Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

“. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”

Post by Meleket » 10 Mar 2021, 05:09

“. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ” :mrgreen:

“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ ዲጂታሎቿንም ያስመረረ ኤርትራዉያንን በጀግንነት ያንቀባረረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ዘንድሮም በኤርትራዊ ልበሙሉነት ይተረካል!!! :lol:
Meleket wrote:
07 Mar 2019, 02:14
የሚከተለው ታሪክ “ዝኽርታት ሓመድ ድበ ናደው” ማለትም “የናደው ቀብር ሲዘከር” በሚል ርእስ “ሕድሪ’” የሚባለው አሳታሚ ድርጅት ካዘጋጀው መጸሐፍ የተጨለፈ ታሪክ ነው። ታሪኩ የኤርትራ ህዝብና የነጻነት ታጋይ ልጆቹ ታሪክ ነው። ታሪክ እንዳይሰረቅ ከትውልድ ወደ ትውልድም ይሸጋገር ዘንድ በመጸሐፉ መጀመሪያ ክፍል ያለውን ይዘት እንዳለ ኣቅርበነዋል። ይህን ብርቅ ታሪክ የፈጸሙትም ኤርትራዉያን እንደመሆናቸው መጠን፣ ለታሪክ ተመራማሪዎች “የኤርትራዉያንን እይታ” ይገነዘቡ ዘንድ ይህን ‘ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ አኹሪና ብርቕ ታሪክ እዚህ በተወላገደው አማርኛችን እዚህ አቅርበነዋል። መልካም ንባብ!!! በዚያን ግዜ ሕወሓት የኤርትራ ነጻነት ታጋዮችን በማንቋሸሽና በማጥላላት ዘመቻ ተጥዳ ፖለቲካዊ መጨማለቕ ታሳይ ነበር፣ ኤርትራዉያን ታጋዮች ደግሞ ጥበብ በተሞላበት ቅልጣፌን በተካነ ሁኔታ የጥቃት ፕላናቸውን እንዳገባደዱም፣ እንደ ደርጉ ሁሉ ሕወሓትም አራ፣ አፍራና ተደናብራ ነበር ምክንያቱም ይሆናል ብላ ያልጠበቀችው ተአምር ነበርና! ከድሉ ማግስት ግን ወያኔዎች ጅራታቸውን እየቆሎ “እንኳን ደስ አላችሁ! ጀግኖች ወዘተ” የሚል መግለጫ ለማውጣት ተሽቀዳድመው ነበር። ከዚህ ታሪክ እስከ ዛሬ ድረስም ሕወሓት የተማረች አትመስልም፣ በኤርትራ ህዝብና በትግሉ ታዝላ ዝንተዕለት ለመኖር ትሻለች፣ የኤርትራ ህዝብ ግን “በቃ” ብሏታል፣ አሁንም ያለምንም ማንገራገር ከኤርትራ ልዑላዊ ግዛት ብትወጣና ለህግ የበላይነት ብትገዛ አይበጃትም ትላላችሁ?

የናደው እዝ ቀብር ሲዘከር

መግቢያ

“. . . ህዝባዊ ግንባር፡ የናቅፋ ግንባር ድሉን የሚመዝነው፡ በረዢሙ የኤርትራ ህዝብ ትጥቅ ትግል ተጋድሎና በተለይም ባለፉት አስር ኣመታት ውስጥ በታየው ወታደራዊ ክስተቶች ኣዃያ ነው። የሰነዘርነው ጥቃት ኃያል፣ ቅጽበታዊና ትልቅ ጠባሳ ጠላት ላይ እንዳሳረፈ ኣይካድም። ኢትዮጵያዉያን ኤርትራን በኃይል ከያዙበት ግዜ ወዲህ፡ ለመጀመሪያ ግዜ በአእምሯቸው ውስጥ፡ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ ኤርትራን ማስተዳደሯን (‘መግዛቷን’) ትቀጥላለች ወይስ ኣትቀጥልም?” የሚል ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽን የሚሻና ፋታ የማይሰጥ ብርቱ ጉዳይ እንዲሆን ያስደረገ ወታደራዊ ጥቃትን ፈጽመን ነው ድልን የተጎናጸፍነው። . . . ” ታጋይ ኢሳይያስ አፈወርቅ የህ.ግ.ሓ.ኤ. ዋና ጸሃፊ፡ በሳግም መጽሔት ቁ.14)

በመጋቢት ወር 1988 ናቅፋ ግንባር ላይ መሽጎ የነበረውንና “ናደው እዝ” ተብሎ የሚጠራዉን ግዙፍ የኢትዮጵያ ሰራዊት ክፍል፡ በፍጹም ከበባ ውስጥ በማስገባት የተካሄደ ደምሳሽ ቀለበታዊ ጥቃት፡ በወርቃዊ ድሎች ባሸበረቀውና በተመላው የኤርትራ ህዝብ የተጋድሎ ታሪክ ውስጥ እንደ የአዲስ ምዕራፍ በር ከፋች ሊጠቀስ የሚችል፣ ትልቅ ስትራቴጂያዊ ጥቅም የነበረው ፍጻሜ ነው።

ናደው እዝን የደመሰሰው ወታደራዊ ድላችን በነጻነት ትግላችን ውስጥ ጎልቶ የሚታይ ይሁን እንጂ፡ የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ሰራዊት፡ ወደዚህ ግዙፍ ስትራቴጂያዊ የማጥቃት እርምጃ ለመሸጋገር፡ አስቀድሞ ያሳለፋቸው ፋታ የማይሰጡ ተደጋጋሚ ውጊያዎች፡ እጅግ ረዢም ትዕግስትና ብርቱ ጽናት የሚጠይቁ ነበሩ። ስለሆነም የናደው እዝ መደምሰስ፡ አስቀድሞ ለአስር አመታት በቋሚ ሰንሰለታዊ ምሽጎች ናቕፋ ሰሜናዊ ምስራቕ ሳሕልና ባርካ ላይ የተካሄዱት ብርቱ ውጊያዎች ፍሬ ወይ ምርት ነው። በተጨማሪም በጠላት ወረዳ ውስጥ በደፈጣ ውጊያ በፈንጅ ቀበራና በመሳሰሉት የተቀነባበሩ እረፍት የማይሰጡ ውጊያዎች ታግዞ፡ የኢትዮጵያ ሰራዊትና አጋሮቹ መቆሚያና መቀመጫ እስኪያጡ ድረስ የተካሄዱ ተደጋጋሚ ውጊያዎች ፍሬ ነው።

አጭር ቅድመ ታሪክ

በ1977-1978 አምስት ተከበው ከቀሩ ከተሞች በስተቀር፡ መላው ኤርትራ በኤርትራዉያን ታጋዮች ቁጥጥር ስር ሆኖ ነበር። የደርግ ስርዓት ኤርትራዉያን ታጋዮች በሚሰነዝሩበት ጥቃት ብቻ ሳይሆን፡ ከሶማሊያ ጋር ያካሂደው በነበረ ውጊያ ወተሃደራዊ ኣቅሙ እጅግ ተዳክሞ ነበር። የኤርትራ ህዝብ ከዛሬ ነገ ነጻነቴን እጎናጸፋለው ይል በነበረበት ወቅት ግን፡ በወታደራዊ የኃይል አሰላለፍ ሚዛን የሚያዛባ መሰረታዊ ለውጥ ያስከተለ የልዕለኃያሏ ሃገር የሶብየት ህብረት እጅ ቀጠናችን ውስጥ ገባ። ደርግም የሶቭየት ህብረትን ግዙፍ ድጋፍ ኣግኝቶ፣ ባጭር ጊዜ 300,000 ዘመናዊ መሳርያ የታጠቀ፡ በጥቁር አፍሪካ ውስጥ እጅግ ብርቱውን ወታደራዊ ኃይል አንጾ፣ ከመቅጽበት ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋገረ።

በ1978 አጋማሽ፡ ደርግ በሶማሊያ ሃይሎች ላይ እጅግ ግዙፍ ጥቃት ከፈተ። በሳምንት ውስጥም የሶማሊያን ጦርነት በድል አገባዶ፡ “የምስራቅ ድል በሰሜን ይደገማል!” በሚል መፈክር ታጅቦ፡ ወደ ሰሜን በማቅናት የኤርትራን ህዝብ ትግል “ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ” ብሎ በሰየመው ጥቃት ለመደምሰስ እጅግ ግዙፍ ወረራን ጀመረ። ጦርነቱ “በጉንዳንና በዝሆን” መካከል እንደሚደረግ ኣይነት ግጥሚያ ነበር። ስለሆነም ህዝባዊ ግንባር አቅሙንና ብቃቱን ገምግሞ ይህን እጅግ ግዙፍ የሆነ ወራሪ ሰራዊት በተራዘመ ውጊያ ለማዳከም፡ ነጻ አውጥቷቸው ከነበሩ ቦታዎች ደረጃ በደረጃ እያፈገፈገ፡ የጠላትን ኃይል በአመቸው ቦታና ግዜ እየገጠመ፡ ስትራቴጂያዊ ማፈግፈግ ለማድረግ ወሰነ። በዚህ መሰረትም፡
በመጀመርያው ወረራ፡ ህ.ግ. ከደቡባዊና ምስራቃዊ ኤርትራ ሲያፈገፍግ
በሁለተኛው ወረራ ከሰሜናዊ ግንባር አፈገፈገ
በሶስተኛው ወረራም፡ ከከረንና አፍዓበት አካባቢ በማፈግፈግ ቋሚ ምሽጉ ይሆን ዘንድ ወደ መረጠው የናቅፋ ተራራዎችና ሰሜናዊ ምስራቅ ሳሕል አቀና። (የህዝባዊ ሰራዊት ስትራቴጅ ቀድሞም ቢሆን እያፈገፈግክ በሚመችህ ቦታ ጠላትን ድባቅ መምታት መሆኑ የሚያውቅ ነው ሚያውቀው።)

