Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4931
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

“የአማራ መንገድ” - "ግዮናዊነት" ከሚለው የምስጋናው አንዱዓለም ምሕረቴ መጽሓፍ ዬተቀነጨበ ብርቅ እይታ

Post by Meleket » 12 Feb 2026, 10:18

“የአማራ መንገድ” - "ግዮናዊነት" ከሚለው የምስጋናው አንዱዓለም ምሕረቴ መጽሓፍ ዬተቀነጨበ ብርቅ እይታ እይታ- ከጻፉ አይቀር እንዲህ ነዉ እንጂ! :mrgreen:
Meleket wrote:
17 Nov 2022, 06:28
ለግንዛቤ ያህል ነው። ምንም እንኳ በመጸሐፉ ሙሉ ይዞታ ሙሉ በሙሉ ባንስማማም፤ የደራሲውን ትጋት በፍጹም አለማድነቅ አይቻልም። አማራ ነኝ የሚል ሰው ሁሉ ቢያነበው ብዙ ቁምነገር ሳይቀስምበት አይቀርም። ትንሽ እስቲ ከመጸሐፉ ይዞታ ቀንጨብ አድርገን እናካፍላችሁ።

"የግዮናዊነት" ደራሲው ምስጋናው አንዱዓለም ምሕረቴ “መሪ ኣንቀጽ” ባለው አርእስት ስር ስለመጸሐፉ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል
ይህንን መጽሃፍ ሳዘጋጅም አብዛኛውን ማስረጃ የወሰድኩት በሳይንሳዊ መንገድ የተጻፉ ሰነዶችን ተገቢ እና ትክክለኛ በሆነ አግባብ በማጣቀስ ነው። በሳይንሳዊ መድብሎች ያልታተሙ የአገር ውስጥ ጸሀፍት የስራ ውጤቶችም ጥቅም ላይ መዋላቸው ሳይዘነጋ፡፡ እናም መጽሀፉ ረዘም ያለ ጊዜ የወሰደ እና ብርቱ ጥረት የተደረገበት የጥናትና ምርምር ውጤት ነው፡፡


ጸሃፊው ስለ "ቤተ አማራ እንቅስቃሴ" በገጽ 18-19
1) አማራ እንደህዝብ ህልውናው ላይ የተደቀነበት አደጋ፤
2) አማራ በተናጠል እየገጠመው ያለው የየእለት ስጋት፤
3) አማራ የተዘፈቀበት አሰቃቂ የድህነት አረንቋ
4) ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች የደረሱበት የብሔረተኝነት ደረጃ
5) የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀለኞች ለፍረድ አለመቅረብ
6) ራሱን አቅልጦ የሰራት አገር ያልበጀችው መሆኑ፤
7) እስካሁን አማራ ላይ የደረሰው በደል አብሮነትን አደጋ ላይ የጣለው መሆኑ
8. ሁሉም ብሔረሰቦች የየራሳቸው ጸረ አማራ ድርጅት ሲኖራቸው አማራ ግን ለራሱም የሚሆን የሌለው መሆኑ
9) በህብረ ብሔራዊ አደረጃጀት ውስጥ መቆየት ጉዳት እንጅ ጥቅም የሌለው መሆኑ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡


ደራሲው ስለ "የአማራ መንገድ" በገጽ 155-157

ብዙ መንገድ ተጉዟል፡፡ ሲወድቅ ሲነሳ አያሌ ፈተናዎችን አሳልፎ እዚህ ደርሷል፡፡ ይሄንን መንገዱን ከማሰሳችን በፊት አማራ ማን ነው የሚለውን ከኮግኒቲቭ (ስነአእምሮአዊ) ሳይንስ (አንትሮፖሎጅ እና ሳይኮሎጅ) አንጻር እንየው፡፡ ማለትም የሚከተለው ዝርዝር የማንነት ገለጻ የተመሰረተው ከኮግኒቲቭ አንትሮፖሎጅ ንድፈ-ሀሳቦች ውስጥ በአንዱ ስኬማ ንድፈ-ሀሳብ ወይም የራስ ትውስታና ምልከታ ዓለም ንድፈ-ሀሳብ (Cultural schema theory) ላይ ነው፡፡ በካልቸራል ስኬማ ንድፈ ሀሳብ (እሳቤ-ምናብ) መሰረት የአማራ ህዝብ የሚጋራቸው፣ የራሱ ብቻ የሆኑ መገለጫዎች አሉት፡፡ እነዚህ መገለጫዎች ሌሎች ብሄሮች/ዘውጌዎች ከአማራው የተለየ የራሳቸው ስኬማ እንዳላቸውም የሚያሳይ ነው፡፡ ይሄንን አስተሳሰብ በቀላሉ ለማስረዳት ለምሳሌ በግለሰብ ደረጃ አዛሉ ስለራስዋ ያላት ትውስታ፣ የህይወት ምልከታ፣ ያለፈችበት ታሪክ፣ ምልከተ ዓለም ወዘተ ከታደሰ የተለየ ነው፡፡ ሁለቱ የየራሳቸው ስኬማ አላቸው፡፡ ወደ አማራ እንደ ህዝብ ስንመጣ ደግሞ የራሱ ህዝባዊ የሆነ እሳቤ-ምናብ አለው፡፡ (ለበለጠ ግንዛቤ የካስቶን ሮናልድን325 Schemata in Cognirive Anthropology አንብብ፡፡)

