@seblet148
1 hour ago
አባ ህፃን እንደስምህ ህፃን, በዛ በመከራ ግዜ የትግራይ አባቶችን እየጠቆምክ ማስያዝህ እንዳይበቃ ዛሬ ደሞ አፍ አለኝ ብለህ ታወራለህ? ኧረ ያንተስ የተለየ ነዉ ......እግዚያብሄር ፍርድ ይሰጣል☝
ወንድም አሠግድ፤ ሰላም የስራ ሳምንት እንዲኖንልህ ምኞቴ ነው። ስለ የትግራይ ዳያስፖራ ያለህ ምልከታ በጣም ከreality የራቀ ይመስለኛል። እንደሚመስለኝ ከሆነ፤ ባለፉት 3 የጦርነት ዓመታት የሆነው በደምብ ካለመንገንዘብ የሚነሳ ይመስለኛል። ጦርነቱ ከአንድ ፓርቲ ጋር የተደረገ የዜግነት ፖለቲካ (አሃዳዊ ስርዓት ተብሎ ይነበብልኝ) ለመመለስ የተደረገ ግጭት ኣድርገህ እንደምትመለከተው ይመስለኛል። ለዛም ይመስለኛል ሌላ ሰው ዳግም ቢሞክረውም የምትደግፈው።Assegid S. wrote: ↑03 Aug 2023, 11:59ሰላም ወንድሜ Sarcasm; ምርጫው ላይ ለመሳተፍ በእድሜዬ ብቁ ብሆንም በኃይማኖቴ 'ሩቅ' ነኝና ... ራቅ ብዬ ራቅ ላሉት የትግራይ ዲያስፖራ ትንሽ እንድል ፍቀድልኝ![]()
የትግራይን ህዝብ ከኣማራው ጋር አስተሳስራ ያለች ኣንዲት ክር ብትኖር ኃይማኖት ነበረች። ይህቺን ኣንዲት ክር ... ዲያስፖራ ለሆኑ የትግራይ ተወላጆች እና ለውጭ መንግስታት በቅጥረኝነት ለሚያገለግሉ ፖለቲከኞች ፍላጎት ሲባል መዞ ማውጣት የሚያመጣው ጣጣ ቀላል አይሆንም።
የግለሰብንም ሆነ የማህበረሰብን ደህንነት ለማስጠበቅ ሚና የሚኖራቸው የሕግ አስከባሪ አካላትና ተቋማት ፈፅሞ የሉም ወይንም እጅግ ደካማ ናቸው በሚባልባት በዛሬዋ ኢትዮጵያ፥ ለማህበረሰቡ ደህንነት ዋስትና እየሰጠ ያለው ፈርሃ-እግዚአብሔር ወይንም በሰዎች መካከል በጋራ ለሚመለከው መለኮታዊ ኃይል ያለ ፍራቻ (ክብር) ነው። ለዛም ነው ኣንዳንዴ ሰዎች ‘ሰው ባያየኝ … እግዚአብሔር ያየኛል’ በሚል አስተሳሰብ በስውር እንኳ ሊከውኑት ካሰቡት መልካም ያልሆነ ተግባር የሚታቀቡት። ኣብዛኛው የትግራይ ተወላጅ ከክልሉ ውጪ ተበትኖ እያለ፣ የዚህን religious value ምሰሶ መቦርቦር ጉዳቱ ለማን እና እስከምን ድረስ እንደሆነ ግልፅ ነው።
በእርግጥ ከሰቆቃው ሥፍራ በውቅያኖስ ርቅት ያሉ ዲያስፖራዎችና ፖለቲከኞች ለሚጠፋው ህይወትና ንብረት ግድ እንደሌላቸው በሚገባ እረዳለሁ። ዲያስፖራዋ … ወልቃይት ለባለቤቱ ለኣማራው ተመልሳ፥ አንገትዋ ላይ ያንጠለጠለችው የትግራይ ክልል የወርቅ ሐብል ቀልጦ ቅርፁ ከሚቀየር፣ ዳግም ኣንድ ሚልዮን የደሃ ልጅ እርጥብ ስጋ በድሮን እሳት እንደ ጧፍ ነዶ … ከስሎ ማየትን ትመርጣለች። አሳዛኝ ትውልድ! የሰው ልጅ ቤተሰቡን ይጦራል እንጂ እንዴት ከሩቅ ሆኖ በጦር ይወጋል-ያስወጋል ?