የህዝባዊ ግንባር ሰራዊት በተመቸው ስፍራ ሁሉ ብርቱ ተቃውሞ እያደረገ እያጓራ በመጣበት ጠላት ላይ ከባድ ኪሳራን እያከናነበ በየካቲት 1979 ናቅፋ አካባቢ ደረሰ። በናቅፋ መግቢያ በርም በግራና ቀኝ “እምባ ደንደን” በተባለ ተራራ ላይ መሸገ። ይህ ስፍራ የመጨረሻ የመከላከያ መስመር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ በጥናት የመረጠው ቦታ ነበር። ሆኖም የናቅፋ ግንባር ልክ በዚህ ሁኔታና ግዜ ነበር የተመሰረተው። መጀመሪያ ላይ የግንባሩ ስፋት እጅግ ውሱንና ጠባብ ነበር። የጠላት ሰራዊት በተወሰነ ቦታ ጥሶ ወይ በስቶ ለማለፍ የሚያደርጋቸው ተከታታይና ተደጋጋሚ ጥቃቶች ውጤት አልባ ሲሆኑበት ግዜ፡ በቀጣይ ወረራዎቹ ማለትም (በ4ኛ 5ኛና 6ኛ) ወረራዎቹ ወቅት፡ ሆን ብሎ የወገንን ኃይል ሚዛን ለማሳሳትና ለማራራቅ፡ በግንባሩ ሁለት ክንፎች የሰራዊቱን ይዞታ እየለጠጠ ሰፊ ቦታ ለመሸፈን ብርቱ ጥረት አካሄደ። ከናቅፋ ግንባር በተጨማሪም የሰሜናዊ ምስራቅ ሳህል ግንባርና የሓልሓል ግንባርም በተመሳሳይ መልኩ ይዞታቸው እየሰፋ በመሄዱ በመጨረሻ ሶስቱም ግንባሮች እርስ በርስ ተሳስረው ነበር ለማለት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተደረሰ። በዚህም ለአስር ዓመታት ያህል ያለማቋረጥ በተደረገ ብርቱ የምከታ ውጊያ፡ ሁለቱም ተጻራሪ ወገኖች ምሽጋቸውን የማደላደል ስራ በቀጣይነት ይተገብሩ ስለነበር፡ በሁለቱም ወገኖች መካከል በፈንጅ የታጠረ የ667 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው ብርቱ ምሽግ ተፈጥሮ ነበር። (የኤርትራ ህዝብ የሕወሓትን አካሄድና የድንበር ብይንን አፈታት በተመለከተም ተመሳሳይ ስትራቴጂ የተከተለ ይመስላል፡ ከብርቱ የእልህ ምከታ በኋላ ድንበሩን የሚያስከብርበትና ልዑላዊ ግዛቱን በጠቅላላ ያለአንዳች መሸራረፍ የሚያስተዳድርበት መድረክ ላይ ከትናንት ይልቅ ዛሬ ይበልጥ ተቃርቧል ለማለት ይቻላል።)

ከ1978 አጋማሽ እስከ 1988 ለአስር ዓመታት የቀጠለ ብርቱ የመረባረብ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ፡ ያ ልዕለ ኃያል በሆነችው የሶቭየት ህብረት እጅግ ግዙፍ በሆነ ወታደራዊ፣ ገንዘባዊና ቴክኒካዊ ምክር እየተለገሰለት፡ የኤርትራን ህዝብ ትግል ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመደምሰስ የተነሳው ወራሪ የኢትዮጵይ ሰራዊት፡ ከባድ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳቱን ተሸክሞ፡ ከማጥቃት ወደ መከላከል ስትራቴጂውን እንዲቀይር ተገዷል። ውጊያም ያለ እረፍት በመቀጠሉና ስለተራዘመበትም፡ የኢትዮጵያ ሰራዊት መጨረሻ ላይ ተስፋ እየቆረጠ፣ የመዋጋት ወኔው እየጠፋበት ሞራሉ እየላሸቀ ሂዷል።

እጅግ ረቂቅና ውስብስብ የስለላ ጥናት በማድረግ፡ የጠላት ሁኔታ፡ ከዕለት ወደ ዕለት በትክክል ይገመግም የነበረው የህዝባዊ ግንባር አመራርም፡ በ1987 የጠላትን ቀልብ ከቅድመ ግንባር ወደ መሃል ወይም የጠላት ይዞታ ውስጥ የሳበ፡ ተከታታይ የደፈጣና አጥቅቶ የመሰወር ተልዕኾዎችን ሆን ብሎ ተያያዘው። በግንባር ላይ የነበረውን የጠላት ሁኔታ ለመፈተሽም በታሕሳስ ወር 1987 በናቅፋ ግንባር መካከለኛ መስመር ላይ፡ በተወሰኑ አካባቢዎች መጠኑ አንስተኛ የሆነን ጥቃት በማካሄድ፡ ጠላትን በመግፋት ናደው እዝን ለመደምሰስ ለቀጣዩ ብርቱ የማጥቃት እርምጃ መረማመጃ የሚሆነውን ስትራቴጂያዊ ቦታዎችን በቁጥጥሩ ስር አዋለ።

በነዚህ ብርቱ ጥቃቶች የደነገጠው የደርግ ስርዓት መሪ መንግስቱ ሃይለማርያምም፡ በየካቲት 1988 ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ በመምጣት፡ መላ ኤርትራ ውስጥ የነበረውን የሁለተኛ አብዮታዊ ሰራዊት ብሎ የሚጠራዉን ሰራዊት አመራሮች ጋር ስብሰባ ካካሄደ በኋላ፡ ናደው እዝ እንዲዳከም ምክንያት የሆኑት እንዲሁም በወርሓ ታሕሳስ ግንባር ናቅፋ ላይ ላጋጠመው ሽንፈት ዋንኛ ተጠያቂ ነው ያለውን፣ የግንባሩን ኣዛዥ ብሪጋዴር ጀነራል ታሪኩ ያይኔ መሆኑን በመግለጽ፡ ከሰራዊት ፊት እንዲረሸን አደረገ። በደጋማው የኤርትራ ክፍል በደፈጣ ውጊያ በደርግ ሰራዊት ላይ ለደረሰው ኪሳራም የመክት እዝን ሃላፊ ብሪጋዴር ጀነራል ከበደ ጋሼን ተጠያቂ መሆኑን ኋላፊነት በማሸከም፡ ከሰራዊቱ ፊት ማእረጉን በመግፈፍ ያለ ጥሮታ እንዲባረር አደረገ። የሁለተኛው አብዮታዊ ሰራዊት ማለትም የ‘ሁ.አ.ሰ.’ አዛዥ የነበሩት ሜጀር ረጋሳ ጂማንና ምክትሉን ሸዋረጋ ቢሆነኝን ከሌሎች ከ20 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ የሰራዊት አዛዦችንም፡ ከኤርትራ ወደ የኢትዮጵያ ሌላ ክፍል ቀየራቸው።

በዚያን ወቅት መንግስቱ ሃይለማርያም የወሰደው የተስፋ መቁረጥ እርምጃ የሰራዊቱን ድክመት እንደገና አባብሶት ነበር። የደርግ ስርዓት፡ ከዚህ ሌላ፡ በኤርትራ ደጋማ ክፍሎች በተከታታይ ይደርስበት የነበረውን ብርቱ የደፈጣ ውጊያ ሊቋቋም ባለመቻሉ፡ ይህን ውስጣዊ መስመሩን ወይም ውስጣዊ ይዞታውን ለማደላደል ከዋና የግንባር ክፍሎች ቀስ በቀስ ሃይሉን እያመጣ በውስጣዊ ይዞታው እንዲያሰፍር ይገደድ ነበር።
ይህን ወታደራዊ ሁኔታ በትኩረት ይከታተል የነበረው የህዝባዊ ግንባር አመራርም፡ ‘ናደው እዝ’ን ለመደምሰስ አስቀድሞ ያካሂደው የነበረውን ጥናትና ይመረምረው የነበረን የማጥቃት ውጥን ተግባር ላይ የሚያውልበት የዜሮ ሰዓት እንደተቃረበ ገመገመ። የናደው እዝን የመደምሰስ ተልእኮ ከመከናወኑ በፊት ማለትም ከየካቲት 25-28 1988 የተካሄደው ሁለተኛው የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባም ይህን የሚያመላክት አንድምታ ነበረው።