ከስኬማ ወይም ምልከታ-ዓለም-ወትውስታ አንጻር ይህ አማራ የህዝብም፣ በግለሰብም የየራሱ የሆነ መገለጫም ያለው ህዝብ ነው፡፡ ሲራመድ ዝግ ብሎ የሚሄድ፤ አጠገቡ ላለ እንቅፋት የማይሆን፤ የራሱን መንገድ ብቻ የሚሄድ፤ የወደቀ ሰው ካገኘ የሚያነሳ፤ ደካማን ረግጦ የማያልፍ ህዝብ ነው፡፡ አማራ ቤት የእግዜር ነው ብሎ አልጋውን ለእንግዳ ለቆ ወለል ላይ የሚተኛ ህዝብ ነው፡፡ እርቦት እንኳ ቢሆን የያዘውን ለአላፊ ወይም ለእንግዳ የሚያበላ፤ ጾሙን አድሮ ፈጣሪውን “ለእንግዳየ የማበላው ስላላሳጣሀኝ አመሰግንሀለሁ” ብሎ አይኑን ወደ ሰማይ ከፍ አድርጎ የሚያመሰግን፡፡ እንኳን መብላት ማብላት ይቀራል የሚል አስገራሚ የሆነ ራሱን ጥሎ ለሌላው የሚኖር ባህል ያለው፡፡ ክፉን በክፉ አልመልስም ብሎ እየተገፋም በትእግስት አሜን ብሎ የሚኖር፡፡ እሱ ዛኒጋባ ውስጥ እየኖረም ቢሆን እንኳ የአምላኩን ቤት አስጊጦ የሚሰራ፡፡ ምግብና መጠጥን ለሞተ እህል ትዝብት ውስጥ አልወድቅም በማለት በልግስና የሚያበላ፤ የሚያጠጣ፡፡ ያበደረውን ገንዘብ ሲያልፍልህ ትሰጠኛለህ በማለት ራሱን ችግር ላይ የሚጥል፡፡ ባለው ነገር ሁሉ የማይኮራ፤ ዓለምና የዓለም ሁሉ አላፊ ጠፊ ነው ብሎ የወዲያኛውን ዓለም በማሰብ ራሱን ረስቶ የሚኖር፡፡

አማራ በጣም የሚያስገርም ለሌላው መስዋእት የመሆን ስሜት ያለው፡፡ ዘር ማንዘሬ ብሎ አድሎ የማይሰራ፤ በወንድሙና በሩቅ ሰው መሀል እኩል የሚፈርድ፡፡ ፍትህን የማያጣምም፤ ታማኝ እና እውነተኛ፡፡ ሲናገር አስቦና አስልቶ፤ ክፉና በጎውን መዝኖ የሚናገር፡፡ ለተጎዳ ሁሉ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ፡፡ ራሱን መውደድን እንደ ነውር የሚቆጥር፤ እኩልነት የሚለውን ብሂል በእምነት፣ በሀሳብ፣ በስራ እና በኑሮ የሚተገብር፡፡ ታላቁን አክባሪ፤ የማይቅለበለብና በአደባባይ ሁሉ ኩሩ የሆነ፤ ለራሱ ያለውን ክብር በመብልም ሆነ በመጠጥ የማይሸጥ፤ ክብርን ከመጣል ራስን መጉዳት የሚመርጥ፡፡ ቢማርም ባይማርም አርቆ የሚያስብ፡፡ ከጫፍ እስከጫፍ ከአንድነቱ የተነሳ በአይን ጥቅሻ ብቻ የሚግባባ፡፡ ትእግስትን እንደ ሀብት የሚቆጥር እና የሚንከባከባት፤ ተበድሎ እንኳ ፍቅርን የሚያሳይ፤ ይቅርታን የሚያደርግ፤ ምህረትን የሚወድ፡፡ ስርቆትና ቅጥፈትን እንደ ነውር የሚቆጥር፤ ሀቅን ሀብቱ ያደረገ፤ ለልጆቹ ማታ ማታ ሰብስቦ መልካምነትን እና ጀግንነትን የሚያስተምር፡፡ ጭካኔና አረመኔነት በልቡ የሌለበት፤ ቆራጥ እና ገደቡን ሲያልፍ አትንኩኝ ባይ፡፡ መማርን እና ማወቅን እንዲሁም ማስተማርን የሚወድ፡፡ ላመነበት ነገር የማያመነታ፤ ብርቱ ወታደር እና ታማኝ አገር ጠባቂ፡፡ አድሎን የማይወድ፡፡ ታሪኩን ጠንቅቆ የሚያውቅ፡፡ በሆይ ሆይታ የማይመራ፡፡ አሽሙረኝነትን የሚጠላ እና እውነትን ፊት ለፊት የሚጋፈጥ፡፡ አገርና ወገኑን የሚወድ፤ ክብርን የሚወድ እና ሰውን የሚያከብር፡፡ የማይከዳ እና ሸፍጥ የሌለው፤ ቀልማዳነትን የሚጸየፍ ቀጥተኝነት ያለው ነው--አማራ ማለት፡፡

