የአቢይ አህመድ እና ጉራጌዎች የ4 ኪሎ ስብሰባ ግሩም ዘገባ!
አቢይ አህመድ ወደደም ጠላም ጉራጌ እራሱን በራሱ ያስተዳድራል !
Last edited by Horus on 24 Mar 2023, 14:30, edited 1 time in total.
Re: ጉራጌ ወደደም ጠላም ክልልነት አልሰጠውም አቢይ አህመድ በሃሙሱ ስብሰባ! እና የብርሃኑ ነጋ ቅሌት! መሰማት ያለበት ዘገባ !
አብይ አህመድ እና ብርሃኑ ነጋ ጉራጌ ክልል እንዳይሆን ከፈለጉ፤ መጀመሪያ ኦሮሞ ክልል መሆን የለበትም፤ሌሎችም እንደ አሸን የተፈጠሩት እንድሁ። አብይ አህመድ ኦሮምያ የሚባል አገር እና ኦሮሚያዊ የሚባል ዜጋ እፈጥራለሁ እያለ እየፎከረ ፤ ጉራጌም ኦሮሚያዊ የሚል ፓስፓርት እንደሸከም ተፈልጎ ነው?
-
Union
Re: ጉራጌ ወደደም ጠላም ክልልነት አልሰጠውም አቢይ አህመድ በሃሙሱ ስብሰባ! እና የብርሃኑ ነጋ ቅሌት! መሰማት ያለበት ዘገባ !
ጉራጌ ክልል ከሆነ ለአቀድሉት ስልቀጣ አያመችም። ብርሀኑ ደግሞ ለግል ጥቅሙ ሲታገል የነበረ ሰው መሆኑ በደንብ ተጋለጠ። በዚህ ሰአት ቢያንስ ለጉራጌ ህዝብ እንኳን መቆም ካልቻለ ምን አባቱ ነው የሚሰራው
Re: የአቢይ አህመድ እና ጉራጌዎች የ4 ኪሎ ስብሰባ ግሩም ዘገባ!
ጨንቋቸውኮ ነው! ጉራጌ ያነሳው ጥያቄ ጉሮሮ ውስጥ የሚቀረቀር ነው ። ባጭሩ ያልነው ይህን የጎሳ ሕገ እንግስት ወይ ይቀየር ወይ ይከበር ነው ያልነው። አቢይና የቀሩት ብሄርተኛ አዳሪዎች የመለስ ሕገ እንግስት እንዲነካ አይፈልጉም ። ያቢይ አህመድ መጋለቢያ ፈረሱ ስለሆነ ። እሺ በህጉ መሰረት እኛም ክልል እንሁን ስንላቸው አይ አገር ማፍረስ ስለሆነ አትችሉም ይሉናል ። አገር አይፈርስም፣ የፈረሰው የደቡብ ኢትዮጵያ ውጥንቅጥ ነው ።
የደቡብ ደባደቦ ሁለተኛ አይመለስ ። ደቡብ ፈርሷል። ከዚህ በኋላ አቢይም ሆነ ሌላ ብርሃኑ ነጋም ቢሆን ማድረግ የሚችሉትና ያለባቸው ሕዝቡ በጠየቀው መንገድ ፌፈረንደም መስጠትና የቱ ሕዝብ ከየተኛው አብሮ ክፍለ ሃገር ማዋሃድ እንደ ሚፈልግ ጠይቆ የፌዴራል ክፍለ ሃገሮችን መቅረጽ ብቻ ነው ።
የብልጽ ኛ የዲክታተር ካርታ ማንም በንጨት አይነካውም! አቢይ ይህን በግልጽ ተነግሮታል ! እኔ ብቻ አውቅልሃለሁን እርሱት !!!