Finfinne Press
EBC እና ፋና ቴሌቪዥን በመላ ሀገሪቱ የተከበረውን የኢድ አልፈጥር በአል ድባብ እያሳዩን ነው። ትንንሽ ከተማዎች ላይ ሳይቀር አከባበሩን እየዘገቡ ነው። ከመቐለ እስከ ሞጣ ከደሴ እስከ ሆሳዕና እየዳሰሱ ነው።
እስካሁን ግን የምስራቋ ትልቋ ከተማ በሆነችው ጅጅጋ ከተማ የተደረገውን የኢድ ሰላትና የአከባበር ስነስርዓት አልዘገቡም
#አብይ ከሙስጠፌ ጋር ስለተጋጨ በሶማሌ ጅጅጋ በአል አይከበርም ነው ?? .. ሙስጠፌ በበአሉ ስለሚታደም የሚዲያ ሽፋን አያስፈልገውም ነው ?? ወይስ ፋናና EBC ሙስጠፌን ከአብይ እኩል አኩረፈውታል
#የብልፄ ነገር የሚገርም ነው ... ለፖለቲካ ተብሎ እንኳን ማስመሰል አይችሉም። ፓርቲው ውስጥ የሆነ ነገር ከተፈጠረ ከጠ/ሚኒስትሩ እስከ አውራጃ ድረስ ያለው ካድሬ ይጋጫል ያኮርፋል። ሚዲያውን የሚመራው ዳንኤል ክብረት ደግሞ እገሌን አብይ ስላኮረፈው እናንተም በዜና ዘገባችሁ አኩሩፉ ብሎ ትዕዛዝ ያስተላልፋል። ይፈፀማል !
አይ #ብልፄ ... አሁን ኩርፊያውን ተውና ሙስጠፌ የታደመበትን የኢድ ሰላት አሳዩን። እኛም ደህንነቱን እናረጋግጥ