Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Fiyameta
Senior Member+
Posts: 21051
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

⚖️☀️ « የኤርትራ ዶክትሪን » ☀️ ⚖️

Post by Fiyameta » 12 Jan 2026, 04:04

ከሰላሳ ዓመታት በፊት በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ይፋ የተደረገውና “አፍሪካ ለአፍሪካውያን” የሚለው መርህ፣ ባሁኑ ወቅት በድጋሜ ነፍስ ዘርቶ እየታየ ነው። ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ የሚፈጠር ማንኛውንም የውጭ ኃይል ተፅዕኖ በኃይልም ቢሆን ለማስወገድ ቆርጣ መነሳቷን በተከታታይ እርምጃዎቿ እያሳየች ትገኛለች። ይህ “የኤርትራ ዶክትሪን” ተብሎ የሚታወቀው አዋጅ ፣ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ መገኘት እንዳለበት በማመን፣ ከውክልና ጦርነት የሚያተርፉ የጦር መሳሪያ ነጋዴዎቹ ብቻ ናቸው የሚል ፅኑ አቋም አለው።