Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7158
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ታቦት፣ ፋኖነት፣ እና ፊደል፥ መሠረት ያላቸዉ የጥንታዊ ኢትዮጵያ የሃይማኖት፣ የጀግንነት፣ እና የፈጠራ እሴቶች ናቸዉ

Post by Naga Tuma » 21 Feb 2026, 15:47

ታቦት በቃሉ ወይም ቃልቻ ምሳሌነት የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ ቃላት ጠባቂ ነዉ ከተባለ ሃምሳ ዓመታት ኣልፈዋል።

ይህ ማለት ታቦት ከጥንት ኢትዮጵያ ጀምሮ መሠረት ያለዉ እና ያልተቋረጠ መለኮታዊ መስመር ላይ ያለ ነዉ።

ስለዚህ ታቦት የኢትዮጵያ የሃይማኖት እሴት ነዉ።

ስለ ፋኖነት እና ባንዳነት በልጅነቴ የሰማሁኝ የቅርብ ግዜ የነበረ ታሪክ ወጎች ዉስጥ ነበር።

በኣጭር ቃላት ፋኖዎች የወራሪ ጣልያን ወታደሮች ቺዝ ምን እንደሚመስል ፈጽሞ ያላዩ እና ባንዳዎች የወራሪ ጣልያን ወታደር ስር ገብተዉ ቺዛቸዉን በልተዉ ይገማል ያሉ ነበሩ።

የጣልያን ወራሪ ወታደሮች ቺዝ ይዘዉ የሞቀ ሃገር ዉስጥ ገብተዉ ለባንዳዎች ቢወረዉሩ ባንዳዉ በወራሪዉ የተወረወረለት ቺዝ ይገማል ማለት ጀምሮ ነበር።

ፀጋዬ ዳንደና በዘ ዘመን የኖረ ቢሆን ኖሩ ዘፈኑ ማፍ ከጄላ ዸቅጤ ቺዚ ግራዝያኒ እንደሚሆን መገመት ይቻላል።

የዛን ዘመን ፋኖዎችን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ፣ እና በዉጪም ሃገር ማጋነን ኣይቻልም። የዘላለም ገናና ስለሆነ ነዉ።

ካልተሳሳትኩ ፊደል ከላቲን ኣልፋቤት በፊት የተፈጠረ እና የበለጸገ የሰዉ ልጅ ፈጠራ ነዉ።

ሀ ግዕዝ፣ ሁ ካብዕ፣ ሂ ሳልስ፣ ወዘተ እና አ ቡ ጊ ዳ እያለ የበለጸገ ሌላ ኣልፋቤት መኖሩን ኣላዉቅም።

የህዳሴ ዘመን ከተባለ ማደስ እነዚህ ሁሉ የሃገር መሠረታዊ እሴቶችን ነዉ። ኣይዴለም?

ከሆነ ስለ እነዚህ መሠረታዊ እሴቶች ላይ ኣዋቂ ነን ባዮች ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ተወያይተዉ መስማማት ኣይችሉም?

ሁሉም ካልተስማሙ የሚስማሙት ክፍል ሆነ ብለዉ ወደፊት ማራመድ ኣይችሉም?