Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5087
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 10 Mar 2021, 05:09
“. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”
“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ ዲጂታሎቿንም ያስመረረ ኤርትራዉያንን በጀግንነት ያንቀባረረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ዘንድሮም በኤርትራዊ ልበሙሉነት ይተረካል!!!
Meleket wrote: ↑07 Mar 2019, 02:14
የሚከተለው ታሪክ “ዝኽርታት ሓመድ ድበ ናደው” ማለትም “የናደው ቀብር ሲዘከር” በሚል ርእስ “ሕድሪ’” የሚባለው አሳታሚ ድርጅት ካዘጋጀው መጸሐፍ የተጨለፈ ታሪክ ነው። ታሪኩ የኤርትራ ህዝብና የነጻነት ታጋይ ልጆቹ ታሪክ ነው። ታሪክ እንዳይሰረቅ ከትውልድ ወደ ትውልድም ይሸጋገር ዘንድ በመጸሐፉ መጀመሪያ ክፍል ያለውን ይዘት እንዳለ ኣቅርበነዋል። ይህን ብርቅ ታሪክ የፈጸሙትም ኤርትራዉያን እንደመሆናቸው መጠን፣ ለታሪክ ተመራማሪዎች “የኤርትራዉያንን እይታ” ይገነዘቡ ዘንድ ይህን ‘ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ አኹሪና ብርቕ ታሪክ እዚህ በተወላገደው አማርኛችን እዚህ አቅርበነዋል። መልካም ንባብ!!! በዚያን ግዜ ሕወሓት የኤርትራ ነጻነት ታጋዮችን በማንቋሸሽና በማጥላላት ዘመቻ ተጥዳ ፖለቲካዊ መጨማለቕ ታሳይ ነበር፣ ኤርትራዉያን ታጋዮች ደግሞ ጥበብ በተሞላበት ቅልጣፌን በተካነ ሁኔታ የጥቃት ፕላናቸውን እንዳገባደዱም፣ እንደ ደርጉ ሁሉ ሕወሓትም አራ፣ አፍራና ተደናብራ ነበር ምክንያቱም ይሆናል ብላ ያልጠበቀችው ተአምር ነበርና! ከድሉ ማግስት ግን ወያኔዎች ጅራታቸውን እየቆሎ “እንኳን ደስ አላችሁ! ጀግኖች ወዘተ” የሚል መግለጫ ለማውጣት ተሽቀዳድመው ነበር። ከዚህ ታሪክ እስከ ዛሬ ድረስም ሕወሓት የተማረች አትመስልም፣ በኤርትራ ህዝብና በትግሉ ታዝላ ዝንተዕለት ለመኖር ትሻለች፣ የኤርትራ ህዝብ ግን “በቃ” ብሏታል፣ አሁንም ያለምንም ማንገራገር ከኤርትራ ልዑላዊ ግዛት ብትወጣና ለህግ የበላይነት ብትገዛ አይበጃትም ትላላችሁ?
የናደው እዝ ቀብር ሲዘከር
መግቢያ
“. . . ህዝባዊ ግንባር፡ የናቅፋ ግንባር ድሉን የሚመዝነው፡ በረዢሙ የኤርትራ ህዝብ ትጥቅ ትግል ተጋድሎና በተለይም ባለፉት አስር ኣመታት ውስጥ በታየው ወታደራዊ ክስተቶች ኣዃያ ነው። የሰነዘርነው ጥቃት ኃያል፣ ቅጽበታዊና ትልቅ ጠባሳ ጠላት ላይ እንዳሳረፈ ኣይካድም። ኢትዮጵያዉያን ኤርትራን በኃይል ከያዙበት ግዜ ወዲህ፡ ለመጀመሪያ ግዜ በአእምሯቸው ውስጥ፡ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ ኤርትራን ማስተዳደሯን (‘መግዛቷን’) ትቀጥላለች ወይስ ኣትቀጥልም?” የሚል ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽን የሚሻና ፋታ የማይሰጥ ብርቱ ጉዳይ እንዲሆን ያስደረገ ወታደራዊ ጥቃትን ፈጽመን ነው ድልን የተጎናጸፍነው። . . . ” ታጋይ ኢሳይያስ አፈወርቅ የህ.ግ.ሓ.ኤ. ዋና ጸሃፊ፡ በሳግም መጽሔት ቁ.14)
በመጋቢት ወር 1988 ናቅፋ ግንባር ላይ መሽጎ የነበረውንና “ናደው እዝ” ተብሎ የሚጠራዉን ግዙፍ የኢትዮጵያ ሰራዊት ክፍል፡ በፍጹም ከበባ ውስጥ በማስገባት የተካሄደ ደምሳሽ ቀለበታዊ ጥቃት፡ በወርቃዊ ድሎች ባሸበረቀውና በተመላው የኤርትራ ህዝብ የተጋድሎ ታሪክ ውስጥ እንደ የአዲስ ምዕራፍ በር ከፋች ሊጠቀስ የሚችል፣ ትልቅ ስትራቴጂያዊ ጥቅም የነበረው ፍጻሜ ነው።
