Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15415
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ቴዲ-አፍሮ የሰላም ወንጌል ሓዋርያ:ቴዲ ዘ-ኢትዮጵያ እንደ ነብዩ ኤርምያስ "የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ማቅ ልበሺ፤ በዐመድም ላይ ተንከባለይ፤ አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ምርር ብለሽ አልቅሺ" 6፥26።

Post by Abere » Yesterday, 10:49

ቴዲ-አፍሮ የሰላም ወንጌል ሓዋርያ:ቴዲ ዘ-ኢትዮጵያ እንደ ነብዩ ኤርምያስ "የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ማቅ ልበሺ፤ በዐመድም ላይ ተንከባለይ፤ አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ምርር ብለሽ አልቅሺ" 6፥26። ታዲያ ማነው ወንጌል የገባው?
ነብይ በአገሩ አይከበርም እንዳለው አነ አፈ-ሰፊ ኦሮሙማዎች እና ጴንጤ ነብይነን ባይ ወጠምሻዎች ቴዲ-ተላልፎ የሰጠን፤ እስረው እስረው፤ ይጮኻሉ።
ምን አጠፋ? ነውራቸውን መስተዋት ሁኖ ጉድፋቸው እንድታያቸው በጨለማ ሳይሆን በብርሃን እንድሰናዱ በገሰጸ። በእውነት ኢትዮጵያ ደህና ነች? ልጆቿ በየክፍለ ሀገረ በሰላም ወጥተው ይገባሉ ፤ ዱር ሜዳ፤ ጋራ ሸንተረሩ፤ አድባሩ፤ የአራዊት እንሰሳው በጸጥታ ሀሴት ለፈጣሪያቸው ያደርጋሉ ወይስ በተኩስ እሩምታ ይታወካሉ? አሰገዳደል እና ሰው አሰቃቀል የፋሽን ቄንጥ አልወጣለትም? ታዲያ ይህ እኩይ ምግባር ይብቃ፤ ወንጌላዊ ስራ ብቻ ሳይሆን ሃይማኖት ዐልባ ለሆነ ሰዋዊ ፍጥረት እንኳ ሞራላዊ ነው።

በዘፈን እና ዳንስ ለመደሰት እኮ ቴድ አፍሮ ኮንስረት ከመሄድ ከጴንጤ ጉባዔ መሄድ ይመረጣል። የጴንጤ ዘፈን ወገብ ያስፈትሻል፤ ስሜት ያነቃቃል፤ ቆነጃጅት ጠቦት ለመምዘዝ የደራ ገባያ ስፍራ ነው፡