ፅኑ ነው እምነቴ ሆሆሆ
ፅኑ ነው እምነቴ ሀሀሀ
የጠላቴ ሳንጃ አሀሀ
ቢደቀን ከፊቴ አሀሀ
አላፈገፍግም እቆማለሁ እኔ
በእሳት ለነደደው ቤተ እምነቴ
ለተደፈረችው ለምስኪኗ እህቴ
በግፍ ለታረደው ወንድሜ
ባጭር ለተቀጨው ለህፃኑ ልጄ
በግፍ ለታረደው ወገኔ
አላፈገፍግም እቆማለሁ እኔ
አላፈገፍግም አሃሃ
ፅኑ ነው እምነቴ ሆሆሆ
የጠላቴ ሳንጃ አሃሃ
ቢደቀን ከፊቴ ሆሆ
አላፈገፍግም እቆማለሁ እኔ
በትግል መንገድ ላይ ወድቄ (2)
ጓዶቼን መቼ አጣሁ ፈልጌ (2)
የግጥሙ ደራሲ በአገዛዙ የግፍ እስረኛ የሆነው ዶ.ር ወንዶሰን አሰፋ ኃ/ማርያም