ሰላም Brother Sarcasm; ለሰጠኸኝ መልስ ብዙ አመስግኛለሁ። ይሁንና ግን ባለፉት ሦስት ዓመታት ምን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን ለምን እንደሆነም ጭምር በሚገባ እገነዘባለሁ … የህወሃትን ክልላዊ ምርጫ የማድረግ ጥድፊያንም ጨምሮ ማለቴ ነውsarcasm wrote: ↑03 Aug 2023, 20:57ወንድም አሠግድ፤ ሰላም የስራ ሳምንት እንዲኖንልህ ምኞቴ ነው። ስለ የትግራይ ዳያስፖራ ያለህ ምልከታ በጣም ከreality የራቀ ይመስለኛል። እንደሚመስለኝ ከሆነ፤ ባለፉት 3 የጦርነት ዓመታት የሆነው በደምብ ካለመንገንዘብ የሚነሳ ይመስለኛል። ጦርነቱ ከአንድ ፓርቲ ጋር የተደረገ የዜግነት ፖለቲካ (አሃዳዊ ስርዓት ተብሎ ይነበብልኝ) ለመመለስ የተደረገ ግጭት ኣድርገህ እንደምትመለከተው ይመስለኛል። ለዛም ይመስለኛል ሌላ ሰው ዳግም ቢሞክረውም የምትደግፈው።
የጦርነቱ ጥልቅ ትርጉም ግን ሁሉም ተፋላሚዎችና ሕዝቦች ልብ ያሉት ይመስለኛል። የአማራ ሕዝብ መሪ ይህ ሕዝብ የእንትና የእንትና ጠላት ነው .... ይህ ሕዝብ እስካልጠፋ ድረስ ...... ሲል የጦነቱ እውነተኛ ጥልቀትና ስፋት ለመላ ዓለም ግልጽ እያደረገ ነበር። ጦርነቱ የmillennia ቃልኪዳን እያፈረሰ እንደነበር ያልገባው በጣም ጥቂት እንደነበር ይመስለኛል። ኣሁን አማራ ክልል ያለው ሁኔታም የጦርነቱ ጥልቀት የገባቸው ሰዎች ግብግብ ይመስለኛል።
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም (ጦርነቱ የሃይማኖት ጦርነት ይመስል) እንደ አንድ የጦርነቱ መሪ ተዋናይ (በሞራል በገንዘብ እና ጦርነቱ እስከ ታችኛው የሕብረተሰብ እርከን ደገፍ እንዲኖረው በማድረ)፤ የጦርነቱ ኣይቀሬ ጥልቅ consequence መቅመስዋ ሁሉም የጦርነቱ ጥልቀት የገባው ሰው የጠበቀው ነገር ነው። ፓትርያሪኩ በትናንቱ ሲኖዶሱ ለያፍነው በሞከረው ንግግራቸው "ፈጥነን ወደ ውግዘት የምንገባ ከሆነ ግን ለቤተክርስቲያን መለያየት ትልቅ የመሰረት ድንጋይ እንደማስቀመጥ ይቆጠራል" ሲሉ የጦርነቱ ጥልቀት የሚያሳይ አይመስልህም? ብየ ልጠይቅህ ኣሰብኩና፤ "ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው" ብለህ ትመልሰኛለህ ብየ ተውኩት።
To think that የኢትዮጵያ ህዝብ ጭውነትና በፈርሃ-እግዚአብሔር የተሞላ እለታዊ ኑሮ የትግራይ አባቶች በነአቡነ ጴጥሮስ ሲኖዶስ ስር ስለሆኑ ነው፤ ከነአቡነ ጴጥሮስ ሲኖዶስ ስር ሲወጡ ጭውነቱና ፈርሃ-እግዚአብሔሩ ይጠፋል ብሎ ማሰቡ በጣም preposterous ነው። እንዲያውም እውነታው ጭውነቱና ፈርሃ-እግዚአብሔሩ ያለው despite የነአቡነ ጴጥሮስ ሲኖዶስ ነው።
በኔ ኣመለካከት፤ ትልቁ የመሠረት ድንጋይ የተጣለው በሹመቱና በውግዘቱና ሳይሆን፤ ሲኖዶሱ በተግባር ጦርነቱ ደግፎ ሞራላዊ approval ለመስጠት (ጦርነቱ በኦርቶዶክሳውያንና በሌላ ሃይማኖት የተደረገ የሃይማኖት ጦርነት ይመስል) በየአዳራሹና የጦር ግምባሩ ያለ ዕረፍት ላይና ታች ሲሉ፤ በትግራይና በሲኖዶሱ መካከል ሁሉም ነገር አከተመለት። ጣምራ ጦሩ መቀሌን ከተቆጣጠረ ከሁለት ወር በኋላ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ኣመራሮች ከነ አቡነ ጴጥሮስ ወደ መቀሌ ሄደው ነበር። ሁሉም የትግራይ አባቶች ስብሰብው boycott አደረጉት። የመቐለዋ እመቤት የሃይማኖት አባቶችንና ሽማግሌዎችን ያፋጠጠችበት ቪድዮ የሕዝቡና የቤተ ክህነቱን ስሜት (ያኔም አሁንም) በደምብ ነው የሚያሳየው። መልካም እሁድ ይሁንልህ ወንድም አሠግድ።Assegid S. wrote: ↑04 Aug 2023, 12:06
እስቲ ኣንተ ልትጠይቀኝ ባሰብከው 'ጠቋሚ' ጥያቄ ላይ ተንተርሼ እኔም ልጠይቅና ... ለሁለቱ ቤተክርስቲያን መለያየት ትልቅም ይሁን ትንሽ የመሠረት ድንጋይ የሚሆነው የኣዲስ አበባው ሲኖዶስ ህገ-ወጥ አካሄድ ውግዘት ነው ወይንስ የትግራዩ ሲኖዶስ ዘር-ገብ ድርጊትና ግብረገብ?