አማራ ሲናገር፤ ሲራመድ፤ ሲመገብ፤ ሲቆምና ሲቀመጥ አማራነቱን የሚያስታውቅ የስነ ስርዓት ማህተም የታተመበት ህዝብ ነው፡፡ አደራ ጠባቂ፤ ሁልጊዜም ከራሱ አልፎ ቀጣዩን ትውልድ የሚያስብ፤ ለቀጣዩ ትውልድ አገርና በጎ ታሪክ ለማስረከብ የሚታትር፤ ለልጆቹ ክፉውን እየተወ በጎ በጎውን ብቻ የሚያስተምር፤ ሰለራሱም ሆነ ስለሌላው ህዝብ ጥላቻን የማይሰብክ፤ ለልጆቹም ጥላቻን እና ቂምን የማያወርስ፤ ከፍተኛ የሆነ ራሱን የመቻልና የነጻነት መንፈስ ያለው፤ ከውስጥም ከውጭም የገጠሙትን ፈተናዎች አልፎ ለራሱ እዚህ የደረሰ እና ሌሎችን ማሰባሰብ የቻለ፤ ከጥንት እስከዛሬ ድረስ አንድ አይነት ፈተና እያጋጠመው ያለ፤ ሌሎችን እየወደደ እና ለሌሎች እየኖረ ክፉ የሚመለስለት ህዝብ ነው፡፡ ባህሉን ጠባቂ እና ከማንም ማነስን እንደ ነውር የሚቆጥር፤ በራሱ የሚያምን፡፡ በሁሉም አይነት ስነ ምግባር ምሳሌ የሚሆን እና በአንጻራዊነት ሲታይ ይህ ቀረው የማይባል ጨዋ፤ አርቆ አሳቢ፤ እንደግለሰብም እንደህዝብም ሁልጊዜም እያመነ ግን ያመናቸው የሚከዱት፡፡ ተስፋን የሚወድ እና ሁልጊዜም ነገን ብርሀናማ አድርጎ የሚያስብ፤ ጠብ አጫሪነትን እና ተንኳሽነትን ከደሙ የሚጠላ፤ ክፉ በደልን ባይረሳው እንኳ ይቅር የሚል፤ ፍትህን እና ፍርድን የሚወድ፤ ግፍ መስራትን በልጆቸ እንዳይደርስ በማለት አጥብቆ የሚፈራ፤ ከክፋት ሁሉ ለመራቅ የሚጥር፤ በወላጅነቱ ለልጆቹ ብቁ እና መልካም ምሳሌ የሚሆን ህዝብ ነው፡፡ ይህ የአማራ መንገድ ይባላል፡፡ አማራ የመጣበት መንገድ፡፡ አማራ የሚሄድበት መንገድ፡፡

አማራ በጠባቦች መካከል ሁሉን አቀፍ አንድነታዊ ስሜት ይዞ መኖሩ በጅምላ ወደ መጨፍጨፍ አድርሶታልና እየከበደንም ቢሆን፣ ማነስና መጥበብ ቢመስልብንም፤ ወደ አማራዊነት አስተሳሰብ መግባት ግድ ብሎናል። ለመሰንበት፣ ከተጠነሰሰልን የዘር ማጥፋት እራሳችንን ለመታደግ፣ ለወገን መከታ ለመሆን፣ አማራ በአማራነቱ ይደራጅ ዘንድ፤ አማራዊ አስተሳሰብ እና አማራዊ ስነልቦና መላበስ ግድ ነው። በዙሪያችን ካሉ ሊውጡን ካሰፈስፉ ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ማህበረሰቦች ልናመልጥ የምንችለው በመለማመጥና የነሱን አፈታሪክ እንደ እውነት እየተቀበሉ፣ አንድነት እያሉ ጨፍጫፊዎችን በማሽሞንሞን ሳይሆን፣ በራስ ማንነት ኮርቶ፣ ለራስ ቆሞ፣ በራስ ለራስ በማሰብና በመስራት ነው፡፡

