ለአብይ ማስጠንቀቂያ:አገሪቱ ውስጥ ያለም ችግር ከምቼውም ግዜ በላይ አሳስቢ ነው : አብይ ግዜው ሳይመሽበት ቢያስብበት ጥሩ ነው
ኑሮ ውድነት
ዶላር ከ 25 ብር ተነስቶ 157 ብር ገብቷል :: ምንድነው ጥቅሙ? ያመጣውን ጥቅም ለምን አይነግሩንም? ምናልባት ለባለስልጣኖች ጠቅሞ ይሆናል: ምክንያቱም አገሪቱ ሙስና በሙስና ሆናለችና:: ግን የዶላር ጭማሪው ያመጣው መዘዝ ቀላል አይደለም: መዓት ችግር አለው ግን ዋናው አሳሳቢው በመድሃኒት ላይ በየግዜው የሚደረገው ጭማሪ ነው:: መንግስት ከዚህ በፊት ከግል ፋርማሲዎች ብዝበዛ ሕዝቡን ለማዳን ከነማ ፋርማሲን በከተማው በተለያዩ ቦታዎች ከፍቶ ሥራ ከጀመረ ቆይቷል:: ዋጋቸውም አስር ግዜ የማይቀያየር ነበር:: አሁን ግን ከአንድ ሳምንት ብኋላ አስር ብር የነበረው 100 ብር ሆኖ ይገኛል:: አብይ እዚህ አገር ምን አይነት በሽተኞች እንዳሉ የሚያቅ አይመስልኝም :: ብዙዎች አቅም የሌላቸው የታይፕ 1 ስኳር ታማሚዎች ናቸው: ብዙዎቹ ሕፃናት ናቸው:: አነዚህ ሰዎች ሁሌም ካለ እንሱሊን መኖር አይችሉም እናም በየቀኑ ወጪ አለባቸው:: ሲሪንጅ አራት ብር የነበረው 10 ብር እንሱሊን 80 ብር የነበረው አሁን 500 ብር ነው:: የስኳር መጠን መለኪያ stripe (50) ከ 200 ብር ወደ 1300 ገብቷል:: አና እንዴት አርገው ነው የሚችሉት? ይህ ሁሉ ትርጉም የሌለው የዶላርና ብር አለመጣጣም ነው ::
እኔ የምለው ለአብይም ሆነ ለመንግስቱ ሳይምሽብህ አስብበት: አንተ ባታስተካክለው የሚመጣው መንግስት በግዴታው ያስተካክላታል::
ሁለተኛው ችግር አገሪቱ ውስጥ ፍትሃዊ ያልሆነ ደሞዝ አከፋፈል ነው::
አንድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማስተር የተመረቀ ሰው የሚያገኘው ደሞዝ ለምን በየመስሪያ ቤቱ ይለያያል? ዩንቭርስቲ ውስጥ የሚያስተምረው 25 ሺ ሲያገኝ ሌላው የመንግስት መስሪያ ቤታ ያለ ግን 12500 ያገኛል: ለምን?
አንዱ መስሪያ ቤትና ሌላው የመንግስት መስሪያ ቤት ያለው የደሞዝ ስኬል ለምን ይለያያል? ባንክም ሆነ አየር መንገድ የመንግስት መስሪያ ቤት እንደመሆናቸው የሚከፍሉት ከሁሉም መስርያ ቤት ጋር ተመሳሳይ መሆን ነበረበት:: ይህ መስተካከል አለበት::
ከዚሁ ደሞዝ ጋር ተያይዞ በማስትሬት የተመረቁ ሲቪል ሰራተኞች ደሞዝና የፖሊስ አባላት አንዴት ደሞዛቸው አንዴት አይን ባወጣ መልኩ ሊራራቅ ይችላል?
አንድ እረዳት ኢንስፔክተር የሆነ የፖሊስ አባል ደሞዙ 17 ሺ ሲሆን በማስተር የተመረቀ ሰው ደሞ 12500 ነው:: አንዴት ሊሆን ይችላል::በእጃቸው የሚደርሳቸውስ ምን ያህል ነው? ረዳት ኢንስፔክተሩ 17 ሺ ሲያገኝ የማስትሬት ምሩቁ ደሞ 9100 ያገኛል:: ማስትሬት የያዘው ሰው የፈለገ ምንም ዓመት ቢቀመጥ የሚያገኘው 9100 ነው አድገት የለ ጭማሪ የለ: ረዳት ኢንስፔክተሩ ግን አስከ 39 ሺ ይደርሳል:: መንግስት አለው ወይ?