“ማእከላዊው ኮሚቴ . . . . ወታደራዊ ጥቃቶችን ይበልጡኑ ማበረታታትና ይዞታውንም ማስፋት የሚያስችል፡ ጠላትም ዓቅሙን እንዲያሻሽል ፋታ የማይሰጥ ወታደራዊ የስራ መደብንና ፕላንን አዘጋጅቷል።” ይላል ያኔ የወጣው የአቋም መግለጫ።

ይህን ዓላማ ለማሳካት የተመደበው የመጀመሪያ ውጥን፡ ናደው እዝን በመክበብ መደምሰስ ነበር። የህዝባዊ ግንባር አመራር ክፍል ይህን ዓይነት ትልቅና ደፋር እርምጃን ለመውሰድ የወሰነው፡ የጠላትን ኃያልና ደካማ ጎን በትኩረት የገመገመ ረቂቅ የስለላ መረጃዎችን ካጠናና ከመረመረ በኋላ፡ እንዲሁም በደጋማው የጠላት ወረዳ ውስጥ ባካሄደው ተደጋጋሚ የደፈጣ ውጊያ ጠላትን ለማታለልና የጠላትን የትኩረት አቅጣጫ ለማዛባት በመቻሉ ነው።

ከዚህ ትልቅ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ሁለት ወር በፊት፡ የናደው እዝ ኣዛዥ ብሪጋዴር ጀነራል ታሪኩ ያይኔ፡ ለሁለተኛው አብዮታዊ ሰራዊት (ሁ.አ.ሰ.) ኣዛዥ ለጀነራል ረጋሳ ጂማ በላከው ደብዳቤ፡ ህዝባዊ ግንባር በናቅፋ ግንባር ላይ ብርቱ የስለላ ጥናት በማካሄድ ላይ መሆኑን ይህም ብርቱ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነና፡ ‘መክት እዝ’ን ለማገዝ ከግንባር ወደ ደጋማው ኤርትራ ውስጣዊ ቀጠናዎች የተሰማሩት ወይም እንዲሄዱ የተደረጉት 15ኛና 22ኛ ክፍለጦሮች ባስቸኳይ እንዲመለሱለት ጥያቄውን አቅርቦ ነበር። ይሁን እንጂ የሁ.አ.ሰ. አዛዥ የሰጠው መልስ፡ “ባለን መረጃና ግምገማ መሰረት፡ በቅርቡ ሻዕብያ ብርቱና ሰፊ ጥቃት ይፈጽማል ብለን አናምንም። ስለሆነም እነዚያ ሁለት ክፍለጦሮች ለግዜው እዚሁ በደጋማው ክፍል ውስጥ ያለንን ስጋት ለማስወገድ እዚሁ በውስጥ ቀጠና እየሰሩ ይቆያሉ። ለማንኛውም ግን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።” የሚል ነበር።

የሁ.አ.ሰ. አዛዦች “ሻዕብያ በናቅፋ ግንባር የመከላከያ ምሽጉን በማደላደል ላይ እንጂ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል አንዳችም ፍንጭ አይታይበትም” የሚል ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ ያደናገራችው፡
አንዴም ህዝባዊ ግንባር ጠላትን ለማደናገርና ለማታለል፡ ከስድስት በላይ ብርጌዶችን በጠላት የውስጥ ቀጠና ማለትም ብደጋው ክፍል አሰማርቶ የደፈጣ ውጊያን በቀጣይ ይፈጽም ስለነበረ አሊያም በታሕሳስ 1987 በናቅፋ ግንባር በተካሄደው መጠኑ አንስተኛ በሆነው ጥቃት የተቆጣጠራችውን አዳዲስ ስፍራዎች፡ ምሽግ በመቆፈር ይዞታውን ማጠናከር ላይ በቀጣይነት ሲንቀሳቀስ ይታይ ስለነበር ነው።

“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ይቀጥላል!!!

Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: “. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”

Post by Meleket » 15 Mar 2021, 04:53

“. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ” :mrgreen:

“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ ዲጂታሎቿንም ያስመረረ ኤርትራዉያንን በጀግንነት ያንቀባረረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ዘንድሮም በኤርትራዊ ልበሙሉነት ይተረካል!!!
:lol:

Meleket wrote:
11 Mar 2019, 04:56

የተአምራዊው ጥቃት አፈጻጸም

1.1 የሁለቱ ተጻራሪ ወገኖች የሰራዊት ዓቅምና የኃይል አሰላለፍ

አስቀድሞ እንደተገለጠው፡ ናደው እዝን መደምሰስ በህዝባዊ ግንባር አመራሮች ዘንድ ለረዢም ግዜ ሲጠናና ዕቅድ ሲነደፍለት የቆየ ጉዳይ ነው። በዚህም መሰረት፡ ይህን ትልቅ የማጥቃት እርምጃ ለመተግበር ረዢም ግዜ የወሰደ ብርቱ የስለላ ጥናት ውጤትን ምርኩዝ ያደረገ ረቂቅ ግምገማ ተካሂዷል። ጠላትን ለማሞኘትና ለማዘናጋትም በደጋማ ክፍል እንዲሁም በግንባሮች ሁሉ ፋታ የማይሰጡ አደናጋሪ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ይደረጉ ነበር።

ይህ የጥቃት ዕቅድ ትግባሬ የዜሮ ሰዓቱ ሲቃረብም፡ ይህን ሰፊ የጥቃት ንድፍ ተግባር ላይ ለማዋል የተመደቡ የህዝባዊ ግንባር ክፍሎች፡ ማለትም ከእግረኛ የ85ኛ፣ 61ኛ፣ 16ኛ፣ 70ኛና 52ኛ ክፍለጦሮች፣ 74ኛ መካናይዝድ ክፍለጦር እንዲሁም የተለያዩ ድጋፍ ሰጪ የስለያ የመሃንዲስ የሎጂስቲክና የህክምና ወዘተ ክፍሎች ወደየተመደበላቸው ተልእኾና ዒላማ አመሩ። በዚህ የጥቃት ውጥን ትግባሬ ላይ የተሳተፉ የህዝባዊ ግንባር የሰራዊት አባሎች በድምር 10,400 እንደነበሩ የዚያን ግዜ ሪፖርቶች ያመለክታሉ።

ለአስር ያህል ዓመታት በተካሄዱት ከባድ ተከታታይ ውጊያዎች ምክንያት ኤርትራ ውስጥ የነበረው ኢትዮጵያ ሰራዊት ቁጥር አሽቆልቁሏል። በዚህም መሰረት የናደው እዝ ከመደምሰሱ ዋዜማ፡ ደርግ ኤርትራ ውስጥ አሰማርቶት የነበረው የሰራዊት ብዛት እስከ 94,000 ይሆን ነበር።

በደጋማ የኤርትራ ክፍሎች የነበረውመክት እዝ’ 30,000፡

በሓልሓል ግንባር መሽጎ የነበረው መንጥር እዝ’ ከ21,000 በላይ

ባርካ የነበረው በርግድ እዝ’ 14,500፣

ድጋፍ ሰጪ የሁ.አ.ሰ. ክፍሎች ከ7,000 በላይ የሰራዊት ቁጥር ነበሯቸው።

ናደው እዝም ከጠቅላላ ዓቅሙ፡ አስቀድሞ በናቅፋ ግንባር በወረደበት ጥቃት ምክንያት ከ4,700 በላይ አባሎቹ በሞት፣ በመቁሰልና በተለያዩ ምክንያቶች ጎድለውበት ስለነበር፡ የሰራዊቱ አባሎች ወደ 16,500 አሽቆልቁሎ ነበር። ውጊያ በተከፈተበት ሰዓት በሂሊኮፕተር አፍዓበት ላይ ተራግፈው የተደረቡትን የ 15ኛ ክፍለጦር ሁለት ሻለቆች በመደመር፡ በጦርነቱ ወቅት የናደው እዝ ሰብኣዊ ኣቕም 18,000 ያህል ነበር።

በግንባሩ ተሰልፈው የነበሩት የናደው እዝ ክፍሎች

ከእግረኛው ክፍል 21ኛ፣ 19ኛ፣ እና 14ኛ ክፍለጦሮች፣

29ኛ መካናይዝድ ብርጌድ (ዘርኣይ ደረስ)፣

የ157ኛ መድፈኛ ሻለቃና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ተደራቢ ክፍሎች ናቸው።


ናደው እዝ ታጥቆት የነበረው መሳሪያም፦

54 ታንኮች፣

16 የ130ሚ.ሜ. መድፎች፣

36 የ122 ሚ.ሜ. መድፎች፣

12 የ ቢ.ኤም 21 ተወንጫፊ ሮኬቶች፣

55 ከባድ መሳሪያ የተጠመደባቸው መኪኖች
፣ እንዲሁም በርካታ ሞርታሮች፣ መካከኛ መሳሪያዎችና ከ18,000 በላይ ቀላል መሳሪያዎችን ያጠቃልላል።

(የነጻነት ታጋዮች የማጥቃት ዕቅድ ምን ይመስላል በቀጣይ እንሄድበታለን)
ይህን ሁሉ ኃይል ድባቅ የመቱት የነጻነት ታጋዮች ያልተሸራረፈች ኤርትራን ነጻ ለማውጣት ነበር። ጥቃቱን በፈጸሙበት ቅጽበትም ብርቱ የራስ ሕመም በደደቢት በአዲሳአበባና በክሬምሊን ‘ቤተመንግሥቶች’ ውስጥ ተከስቶ እንደነበረ የጊዜው "የሜትሪዮሎጂ" መረጃዎች ጠቁመዋል
:mrgreen:


የናደው እዝ ቀብር ትረካ ይቀጥላል!
:mrgreen:

Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: “. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”

Post by Meleket » 16 Mar 2021, 04:13

“. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ” :mrgreen:

ይህን የናደው እዝን የመደምሰስ ሂደት ስኬታማ በማድረግ ረገድ፡ የመላው የኤርትራ ህዝብና ሠራዊት ድምር የትግል ውጤት ቢሆንም ቅሉ፡ ረሀብና ጥምን ተቋቁመው ለወራት በድብቅ ናደው እዝ የመሸገበትን ስፍራ በሙሉ እንደ እጃቸው መዳፍ ያጠኑት የስለላው ክፍል ተዋናዮች ያንበሳውን ድርሻ እንደያዙ የኤርትራ ህዝብና ታጋይ ልጆቹ ጠንቅቀው የሚያውቁት ታሪካዊ እውነታ ነው።

“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ ዲጂታሎቿንም ያስመረረ ኤርትራዉያንን በጀግንነት ያንቀባረረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ዘንድሮም በኤርትራዊ ልበሙሉነት ይተረካል!!!
:lol:
Meleket wrote:
13 Mar 2019, 03:35

1.2 የጥቃቱ ዕቅድ
ናደው እዝ ይቆጣጠረው የነበረው ቦታ፡ በቅድመ ግንባር እስከ 165 ኪ.ሜ. ርዝማኔ የነበረው ሰንሰለታዊ ምሽግ፡ እንዲሁም ከነዚህ ምሽጎች በስተጀርባም እስከ 70 ኪ.ሜ. ራዲየስ ያካለለ ባጠቃላይ እስከ 12,000 ኪ.ሜ. ስዄር ስፋት የነበረው ቦታ ነው። በዚህ በተጠቀሰው ስፍራ መሽጎ የነበረውን የኢትዮጵያ ማለትም የደርጉን ሰራዊት በሙሉ ፍጹም ከበባ ውስጥ በማስገባት፡ ለመጨፍለቅ የታቀደው ወታደራዊ ንድፍ፡ ስድስት መአዘኖች ወይም የጥቃት አቅጣጫዎች ነበሩት። በዚህ መሰረትም፡ የህዝባዊ ግንባር ሰራዊት በስድስት ምድቦች ተከፍሎ የማጥቃት እርምጃውን ለመጀመር አይምሬ በትሩን አነሳ። አጥቂዎቹ የነጻነት ታጋዮች የተከተሏቸው ስድስት አቅጣጫዎችና ተልእዃቸው የሚከተሉት ነበሩ።

የመጀመሪያው አቅጣጫ
በግራ ክንፍ ማለትም በግንባሩ በስተምስራቅ፡ ‘ቃምጨዋይ’ በተባለው አካባቢ ‘መሸታይ’ ከተባለው ስፍራ በመነሳት ‘ማዕሚደን’ አካልሎ መንጥር ዕዝ እስከ መሸገበት ስፍራ በመዘርጋት የምስራቁን ሜዳማ ክፍሎች ይቆጣጠር የነበረውን የኢትዮጵያን ሰራዊት ማለትም 14ኛ ክፍለጦርንና 29 ሜካናይዝድ ብርጌድን በማጥቃት፡ ‘ማዕሚደን’ በመቆጣጠር በቀጥታ በግራ ክንፍ ወደ አፍዓበት መገስገስ። በዚህ በመጀመሪያው የማጥቃት ኣቅጣጫ የተመደቡት የህዝባዊ ግንባር ሰራዊት አባሎች፡ ከ85ኛው ክፍለጦር ሁለት ብርጌዶች፣ ከ61ኛው ክፍለጦር 87ኛ ብርጌድ ሁለት ሻምበሎች፣ 23ኛው የመካናይዝድ ብርጌድ፣ እንዲሁም አንዳንድ የ63ኛው መካናይዝድ ብርጌድ ክፍሎች ነበሩ።

ሁለተኛው አቅጣጫ
ኢትሓልበብ’ና ‘ክርፍ’ በተባሉት ተራሮች መካከል ባለው ሰርጥ ጨለማን ተነን አድርጎ በመነሳት፡ በጠላት ምሽጎች መካከል ሾልኾ በማለፍ፡ ‘ጉድ’ ወደ ተባለው ወንዝ መቀላቀል፡ ከዚያም ወደ ቀኝ በመታጠፍ ‘ሮሬት’ የተባሉትን ተራሮች መውጣት፣ ከዚያም ከፊሉ ሰራዊት ወደ ሰሜን አቅጣጫ በማቅናት በተራራ ቁጥር 1419 እና 1467 ላይ መሽጎ የነበረውን የኢትዮጵይ ሰራዊት በስተጀርባው ማጥቃት፤ የተቀረው ከፊል ሰራዊት ደግሞ አቅጣጫውን በስተደቡብ ‘ሓራስ ሓርማዝ’ ወደ ተባለው ስፍራ በማቅናት ‘ሓርጠጠት’ በተሰኘው ተራራ ላይ መሽጎ የነበረውን የኢትዮጵያ ሰራዊት ማጥቃት፡ በዚህም በ‘ሮሬት’ ተራራዎችና ‘ሕዳይ’ በተባለው ወንዝ አካባቢ መሽጎ የነበረውን 19ኛ ክፍለጦር ከነ ተደራቢ የታንከኛ መድፈኛና ከባድ መሳሪያ እንዲሁም ሞርታረኛ ክፍሎቹ ባጠቃላይ መደምሰስ። በዚህ የጥቃት ዘመቻ የተመደቡት የህዝባዊ ግንባር የነጻነት ታጋይ ሰራዊቶች፡ ከ61ኛው ክፍለጦር 81ኛ ብርጌድ፣ ከ87ኛው ብርጌድ አንድ ሻምበል፣ እንዲሁም አንድ የእግረኛ ከባድ መሳሪያ የመቶ፣ ከ 52ኛው ክፍለጦር ከ24ኛው ብርጌድ አንድ ሻምበል፣ ከ16ኛው ክፍለጦር ከ26ኛው ብርጌድ አንድ ሻምበል ሲመደቡ ከነዚህ በተጨማሪም ‘ሕዳይ’ በተባለው ወንዝ አቅጣጫ እንዲያጠቁ የተመደቡት 34ኛ እና 63ኛ ሜካናይዝድ ብርጌዶች ነበሩ።

ሶስተኛው አቅጣጫ
ከ‘ኣምባ’ እስከ ‘ኣርሃጸት ዓቢ’ የተባሉ ተረተሮች እንዲሁም እስከ ‘ጠልቀሳ’ የተባለው ወንዝ ድረስ ባለው ስትራቴጂያዊ ቦታዎች ላይ መሽጎ የነበረውን የደርጉ 19ኛና 21ኛ ክፍለጦር ክፍሎች ከነተደራቢ ጓዶቻቸው ጋር መደምሰስ። በዚህ ጥቃት ላይ በሞርታርና በመትረየሶች ታግዞ ከፊት ለፊት እንዲያጠቃ ከተመደበው አንስተኛ ኃይል በተጨማሪ፡ ሁሉም በዚህ ምድብ የተደለደሉት ሻምበሎች በጠላት ምሽግ መካከል በከፍተኛ ጥንቃቄ ሾልከው በመግባት፡ ድምጣቸውን አጥፍተው በመጓዝ የኢትዮጵያን ሰራዊት ከበስተጀርባና በጎን በኩል እንዲያጠቁ ተመደቡ። በዚህ የማጥቃት እርምጃ እንዲሳተፉ የተመደቡት የነጻነት ታጋዮች በስተግራ የ70ኛው ክፍለጦር 26ኛው ብርጌድ ኣባላት፡ እንዲሁም በስተቀኝ የ61ኛው ክፍለጦር 11ኛው ብርጌድ አባላት ሲመደቡ፡ በተጨማሪም ‘ፈርኔሎ’ እና “ቀብርጻዕዳ’ በተባሉት ስፍራዎች በኩልም የ34ኛው ሜካናይዝድ ብርጌድ አባላት ተመድበው ነበር።

አራተኛው አቅጣጫ
ሸገ’ ከተባለው አካባቢ በመነሳት ‘ኣንደብ’ እና ‘ሓሳይድ’ በተባሉ ስፍራዎች መካከል ሰንጥቆ በማለፍ፤ ‘ሓሳይድ’ን በስተደቡብ አጥቅቶ በመቖጣጠር፣ ከአፍዓበት በስተምዕራብ ወደሚገኙት ስትራቴጂካዊ ቦታዎች መገስገስ፣ ‘ገብገብ’ በተባለው ወንዝና ‘ግሎብ’ እንዲሁም ‘ሽኽናብ’ የተባሉትን ስፍራዎች ከጠላት ይዞታነት ሙልጭ አድርጎ በማጽዳት፣ ‘ሃበሮ’ ከተባለው ስፍራ የሚመጣውን ረዳት የደርግ ሰራዊት መግታት። በዚህ ዕቅድ ትግባሬ ላይ የተሰማሩት የነጻነት ታጋዮች የሰራዊት አባላት የ70ኛዉ ክፍለጦር 10ኛ ብርጌድ ሁሉም አባሎች፣ ከ71ኛው ብርጌድ ደግሞ አንዲት ሻምበል፣ እንዲሁም አንድ እግረኛ የከባድ መሳሪያ ሻምበልና ከ34ኛው መካናይዝድ ብርጌድም አንዳንድ አባላቶች ተመድበዋል።