ለህዝባችን ህልውና ይህ የአማራዊነት እንቅስቃሴ ወደርየለሽ ቅዱስ ተግባር ነው፡፡ ይህ አማራዊነት ንቅናቄ ቀድሞ ለኢትዮጵያ ሲባል በአደራ መልክ ያስቀመጥነው የክት ማንነታችን ነው፡፡ አሁን ብንሰፋው ብንሰፋው ሊገናኝ ያልቻለውን የኢትዮጵያዊነት አይጨበጤ አደረጃጀት ትተን ወደ መደበኛውና ጥንተ ማንነት ተመልሰናል፡፡ ተመልሰንም ስንጎበኘው እጅግ ጣፋጭ፤ መሳጭ፤ ኃይል የታመቀበት፤ የሚያጉዋጉዋ ተስፋ ያለው፤ ከክስ የነጻ፤ እጅግ ሰላማዊ፤ እንደ ስሙ ነጻ ህዝብነት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ይህንን ነጻነት ከነ ሙሉ ክብሩ ለመመለስና ለማጣጣም እንቸኩላለን፤ ለዛውም እንታገላለን፡፡ የአማራ አማራነት ንቅናቄ ትክክለኛ ፈውስ ነው፡፡


.....

እንደየ አስፈላጊነቱ፡ አንድ ሁለት ንኡስ አርእስቶቹን መርጠን ልናካፍላችሁ እንሞክራለን። ይዞታውን አንብባችሁ ትገመግሙት ዘንድም ይረዳችኋል፡ በዚህ ጽሁፍ ተገፋፍታችሁም ሙሉ መጸሐፉን ለማንበብም ትበረታቱ ይሆናል። ይህን ጽሑፍ ለታላቁ አጼ ስሱንዮስ ክብር እንዲሁም ለጸሐፊው ክብር ስንል አጋርተናችኋል። :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 4931
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: “የአማራ መንገድ” - "ግዮናዊነት" ከሚለው የምስጋናው አንዱዓለም ምሕረቴ መጽሓፍ ዬተቀነጨበ ብርቅ እይታ

Post by Meleket » 13 Feb 2026, 11:24

Meleket wrote:
17 Nov 2022, 06:28
....

"የግዮናዊነት" ደራሲው ምስጋናው አንዱዓለም ምሕረቴ ....... ስለ "የአማራ መንገድ" በገጽ 155-157

.....

አማራ በጣም የሚያስገርም ለሌላው መስዋእት የመሆን ስሜት ያለው፡፡ ዘር ማንዘሬ ብሎ አድሎ የማይሰራ፤ በወንድሙና በሩቅ ሰው መሀል እኩል የሚፈርድ፡፡ ፍትህን የማያጣምም፤ ታማኝ እና እውነተኛ፡፡ ሲናገር አስቦና አስልቶ፤ ክፉና በጎውን መዝኖ የሚናገር፡፡ ለተጎዳ ሁሉ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ፡፡ ራሱን መውደድን እንደ ነውር የሚቆጥር፤ እኩልነት የሚለውን ብሂል በእምነት፣ በሀሳብ፣ በስራ እና በኑሮ የሚተገብር፡፡ ታላቁን አክባሪ፤ የማይቅለበለብና በአደባባይ ሁሉ ኩሩ የሆነ፤ ለራሱ ያለውን ክብር በመብልም ሆነ በመጠጥ የማይሸጥ፤ ክብርን ከመጣል ራስን መጉዳት የሚመርጥ፡፡ ቢማርም ባይማርም አርቆ የሚያስብ፡፡ ከጫፍ እስከጫፍ ከአንድነቱ የተነሳ በአይን ጥቅሻ ብቻ የሚግባባ፡፡ ትእግስትን እንደ ሀብት የሚቆጥር እና የሚንከባከባት፤ ተበድሎ እንኳ ፍቅርን የሚያሳይ፤ ይቅርታን የሚያደርግ፤ ምህረትን የሚወድ፡፡ ስርቆትና ቅጥፈትን እንደ ነውር የሚቆጥር፤ ሀቅን ሀብቱ ያደረገ፤ ለልጆቹ ማታ ማታ ሰብስቦ መልካምነትን እና ጀግንነትን የሚያስተምር፡፡ ጭካኔና አረመኔነት በልቡ የሌለበት፤ ቆራጥ እና ገደቡን ሲያልፍ አትንኩኝ ባይ፡፡ መማርን እና ማወቅን እንዲሁም ማስተማርን የሚወድ፡፡ ላመነበት ነገር የማያመነታ፤ ብርቱ ወታደር እና ታማኝ አገር ጠባቂ፡፡ አድሎን የማይወድ፡፡ ታሪኩን ጠንቅቆ የሚያውቅ፡፡ በሆይ ሆይታ የማይመራ፡፡ አሽሙረኝነትን የሚጠላ እና እውነትን ፊት ለፊት የሚጋፈጥ፡፡ አገርና ወገኑን የሚወድ፤ ክብርን የሚወድ እና ሰውን የሚያከብር፡፡ የማይከዳ እና ሸፍጥ የሌለው፤ ቀልማዳነትን የሚጸየፍ ቀጥተኝነት ያለው ነው--አማራ ማለት፡፡