ናደው እዝን የደመሰሰው ወታደራዊ ድላችን በነጻነት ትግላችን ውስጥ ጎልቶ የሚታይ ይሁን እንጂ፡ የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ሰራዊት፡ ወደዚህ ግዙፍ ስትራቴጂያዊ የማጥቃት እርምጃ ለመሸጋገር፡ አስቀድሞ ያሳለፋቸው ፋታ የማይሰጡ ተደጋጋሚ ውጊያዎች፡ እጅግ ረዢም ትዕግስትና ብርቱ ጽናት የሚጠይቁ ነበሩ። ስለሆነም የናደው እዝ መደምሰስ፡ አስቀድሞ ለአስር አመታት በቋሚ ሰንሰለታዊ ምሽጎች ናቕፋ ሰሜናዊ ምስራቕ ሳሕልና ባርካ ላይ የተካሄዱት ብርቱ ውጊያዎች ፍሬ ወይ ምርት ነው። በተጨማሪም በጠላት ወረዳ ውስጥ በደፈጣ ውጊያ በፈንጅ ቀበራና በመሳሰሉት የተቀነባበሩ እረፍት የማይሰጡ ውጊያዎች ታግዞ፡ የኢትዮጵያ ሰራዊትና አጋሮቹ መቆሚያና መቀመጫ እስኪያጡ ድረስ የተካሄዱ ተደጋጋሚ ውጊያዎች ፍሬ ነው።
አጭር ቅድመ ታሪክ
በ1977-1978 አምስት ተከበው ከቀሩ ከተሞች በስተቀር፡ መላው ኤርትራ በኤርትራዉያን ታጋዮች ቁጥጥር ስር ሆኖ ነበር። የደርግ ስርዓት ኤርትራዉያን ታጋዮች በሚሰነዝሩበት ጥቃት ብቻ ሳይሆን፡ ከሶማሊያ ጋር ያካሂደው በነበረ ውጊያ ወተሃደራዊ ኣቅሙ እጅግ ተዳክሞ ነበር። የኤርትራ ህዝብ ከዛሬ ነገ ነጻነቴን እጎናጸፋለው ይል በነበረበት ወቅት ግን፡ በወታደራዊ የኃይል አሰላለፍ ሚዛን የሚያዛባ መሰረታዊ ለውጥ ያስከተለ የልዕለኃያሏ ሃገር የሶብየት ህብረት እጅ ቀጠናችን ውስጥ ገባ። ደርግም የሶቭየት ህብረትን ግዙፍ ድጋፍ ኣግኝቶ፣ ባጭር ጊዜ 300,000 ዘመናዊ መሳርያ የታጠቀ፡ በጥቁር አፍሪካ ውስጥ እጅግ ብርቱውን ወታደራዊ ኃይል አንጾ፣ ከመቅጽበት ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋገረ።
በ1978 አጋማሽ፡ ደርግ በሶማሊያ ሃይሎች ላይ እጅግ ግዙፍ ጥቃት ከፈተ። በሳምንት ውስጥም የሶማሊያን ጦርነት በድል አገባዶ፡ “የምስራቅ ድል በሰሜን ይደገማል!” በሚል መፈክር ታጅቦ፡ ወደ ሰሜን በማቅናት የኤርትራን ህዝብ ትግል “ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ” ብሎ በሰየመው ጥቃት ለመደምሰስ እጅግ ግዙፍ ወረራን ጀመረ። ጦርነቱ “በጉንዳንና በዝሆን” መካከል እንደሚደረግ ኣይነት ግጥሚያ ነበር። ስለሆነም ህዝባዊ ግንባር አቅሙንና ብቃቱን ገምግሞ ይህን እጅግ ግዙፍ የሆነ ወራሪ ሰራዊት በተራዘመ ውጊያ ለማዳከም፡ ነጻ አውጥቷቸው ከነበሩ ቦታዎች ደረጃ በደረጃ እያፈገፈገ፡ የጠላትን ኃይል በአመቸው ቦታና ግዜ እየገጠመ፡ ስትራቴጂያዊ ማፈግፈግ ለማድረግ ወሰነ። በዚህ መሰረትም፡
በመጀመርያው ወረራ፡ ህ.ግ. ከደቡባዊና ምስራቃዊ ኤርትራ ሲያፈገፍግ
በሁለተኛው ወረራ ከሰሜናዊ ግንባር አፈገፈገ
በሶስተኛው ወረራም፡ ከከረንና አፍዓበት አካባቢ በማፈግፈግ ቋሚ ምሽጉ ይሆን ዘንድ ወደ መረጠው የናቅፋ ተራራዎችና ሰሜናዊ ምስራቅ ሳሕል አቀና። (የህዝባዊ ሰራዊት ስትራቴጅ ቀድሞም ቢሆን እያፈገፈግክ በሚመችህ ቦታ ጠላትን ድባቅ መምታት መሆኑ የሚያውቅ ነው ሚያውቀው።)
የህዝባዊ ግንባር ሰራዊት በተመቸው ስፍራ ሁሉ ብርቱ ተቃውሞ እያደረገ እያጓራ በመጣበት ጠላት ላይ ከባድ ኪሳራን እያከናነበ በየካቲት 1979 ናቅፋ አካባቢ ደረሰ። በናቅፋ መግቢያ በርም በግራና ቀኝ “እምባ ደንደን” በተባለ ተራራ ላይ መሸገ። ይህ ስፍራ የመጨረሻ የመከላከያ መስመር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ በጥናት የመረጠው ቦታ ነበር። ሆኖም የናቅፋ ግንባር ልክ በዚህ ሁኔታና ግዜ ነበር የተመሰረተው። መጀመሪያ ላይ የግንባሩ ስፋት እጅግ ውሱንና ጠባብ ነበር። የጠላት ሰራዊት በተወሰነ ቦታ ጥሶ ወይ በስቶ ለማለፍ የሚያደርጋቸው ተከታታይና ተደጋጋሚ ጥቃቶች ውጤት አልባ ሲሆኑበት ግዜ፡ በቀጣይ ወረራዎቹ ማለትም (በ4ኛ 5ኛና 6ኛ) ወረራዎቹ ወቅት፡ ሆን ብሎ የወገንን ኃይል ሚዛን ለማሳሳትና ለማራራቅ፡ በግንባሩ ሁለት ክንፎች የሰራዊቱን ይዞታ እየለጠጠ ሰፊ ቦታ ለመሸፈን ብርቱ ጥረት አካሄደ። ከናቅፋ ግንባር በተጨማሪም የሰሜናዊ ምስራቅ ሳህል ግንባርና የሓልሓል ግንባርም በተመሳሳይ መልኩ ይዞታቸው እየሰፋ በመሄዱ በመጨረሻ ሶስቱም ግንባሮች እርስ በርስ ተሳስረው ነበር ለማለት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተደረሰ። በዚህም