ይህ ከቅናት የመነጨ አይደለም:: ማስትሬት ለማያዝ አንድ ሰው የሚያየው ፍዳ ቀላል አይደለም:: አድሜውን ሁሉ በትምህርት ነው የሚጨርሰው:: አስራ ሁለትኛን ክፍል በጥሩ ውጤት አልፎ አንደኛ ዲግሪውን ይዞ አንደገና ማስትሬት ለማግኘት ቀላል አይደለም::
ረዳት ኢንስፔክተር ግን እንዴት እዚህ ደረሰ? ምንም ትምህርት ሳይኖረው ፖሊስ ይሆናል ሁለት ዓመት ይሰራል መአረግ ያገኛል እንዲህ እንዲህ እያለ በየሁለት ዓመት መአረግ እያገኘ ኢንስፔክተር ይሆናል:: አና ይህን ሰው ነው ከማስተር ካገኘ የበለጠ አይተከፈለ ያለው::
እዚህ አገር ፖሊስ ሲባል scam ነው የአጭበርባሪ ስብስብ :: መከላከያ ይሻላል፡፡
አሁንም እላለሁ መንግስት ሳይመሽብህ አስተካክል ::
ሌላው ትልቁ ነገር ሙስና ነው: ከግብር ከህዝቡ የሚሰበሰበው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በጣም ብዙ ነው:: ግን የት ይገባል? ይሄ መንግስት ከመጠን በላይ በሙስና የተዘፈቀ ነው :: እናም መንግስት ይሄን የሙስና ሃረግ ሊበጥስ ይገባል:: አልሰማም ካልክ ዋጋውን ያገኛል፡፡ እናም የሚመጣው መንግስት ያስተካክለዋል::
ሲጠቃለል :
የመድሃኒት ዋጋው እንደነበረው ይሁን
የስቪል ሰራተኛ ደሞዝ እንደገና ይታይ:: ሁሉም ሰራተኞች የሚከፈላቸው ፍትሃዊ ይሁን የመንግስት ሰራተኞች አድገትና ጥቅማጥቅም ይኑራቸው:: ሁሉም ሰራተኞች በተመሳሳይ ላይ ያሉ አኩል ይከፈላቸው::
በሙስና የተተበተበው መንግስት ራሱን ያጥራ
Last edited by Abaymado on 16 Mar 2026, 13:22, edited 1 time in total.
-
Digital Weyane
- Senior Member
- Posts: 10130
- Joined: 19 Jun 2019, 21:45
Re: ለአብይ ማስጠንቀቂያ:አገሪቱ ውስጥ ያለም ችግር ከምቼውም ግዜ በላይ አሳስቢ ነው : አብይ ግዜው ሳይመሽበት ቢያስብበት ጥሩ ነው
በመዲናችን አዲስ አበባ አንድ ስኩዌር ኪሎሜትር የቆዳ ስፋት ያለው ቦታ ቡዙ ቢልዮን ዶላሮች ፈሶበት ጥቂት ሰዎች ተንደላቀው የሚኖሩበት ዱባይ መስሏል።
ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀልና በከፍተኛ የውጭ ብድር የተገነባው ስፍራ የከተማው ነዋሪዎች <<አፓርታይድ ሰፈር>> ብለው ይጠሩታል ምክንያቱም ለድሆች የተከለከለ ብልፅግናዎች ብቻ የሚኖሩበት ሰፈር ነውና።
ኢትዮጵያ ሃገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ
ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀልና በከፍተኛ የውጭ ብድር የተገነባው ስፍራ የከተማው ነዋሪዎች <<አፓርታይድ ሰፈር>> ብለው ይጠሩታል ምክንያቱም ለድሆች የተከለከለ ብልፅግናዎች ብቻ የሚኖሩበት ሰፈር ነውና።
ኢትዮጵያ ሃገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ
Re: ለአብይ ማስጠንቀቂያ:አገሪቱ ውስጥ ያለም ችግር ከምቼውም ግዜ በላይ አሳስቢ ነው : አብይ ግዜው ሳይመሽበት ቢያስብበት ጥሩ ነው
እንደ እኔ ከሆነ ፖሊስ የሚባል እንደገና መዋቀር አለበት፡፡ ይህንን ፖሊስ ያቋቋመው ወያኔ ነበር፡ ወያኔን እንዲመስል ተደርጎ ነው የተሰራው፡፡ ፌድራልም ሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ቢፈርስ ጥሩ ነው፡፡፡
ሌላው ነገር እነዚህ ፖሊሶች ከከተማ ቦታዎች ቢርቁና በሲቪል ቢተኩ ጥሩ ይመስለኛል፡፡
እንዲሁም ቀበሌ የሚባል ነገር ቢወገድና በዘመናዊ መንገድ ቢቋቋም ጥሩ ሃስብ ነው፡፡
