለበት።
በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ ጉዳዩ የአለማዊ ፖለቲካ ቀውስ ያመጣው ጣጣ ሳይሆን የቅዱስነትና የእርኩስነት ሀይማኖታዊ መንፈሳዊ ካባ ሲደረብለት ተመልክተናል።
ታዲያ ይህንን ጉዳይ ያላስተባበሉ የሀይማኖት አባቶች .. ጦርነቱን ባርከው ያስጀመሩ የሀይማኖት ስር ቁማርተኞች ፤ ከሰማያዊ ከፍታ ወርደው በግልፅ ለአንዱ ወገን ድጋፋቸውን የሰጡ ሼሆች ፓስተሮችና ቄሶች እንደነበሩ ማስታወስ አለብን።
የሀይማኖት አባቶች .. የእኩልነት ፤ የፍትሀዊነት ፤ የመቻቻል ፤ የሰላም ፤ የአንድነት ፤ የእርቅ ፤ የወንድማማችነት ፤ የአብሮነት ፤ የሰብዓዊነት ተምሳሌት መሆን ሲገባቸው በግልፅ ይህንን ሽረው ለአንዱ ወገንተኛ ከሆኑ በኃላ ... ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸው ጉዳዩን አክርሮት ነበር።
ሳጠቃልለው የሀይማኖት አባቶች .. ከሰማያዊና ከስነምግባር አስተምህሮ ዝቅ ብለው ጦርነት ደግፈው መግለጫ ሰጥተዋል።
አለማዊ ፖለቲካ ላይ ተነክረው ተሰሚነታቸው አጥተዋል። ወገንተኛ በመሆን ህዝቡን ለሁለት ከፍለውታል። የሴራ ፖለቲካ ላይ ተነክረው ተፅዕኖቸውን አጥተዋል።
ለዚህ ሁሉ ጥፋቶች የአብይ አህመድ የፖለቲካ አካሄድ ድርሻው የአንበሳው ነው። ለጥቅም ያደሩና ከመንግስት ጋር ያበሩ የሀይማኖት አባቶች ደግሞ ሁለተኛ ተጠያቂዎች ናቸው።
አሁን ላይ ለገባንበት ቀውስ መፍትሔ ሲያቀርቡ የሚደመጡ ተው ሲሉ የሚሰሙ .. ብሎም በህዝቡ የሚፈሩ የሀይማኖት አባቶች የሉንም ማለት ይቻላል። ቢኖሩም ድምፃቸው አይሰማም።
እንደ ሀገር በፖለቲካ ሽኩቻዎች ምክንያት ኢኮኖሚያችንን ወይም ሰላማችንን ብቻ አይደለም ያጣነው... ማህበራዊ ስነልቦናዊ ሀይማኖታዊ እሴቶቻችንም ጭምር ነው የናድነው። ባለቀ ሰአት ሰበብ መደርደር ማላከክ ምንም አይፈይድም።
የሀይማኖት አባቶች ትግራይ ላይ በተፈጠረው ጦርነት ፣ ቀውስ ፤ ውድመት ፣ ግድያ ፣ የዘር ጭፍጨፋ ፣ መፈናቀል ፣ ረሃብ ፣ አስገድዶ መድፈር .. ወዘተረፈ ከፖለቲከኞች እኩል አስተዋጽኦ አላቸው። ባላቸው ተፅዕኖ ልክም ለተፈፀመው በደል ትልቅ ሚና አድርገዋል።
ይህንን ታሪክ ፈፅሞ አይረሳውም !!
Please wait, video is loading...
Finfinne Times