ለአስር ዓመታት ያህል ያለማቋረጥ በተደረገ ብርቱ የምከታ ውጊያ፡ ሁለቱም ተጻራሪ ወገኖች ምሽጋቸውን የማደላደል ስራ በቀጣይነት ይተገብሩ ስለነበር፡ በሁለቱም ወገኖች መካከል በፈንጅ የታጠረ የ667 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው ብርቱ ምሽግ ተፈጥሮ ነበር። (የኤርትራ ህዝብ የሕወሓትን አካሄድና የድንበር ብይንን አፈታት በተመለከተም ተመሳሳይ ስትራቴጂ የተከተለ ይመስላል፡ ከብርቱ የእልህ ምከታ በኋላ ድንበሩን የሚያስከብርበትና ልዑላዊ ግዛቱን በጠቅላላ ያለአንዳች መሸራረፍ የሚያስተዳድርበት መድረክ ላይ ከትናንት ይልቅ ዛሬ ይበልጥ ተቃርቧል ለማለት ይቻላል።)
ከ1978 አጋማሽ እስከ 1988 ለአስር ዓመታት የቀጠለ ብርቱ የመረባረብ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ፡ ያ ልዕለ ኃያል በሆነችው የሶቭየት ህብረት እጅግ ግዙፍ በሆነ ወታደራዊ፣ ገንዘባዊና ቴክኒካዊ ምክር እየተለገሰለት፡ የኤርትራን ህዝብ ትግል ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመደምሰስ የተነሳው ወራሪ የኢትዮጵይ ሰራዊት፡ ከባድ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳቱን ተሸክሞ፡ ከማጥቃት ወደ መከላከል ስትራቴጂውን እንዲቀይር ተገዷል። ውጊያም ያለ እረፍት በመቀጠሉና ስለተራዘመበትም፡ የኢትዮጵያ ሰራዊት መጨረሻ ላይ ተስፋ እየቆረጠ፣ የመዋጋት ወኔው እየጠፋበት ሞራሉ እየላሸቀ ሂዷል።
እጅግ ረቂቅና ውስብስብ የስለላ ጥናት በማድረግ፡ የጠላት ሁኔታ፡ ከዕለት ወደ ዕለት በትክክል ይገመግም የነበረው የህዝባዊ ግንባር አመራርም፡ በ1987 የጠላትን ቀልብ ከቅድመ ግንባር ወደ መሃል ወይም የጠላት ይዞታ ውስጥ የሳበ፡ ተከታታይ የደፈጣና አጥቅቶ የመሰወር ተልዕኾዎችን ሆን ብሎ ተያያዘው። በግንባር ላይ የነበረውን የጠላት ሁኔታ ለመፈተሽም በታሕሳስ ወር 1987 በናቅፋ ግንባር መካከለኛ መስመር ላይ፡ በተወሰኑ አካባቢዎች መጠኑ አንስተኛ የሆነን ጥቃት በማካሄድ፡ ጠላትን በመግፋት ናደው እዝን ለመደምሰስ ለቀጣዩ ብርቱ የማጥቃት እርምጃ መረማመጃ የሚሆነውን ስትራቴጂያዊ ቦታዎችን በቁጥጥሩ ስር አዋለ።
በነዚህ ብርቱ ጥቃቶች የደነገጠው የደርግ ስርዓት መሪ መንግስቱ ሃይለማርያምም፡ በየካቲት 1988 ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ በመምጣት፡ መላ ኤርትራ ውስጥ የነበረውን የሁለተኛ አብዮታዊ ሰራዊት ብሎ የሚጠራዉን ሰራዊት አመራሮች ጋር ስብሰባ ካካሄደ በኋላ፡ ናደው እዝ እንዲዳከም ምክንያት የሆኑት እንዲሁም በወርሓ ታሕሳስ ግንባር ናቅፋ ላይ ላጋጠመው ሽንፈት ዋንኛ ተጠያቂ ነው ያለውን፣ የግንባሩን ኣዛዥ ብሪጋዴር ጀነራል ታሪኩ ያይኔ መሆኑን በመግለጽ፡ ከሰራዊት ፊት እንዲረሸን አደረገ። በደጋማው የኤርትራ ክፍል በደፈጣ ውጊያ በደርግ ሰራዊት ላይ ለደረሰው ኪሳራም የመክት እዝን ሃላፊ ብሪጋዴር ጀነራል ከበደ ጋሼን ተጠያቂ መሆኑን ኋላፊነት በማሸከም፡ ከሰራዊቱ ፊት ማእረጉን በመግፈፍ ያለ ጥሮታ እንዲባረር አደረገ። የሁለተኛው አብዮታዊ ሰራዊት ማለትም የ‘ሁ.አ.ሰ.’ አዛዥ የነበሩት ሜጀር ረጋሳ ጂማንና ምክትሉን ሸዋረጋ ቢሆነኝን ከሌሎች ከ20 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ የሰራዊት አዛዦችንም፡ ከኤርትራ ወደ የኢትዮጵያ ሌላ ክፍል ቀየራቸው።
በዚያን ወቅት መንግስቱ ሃይለማርያም የወሰደው የተስፋ መቁረጥ እርምጃ የሰራዊቱን ድክመት እንደገና አባብሶት ነበር። የደርግ ስርዓት፡ ከዚህ ሌላ፡ በኤርትራ ደጋማ ክፍሎች በተከታታይ ይደርስበት የነበረውን ብርቱ የደፈጣ ውጊያ ሊቋቋም ባለመቻሉ፡ ይህን ውስጣዊ መስመሩን ወይም ውስጣዊ ይዞታውን ለማደላደል ከዋና የግንባር ክፍሎች ቀስ በቀስ ሃይሉን እያመጣ በውስጣዊ ይዞታው እንዲያሰፍር ይገደድ ነበር።
