Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 44433
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

7ኛ የጥንቷ የጥዋቷ ፣ አዲስ ከተማ በመስከረም ትፈርሳለች! ተሰናበቷት!

Post by Horus » 29 Jul 2026, 21:35

ያ ማለት ደሞ አብነት ፣ ሞላ ማሩ እና አማኑኤል እስከ መሳለሚያ ሁሉ ይሰናበታል ማለት ነው። ይህ ሰፈር ከ100 አመት በላይ ታሪክ አለው ። 7ኛ ፍርድ ቤት ጎን ያለው ሰፈር ካሳ ገብሬ ሰፈር ይባል ነበር ። ከ7ኛ እስከ ል ዕ ልት ጸሃይ ሆስፒታል (ጦር ኃሎች) ድረስ የነበረው መንገድ ጅማ መንገድ ይባል ነበር ። ከ7ኛ እስከ አማኗኤል ቤተ ክርስቲያን ያለው የዛሬ ኮንጎ ጎዳና ዝም ብሎ የጭቃ መንገድ ነበር ። አማኑኤል ፊት ለፊት ያለው ሰፊ ባዶ መሬት የበቀለ ወያ ቤት የነበረበትና በቀለ ወያ ሜዳ ይባል ነበር ። ዙሪያ በሙሉ የዛፍ ጫካ ነበር!