በጦርነቱ የወደሙ አካባቢዎች መልሶ ግንባታ ተጠያቂነትን እና ዓለም አቀፍ መርሕን በጠበቀ አግባብ ይከናወናል”፦ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ
*********************
በሰሜኑ ጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን የመልሶ ግንባታ እና ማቋቋም ሥራ ተጠያቂነትንና ዓለም አቀፍ መርሕን በጠበቀ አግባብ የሚከናወን መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ተናገሩ።
በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት በተለይም በአማራና አፋር ክልሎች በርካታ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱ ይታወቃል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ፤ በጦርነቱ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት መንግሥት የአምስት ዓመታት ዕቅድ ይዞ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። Sarcasm's comment: Does that mean for the next 5 years, Ethiopia will working to reach where it was 7 years ago?
በልማት ድርጅቶች ከሚከናወነው የመልሶ ግንባታ በተጨማሪ መንግሥት የራሱን በጀት መድቦ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በ2015 በጀት ዓመት ብቻ ለመልሶ ግንባታው በመንግሥት በኩል 15 ቢሊየን ብር ስለመመደቡም ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል።
የመልሶ ግንባታው በተለይም በትምህርት እና የጤና ተቋማት ላይ ቀደም ብሎ መጀመሩን አስታውሰው በተያዘው በጀት ዓመት የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማስቀጠል እና የወደሙትን መልሶ መገንባት መሆኑን አብራርተዋል።
በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚውን መዛባት የማስተካከልና የዕዳ ክፍያን ለማቃለል ሲባል በበጀት ዓመቱ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የመጀመር እቅድ የለም ብለዋል።
ለመልሶ ግንባታው ከዓለም ባንክ የተገኘው 300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከደረሰው ውድመት አኳያ በቂ እንዳልሆነ ገልጸው የልማት አጋሮችን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ይሻል ብለዋል።
ከባንኩ የተገኘው ድጋፍ በአማራና አፋር ክልሎች በመንግሥት በኩል ገቢራዊ የሚደረግ ሲሆን በትግራይ ክልል ግን በሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ይከናወናል ነው ያሉት።
መልሶ ማቋቋሙን የሚያከናውነው ሶስተኛ ወገን ለዓለም አቀፍ መርሕና ተጠያቂነትን ታሳቢ ባደረገ አግባብ ተፈጻሚ እንደሚሆን ስምምነት መደረጉንም አስረድተዋል።
የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች በታለመላቸው መልኩ እንዲፈጸሙ እንደማንኛውም የልማት ፕሮግራም ተጠያቂነት ባለው አግባብ እንደሚፈፀም በገንዘብ ሚኒስቴር፣ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማትን ያካተተ አደረጃጀት መዋቀሩንም ተናግረዋል።
የገንዘብ ፍሰቱን የሚመለከት በገንዘብ ሚኒስቴር ስር ጽህፈት ቤት መቋቋሙንና የፕሮግራም አፈጻጸሙም በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እየተገመገመ እንደሚፈጸም ነው ያብራሩት።
Please wait, video is loading...