Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7758
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ግምታዊ መለኮታዊ ጥያቄ፥ የኣፄ ሀይለ ሥላሴ መንገስ እና የመንግስታቸዉ መናጋት በከፊል የትንቢቱ መፈጸም ኣካል ሊሆን ይችላል?

Post by Naga Tuma » 19 Jul 2026, 18:48

ይህን ጥልቅ ጥያቄ የምጠይቀዉ የሁለት ትዉልድ መለኮታዊ ክስተቶች ግዙፍ እንቆቅልሾች ስለሆኑብኝ ነዉ።

በኣንድ ጎሳ ቤተሰብ ዉስጥ የተከሰቱ መለኮታዊ ነገሮችን በአደባባይ ማንሳት ይከብዳል።

መለኮታዊ ነገሮችን እያስተዋሉ የተሳሳተ መንገድ ላይ ያሉ የሚመስለኝን ለመምከር ኣለመጣር ስህተት ሊሆንብኝ ይችላል።

የጥያቄዉ ኣንዱ መሠረት የኣፄ ሀይለ ሥላሴ ከዙፋን የተነሱ ዕለት እና የራሳቸዉን ህይወት ማለፍ ኣስቀድሞ ሕልም ያዩ መምህሬ ያረፉ ቀን መገጣጠም ወይም መቀራረብ ነዉ።

ሁለቱ የተከባበሩ እንደነበሩ ግምት ኣለኝ።

በቅርብ የሰማሁኝ ታሪክ ኣፄ ሀይለ ሥላሴ መምህሬዉ ይኖሩበት የነበረ አከባቢ የታወቀ እና ስሙ ይከበር ነበረ የተባለ ቃሉን ኣንድ ግዜ ካባ ኣልብሰዉት ነበር ይላል።

ኣፄ ሀይለ ሥላሴ የአከባቢዉን ከተማ ሃገረ ህይወት ብለዉ ሰይመዉት ነበር።

በእነዚህ ታሪኮች ላይ ተጨማሪ የሆነዉ መለኮታዊ እንቆቅልሽ የትላንትና ሁለት ወር ያየሁኝ ተዓምራዊ ሕልም ነዉ።

የመምህሬዉ ወንድም ልጅን፣ የእኔም እናት ወንድም ልጅን በሕልም ኣየሁኝ።

ሕልሙ ኣሳዛኝ ባይመስለኝም ማስታወሻ ጽፌ ኣለፍኩኝ።

ሰንበት ብዬ ህይወቷ ማለፉን መርዶ ሰምቼ በጣም ኣዘንኩኝ። መርዶዉን ሳስታዉስ ሁሌ የሚተናነቀኝ ያየሁኝ ሕልም የመሰለኝ እና መርዶዉ ተቃራኒ ስለሆኑብኝ ነዉ።

ቢሆንም የሕልሙ ተዓምራዊነት መለኮታዊ አሰራር ስለመኖሩ ተገልጦልኝ ኣረፈች ሳይሆን እግዝኣብሔር ዬለም ያለዉን ልትቀብር ሄደች እያልኩ ኣነባለሁ።

ይህ የሁለት ትዉልዶች ሕልም በኣንድ ቤተሰብ ዉስጥ መከሰት ምን ያመለክታሉ እያልኩ እራሴን እጠይቃለሁ።

በቤተሰቡ ዉስጥ ያለ ስም ኣንዴ ከዚህ ነዉ፣ ሌላ ግዜ ከዝያ ነዉ እየተባለ ለረጅም ግዜ ኣወዛጋቢ ሆኖብኝ ተመሳሳይ የፈረዖ ስም እንደነበረ ከወራት በፊት ለመጀመርያ ግዜ ኣነበብኩኝ።

እኔ ስለ መለኮታዊ ነገር ያላጠናሁ ብሆንም እነዚህ ታሪኮች ስለ ሁለት መንፈሳዊ ነገሮች ኣለመጣጣም ኣመልካቾች ይሆናሉ ወይ እላለሁ።

የአሓዱ ኣምላክ ቀዳማዊ ነብይ ጥንታዊ ኢትዮጵያዊ ፈረዖ ነበረ።

ምናልባት ያ መንፈስ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያልነጠፈ ይሆን?

ያልነጠፈ መንፈስ ለመሆኑ ኣመልካቾች አሓዱ ዓምላክ ማለት እና በተጨማሪም ነብ እና ደንፋ ተብለዉ የሚከበሩ ናቸዉ።

ከብዙ ዓመታት በፊት በጣም የደነቁኝ ነገሮች በጀርመን ደንፋ እና ፕፈርድ የሚሉ ቃላት መኖራቸዉ እና በኣንድ ወቅት የጀርመን ባንዲራ ቀለማት ጥቁር፣ ቀይ፧ እና ነጭ ቀለማት የነበረ መሆኑ ነዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ያልነጠፈ የስደት ዘመን መንፈስ ኣለ ወይ ኣንዱ ጥያቄ ነዉ።

ሌላዉ መንፈስ የእስራኤሉ እየሱስ የሚባለዉ ነዉ ማለት ይቻላል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የኖረ ቀዳማዊ መንፈስ እና በኋላ የመጣዉ የእስራኤሉ እየሱስ መንፈስ የማይጣጣሙ ከሆነ ካባ ኣስለብሶ፣ ሃገረ ህይወት ኣስብሎ የሚጋፋ መንፈስ ሊሆን ይችላል?

እኔ ለዚህ ጥያቄ መልስ በፍጹም ዬለኝም።

መመለስ የሚችሉት ስለ መለኮታዊ ነገሮች ኣጥንታዉ እናዉቃለን የሚሉ ሰዎች ናቸዉ።

ስለ መለኮታዊ ነገሮች ባለሙያ ባልሆንም እግዝኣብሔር ጽድቅን የሚባርክ፣ ሃጥዓትን የሚገስጽ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።