ይህን ወታደራዊ ሁኔታ በትኩረት ይከታተል የነበረው የህዝባዊ ግንባር አመራርም፡ ‘ናደው እዝ’ን ለመደምሰስ አስቀድሞ ያካሂደው የነበረውን ጥናትና ይመረምረው የነበረን የማጥቃት ውጥን ተግባር ላይ የሚያውልበት የዜሮ ሰዓት እንደተቃረበ ገመገመ። የናደው እዝን የመደምሰስ ተልእኮ ከመከናወኑ በፊት ማለትም ከየካቲት 25-28 1988 የተካሄደው ሁለተኛው የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባም ይህን የሚያመላክት አንድምታ ነበረው።
“ማእከላዊው ኮሚቴ . . . . ወታደራዊ ጥቃቶችን ይበልጡኑ ማበረታታትና ይዞታውንም ማስፋት የሚያስችል፡ ጠላትም ዓቅሙን እንዲያሻሽል ፋታ የማይሰጥ ወታደራዊ የስራ መደብንና ፕላንን አዘጋጅቷል።” ይላል ያኔ የወጣው የአቋም መግለጫ።
ይህን ዓላማ ለማሳካት የተመደበው የመጀመሪያ ውጥን፡ ናደው እዝን በመክበብ መደምሰስ ነበር። የህዝባዊ ግንባር አመራር ክፍል ይህን ዓይነት ትልቅና ደፋር እርምጃን ለመውሰድ የወሰነው፡ የጠላትን ኃያልና ደካማ ጎን በትኩረት የገመገመ ረቂቅ የስለላ መረጃዎችን ካጠናና ከመረመረ በኋላ፡ እንዲሁም በደጋማው የጠላት ወረዳ ውስጥ ባካሄደው ተደጋጋሚ የደፈጣ ውጊያ ጠላትን ለማታለልና የጠላትን የትኩረት አቅጣጫ ለማዛባት በመቻሉ ነው።
ከዚህ ትልቅ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ሁለት ወር በፊት፡ የናደው እዝ ኣዛዥ ብሪጋዴር ጀነራል ታሪኩ ያይኔ፡ ለሁለተኛው አብዮታዊ ሰራዊት (ሁ.አ.ሰ.) ኣዛዥ ለጀነራል ረጋሳ ጂማ በላከው ደብዳቤ፡ ህዝባዊ ግንባር በናቅፋ ግንባር ላይ ብርቱ የስለላ ጥናት በማካሄድ ላይ መሆኑን ይህም ብርቱ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነና፡ ‘መክት እዝ’ን ለማገዝ ከግንባር ወደ ደጋማው ኤርትራ ውስጣዊ ቀጠናዎች የተሰማሩት ወይም እንዲሄዱ የተደረጉት 15ኛና 22ኛ ክፍለጦሮች ባስቸኳይ እንዲመለሱለት ጥያቄውን አቅርቦ ነበር። ይሁን እንጂ የሁ.አ.ሰ. አዛዥ የሰጠው መልስ፡ “ባለን መረጃና ግምገማ መሰረት፡ በቅርቡ ሻዕብያ ብርቱና ሰፊ ጥቃት ይፈጽማል ብለን አናምንም። ስለሆነም እነዚያ ሁለት ክፍለጦሮች ለግዜው እዚሁ በደጋማው ክፍል ውስጥ ያለንን ስጋት ለማስወገድ እዚሁ በውስጥ ቀጠና እየሰሩ ይቆያሉ። ለማንኛውም ግን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።” የሚል ነበር።
የሁ.አ.ሰ. አዛዦች “ሻዕብያ በናቅፋ ግንባር የመከላከያ ምሽጉን በማደላደል ላይ እንጂ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል አንዳችም ፍንጭ አይታይበትም” የሚል ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ ያደናገራችው፡ አንዴም ህዝባዊ ግንባር ጠላትን ለማደናገርና ለማታለል፡ ከስድስት በላይ ብርጌዶችን በጠላት የውስጥ ቀጠና ማለትም ብደጋው ክፍል አሰማርቶ የደፈጣ ውጊያን በቀጣይ ይፈጽም ስለነበረ አሊያም በታሕሳስ 1987 በናቅፋ ግንባር በተካሄደው መጠኑ አንስተኛ በሆነው ጥቃት የተቆጣጠራችውን አዳዲስ ስፍራዎች፡ ምሽግ በመቆፈር ይዞታውን ማጠናከር ላይ በቀጣይነት ሲንቀሳቀስ ይታይ ስለነበር ነው።
“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ይቀጥላል!!!
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5087
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 15 Mar 2021, 04:53
“. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”
“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ ዲጂታሎቿንም ያስመረረ ኤርትራዉያንን በጀግንነት ያንቀባረረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ዘንድሮም በኤርትራዊ ልበሙሉነት ይተረካል!!!