አምስተኛው አቅጣጫ
የናደው እዝን ለማጥቃት በግንባር በኩል ጥቃቱ በሚሰነዘርበት ሰዓት፡ አፍዓበትንና ከረንን በሚያገኘው መንገድ ሾልኮ በመግባት፡ ከከረን 30 ኪ.ሜ. ርቀት ውስጥ በሚገኙት ስትራቴጂያዊና ለደፈጣም አመቺ የሆኑትን የ’መስሓሊት’ የተራራ ሰንሰለቶችን በመቆጣጠር፡ የናደው እዝ ሊያመልጥበት የሚችልበትን ቀዳዳ ሁሉ በመድፈን ሙሉ በሙሉ ከባባ ውስጥ ማስገባት፡ ከከረንም ረዳት እንዳይደርስለት ማገት፣ ከአፍዓበትም የሚሸሸውን ማንኛውም የኢትዮጵያ (የደርግ) ሰራዊትን ከነ ሙሉ ትጥቁ ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ስር ማዋል። በዚህ የማጥቃት ምድብ ውስጥ የተመደቡት የነጻነት ታጋዮች ክፍሎች፣ 52ኛው ክፍለጦር በሙሉ እንዲሁም አንድ የእግረኛ ከባድ መሳሪያ ሻምበል ነበሩ። ይህ አጥቂ ኃይል፣ ከጠላት ይዞት ውስጥ ማለትም ‘ማይ መደፍ’ ከተባለ አካባቢ በመነሳት ‘ደርሰነይ’ የተባለውን ስፍራ በማለፍ፡ ከከረን አስመራ የተዘረጋውን መንገድ ‘ሽንድዋ’ በተባለው ስፍራ ቆርጦ በማለፍ፡ በ’ምራራ’፣ ‘ዒራዒሮ’ እንዲሁም ‘እምባ’፣ ‘አፍሉቕ’ እና ‘እንስ’ የተባሉትን ስፍራዎች በማለፍ፡ ከአፍዓበት ወደ ከረን የሚወስደውን መንገድ እንዲቆጣጠር ነው የተመደበው።

ስድስተኛው አቅጣጫ
ከ‘ሰሜናዊ ባሕሪ’’ ጫካዎች በመነሳት፡ ከአፍዓበት ከተማ በስተምስራቅ ማለትም በ‘ኣዛህራ’ና ‘ጋድም ሓሊብ’ በኩል የነበረን የኢትዮጵያ ሰራዊት ምሽግ በማጥቃት፣ ከግንባሩ በስተቀኝ አቅጣጫ ማለትም ‘ፈልከት’ በተባለው ስፍራ በኩል ከሚመጣው የወገን ሰራዊት ጋር በመተሳሰር አፍዓበት ከተማን መቆጣጠር። ይህ አጥቂ ኃይል ጥቃቱ በተጀመረበት ዕለት፡ በደቡብና ደቡባዊ ምስራቅ የነበረው የደርጉ ሰራዊት እስኪያፈገፍግ ወይም እስኪጠቃ ድረስ ጠብቆ፡ በሁለተኛው ቀን የውጊያ ውሎው ተልእኾውን ለመፈጸም የተመደደ ነው። በዚህ የማጥቃት አቅጣጫ የተሰለፉት የነጻነት ታጋዮች፡ የ85ኛው ክፍለጦር 22ኛው ብርጌድ እንዲሁም 5 እግረኛ የከባድ መሳሪያ የመቶዎች ጋር ነው። ከ61ኛው ክፍለጦርም የ13ኛው ብርጌድ 2 ሻምበሎችና አንድ የከባድ መሳርያ ሻምበልም ይህን ተልዕኾ ለማሳካት ተመድቧል።

የማጥቃት ዕቅዱ ይህን ሲመስል፡ በሚቀጥለው ክፍል ከመጋቢት 17-19 የተካሄደው ውጊያ ምን ይመስላል የሚለውን እናብላላለን እናብራራለንም!

ደርግን በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ፡ ዲጅታሎቹን ያስመረረ- ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር - ታሪክ ይቀጥላል
የናደው እዝ ቀብር ትረካ ይቀጥላል! :mrgreen:

Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: “. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”

Post by Meleket » 17 Mar 2021, 04:43

ሰይብል ብከረባብስ! :mrgreen:

ውጥን ናይ ክሬምሊን፡ ጌርካዮ ኪነሚን!

ውጥን ናይ ደደቢት፡ ቀቢርካዮ ኣብ ድበት!

ውጥን አራት ኪሎ፡ ሓምሸሽካዮ ብድሎ!



“. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ” :mrgreen:

ይህን የናደው እዝን የመደምሰስ ሂደት ስኬታማ በማድረግ ረገድ፡ የመላው የኤርትራ ህዝብና ሠራዊት ድምር የትግል ውጤት ቢሆንም ቅሉ፡ ረሀብና ጥምን ተቋቁመው ለወራት በድብቅ ናደው እዝ የመሸገበትን ስፍራ በሙሉ እንደ እጃቸው መዳፍ ያጠኑት የስለላው ክፍል ተዋናዮች ያንበሳውን ድርሻ እንደያዙ የኤርትራ ህዝብና ታጋይ ልጆቹ ጠንቅቀው የሚያውቁት ታሪካዊ እውነታ ነው።

“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ ዲጂታሎቿንም ያስመረረ ኤርትራዉያንን በጀግንነት ያንቀባረረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ዘንድሮም በኤርትራዊ ልበሙሉነት ይተረካል!!!
:lol:
Meleket wrote:
15 Mar 2019, 03:25
1.3 የውጊያው አፈጻጸም ሂደት (17-19 መጋቢት)

የህዝባዊ ግንባር ሰራዊት አስቀድሞ በተጠቀሰው አሰላለፍ፡ መጋቢት 17 1988 ማለዳ በአምስቱ ማእዘኖች የማጥቃት እርምጃውን ጀመረ። ምንም እንኳን የኢትዮጵያ (የደርጉ) ሰራዊት በርትቶና ወጥሮ ለመዋጋት ቢሞክርም፡ ቀኑን ሙሉ በቀጠለው ውጊያ፡ የመጀመሪያና ሁለተኛ የመከላከያ ወረዳውን ለቆ ሲያፈገፍግ፡ ከግንባሩ ውጪ ማለትም በተለያዩ ማእዘኖች እንዲያጠቁ ተመድበው የነበሩት የነጻነት ታጋዮች፡ በጠላት ወረዳ ውስጥ ከከረን አፍዓበት የሚወስደውን መንገድ እንዲያጠቁ የተመደቡትም ጭምር ዓላማቸውን በእቅዱ መሰረት አሳኩ። በኢትዮጵያ ሰራዊት ወረዳ ውስጥ እንዲያጠቃ የተመደበው የነጻነት ታጋዮች 52ኛ ክፍለጦር፣ በዚሁ ዕለት ‘መስሓሊት’ በተባለ ስፍራ በመመሸግ፡ ከከረን ወደ ኣፍዓበት ለረዳትነት የተንቀሳቀሰውን የኢትዮጵያ ሰራዊት ሲከላከል ዋለ።

ውጊያው በሚካሄድበት በሁለተኛው ቀን ማለትም መጋቢት 18፡ በአምስቱ ማእዘኖች የጥቃት እርምጃውን ያካሄደው የነጻነት ታጋዮች ኃይል፡ ብርቱ ረሃብ፣ ጥምንና ድካምን ተቆቁሞ፡ የጎደለውን መሳርያና ጥይት ከኢትዮጵያ ሰራዊት እየማረከና እየተጠቀመ፡ በቅጽበት በመገስገስ፡ ሰፊ ቦታዎችን ተቆጣጠረ። የደርጉ ማለትም የኢትዮጵያ ሰራዊትም በዚህ ሃያልና ፋታ የማይሰጥ የማጥቃት እርምጃ አደረጃጀቱ ተዛብቶ፡ አዛዥና ታዛዥ ተደበላልቆ፡ የእዝ ሰንሰለት ተጥሶ፡ አብዛኛው ክፍሉ ቅጥ ባጣ መልኩ ወደኋላ ለመሸሸት ተገደደ።

