Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42493
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ብርሃንና አምፖል፤ የኢዜማና ብልጽግና ድንቅ የምርጫ ፖለሚክስ

Post by Horus » 24 Feb 2021, 22:24

በእኔ ግምት ብልጽግና የምልክት (ሎጎ) እና የብራንድ (አርማ) ችግር አለበት ።

ይህን ተመልከቱ፤ የብልጽግና ፓርቲ መሰረታዊ ፍልስፍናው ሃብት ነው ወይም እድገት ነው ። ነገር የፓርቲው አርማ ያንድነት (የህብረት) ወይም የመደመር ምስል ነው። አሁን ደሞ ለምርጫ ምልክትነት ያቀረበው አምፖል ነው። ያ ደሞ የሚያመለክተው ብርሃን ነው ። የብርሃን ትርጉም እውቀት እንጂ መደመርም ሆነ ሃብታምነት አይደለም ።

ስለዚህ ፓርቲው መደመር፣ መበልጸግ ፣ እወቀት (ትምህርት) በሚሉ የተለያዩት ትኩረቶች መሃል ችግር አለበት ። ይህም ማለት ሃሳቡን ዲዛይን ያደረጉት ሰዎች ጥልቅ ህተት ነው።

በሌላ በኩል ኢዜማን ተመልከቱ ። የፓርቲው መሰረታዊ ፍልስፍና ፍትህ ነው ። የፓርቲው አርማ ብዕር (እውቀት) እና ሚዛን (ፍትህ) ነው ። ማለትም የብርሃን ሃሳብና ምልክት ያለው ባኢዜማ አርማ ውስጥ ነው ። አሁን ደግሞ የምርጫ ምልክቱ ያው ሚዛን ነው ። ትክክለኛ ዲዛይን ማለት ይህ ነው።

ይህም ሆነ ያ ብርሃኑ ነጋና አቢይ አህመድ ስለ ብርሃንና አምፖል የሚያደርጉት ስልጡን የምርጫ ፖለሚክስ እጅግ ውብ ነው !!!

እርግጥ ብርሃን የሚመነጨው ከአምፖል ነው ወይስ ከኤሌክትሪክ የሚለው ጉዳይ ወደ ፊት የምናየው ይሆናል :?: :!: