አሁን በየከተሞች የፌዴራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና የተለያዩ የፀጥታ ኃይሎች አልባሳትን ለጁንታ እና ሸኔ ደጋፊ ኃይላት ሰፍተው በማዘጋጀት ላይ ያሉ ታድነው እየታዙ ይገኛሉ።
በሰሜን ወሎ እና ተያያዥ ቦታዎች እንደታየው እና በቀጣይ ሌሎች ከተሞችም በተስተዋለው መሰረት አማፂ ኃይላትን በከተሞች ታዩ ብሎ በፎቶ ለማሳየት የሚደረገው ቅንጅታዊ እንቅስቃሴዎችን የሀገር ደህንነት ኃይላት አንጥረው እያጋለጡ ይገኛሉ።
ከእነዚህ የተቀናጀ የአሸባሪ ኃይላት እንቅስቃሴ ውስጥ በየከተሞች የመከላከያ እና ሌሎች ፀጥታ የሃይላትን ዩኒፎርሞች አሰፍቶ በምልምል የአሸባሪ አድብቶ ጠባቂ ሃይል በማስለበስ ከተሞች ተያዙ የሚል የሽብር ተግባሮች እየተከናወነ ይገኛል።
የሀገር መከላከያ ዩኒፎርሞችን በመልበስ ህዝብን በቀጥታ በመግደል ፤ “በስመ አስቸካይ ጊዜ አዋጅ ህዝብን እየጨረሰ ይገኛል” የሚል ክስ በመንግስት ላይ ለማቅረብም ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ቅድመ መረጃዎች እየተገኙ ይገኛሉ።
ህዝብ ለህዝብ የማጫረስ ስራን ልክ እንደ ገድል እና ጥበብ የሚቆጥረው የጁንታው ርዝራዥ እና ተላላኪው ሸኔ ለአንዴ እና መጨረሻ ጊዜ የሚቀበርበትን ወቅት እንደ ጣረሞት የሚቆጥረው እንደሆነ ተረጋግጧል ። ይህንን የጸጥታ ሃየላትን ልብስ እየሰፋ ያለውን እና ለጥቃቅን ጥቅም ሲል የጥፋት ሃይልን የማገዝ ፍላጎት የሚያሳይ ማንኛውንም ሃይልን ከመካከላችን የማጋለጥ ስራ ሁላችንም ልንሰራ ይገባል።
የሀገር መከላከያ በተናጠል ወደየትኛውም ሚሽን እንደማይላክ ሁሉም ህዝብ ሊያውቅ ይገባል። የሀገር መከላከል ስራ በጋራ በአመራር እና ሰብዓዊ ጉዳትን በቀነሰ መልክ እንደሚከወን የሚታወቀው ሰራዊት እንዳለን ሁሉም ተረድቶ ለየትኛውም የታቀደ የሃሰት መረጃ እኩይ ስራ ራስን ማጋለጥ አያስፈልግም።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሁላችንም ደጀን ነው ብለን አምነን ጁንታን ካለበት ጠራርጎ የማስወገድ ስራውን በአግባቡ እንደሚወጣ ተስፋ በማድረግ ሁላችንም በምንችለው አማራጭ ማገዝ ያስፈልገናል።
25/02/2014
ጠቃሚ የጤና ትምህርት
የልብ ድካም መንስኤዎችና መከላከያ ወሳኝ መንገዶች። ለጥንቃቄ መታየት ያለበት። መፍትሄዉ በእጃችን ነዉ:: ለማየት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