Meleket wrote: ↑11 Mar 2019, 04:56
የተአምራዊው ጥቃት አፈጻጸም
1.1 የሁለቱ ተጻራሪ ወገኖች የሰራዊት ዓቅምና የኃይል አሰላለፍ
አስቀድሞ እንደተገለጠው፡ ናደው እዝን መደምሰስ በህዝባዊ ግንባር አመራሮች ዘንድ ለረዢም ግዜ ሲጠናና ዕቅድ ሲነደፍለት የቆየ ጉዳይ ነው። በዚህም መሰረት፡ ይህን ትልቅ የማጥቃት እርምጃ ለመተግበር ረዢም ግዜ የወሰደ ብርቱ የስለላ ጥናት ውጤትን ምርኩዝ ያደረገ ረቂቅ ግምገማ ተካሂዷል። ጠላትን ለማሞኘትና ለማዘናጋትም በደጋማ ክፍል እንዲሁም በግንባሮች ሁሉ ፋታ የማይሰጡ አደናጋሪ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ይደረጉ ነበር።
ይህ የጥቃት ዕቅድ ትግባሬ የዜሮ ሰዓቱ ሲቃረብም፡ ይህን ሰፊ የጥቃት ንድፍ ተግባር ላይ ለማዋል የተመደቡ የህዝባዊ ግንባር ክፍሎች፡ ማለትም ከእግረኛ የ85ኛ፣ 61ኛ፣ 16ኛ፣ 70ኛና 52ኛ ክፍለጦሮች፣ 74ኛ መካናይዝድ ክፍለጦር እንዲሁም የተለያዩ ድጋፍ ሰጪ የስለያ የመሃንዲስ የሎጂስቲክና የህክምና ወዘተ ክፍሎች ወደየተመደበላቸው ተልእኾና ዒላማ አመሩ። በዚህ የጥቃት ውጥን ትግባሬ ላይ የተሳተፉ የህዝባዊ ግንባር የሰራዊት አባሎች በድምር 10,400 እንደነበሩ የዚያን ግዜ ሪፖርቶች ያመለክታሉ።
ለአስር ያህል ዓመታት በተካሄዱት ከባድ ተከታታይ ውጊያዎች ምክንያት ኤርትራ ውስጥ የነበረው ኢትዮጵያ ሰራዊት ቁጥር አሽቆልቁሏል። በዚህም መሰረት የናደው እዝ ከመደምሰሱ ዋዜማ፡ ደርግ ኤርትራ ውስጥ አሰማርቶት የነበረው የሰራዊት ብዛት እስከ 94,000 ይሆን ነበር።
በደጋማ የኤርትራ ክፍሎች የነበረው ‘መክት እዝ’ 30,000፡
በሓልሓል ግንባር መሽጎ የነበረው ‘መንጥር እዝ’ ከ21,000 በላይ፣
ባርካ የነበረው ‘በርግድ እዝ’ 14,500፣
ድጋፍ ሰጪ የሁ.አ.ሰ. ክፍሎች ከ7,000 በላይ የሰራዊት ቁጥር ነበሯቸው።
ናደው እዝም ከጠቅላላ ዓቅሙ፡ አስቀድሞ በናቅፋ ግንባር በወረደበት ጥቃት ምክንያት ከ4,700 በላይ አባሎቹ በሞት፣ በመቁሰልና በተለያዩ ምክንያቶች ጎድለውበት ስለነበር፡ የሰራዊቱ አባሎች ወደ 16,500 አሽቆልቁሎ ነበር። ውጊያ በተከፈተበት ሰዓት በሂሊኮፕተር አፍዓበት ላይ ተራግፈው የተደረቡትን የ 15ኛ ክፍለጦር ሁለት ሻለቆች በመደመር፡ በጦርነቱ ወቅት የናደው እዝ ሰብኣዊ ኣቕም 18,000 ያህል ነበር።
በግንባሩ ተሰልፈው የነበሩት የናደው እዝ ክፍሎች፣
ከእግረኛው ክፍል 21ኛ፣ 19ኛ፣ እና 14ኛ ክፍለጦሮች፣
29ኛ መካናይዝድ ብርጌድ (ዘርኣይ ደረስ)፣
የ157ኛ መድፈኛ ሻለቃና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ተደራቢ ክፍሎች ናቸው።
ናደው እዝ ታጥቆት የነበረው መሳሪያም፦
54 ታንኮች፣
16 የ130ሚ.ሜ. መድፎች፣
36 የ122 ሚ.ሜ. መድፎች፣
12 የ ቢ.ኤም 21 ተወንጫፊ ሮኬቶች፣
55 ከባድ መሳሪያ የተጠመደባቸው መኪኖች፣ እንዲሁም በርካታ ሞርታሮች፣ መካከኛ መሳሪያዎችና ከ18,000 በላይ ቀላል መሳሪያዎችን ያጠቃልላል።
(የነጻነት ታጋዮች የማጥቃት ዕቅድ ምን ይመስላል በቀጣይ እንሄድበታለን)
ይህን ሁሉ ኃይል ድባቅ የመቱት የነጻነት ታጋዮች ያልተሸራረፈች ኤርትራን ነጻ ለማውጣት ነበር። ጥቃቱን በፈጸሙበት ቅጽበትም ብርቱ የራስ ሕመም በደደቢት በአዲሳአበባና በክሬምሊን ‘ቤተመንግሥቶች’ ውስጥ ተከስቶ እንደነበረ የጊዜው "የሜትሪዮሎጂ" መረጃዎች ጠቁመዋል።
የናደው እዝ ቀብር ትረካ ይቀጥላል! 