ናደው እዝ ሲደመሰስ እጅግ ብርቱ ውጊያ የተካሄደት ስፍራ ‘ሞጋዕ ቀጣሪት”ና ‘ቃምጨዋ’ ይባላሉ። የኢትዮጵያ ሰራዊት አዛዦች፡ ከተራራማ ገዢና ስትራቴጂያዊ ስፍራዎች ተገፍቶ ብትንትኑ ወጥቶ ወደ ተጠቀሱት ሰርጦችና ጅረቶች የወረደውን እግረኛ ሰራዊት፡ ዳግም ተደራጅቶ የከባድ መሳርያ መሽጎበት የነበረውን የደጀን ቦታቸውን ሊከላከልላቸው እንደማይችል በመገምገም፡ እዚያ አካባቢ የነበረውን ማንኛውም መሳርያቸው እንዳይማረክባቸው በአፋጣኝ እንዲያፈገፍጉ ወሰኑ። በዚህም መሰረት ከ 70 እስከ 80 የሚሆኑ ታንኮችና ተሽከርካሪዎች፡ በቀትር ወደ አፍዓበት ጉዟቸውን ተያያዙት። ነገር ግን በ15፡30 አካባቢ እነዚህ በርካታ ታንኮችና ተሽከርካሪዎች፡ ‘ዓሽሩም’ የተባለውን ዳገት ተሰልፈው ይወጡ በነበሩበት ወቅት፡ በ‘ሕዳይ’ ወንዝ በኩል አልፈው ሁነኛ ቦታ ላይ ተዘጋጅተው ይጠብቁ በነበሩ የነጻነት ታጋይ ታንከኞች ዒላማ ውስጥ ገቡ። ከነጻነት ታጋዮች 34ኛ ታንከኛ ብርጌድ ታንኮች አንዷም፡ በርቀት በተኮሰችው ጥይቷ፡ ዓሽሩም ጫፍ ላይ ደርሳ የነበረችን አንዲት ቢ.ኤም. 21 ተወንጫፊ ሮኬት የጫነች መኪናን አቃጠለች። ሁለተኛዋ ከታንኳ የተተኮሰው ጥይትም፡ አቀበቱ መሃል የነበረችን አንዲት ታንክ አቃጠለች። በዚህም ምክንያት “ዘርአይ ደረስ” ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ ሰራዊት እጅግ የሚመካበት 29ኛው መካናይዝድ ብርጌድ ተሽከርካሪዎችና ታንኮች መፈናፈኛ መንገድ አጥተው ለብርቱ አደጋ ተጋለጡ።

ይህን ያህል ከባድ መሳርያ የጫኑ መኪናዎችና ታንኮች ማፈግፈጊይና መውጫ ቀዳዳው ሲጠፋቸው፣ ውጊያውን ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ (ሁ.አ.ሰ.) አዛዥ ሜጀር ጀነራል ውበቱ ጸጋየ፣ ያ ሁሉ የታገተውና ወጥመድ ውስጥ የገባው ከባድ መሳርያና ታንክ በነጻነት ታጋዮች ቁጥጥር ስር እንዳይገባ፡ የውጊያ አውሮፕላኖች እንዲያጋዩት መመሪያ ሰጠ። በዚያን ቀውጢ ሰዓትም፡ የወገኑን ከባድ መሳርያዎችና ታንኮች እንዲያጋይ ትእዛዝ የተሰጠው የውጊያ ጄት አብራሪም፡ “አዬ መንግስት ሲወድቅ” ብሎ ሲናገር በሬዲዮ ሞገድ ተጠለፈ። በርግጥ ያ እጅግ ሰፊ የሆነው ደምሳሽ የማጥቃት እርምጃ የኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ያሳረፈው ግዙፍ ጠባሳ እጅጉኑ ጎልቶ የታየው ‘ዓሽሩም’ በተባለው ዳገት ላይ ነው።

በመጋቢት 18 የውጊያ ውሎም፡ ሲሶው የኢትዮጵያ ሰራዊት ዓቅም ተወቅጦ፡ በግምባር በኩልም ያጠቃ የነበረው የነጻነት ታጋዮች ክፍልም 40 ኪ.ሜ. ወደፊት ገፍቶ፡ የደርጉን ሰራዊት አሉ ከሚባሉት ስትራቴጂያዊ ተረተሮች ጠራርጎ ሲያወርደው፡ በግራና ቀኝ ክንፎች ያጠቁ የነበሩት የነጻነት ታጋዮች ክፍሎች ደግሞ፡ አፍዓበት ከተማ መዳረሻ አካባቢን ተቆጣጥሮ አደረ። ከበስተኋላ ከከረን ወደ አፍዓበት የሚወስደውን መንገድ ግጥም አርጎ ዘግቶት የዋለው የነጻነት ታጋዮች 52ኛ ክፍለጦርም፡ ከከረን ለረዳትነት ይመጣ የነበረን ግዙፍ የደርግ ሰራዊት በብርቱ መስዋእትነት መክቶት ዋለ። ስለሆነም የናደው እዝ በሁሉም አቅጣጫዎች እየተነዳ አፍዓበት አካባቢ እጅግ ጠባብ ቀለበት ውስጥ ለመከበብ ተገደደ።

በሶስተኛው ቀን ማለትም መጋቢት 19 1988 ማለዳ 5፡30 ላይ አፍዓበትን ከቦ ያደረው የነጻነት ኃይሎች ታጋይ ሰራዊት የመጨረሻ የጥቃት እርምጃዎቹን ሰነዘረ። በሁለቱ የማጥቃት ቀናት ከባድ ኪሳራ አጋጥሞት እጅግ የተዳከመው የኢትዮጵያ (ደርጉ) ሰራዊት፣ ለአጭር ጊዜ ተቃውሞ በማድረግ ለመከላከል ቢሞክርም፡ የነጻነት ታጋይ ሃይሎች የጥቃት እርምጃ እጅግ ከባድ ስለነበረ፡ የደርጉ ሰራዊት ንብረቱን እያቃጠለ መሸሸት ጀመረ። በከተማዋ ምስራቅና ደቡባዊ ምስራቅ አቅጣጫ ተጠግቶ ያደረው የነጻነት ሃይሎች ተዋጊ ሰራዊትም ማለዳ 9:00 (3፡00) አፍዓበት ከተማ ገስግሶ ገባ። በሰሜንና በሰሜናዊ ምዕራብ ሲገሰግስ ያደረው የነጻነት ታጋዮች ተዋጊ ኃይልም፡ ከረፋዱ 10፡00 (4፡00) ተልእኾውን ፈጽሞ አፍዓበት ከተማ በድል ገባ።

አፍዓበትን ለመቆጣጠር ማለዳ ‘ሻባይ መንደር’ በተባለው ስፍራ በተካሄደው አጭርና ብርቱ ውጊያም፡ የ61ኛው ክፍለጦር 87ኛ ብርጌድ 3ኛ ሻምበል፡ 3 የሶብየት ሕብረት ከፍተኛ የጦር አማካሪዎችንና ሌሎች ኢትዮጵያዉያን መኮንኖችን ማረከች።

ከዚህ በኋላም በአፍዓበትና በአካባቢዋ በተደረገ ውጊያ ከሞትና ከመማረክ አምልጦ፡ ጥቂት ታንኮቹንና ተሽከርካሪዎችን ይዞ ወደ ከረን ለማምረጥ የሞከረ የኢትዮጵያ ሰራዊት፡ የነጻነት ታጋዮች 52ኛው ክፍለጦር አዘጋጅቶት በቆየ ወጥመድ ውስጥ ስለገባ፡ ንብረቱን ጥሎ እግሬ አውጪኝ ብሎ በ ‘ግዝግዛ’ ‘ቀልሃመትና’ ‘ሂካኖ’ በተባሉት ስፍራዎች ብትንትኑ ወጣ።

የናደውን እዝ የመደምሰስ ብርቱ ውጊያም፡ መጋቢት 19 1988 ከቀትር በኋላ ‘ግዝግዛ’ በተባለው ስፍራ በተካሄደ የመጨረሻ ውጊያም ተደመደመ። ከውጊያው በፊት ከነጻነት ታጋይ የሰራዊት አዛዦች አንዱ እንደተነበየውም፡ ደርጉ እጅግ ይመካበት የነበረው ብርቱ የሰራዊቱ ክፍል የሆነው “ናድው እዝ” የቀብር ስነስርዓቱ በኤርትራዉያን ታጋዮች ድል ተፈጸመ

የኤርትራ የነጻነት ታጋዮች፡ አስር ዓመታት ያህል ያለመታከት በናቅፋ ግንባር ያደርጉትን የመመከት ተልዕኾ አገባደው፡ ‘መስሓሊት’ በተባለው ስፍራ አካባቢ “ የከረን ግንባር” የሚባል አዲስ ግንባር በመክፈት፡ ወደ አዲስ የማጥቃት ስትራቴጂካዊ መድረክ የሚያሸጋግር የበላይነቱን ጨበጡ።

በቀጣይ ናድው እዝን የመደምሰሱ ተልእኾ በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ያሳደረው ተጽእኖና የዚህን ጦርነት ልዩ ገጽታ እናያለን።


ደርግን በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ፡ ዲጅታሎቹን ያስመረረ- ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር - ታሪክ ይቀጥላል
የናደው እዝ ቀብር ትረካ ይቀጥላል! :mrgreen:


Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: “. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”

Post by Meleket » 19 Mar 2021, 11:37

“. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ” :mrgreen:

ይህን የናደው እዝን የመደምሰስ ሂደት ስኬታማ በማድረግ ረገድ፡ የመላው የኤርትራ ህዝብና ሠራዊት ድምር የትግል ውጤት ቢሆንም ቅሉ፡ ረሀብና ጥምን ተቋቁመው ለወራት በድብቅ ናደው እዝ የመሸገበትን ስፍራ በሙሉ እንደ እጃቸው መዳፍ ያጠኑት የስለላው ክፍል ተዋናዮች ያንበሳውን ድርሻ እንደያዙ የኤርትራ ህዝብና ታጋይ ልጆቹ ጠንቅቀው የሚያውቁት ታሪካዊ እውነታ ነው።