ሌላው ነገር እነዚህ ፖሊሶች ከከተማ ቦታዎች ቢርቁና በሲቪል ቢተኩ ጥሩ ይመስለኛል፡፡
እንዲሁም ቀበሌ የሚባል ነገር ቢወገድና በዘመናዊ መንገድ ቢቋቋም ጥሩ ሃስብ ነው፡፡
-
ethiopianunity
- Senior Member
- Posts: 10884
- Joined: 30 Apr 2007, 17:38
Re: ለአብይ ማስጠንቀቂያ:አገሪቱ ውስጥ ያለም ችግር ከምቼውም ግዜ በላይ አሳስቢ ነው : አብይ ግዜው ሳይመሽበት ቢያስብበት ጥሩ ነው
ብር የሚጥሉት የውጭ ሰዎች እንደልባቸው ገብተው እንዲገዙ እንዲጠቀሙ ነው። ለህዝቡ መኖር ውድቀት ነው። አብዛኛው መለስተኛ ሀገሮች፣ የሀብታም አገርን ለመሳብ ሴቶቻቸውን ሀጻናትን፣ ማእድንን ወዘተ ይሸጣሉ። አገሩን ሁሉ ነገር ለመሸጥ ነው።
ያልከው ትክክል ነው። ግን ሁሉም እኩል ይከፈል የማለት አልስማማም ምክንያቱም ስራው በጣም ለአገሪቱ የሚጠቅም ነገር እውነታ በሆነ ስራላይ የሚሳተፉ ለምሳሌ ውትድርና የህይወት ጉዳይ ስለሆነ በደንብ መከፈል ይኖርበታል። ሙስና ሙሉ በሙሉ መወገድ ይኖርበታል። ለምን ወታደሩም ጥሩ ቢከፈለው፣ በደንብ ስራውን ላይሰራ ይችላል በማስመሰል።
ያልከው ትክክል ነው። ግን ሁሉም እኩል ይከፈል የማለት አልስማማም ምክንያቱም ስራው በጣም ለአገሪቱ የሚጠቅም ነገር እውነታ በሆነ ስራላይ የሚሳተፉ ለምሳሌ ውትድርና የህይወት ጉዳይ ስለሆነ በደንብ መከፈል ይኖርበታል። ሙስና ሙሉ በሙሉ መወገድ ይኖርበታል። ለምን ወታደሩም ጥሩ ቢከፈለው፣ በደንብ ስራውን ላይሰራ ይችላል በማስመሰል።
Re: ለአብይ ማስጠንቀቂያ:አገሪቱ ውስጥ ያለም ችግር ከምቼውም ግዜ በላይ አሳስቢ ነው : አብይ ግዜው ሳይመሽበት ቢያስብበት ጥሩ ነው
ለምን 100 ሺ ኣይከፍላቸውም፣ ግን ለሁሉም ተገቢ የሆነ መሆን ኣለበት፤ ወታደርና ፖሊስ የተለያዩ ናቸው፤ ወታደር ይገባዋል ግን አሱም ቢሆን በተጠና መልኩ መሆን አለበት፤ ሌላው አገር የሚከፍለው አንዴት ነው? ወታደር ከተማረ በላይ ያገኛል?ethiopianunity wrote: ↑16 Mar 2026, 15:08ብር የሚጥሉት የውጭ ሰዎች እንደልባቸው ገብተው እንዲገዙ እንዲጠቀሙ ነው። ለህዝቡ መኖር ውድቀት ነው። አብዛኛው መለስተኛ ሀገሮች፣ የሀብታም አገርን ለመሳብ ሴቶቻቸውን ሀጻናትን፣ ማእድንን ወዘተ ይሸጣሉ። አገሩን ሁሉ ነገር ለመሸጥ ነው።
ያልከው ትክክል ነው። ግን ሁሉም እኩል ይከፈል የማለት አልስማማም ምክንያቱም ስራው በጣም ለአገሪቱ የሚጠቅም ነገር እውነታ በሆነ ስራላይ የሚሳተፉ ለምሳሌ ውትድርና የህይወት ጉዳይ ስለሆነ በደንብ መከፈል ይኖርበታል። ሙስና ሙሉ በሙሉ መወገድ ይኖርበታል። ለምን ወታደሩም ጥሩ ቢከፈለው፣ በደንብ ስራውን ላይሰራ ይችላል በማስመሰል።
ለምሳሌ ኣሜሪካ ሲቪል ሰራተኛ አና ወታደር ደሞዛቸው ይለያያል? አይደለም በጣም ተቀራራቢ ነው ፥ ቼክ ማረግ ትችላለህ፤
አኔ አያልኩ ያለሁት ከተማ ውስጥ ሲያውደለድል የሚውለውን ፖሊስ ነው፤ አነሱ አድገት ኣላቸው፥ ከፍተኛ ጥቅማጥቅም ኣላቸው አበል አላቸው፤ ሲቪሉ ግን ምንም የለውም::
Just look this information in America:
Here is a comparison based on data from the U.S. Bureau of Labor Statistics (BLS), the U.S. Government's General Schedule (GS) payscale, and the 2025 Military Pay Tables.
1. Entry-Level / New Hires
*Note: Military pay is for new enlistees (E-1 to E-3). Police pay varies wildly by city and state.*