አማራ ሲናገር፤ ሲራመድ፤ ሲመገብ፤ ሲቆምና ሲቀመጥ አማራነቱን የሚያስታውቅ የስነ ስርዓት ማህተም የታተመበት ህዝብ ነው፡፡ አደራ ጠባቂ፤ ሁልጊዜም ከራሱ አልፎ ቀጣዩን ትውልድ የሚያስብ፤ ለቀጣዩ ትውልድ አገርና በጎ ታሪክ ለማስረከብ የሚታትር፤ ለልጆቹ ክፉውን እየተወ በጎ በጎውን ብቻ የሚያስተምር፤ ሰለራሱም ሆነ ስለሌላው ህዝብ ጥላቻን የማይሰብክ፤ ለልጆቹም ጥላቻን እና ቂምን የማያወርስ፤ ከፍተኛ የሆነ ራሱን የመቻልና የነጻነት መንፈስ ያለው፤ ከውስጥም ከውጭም የገጠሙትን ፈተናዎች አልፎ ለራሱ እዚህ የደረሰ እና ሌሎችን ማሰባሰብ የቻለ፤ ከጥንት እስከዛሬ ድረስ አንድ አይነት ፈተና እያጋጠመው ያለ፤ ሌሎችን እየወደደ እና ለሌሎች እየኖረ ክፉ የሚመለስለት ህዝብ ነው፡፡ ባህሉን ጠባቂ እና ከማንም ማነስን እንደ ነውር የሚቆጥር፤ በራሱ የሚያምን፡፡ በሁሉም አይነት ስነ ምግባር ምሳሌ የሚሆን እና በአንጻራዊነት ሲታይ ይህ ቀረው የማይባል ጨዋ፤ አርቆ አሳቢ፤ እንደግለሰብም እንደህዝብም ሁልጊዜም እያመነ ግን ያመናቸው የሚከዱት፡፡ ተስፋን የሚወድ እና ሁልጊዜም ነገን ብርሀናማ አድርጎ የሚያስብ፤ ጠብ አጫሪነትን እና ተንኳሽነትን ከደሙ የሚጠላ፤ ክፉ በደልን ባይረሳው እንኳ ይቅር የሚል፤ ፍትህን እና ፍርድን የሚወድ፤ ግፍ መስራትን በልጆቸ እንዳይደርስ በማለት አጥብቆ የሚፈራ፤ ከክፋት ሁሉ ለመራቅ የሚጥር፤ በወላጅነቱ ለልጆቹ ብቁ እና መልካም ምሳሌ የሚሆን ህዝብ ነው፡፡ ይህ የአማራ መንገድ ይባላል፡፡ አማራ የመጣበት መንገድ፡፡ አማራ የሚሄድበት መንገድ፡፡ .....፡፡


.....

እንደየ አስፈላጊነቱ፡ አንድ ሁለት ንኡስ አርእስቶቹን መርጠን ልናካፍላችሁ እንሞክራለን። ይዞታውን አንብባችሁ ትገመግሙት ዘንድም ይረዳችኋል፡ በዚህ ጽሁፍ ተገፋፍታችሁም ሙሉ መጸሐፉን ለማንበብም ትበረታቱ ይሆናል። ይህን ጽሑፍ ለታላቁ አጼ ስሱንዮስ ክብር እንዲሁም ለጸሐፊው ክብር ስንል አጋርተናችኋል። :mrgreen:

Post Reply