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5087
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 19 Mar 2021, 11:37
“. . . ከምዚ ሕጂ ይደልዩ’ዶ ፀ(ጨ)ሓይ? . . . ”
ይህን የናደው እዝን የመደምሰስ ሂደት ስኬታማ በማድረግ ረገድ፡ የመላው የኤርትራ ህዝብና ሠራዊት ድምር የትግል ውጤት ቢሆንም ቅሉ፡ ረሀብና ጥምን ተቋቁመው ለወራት በድብቅ ናደው እዝ የመሸገበትን ስፍራ በሙሉ እንደ እጃቸው መዳፍ ያጠኑት የስለላው ክፍል ተዋናዮች ያንበሳውን ድርሻ እንደያዙ የኤርትራ ህዝብና ታጋይ ልጆቹ ጠንቅቀው የሚያውቁት ታሪካዊ እውነታ ነው።
“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ ዲጂታሎቿንም ያስመረረ ኤርትራዉያንን በጀግንነት ያንቀባረረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ዘንድሮም በኤርትራዊ ልበሙሉነት ይተረካል!!!
Meleket wrote: ↑18 Mar 2019, 09:49
የናደው እዝን የደመሰሰው የማጥቃ እርምጃ አስተዋጽኦና ብርቅነቱ
የናደው እዝን ለመደምሰስ የተካሄደው የማጥቃት እርምጃ፣ በኤርትራ ህዝብ የነጻነት ትግል ታሪክ ውስጥ በዓይነቱም ሆኑ በውጤቱ እጅግ ልዩ ደማቅና አንጸባራቂ ወታደራዊ የድል ታሪክ ነው። ይህን ድል ልዩና ብርቅ የሚያደርጉ ምክንያቶችም፡ አንድ እጅግ ግዙፍ የሆነን ጨቋኝ ሰራዊትን ሙሉ በሙሉ ከበባ ውስጥ በማስገባት ለወሬ ነጋሪ እንኳን ሳታስቀር ሙሉ በሙሉ የመደምሰስ ሂደት በመከናወኑ ነው። ከዚህ የማጥቃት እርምጃ በፊት የነበረው መድረክ፡ የነጻነት ታጋዮች በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ብዙ ግዙፍና ጥቃቅን ጥቃቶችን ያካሂድ የነበረ ቢሆንም እንኳን፡ ሁሉም እነዚህ የማጥቃት እርምጃዎች፡ ጠላትን በመገፍተርና በመግፋት ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ለመቆጣጠር ያተኮሩ ነበሩ እንጂ እንደዚህኛው የጥቃት እርምጃ ጠላትን ቀለበት ውስጥ በመክበብ ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ ያለሙ አልነበሩም።
የነጻነት ታጋዮች ሃይል ከ1978 አጋማሽ ጀምሮ ለአስር አመታት የተካሄደን ረዢም የህልውና ውጊያ፡ ከጠላት በርካታ መሳሪያዎችና ታንኮችን በመማረክ የተኩስ ብቃቱን ለማጎልበት በቅቷል። ናደው እዝን በመደምሰሱም፡ የተኩስ አቅሙን ይበልጥ የሚያጎለብቱ፡ ከዚያ በፊት ማርኮ የማያቃቸውን የ130 ሚ.ሜ. መድፍና ቢ.ኤም 21 ተወንጫፊ ሮኬት ሚካይሎችን ሲማርክ፡ ከ50 በላይ ታንኮች የሚገኙባቸው በርካታ መሳሪያዎችንና ጥይቶችን ለመማረክ ችሏል። ከዚህም በተጨማሪ፡ የናድወ እዝን በመደምሰስ ሂደት፡ የነጻነት ታጋዮች ለመጀመሪያ ግዜ ሶስት የሶቭየት ህብረት ዜጋ የሆኑ የጦርነት አማካሪዎችን ለመማረክ ችለዋል።
ይህ ግዙፍና ቅጽበታዊ የማጥቃት እርምጃ በደርጉ ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ ነውጥንና ሽብርን ፈጥሯል። በመሆኑም ከጥቃቱ ማግስት ማለትም መጋቢት 31 1988 በተካሄደ አስቸኳይ የኢ.ሰ.ፓ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ወቅት፡ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅና የክተት አዋጅ ለማውጣት ተገዷል። መንግስቱ ኃይለማርያም በስብሰባው ባሰማው ንግግርም፡ የኢትዮጵያ ህልውና ስጋት ውስጥ መውደቁን በመግለጽ፡ “[b]ጥያቄው ወንበዴዎች ይጥፉ ወይስ እኛ እንጥፋ ነው?[/b]” በማለት ደንፍቷል። በዚያ ወቅት በወጣው የክተት አዋጅም፡ በተለያየ ምክንያት ከሰራዊት ተሰናብተው የነበሩ የሰራዊቱ መደበኛ አባላት እንዲሁም የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት አባላት፡ ወደ ሰራዊቱ እንዲመለሱ ሲደረግ፡ ስልጠና ላይ የነበሩት 5ኛ ዙር የብሄራዊ አገልግሎት ወታደሮች በአጭር ግዜ ስልጠናቸውን አገባደው ቅድመ ግንባር ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል።