Civilian (National Average): Roughly $40,000 – $55,000 per year for a bachelor's degree holder in a general field (admin, sales, junior tech).
Police Officer: Roughly $45,000 – $65,000 per year. This varies significantly. A small-town officer might start near $38k, while a large city like NYC, LA, or Chicago can start over $60k (excluding overtime).
Military (Enlisted): Roughly $25,000 – $35,000 in Base Pay.
However: If you add in Basic Allowance for Housing (BAH) and Basic Allowance for Subsistence (BAS), which are tax-free, the total cash compensation for a junior enlisted member is often closer to $45,000 – $55,000, depending on where they are stationed and if they have dependents.
2. Mid-Career (5–10 Years Experience)
*Military: Sergeant (E-5) or Staff Sergeant (E-6). Police: Officer with seniority or Corporal. Civilian: Experienced professional.*
Civilian (National Average): $65,000 – $90,000.
Police Officer: $70,000 – $95,000.
Key Factor: Police at this level often earn significantly more through overtime. In many major cities, police officers can earn $100k+ by working details or extra shifts, which is not typical for salaried civilians.
Military (Enlisted): $35,000 – $50,000 in Base Pay.
Total Compensation: With BAH, BAS, and potentially Cost of Living Allowance (COLA) , the total cash package is usually $60,000 – $85,000. Because BAH is based on local housing costs, a military member in San Diego or NYC will have a higher total cash compensation than one in a rural area to keep their purchasing power equal.
3. Senior / Leadership Level
*Military: Senior NCO (E-7 to E-9) or Officer (O-3/O-4). Police: Sergeant, Lieutenant, or Chief. Civilian: Manager/Director.*
Civilian (National Average): $95,000 – $150,000+.
Police (Supervisor/Chief): $90,000 – $120,000 (Supervisors). Police Chiefs in major cities can earn $150,000 – $250,000+.
Military (Officer/O-4):
Base Pay: $75,000 – $95,000.
Total Compensation: With allowances, often $100,000 – $140,000.