https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=247434
ሰላም Brother Sarcasm; ስለ ቪዲዮው በጣም አመሰግናለሁ። የመቀሌዋን እመቤት በድምፅ ብቻ ሳይሆን በምስልም ጭምር ተመልክተናት፥ የትና እንዴት እንደተቀረፅ መረጃው ቢኖረን መልካም ነበር። You know what … ባለፉት ዓመታት ካለኝ ተሞክሮ የተነሳ ነገሮችን at face value ለመቀበልና ለማመን በጣም ጠርጣራ ሆኛለሁ። "ዕድሜ ለህወሃት" ልል ነበር ግን ዕድሜ ቢሰጣቸውስ ብዬ ተውኩትsarcasm wrote: ↑05 Aug 2023, 19:48በኔ ኣመለካከት፤ ትልቁ የመሠረት ድንጋይ የተጣለው በሹመቱና በውግዘቱና ሳይሆን፤ ሲኖዶሱ በተግባር ጦርነቱ ደግፎ ሞራላዊ approval ለመስጠት (ጦርነቱ በኦርቶዶክሳውያንና በሌላ ሃይማኖት የተደረገ የሃይማኖት ጦርነት ይመስል) በየአዳራሹና የጦር ግምባሩ ያለ ዕረፍት ላይና ታች ሲሉ፤ በትግራይና በሲኖዶሱ መካከል ሁሉም ነገር አከተመለት። ጣምራ ጦሩ መቀሌን ከተቆጣጠረ ከሁለት ወር በኋላ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ኣመራሮች ከነ አቡነ ጴጥሮስ ወደ መቀሌ ሄደው ነበር። ሁሉም የትግራይ አባቶች ስብሰብው boycott አደረጉት። የመቐለዋ እመቤት የሃይማኖት አባቶችንና ሽማግሌዎችን ያፋጠጠችበት ቪድዮ የሕዝቡና የቤተ ክህነቱን ስሜት (ያኔም አሁንም) በደምብ ነው የሚያሳየው። መልካም እሁድ ይሁንልህ ወንድም አሠግድ።
Re: የመቐለዋ እመቤት የሃይማኖት አባቶችንና ሽማግሌዎችን ያፋጠጠችበት ቪድዮ (በአማርኛ)
"ኦርቶዶክስ የተበተነችው በአማራ ብሔርተኛ ፖአቲከኛ ነው። ኦርቶዶክስን ምሽግ ካደርግኩ፤ ፖለቲካየ አሸናፊ ይሆናል ብሎ . . . . "sarcasm wrote: ↑05 Aug 2023, 19:48በኔ ኣመለካከት፤ ትልቁ የመሠረት ድንጋይ የተጣለው በሹመቱና በውግዘቱና ሳይሆን፤ ሲኖዶሱ በተግባር ጦርነቱ ደግፎ ሞራላዊ approval ለመስጠት (ጦርነቱ በኦርቶዶክሳውያንና በሌላ ሃይማኖት የተደረገ የሃይማኖት ጦርነት ይመስል) በየአዳራሹና የጦር ግምባሩ ያለ ዕረፍት ላይና ታች ሲሉ፤ በትግራይና በሲኖዶሱ መካከል ሁሉም ነገር አከተመለት። ጣምራ ጦሩ መቀሌን ከተቆጣጠረ ከሁለት ወር በኋላ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ኣመራሮች ከነ አቡነ ጴጥሮስ ወደ መቀሌ ሄደው ነበር። ሁሉም የትግራይ አባቶች ስብሰብው boycott አደረጉት። የመቐለዋ እመቤት የሃይማኖት አባቶችንና ሽማግሌዎችን ያፋጠጠችበት ቪድዮ የሕዝቡና የቤተ ክህነቱን ስሜት (ያኔም አሁንም) በደምብ ነው የሚያሳየው። መልካም እሁድ ይሁንልህ ወንድም አሠግድ።Assegid S. wrote: ↑04 Aug 2023, 12:06
እስቲ ኣንተ ልትጠይቀኝ ባሰብከው 'ጠቋሚ' ጥያቄ ላይ ተንተርሼ እኔም ልጠይቅና ... ለሁለቱ ቤተክርስቲያን መለያየት ትልቅም ይሁን ትንሽ የመሠረት ድንጋይ የሚሆነው የኣዲስ አበባው ሲኖዶስ ህገ-ወጥ አካሄድ ውግዘት ነው ወይንስ የትግራዩ ሲኖዶስ ዘር-ገብ ድርጊትና ግብረገብ?