የደርጉ መሪ መንግስቱ ኃይለማርያምም በዚያን ሰሞን ከሶማሊያው መሪ ከሲያድ ባረ ጋር በጥድፊያ የሰላም ስምምነት እንዲፈርም ያስገደደውም ይህ የናደው እዝ በመደምሰሱ የተገኘ ፍሬ ነው። ያኔዉኑም በምስራቅ ከነበረው ሰራዊቱ ግዙፍ ክፍሉን ወደ ኤርትራ አጓጉዟል። በትግራይና በምእራብ ኢትዮጵያ የነበሩትን የ3ኛ 9ኛና 10ኛ ክፍለጦሮችንም ወደ ኤርትራ በጥድፊያ አጓጉዟል። ደርጉ ትግራይ ውስጥ ለጥበቃነት ያቆየው የሰራዊት ዓቅሙ በጥቂት ከተሞች ብቻ በመወሰኑ፡ ብዙው የትግራይ ክፍል በቀላሉ ከደርጉ ቁጥጥር ውጭ ሆነ። (ትግራይ ነጻ የምትወጣው ኤርትራ ውስጥ በተካሄደ ውጊያ ወላፈን አማካኝነት ነው ማለት ነው።) በቅጽበት ደርግ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወደ ኤርትራ ያጋዘው የሰራዊት ብዛት ከ90,000 በላይ ሆኖ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም ደርጉ፡ በምዕራብ ኤርትራ ከከረን እስከ ተሰነይ አሰልፎት የነበረው “በርግድ እዝ’ የተባለው ሰራዊቱ በቅጽበት እንዲያፈገፍግ ተገዷል። በምስራቅም የነጻነት ታጋዮች ሳህልን ከሰሜናዊ ባሕሪና የሰምሃር ሜዳዎች ጋር የሚያገናኘውን ሰፊ ቦታ ለመቆጣጠር ችለዋል። እነዚህን ቦታዎች መቆጣጠራቸውም በቀጣይነት “ፈንቅል” የተባለውን ልዩ ጥቃትና ብርቅ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ያስገኘን ጥቃት ለመሰንዘር በር ከፍቷል።
ናደው እዝን ከደመሰሰ በኋላ የነጻነት ታጋዮች ኃይል የጨበጠውን ድል ለማስጠበቅና ይበልጥም ለማስፋት ይችል ዘንድ፡ በሓልሓል ግንባር ላይ መሽጎ በነበረው “መንጥር እዝ ’ ላይ ከፍተኛ አይምሬ ጥቃትን በመሰንዘር ከባድ ኪሳራ በደርጉ ላይ አድርሶ ሰፊ ቦታዎችን ሲቆጣጠር፣ በከረን አካባቢም ተደጋጋሚ የማጥቃት እርምጃዎች በመሰንዘር፡ አዲሱን የመከላከያ ወረዳውን ለማደላደል ችሏል። የደርጉም የነጻነት ታጋዮች የተጎናጸፉትን ድል ለመቀልበስ ከየቦታው አሰባስቦ ባመጣውን ግዙፍ ሰራዊት አድርጎ በአዲሱ የከረን ግንባር በኩል ሰፊ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ወሰደ። በሮራ መንሳዕና እንሲ፡ በግልንዲ፣ ግዝግዛ፣ ዓጋመትና እንዲሁም በዓንሰባ ወንዝና ሓልሓል በኩልም ለወራት የዘለቀ ብርቱ ውጊያ ተካሄደ። ደርጉ በግንባር በኩል ያካሂደው ከነበረው ውጊያ በተጨማሪ የ102ኛ አየር ወለድ ሰራዊቱን በስውር አንቀሳቅሶ፡ በምስራቃዊው ሜዳማ ቦታዎች በኩል ተዟዙሮ ወደ አፍዓበት የመግባት ያለመ የከሸፈ ጥቃትን ሰንዝሮ ነበር። በዚህ ያልተጠናና የጥድፊያ የጥቃት እርምጃ፣ ክፍለጦሩ በሙሉ ገና ጥቃት እንኳን ሳይሰነዝር፡ በውሃ ጥምና በረዢም ጉዞ ተሸንፎ፡ ምንም ፍሬ ሳያፈራ ለሞትና ለምርኾኛነት ተዳርጓል።
በወታደራዊ ስትራቴጂ አኳያ ናደው እዝን የመደምሰሱ ሂደትና ተጽዕኖው ሊገለጽ የሚችለው፡ ቀጥሎ ከተካሂዱት የማጥቃት እርምጃዎችና የመልሶ ማጥቃት ውጊያዎች ጋር በሰፊ ዓውድ ነው። በዚህ ለወራት በቆየ የደርጉ የማጥቃትና የመልሶ ማጥቃት ውጊያ ወቅት፡ ደርጉ የከሰረው የሰው ኃይልና ዓቅም፡ ናደው እዝን በመደምሰስ ሂደት ከከሰረው ቢበዛ እንጂ አያንስም። በነዚህ ውጊያዎች የነጻነት ታጋዮች ናደው እዝን በመደምሰስ ሂደት የተቆጣጠሯቸውን ሰፊ ቦታዎች ለማቀብ መቻላቸው፡ ደርጉም ብዙ የማጥቃት እርምጃዎችን ቢሰነዝርም ፋይዳቢስ ሆኖ በመቅረቱ፡ ወታደራዊው ሚዛን ሙሉ በሙሉ ወደ ኤርትራዉያን ታጋዮች ማጋደሉን አጉልቶ የሚያሳይ ነው። ናደው እዝን ለመደምሰስ የተሰነዘረው ብርቱ በትር መላዋን ኢትዮጵያን የናጠ፡ (ወያኖችንም በፍራት አንቀጥቅጠው እንደነበሩ ተራኪው አልገለጸውም፡ እኛም ይሁና ብለን ታዝበነዋል) ተጽዕኖው እስከ ሞቃዲሾና የሶቭየት ህብረት ቤተመንግስት ክሬምሊን ድረስ የደረሰ ነበር። ይህም ሲባል ከናደው እዝ መደምሰስ በኋላ ሶስት ከፍተኛ መኮንኖቿ በውጊያው የተማረኩባት ሶቭየት ህብረትም ብትሆን፡ ደርጉ እንደማያሸነፍ ገምግማለች። ልክ በዚያ የታሪክ መድረክም በሶቭየት ህብረት ውስጥ የመጣው የፖሊሲ ለውጥ ወይም ተሃድሶው ተጨምሮበት የክሬምሊን ሰዎች ከደርጉ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት አቀዝቅዘውት ነበር።
