Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4772
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

የሁለት ኤርትራዉያን የሃረር አካዳሚ ካዴቶች ብርቅ ወግ

Post by Meleket » 11 Nov 2025, 05:16

የሁለት ኤርትራዉያን የሃረር አካዳሚ ካዴቶች ብርቅ ወግ

ክፍል 1
https://youtu.be/d5qLI7ibH1g?si=mLzG_f1U6wctGRbk


ክፍል 2
https://youtu.be/1nYjog4RBoM?si=OLYtY1aRXd4IvXdT

Meleket
Member
Posts: 4772
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የሁለት ኤርትራዉያን የሃረር አካዳሚ ካዴቶች ብርቅ ወግ

Post by Meleket » 11 Nov 2025, 08:04

Meleket wrote:
11 Nov 2025, 05:02
የነዚህ ሁለት የሃረር አካዳሚ ካዴቶች የማለዳ ጽምዶና ትረካ መሳጭ ነው! ገርሞናል። ልብ ለልብ የሚናበቡ ብርቕ ኤርትራዉያን! እንኳን ተወለዳችሁ ብለናል እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር!

ጃንሆይ እንደወደቁ፡ እኔ የደርግ ደጋፊ ነበርኩ። ደርግ አብዮታዊ ነው ብዬ አምን ነበር። እንኳን ሃይለስላሴ ወደቁ እንጂ ንግስና ምናምን ብሎ ጉዳይ ያከትማል፡ የኤርትራ ጉዳይም ይፈታል ብዬ አምኜ ነበር። እኔ በንግስና አላምንም፡ በመሬት ላራሹ ግን አምን ነበር።

ለትምህርት ሚያሚ በነበርኩት ወቅት፡ የኛ የሁለት ዓመት ሲንዬር ጓደኛችን የነበር አሜሪካም ተምሮ የነበረው ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፡ ኢትዮጵያ ሄዶ በደርግ ተሹሞ ወደ አሜሪካ ተመልሶ መጣ። ኒውዮርክ ውስጥ አንድ የሃዘን ኣጋጣሚ ሰዎች ተሰባስበን ስንጨዋወትም፡ እኔ “ስማ ዳዊት፡ አሁን ነገሮች መልካም ሆነዋል፡ እኔም አብዮቱን እደግፋለሁ፡ የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ አንድ ነገር አድርጉ፡” ስለው “ምን ማለትህ ነው?” አለኝ። እኔም “መጀመርያ ፊደሬሽኑን ወደ ነበረበት መልሱት” ስለው። ና እስቲ በላይ እፈልግሃለሁ ብሎ ከተሰበሰቡት ሰዎች ገለል አድርጎ፡ “በላይ ወደ ሃገርህ መመለስ አትፈልግም እንዴ?” አለኝ። “ምነው ምን ተፈጠረ” ስለው፡ “እዛ ውስጥ ምን እንዳልክ ረሳከው እንዴ” አለኝ። “ምን አልኩህ ደግሞ” ስለው፡ “ፌደሬሽን ምናምን” ሲለኝ። እኔም “እንዴ ፌደረሽንማ የመጀመርያው እርምጃ ነው፡ መጀመርያ ፌደርሽንን መልሳችሁ፡ ከዚያ በረሀ ካሉት ኣካላት ጋር በስነስርዓት ንግግር አድርጋችሁ፡ በሰላማዊ መንገድ ጉዳዩን ፍቱት፡ ሁከትና ግርግር ውስጥ የሚያስገባ ምንም ዓይነት ምክንያት የለም።” አልኩት። ዳዊትም “አብደሃል እንዴ! እንዲህ የምታስብ ከሆነ ባትመለስ ይሻልሃል” አለኝ። እኔ ግን የዳዊት አባባል ምኑም አልገባኝም፡ ምክንያቱም ደርግ ከምር አብዮታዊ ነው ብዬ ነው አስብ የነበርኩት። ነገሮችንም በውይይት ይፈታል የሚል እምነት ነበረኝ።

