እኔ ለራሴ ነፍስ ካወቅኩኝ ጀምሮ ሰንደቅ አላማዬን ጥዬ አላውቅም! ዛሬም ሰንደቅ አላማ አለኝ ።
የእኔ ሰንደቅ አላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው! አለቀ!
በሕይወት እስካለሁም የሚኖረኝ ሰንደቅ ይህ ብቻ ነው
ዛሬ ቴዲ አፍሮ ባነሳው የሰንደቅ አላማ ማንሳት ጥሪ ላይ ያለኝ አቋም አንድና ግልጽ ነው ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው።
በየዘመኑ የሚነሱና የሚወድቁ መንግስቶች የራሳቸውን አርማ ሊጨምብሩበት ይችላሉ ፣ ለምሳሌ አንበሳ ፣ ኦዳዛፍ ማጭድና መዶሻ ወዘተ ይህ አንድ መንግስት በራሱ ቢሮዎች የሚሰቅለው አርማ ነው።
ተራው ሕዝብን ግ ን ልሙት ባንዲራ እንዳይጠቀም የማድረግ መንግስት ምንም አይነት መብት የለውም።
ሌሎች ጎሳዎች ፣ ድርጅቶች ያሻቸውን ባንዲራ መስቀል ይችላሉ ። ነገር ግ ን መንግስት በፍጹም አንድን ዜጋ አረንጓዴ ቢጫ ቀyሰንደቅ አታውለብልብ የማለት መብት የለውም
ስለዚህ ከቴዲ ጥሪ ጋር የሚስማሙት ወጣቶች ባንዲራቸውን ያለ ፍርሃት ማውለብለብ አለባቸው