“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ ዲጂታሎቿንም ያስመረረ ኤርትራዉያንን በጀግንነት ያንቀባረረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ዘንድሮም በኤርትራዊ ልበሙሉነት ይተረካል!!!
:mrgreen:
Meleket wrote:
18 Mar 2019, 09:49
የናደው እዝን የደመሰሰው የማጥቃ እርምጃ አስተዋጽኦና ብርቅነቱ

የናደው እዝን ለመደምሰስ የተካሄደው የማጥቃት እርምጃ፣ በኤርትራ ህዝብ የነጻነት ትግል ታሪክ ውስጥ በዓይነቱም ሆኑ በውጤቱ እጅግ ልዩ ደማቅና አንጸባራቂ ወታደራዊ የድል ታሪክ ነው። ይህን ድል ልዩና ብርቅ የሚያደርጉ ምክንያቶችም፡ አንድ እጅግ ግዙፍ የሆነን ጨቋኝ ሰራዊትን ሙሉ በሙሉ ከበባ ውስጥ በማስገባት ለወሬ ነጋሪ እንኳን ሳታስቀር ሙሉ በሙሉ የመደምሰስ ሂደት በመከናወኑ ነው። ከዚህ የማጥቃት እርምጃ በፊት የነበረው መድረክ፡ የነጻነት ታጋዮች በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ብዙ ግዙፍና ጥቃቅን ጥቃቶችን ያካሂድ የነበረ ቢሆንም እንኳን፡ ሁሉም እነዚህ የማጥቃት እርምጃዎች፡ ጠላትን በመገፍተርና በመግፋት ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ለመቆጣጠር ያተኮሩ ነበሩ እንጂ እንደዚህኛው የጥቃት እርምጃ ጠላትን ቀለበት ውስጥ በመክበብ ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ ያለሙ አልነበሩም።

የነጻነት ታጋዮች ሃይል ከ1978 አጋማሽ ጀምሮ ለአስር አመታት የተካሄደን ረዢም የህልውና ውጊያ፡ ከጠላት በርካታ መሳሪያዎችና ታንኮችን በመማረክ የተኩስ ብቃቱን ለማጎልበት በቅቷል። ናደው እዝን በመደምሰሱም፡ የተኩስ አቅሙን ይበልጥ የሚያጎለብቱ፡ ከዚያ በፊት ማርኮ የማያቃቸውን የ130 ሚ.ሜ. መድፍና ቢ.ኤም 21 ተወንጫፊ ሮኬት ሚካይሎችን ሲማርክ፡ ከ50 በላይ ታንኮች የሚገኙባቸው በርካታ መሳሪያዎችንና ጥይቶን ለመማረክ ችሏል። ከዚህም በተጨማሪ፡ የናድወ እዝን በመደምሰስ ሂደት፡ የነጻነት ታጋዮች ለመጀመሪያ ግዜ ሶስት የሶቭየት ህብረት ዜጋ የሆኑ የጦርነት አማካሪዎችን ለመማረክ ችለዋል።

ይህ ግዙፍና ቅጽበታዊ የማጥቃት እርምጃ በደርጉ ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ ነውጥንና ሽብርን ፈጥሯል። በመሆኑም ከጥቃቱ ማግስት ማለትም መጋቢት 31 1988 በተካሄደ አስቸኳይ የኢ.ሰ.ፓ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ወቅት፡ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅና የክተት አዋጅ ለማውጣት ተገዷል። መንግስቱ ኃይለማርያም በስብሰባው ባሰማው ንግግርም፡ የኢትዮጵያ ህልውና ስጋት ውስጥ መውደቁን በመግለጽ፡ “[b]ጥያቄው ወንበዴዎች ይጥፉ ወይስ እኛ እንጥፋ ነው?[/b]” በማለት ደንፍቷል። በዚያ ወቅት በወጣው የክተት አዋጅም፡ በተለያየ ምክንያት ከሰራዊት ተሰናብተው የነበሩ የሰራዊቱ መደበኛ አባላት እንዲሁም የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት አባላት፡ ወደ ሰራዊቱ እንዲመለሱ ሲደረግ፡ ስልጠና ላይ የነበሩት 5ኛ ዙር የብሄራዊ አገልግሎት ወታደሮች በአጭር ግዜ ስልጠናቸውን አገባደው ቅድመ ግንባር ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል።

የደርጉ መሪ መንግስቱ ኃይለማርያምም በዚያን ሰሞን ከሶማሊያው መሪ ከሲያድ ባረ ጋር በጥድፊያ የሰላም ስምምነት እንዲፈርም ያስገደደውም ይህ የናደው እዝ በመደምሰሱ የተገኘ ፍሬ ነው። ያኔዉኑም በምስራቅ ከነበረው ሰራዊቱ ግዙፍ ክፍሉን ወደ ኤርትራ አጓጉዟል። በትግራይና በምእራብ ኢትዮጵያ የነበሩትን የ3ኛ 9ኛና 10ኛ ክፍለጦሮችንም ወደ ኤርትራ በጥድፊያ አጓጉዟል። ደርጉ ትግራይ ውስጥ ለጥበቃነት ያቆየው የሰራዊት ዓቅሙ በጥቂት ከተሞች ብቻ በመወሰኑ፡ ብዙው የትግራይ ክፍል በቀላሉ ከደርጉ ቁጥጥር ውጭ ሆነ። (ትግራይ ነጻ የምትወጣው ኤርትራ ውስጥ በተካሄደ ውጊያ ወላፈን አማካኝነት ነው ማለት ነው።) በቅጽበት ደርግ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወደ ኤርትራ ያጋዘው የሰራዊት ብዛት ከ90,000 በላይ ሆኖ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪም ደርጉ፡ በምዕራብ ኤርትራ ከከረን እስከ ተሰነይ አሰልፎት የነበረው “በርግድ እዝ’ የተባለው ሰራዊቱ በቅጽበት እንዲያፈገፍግ ተገዷል። በምስራቅም የነጻነት ታጋዮች ሳህልን ከሰሜናዊ ባሕሪና የሰምሃር ሜዳዎች ጋር የሚያገናኘውን ሰፊ ቦታ ለመቆጣጠር ችለዋል። እነዚህን ቦታዎች መቆጣጠራቸውም በቀጣይነት “ፈንቅል” የተባለውን ልዩ ጥቃትና ብርቅ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ያስገኘን ጥቃት ለመሰንዘር በር ከፍቷል።

ናደው እዝን ከደመሰሰ በኋላ የነጻነት ታጋዮች ኃይል የጨበጠውን ድል ለማስጠበቅና ይበልጥም ለማስፋት ይችል ዘንድ፡ በሓልሓል ግንባር ላይ መሽጎ በነበረው “መንጥር እዝ ’ ላይ ከፍተኛ አይምሬ ጥቃትን በመሰንዘር ከባድ ኪሳራ በደርጉ ላይ አድርሶ ሰፊ ቦታዎችን ሲቆጣጠር፣ በከረን አካባቢም ተደጋጋሚ የማጥቃት እርምጃዎች በመሰንዘር፡ አዲሱን የመከላከያ ወረዳውን ለማደላደል ችሏል። የደርጉም የነጻነት ታጋዮች የተጎናጸፉትን ድል ለመቀልበስ ከየቦታው አሰባስቦ ባመጣውን ግዙፍ ሰራዊት አድርጎ በአዲሱ የከረን ግንባር በኩል ሰፊ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ወሰደ። በሮራ መንሳዕና እንሲ፡ በግልንዲ፣ ግዝግዛ፣ ዓጋመትና እንዲሁም በዓንሰባ ወንዝና ሓልሓል በኩልም ለወራት የዘለቀ ብርቱ ውጊያ ተካሄደ። ደርጉ በግንባር በኩል ያካሂደው ከነበረው ውጊያ በተጨማሪ የ102ኛ አየር ወለድ ሰራዊቱን በስውር አንቀሳቅሶ፡ በምስራቃዊው ሜዳማ ቦታዎች በኩል ተዟዙሮ ወደ አፍዓበት የመግባት ያለመ የከሸፈ ጥቃትን ሰንዝሮ ነበር። በዚህ ያልተጠናና የጥድፊያ የጥቃት እርምጃ፣ ክፍለጦሩ በሙሉ ገና ጥቃት እንኳን ሳይሰነዝር፡ በውሃ ጥምና በረዢም ጉዞ ተሸንፎ፡ ምንም ፍሬ ሳያፈራ ለሞትና ለምርኾኛነት ተዳርጓል።

