Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11976
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

አዲስ ጥቃት : በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ በሚገኙ አካባቢዎች በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ መጠነ-ሰፊ ጥቃት

Post by MINILIK SALSAWI » 01 Jun 2026, 23:52

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን ዒላማ ባደረገ አዲስ ጥቃት 10 ክርስቲያኖች መገደላቸውን፣ ንብረታቸው መውደሙንና የተቀሩትም መፈናቀላቸው ተዘገበ።

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ከ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተቀሰቀሰው በዚህ ጥቃት የሰው ሕይወት ከመጥፋቱም ባሻገር ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸውንና ከፍተኛ የንብረት ዘረፋና ውድመት መድረሱን የአካባቢው መረጃዎች አመልክተዋል። በዚህ ጥቃት ከ101 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የጠላታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ ወድሟል። የካራ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ንብረት የሆኑ ልዩ ልዩ የአገልግሎት መስጫ ቤቶችም ተቃጥለዋል።

የሰው ኃይል ጉዳት እና መፈናቀል በወረዳው ሥር በሚገኘው ጠላታ ጨፋ ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃት እስካሁን የ10 ሰዎች ሕይወት በግፍ ማለፉ ተረጋግጧል።

በጥቃቱ ወቅት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መኖሪያ ቤቶች ተለይተው እየተቃጠሉና ከብቶቻቸውን ጨምሮ በርካታ ንብረቶቻቸው እየተዘረፉ መሆኑ ተመልክቷል።

በዚህም ምክንያት ነዋሪዎቹ አካባቢያቸውን ለቀው ሱንቴ ወደሚባል ስፍራ ለመሰደድ ተገደዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በዛው ወረዳ በሚገኘው ካራ ኩፍቴና ቀበሌ የነዋሪዎች ቤቶች እየተቃጠሉ በመሆኑ፣ ሕዝቡ የመድኃኔዓለምን ታቦት ይዞ ሕይወቱን ለማዳን ወደ ሱንቴ አካባቢ መሸሹ ታውቋል።

የጥቃቱ ወቅታዊ ሁኔታ የአካባቢው ምንጮች እንደሚጠቁሙት፣ ጥቃቱ የተፈጸመው በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለው አጠቃላይ ትኩረት ወደ አገራዊ ምርጫው ባዘነበለበት ማግስት፣ የተፈጠረውን የጸጥታ ክፍተት እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ነው።

ይህ በተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚፈጸምበት የሚነገረው የአርሲ አካባቢ ኦርቶዶክሳውያን፣ አሁንም በምርጫው ዋዜማና ዕለት የጥቃት ሰለባ ሆኗል።

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ በሚገኙ አካባቢዎች በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ መጠነ-ሰፊ ጥቃት በአዲስ መልክ እየተፈጸመ ያለው የሁሉም ትኩረት በሀገራዊ ምርጫ ላይ ማረፉን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ነው ሲል ዜናውን ያጠናቀረው "ስምዐ ጽድቅ" የተሰኘ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ዘግቧል።



Post Reply