ናደው እዝን የመደምሰስ ውጊያ፡ ደርጉ የኤርትራዉያን ታጋዮችን እንቅስቃሴ ለመግታት የነበረውን ህልም ሙሉ በሙሉ ያበነነ፡ የኤርትራ ነጻነት በፍጹም አይቀሬ መሆኑን ለዓለም ግልጽ ያደረገ ድል ነው። ስለሆነም ከናደው እዝ መደምሰስ በኋላ የኤርትራ ጉዳይ በዓለም የዜና መድረክ ውስጥ ትልቅ ትኩረት አግኝቶ ነበር። ታዋቂው የታሪክ ተመራማሪና ጸሓፊው እንግሊዛዊው በዚል ደቪድሰን የጦርነቱን ውጤት በዓይኑ ከታዘበ በኋላ “ከድየን ብየን ፉ በኋላ፡ በአንድ የነጻነት እንቅስቃሴ የተከናወነ ግዙፍ ወታደራዊ ኦፕሬሽን” በማለት የኤርትራዉያን ታጋዮችን ድል ገልጾታል። የድየን ብየን ፉና ናደው እዝን የመደምሰስ ውጊያዎች በተጽዕኗቸው ማለትም የገዢዎችን ዕድሜ በማሳጠር ረገድ ተመሳሳይ ቢሆኑም እንኳን፡ እንደ ወታደራዊ ክንውን ግን ናደው እዝን የመደምሰስ ሂደት ከድየን ብየን ፉ’ዉ እጅግ የላቀና የገዘፈ ነው። ከዚህ የኤርትራዉያን ድል በኋላ በርካታ ሃገሮች የኤርትራ ጉዳይ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ አድርገዋል። ደርጉም አስቀድሞ አሻፈረኝ ሲል እንዳልነበረ የሰላም ውይይትን ለማድረግ ተገዷል።
ምንም እንኳን የታሪኩ ጸሃፊ ( ታጋይ ሰለሙን በርሀ) ከዚህ ብርቅ የኤርትራዉያን ታጋዮች ድል አንጻር የሕወሃትን መደናበር በቅጡ ባያቀርበውም ላደረገው ታሪክን በበኩሉ የመመዝገብ እርምጃ ምስጋናችንን እናቀርብለታለን።
ይህን በመሰለ የበርካታ ዓመታት ውጊያ ነጻ የወጣችን ልዑላዊት ሃገር በመደመር ይሁን በማባዛት ስሌት ‘አፈፍ’ ለማድረግ የምትቋምጡ ጅሎች ካላችሁ ደግሞ ህልም ወይም የቀን ቕዥት መሆኑን ለመግለጽም እንወዳለን። ህወሃቶችም የኤርትራን ህዝብ የተባበረ ጡንቻና የኤርትራ ህዝብን ትዕግስት በደንብ አድርጋችሁ ታውቁታላችሁ አግአዚ ይሁን ትግራይ ትግርኝ ይሁን ሌላ ፍልስፍና ኤርትራዉያንን አያወናብድም፡ ይልቅ ካርታችሁን አሻሽላችሁ መሬታችሁ ያልሆነን መሬት ለባለቤቱ ለኤርትራ ህዝብ በሰላም አስረክባችሁ በንስሃና በፍቅር ኑሩ ለማለት ነው። በሚገባችሁ ቋንቋ ግልጽ ለማድረግ “ናይና አይንህብይ ላይ እንዳማትና'ለ ኣይንደልይ!!!”
ደርግን በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ፡ ዲጅታሎቹን ያስመረረ- ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር - ታሪክ ዘላለም ይኖራል እየተነገረ!!!
ሰይብል ብከረባብስ!
“ውጥን ናይ ክሬምሊን፡ ጌርካዮ ኪነሚን!”
“ውጥን ናይ ደደቢት፡ ቀቢርካዮ ኣብ ድበት!”
“ውጥን አራት ኪሎ፡ ሓምሸሽካዮ ብድሎ!”
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5087
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 24 Mar 2022, 11:36
የኤርትራ ህዝብ ፍትሃዊ ትግል = የዩክሬን ህዝብ ፍትሃዊ ትግል = ወራሪንና ዕብሪተኛ ኃይልን ኣሸናፊ ትግሎች 
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5087
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 28 Mar 2022, 09:21
የዩክሬኑ "ዓሽሩም" ታሪክ እንደወረደ ከ https://www.theguardian.com/world/2022/ ... g-for-kyiv ወራሪ እብሪተኛ ሃይልን የመመከት ታሪክ በአውሮፓ ምድር እየተደገመ ነው፡ ዘለንስኪ ያውሮጳው ሻዕብያ ነው ያልነው ያለነገር ኣይደለም። ለመጪው ትውልድ ታሪኩ ታቅቦ ይቆይ ዘንድ ይህን የዩክሬኖች "ዓሽሩም" ገድል ከኛው ጋር አጣምረን እዚህ ዱለነዋል።
ሲጠቃለል
መለስ = ፑቲን = የማሌ (የማርክስና የሌኒን ግርፍ) ልዑላዊ ሃገሮችን የወረሩ ወፈፌ መሪዎች
የታላቋ ትግራይ ህልም = የታላቋ ሩስያ ህልም
ደደቢት ብቻ ኣይደለም ደደብ፤ ሩስያም(ክሬምሊንም) ጭምር ደደብ ነው!
ዘለንስኪ ጀግና ነው!
ድል ለሰፊው የዩክሬን ህዝብ! 