በወታደራዊ ስትራቴጂ አኳያ ናደው እዝን የመደምሰሱ ሂደትና ተጽዕኖው ሊገለጽ የሚችለው፡ ቀጥሎ ከተካሂዱት የማጥቃት እርምጃዎችና የመልሶ ማጥቃት ውጊያዎች ጋር በሰፊ ዓውድ ነው። በዚህ ለወራት በቆየ የደርጉ የማጥቃትና የመልሶ ማጥቃት ውጊያ ወቅት፡ ደርጉ የከሰረው የሰው ኃይልና ዓቅም፡ ናደው እዝን በመደምሰስ ሂደት ከከሰረው ቢበዛ እንጂ አያንስም። በነዚህ ውጊያዎች የነጻነት ታጋዮች ናደው እዝን በመደምሰስ ሂደት የተቆጣጠሯቸውን ሰፊ ቦታዎች ለማቀብ መቻላቸው፡ ደርጉም ብዙ የማጥቃት እርምጃዎችን ቢሰነዝርም ፋይዳቢስ ሆኖ በመቅረቱ፡ ወታደራዊው ሚዛን ሙሉ በሙሉ ወደ ኤርትራዉያን ታጋዮች ማጋደሉን አጉልቶ የሚያሳይ ነው። ናደው እዝን ለመደምሰስ የተሰነዘረው ብርቱ በትር መላዋን ኢትዮጵያን የናጠ፡ (ወያኖችንም በፍራት አንቀጥቅጠው እንደነበሩ ተራኪው አልገለጸውም፡ እኛም ይሁና ብለን ታዝበነዋል) ተጽዕኖው እስከ ሞቃዲሾና የሶቭየት ህብረት ቤተመንግስት ክሬምሊን ድረስ የደረሰ ነበር። ይህም ሲባል ከናደው እዝ መደምሰስ በኋላ ሶስት ከፍተኛ መኮንኖቿ በውጊያው የተማረኩባት ሶቭየት ህብረትም ብትሆን፡ ደርጉ እንደማያሸነፍ ገምግማለች። ልክ በዚያ የታሪክ መድረክም በሶቭየት ህብረት ውስጥ የመጣው የፖሊሲ ለውጥ ወይም ተሃድሶው ተጨምሮበት የክሬምሊን ሰዎች ከደርጉ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት አቀዝቅዘውት ነበር።

ናደው እዝን የመደምሰስ ውጊያ፡ ደርጉ የኤርትራዉያን ታጋዮችን እንቅስቃሴ ለመግታት የነበረውን ህልም ሙሉ በሙሉ ያበነነ፡ የኤርትራ ነጻነት በፍጹም አይቀሬ መሆኑን ለዓለም ግልጽ ያደረገ ድል ነው። ስለሆነም ከናደው እዝ መደምሰስ በኋላ የኤርትራ ጉዳይ በዓለም የዜና መድረክ ውስጥ ትልቅ ትኩረት አግኝቶ ነበር። ታዋቂው የታሪክ ተመራማሪና ጸሓፊው እንግሊዛዊው በዚል ደቪድሰን የጦርነቱን ውጤት በዓይኑ ከታዘበ በኋላ “ከድየን ብየን ፉ በኋላ፡ በአንድ የነጻነት እንቅስቃሴ የተከናወነ ግዙፍ ወታደራዊ ኦፕሬሽን” በማለት የኤርትራዉያን ታጋዮችን ድል ገልጾታል። የድየን ብየን ፉና ናደው እዝን የመደምሰስ ውጊያዎች በተጽዕኗቸው ማለትም የገዢዎችን ዕድሜ በማሳጠር ረገድ ተመሳሳይ ቢሆኑም እንኳን፡ እንደ ወታደራዊ ክንውን ግን ናደው እዝን የመደምሰስ ሂደት ከድየን ብየን ፉ’ዉ እጅግ የላቀና የገዘፈ ነው። ከዚህ የኤርትራዉያን ድል በኋላ በርካታ ሃገሮች የኤርትራ ጉዳይ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ አድርገዋል። ደርጉም አስቀድሞ አሻፈረኝ ሲል እንዳልነበረ የሰላም ውይይትን ለማድረግ ተገዷል።

ምንም እንኳን የታሪኩ ጸሃፊ ( ታጋይ ሰለሙን በርሀ) ከዚህ ብርቅ የኤርትራዉያን ታጋዮች ድል አንጻር የሕወሃትን መደናበር በቅጡ ባያቀርበውም ላደረገው ታሪክን በበኩሉ የመመዝገብ እርምጃ ምስጋናችንን እናቀርብለታለን።

ይህን በመሰለ የበርካታ ዓመታት ውጊያ ነጻ የወጣችን ልዑላዊት ሃገር በመደመር ይሁን በማባዛት ስሌት ‘አፈፍ’ ለማድረግ የምትቋምጡ ጅሎች ካላችሁ ደግሞ ህልም ወይም የቀን ቕዥት መሆኑን ለመግለጽም እንወዳለን። ህወሃቶችም የኤርትራን ህዝብ የተባበረ ጡንቻና የኤርትራ ህዝብን ትዕግስት በደንብ አድርጋችሁ ታውቁታላችሁ አግአዚ ይሁን ትግራይ ትግርኝ ይሁን ሌላ ፍልስፍና ኤርትራዉያንን አያወናብድም፡ ይልቅ ካርታችሁን አሻሽላችሁ መሬታችሁ ያልሆነን መሬት ለባለቤቱ ለኤርትራ ህዝብ በሰላም አስረክባችሁ በንስሃና በፍቅር ኑሩ ለማለት ነው። በሚገባችሁ ቋንቋ ግልጽ ለማድረግ
“ናይና አይንህብይ ላይ እንዳማትና'ለ ኣይንደልይ!!!”

ደርግን በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ፡ ዲጅታሎቹን ያስመረረ- ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር - ታሪክ ዘላለም ይኖራል እየተነገረ!!!
ሰይብል ብከረባብስ!

“ውጥን ናይ ክሬምሊን፡ ጌርካዮ ኪነሚን!”

“ውጥን ናይ ደደቢት፡ ቀቢርካዮ ኣብ ድበት!”

“ውጥን አራት ኪሎ፡ ሓምሸሽካዮ ብድሎ!”

Fiyameta wrote:
17 Mar 2021, 13:29





Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: “. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”

Post by Meleket » 23 Mar 2022, 03:53

34ኛዉ ኣመት የኣፍዓበት ድል፡ ናደው እዝ የተደመሰሰበት ድንቅ ገድል፡ የሶቭየት ህብረት ወጠጤ የጦር መኮንኖች ያፈሩበት ውጊያ በመዘከር ላይ እንገኛል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች። ከታሪክ የማትማረው ክሬምሊን ልዑላዊቷን ሃገር ሃገረ ዩክሬን ወራለች፡ ወፈፌው ፑቲን ሰላማዊ ሰዎችን በእውር ድንብስ በሚሳይል በመደብደብ ላይ ይገኛል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች የትግል አጋርነታችንን በጀግናው ዘለንስኪ ለሚመራው ሰፊው የዩክሬን ህዝብ ስንለግስ፡ በኤርትራዊ ጭዋነትና የማይናወጥ የዓላማ ጽናት ነው! :mrgreen:

“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ ዲጂታሎቿንም ያስመረረ የጦር ጥቅመኞችን ያንጨረጨረ ኤርትራዉያንን በጀግንነት ያንቀባረረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ዘንድሮም በኤርትራዊ ልበሙሉነት ይተረካል ይዘከራል!!! :mrgreen:

ምስሉ ላይ የሚታዩት እፍረት የተከናነቡ ምርኮኛ የሶቭየት ህብረት የጦር መኮንኖች ናቸው - በዚሁ ጦርነት በጀግኖቹ ኤርትራዉያን ታጋዮች የተማረኩ።


"ድል ለሰፊው የዩክሬን ሕዝብ!" ስንመኝም፡ "የታላቋ ሩስያ ህልም" እንደ "የታላቋ ኢትዮጵያ ሆነ የታላቋ ትግራይ ህልም" ቕዥት ሆኖ እንደሚቀር በመተማመን ነው!
:mrgreen:

Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: “. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”

Post by Meleket » 24 Mar 2022, 11:36

የኤርትራ ህዝብ ፍትሃዊ ትግል = የዩክሬን ህዝብ ፍትሃዊ ትግል = ወራሪንና ዕብሪተኛ ኃይልን ኣሸናፊ ትግሎች :mrgreen:

Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: “. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”

Post by Meleket » 28 Mar 2022, 09:21

የዩክሬኑ "ዓሽሩም" ታሪክ እንደወረደ ከ https://www.theguardian.com/world/2022/ ... g-for-kyiv ወራሪ እብሪተኛ ሃይልን የመመከት ታሪክ በአውሮፓ ምድር እየተደገመ ነው፡ ዘለንስኪ ያውሮጳው ሻዕብያ ነው ያልነው ያለነገር ኣይደለም። ለመጪው ትውልድ ታሪኩ ታቅቦ ይቆይ ዘንድ ይህን የዩክሬኖች "ዓሽሩም" ገድል ከኛው ጋር አጣምረን እዚህ ዱለነዋል። :mrgreen:

ሲጠቃለል
መለስ = ፑቲን = የማሌ (የማርክስና የሌኒን ግርፍ) ልዑላዊ ሃገሮችን የወረሩ ወፈፌ መሪዎች

የታላቋ ትግራይ ህልም = የታላቋ ሩስያ ህልም

ደደቢት ብቻ ኣይደለም ደደብ፤ ሩስያም(ክሬምሊንም) ጭምር ደደብ ነው!

ዘለንስኪ ጀግና ነው!

ድል ለሰፊው የዩክሬን ህዝብ!
:mrgreen:

Post Reply