Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7886
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ፎቶስይንተሲስ ተክል ላይ ተዓምር እንደሚሰራዉ የሰዉ ልጅ ላይ ተዓምር የሚሰራ መንፈስ ይኖር ይሆን?

Post by Naga Tuma » 29 Jul 2026, 05:47

ኣንድ የማልረሳዉ የአስረኛ ክፍል የባዮሎጂ ድንቅ ትምህርት ተክል የእራሱን ምግብ መስራት የሚችል ሲሆን የሰዉ ልጅ የእራሱን ምግብ መስራት ኣይችልም የሚል ነበር።

ኣሁን የምጠይቀዉ ኣዲስ ግንዛቤ መሠይ ነገር የመጣልኝ ወይም የተገለጠልኝ ሓምሌ ቀን 20፣ 2018፣ ዓም ነዉ።

ፎቶስይንተሲስ ማለት በሳይንስ ዉስጥ የታወቀ ነዉ። እንደ ግራቪቲ መኖሩ የታወቀ ቢሆንም የፎቶስይንተሲስ ምጥን የታወቀ ኣይመስለኝም።

ለመጀመርያ ግዜ ሓምሌ 20 የመጣልኝ ግንዛቤ ፎቶስይንተሲስ ለኦምኒፕረዘንት እና ለኦምኒፖተንት ጉልህ ምሳሌ ሆኖ ነዉ።

ኦምኒፕረዘንት የተክል ቅጠል ላይ የሚከሰት ነዉ።

ኦምኒፖተንት የተክል ፍሬ ዉስጥ ያለ ነዉ።

ኦምኒፕረዘንት የተክልን ቅጠል እያሰራ ተክሉ ፍሬ ያፈራል። ፍሬዉ ከፍሬ ወደ ፍሬ ይተላለፋል።

ለምሳሌ ባቄላ ባቄላነቱን ኣይረሳም። ወይን ወይንነቱን ኣይረሳም።

ፎቶስይንተሲስ ፍሬዉ ዉስጥ የምያስቀምጥለት ሜሞሪ ኣለ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ስለዚህ ፎቶስይንተሲስ ለተክል እንደ መንፈስ ነዉ ብሎ ማሰብ የሚቻል ይመስለኛል።

እኔ ያስተዋልኳቸዉ ብዙ ክስተቶችን ኣስታዉሼ ሳሰላስል ኦምኒፕረዘንት ማለት እና ኦምኒፖተንት ማለት ምሳሌዎች ያላቸዉ መሆኑን ተገንዝቤኣለሁ።

እንቆቅልሽ የሆነብኝ የተስተዋሉ ክስተቶችን እንዲከሰቱ የምያደርግ ምንድነዉ?

ለምሳሌ ኣሳማኝ ሕልም የምያሳይ ምንድነዉ?

መንፈስ ነዉ ማለት ይቻላል?

መንፈስ እንዲከሰት የምያደርግ ምንድነዉ?

በኦስሞሲስ እና ፎቶስይንተሲስ ተክል ፍሬ እንደምያፈራዉ የሰዉ ልጅም ባዮሎጂ በተባለዉ ፍሬ ያፈራል።

የተክል ፍሬ ጠንሳሽ የፀሓይ ብርሃን ዋነኛ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

የፀሓይ ብርሃን የሰዉ ልጅ ፍሬን ለመጠንሰስ ቀጥተኛ ሚና ኣለዉ ማለት የሚቻል መሆኑን ኣላዉቅም።

ስለዚህ ምጥኑ የማይታወቅ ፎቶስይንተሲስ በተክል ላይ ተዓምር እንደሚሰራዉ መንፈስ በሰዉ ልጅ ላይ ተዓምር የሚሰራ ነዉ ማልት ይቻላል?

Naga Tuma
Member+
Posts: 7886
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ፎቶስይንተሲስ ተክል ላይ ተዓምር እንደሚሰራዉ የሰዉ ልጅ ላይ ተዓምር የሚሰራ መንፈስ ይኖር ይሆን?

Post by Naga Tuma » 30 Jul 2026, 21:18

ቅዱስ መንፈስ፣ ፎቶስይንተሲስ፣ እና ግራቪቲ ለምድራችን ዋና ምሶሶዎች ወይም ኡቱባዎች መባል የሚችሉ ይሆን?

ከሆነ የዚህ ዋና ምሶሶዎች ኣስተዋዮች ዬትኛዉ የምድር ክፍል ነዉ ማለት ይቻላል?

ማስተዋሉ እኩል ካልሆነ የልዩነቱ ምንጭ ሊሆን የሚችል ምንድነዉ?

እነዚህን ምሶሶዎች ቀድመዉ ያላስተዋሉ ሊንጠለጠሉበት የሚችሉት ምሶሶ ምን ይሆን?

የዕዉቀት ምንጮችም መለኮታዊ ብይን ያላቸዉ ይሆን?

Post Reply