ኢትዮጵያ ከተመለስኩ በኋላ ከወንበዴ ጋር ትገናኛለህ የሚል ክስ ቢጤ ጠበቀኝ። እኔም “ህዝባዊ ግንባር የምትባል አካል የምታራምደውን ዓላማ አምንበታለሁ።” ብዬ በግልጽ ነገርኳቸው። “ሕዝባዊ ግንባር ኤርትራ ትገንጠል ኣላለችም፡ ከኢትዮጵያ ጋርም ትቀላቀል ኣላለችም። ህዝባዊ ግንባር ያለችው፡ የህዝቡ ፍላጎት ይጠየቅ፡ ረፈረንዱም ይደርግ የሚል ነው። እኔም ይህን አባባል አምንበታለው” ስላቸው። “አንተማ ኤርትራ ትገንጠል ነው እያልክ ያለሀው” አሉኝ። እኔም “አይደለም፡ ይህ ምንም ችግር የለውም። በረሃ ያሉት አካላት፡ ህዝብ ከኛ ጋር ነው፡ የህዝብ ፍላጎት እንዲተገበር ደግሞ እየታገልን ነን፡ ነው ያሉት። ይልቅስ ኢትዮጵያ ኤርትራን የምትፈልግ ከሆነ፡ ህዝቡ ፍላጎቱን ሲጠዬቅ ከኢትዮጵያ ጋር እንሁን እንዲል፡ አብዮቱ ለኤርትራ ህዝብ አንዳንድ በጎ ስራዎች ቢሰራ ይበጃል። ህዝቡ እገነጠላለው የሚልበትን ምክንያት ለምን በቅጡ አታጠኑትም ለምንስ አትፈትሹትም ለምንስ አትመረምሩትም። መደረግ የሚገባው፡ በጦርነት የሚፈታ ነገር ስለሌለ፡ ጦርነት ቆሞ፡ በረሃ ካሉት አካላት ጋር ንግግር ማድረግ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ህዝቡ ምን ብሎ እንደሚመርጥ ግልጽ ነው፡ ስለሆነም ህዝቡ ምን ሆኖ ነው የጠላን፡ ለምን ከኛ ራቀ የሚለውን ጉዳይ ግዜ ሰጥታችሁ በቅጡ አጥንታችሁ፡ ህዝቡን ለማቀፍና ለማሳመን መጣር አለባችሁ።” አልኳቸው። ይሄን አቋሜም ደርጎቹ ጠንቅቀው ያውቁታል። ፍስሃ ጓደኛዬ ነው፡ ብርሃኑ ባዬህም እንዲሁ፡ ይህን አቋሜን ያውቁታል፡ ለመንግስቱም ነግረውታል። “ይሄ ሰዉዬ አስቸግሮናል፡ የበረሀኞች አመለካከት ነው ያለው” ብለው አንዳንዶች ከሰውኛል። መንግስቱም፡ “ሰዉዬው ምን እንደሚል እናውቃለን፡ ጠባይ እንደሌለውም እናውቃለን፡ ያለ እረፍት እዬሰራልን እንዳለም እናውቃለን፡ እስቲ ተዉት ስራዉን ይስራበት” አላቸው።. የመንግስቱን ልጆች እኔ ነበር የማክማቸው። ሶስቱም አሁን ዶክተሮች ሆነዋል።

ነገር ግን ባንድ ወቅት አስረውኝ ነበር። ለ 36 ሰዓታት ታሰርኩ። ሊያጠፉኝ ነበር ሃሳባቸው። ሊገድሉንና እስከወዲያኛው ሊያሰናብቱን አስበው ነው በዕለተ ሰምበት ያሰሩን። እግዝሄር ግን አለ፡ ቀንህ ካልደረሰ ምንም ስለማትሆን፡ ወዲያውኑ ነው ከእስሩ የወጣሁት። ያም ሆነ ይህ አቋሜ ግልጽ ነበር። ትገንጠል አላልኳቸውም ግን “ህዝብ ይወስን” እላቸው ነበር። ህዝቡን “ኢትዮጵያ” እንዲል ለምን ስራ አንሰራም፡ በማለት እንደነሱ ሆኘ እነግራቸው ነበር። በረባ ባልረባው ህዝብ ማጉሳቆል እንተወው። እላቸው ነበር።

አባቴ “አንዲት ኢትዮጵያ” እያለ ነው እስከመጨረሻው የሄደው። እኔም ስወለድና ሳድግ “ኢትዮጵያ”ን ነው የማውቀው። የኢትዮጵያን ሰንደቕ ከነ አንበሳዉ እየሳልኩ ነው ያደግኩት። ያኔ እኛ ያሰብነው ወንድሞቻችን እንድትሆኑ፡ አንድ እንድንሆን ነበር። ኤርትራዊ ከጥንት ጀምሮ የጣልያንን ቀኝ ግዛት አልተቀበለም፡ የእንግሊዝንም ቅኝ ግዛት አልተቀበለም። የኢትዮጵያንም ቢሆን፡ እንገዛሃለን ካላችሁት፡ ቀኝ ግዛትን በፍጹም አይቀበልም ኤርትራዊ በሙሉ። በመሆኑም ይህ ጉዳይ በቅጡ ታይቶ ከቀኝ ግዛት ተላቀን፡ አንድ እንሁን ስለተባለ፡ ይህን ለመተግበር ህዝቡን አሳምኑት። እንዴ እዉነት እንነጋገር ከተባለ እኮ፡ ኤርትራን ተዋግታችሁ አይደለም ያገኛችኋት። ራሱ የኤርትራ ህዝብ ከአሜሪካ ጋር በተደረገ ሸፍጥ አማካኝነት አይደለም እንዴ አንድነት ያለው። ብርቱና ፈርጣማ የነበረው የአንድነት ማህበርም ሆ እያለ እዬጨፈረና እያጨበጨበ ነው ያስገባችሁ እንጂ ተዋግታችሁ አይደለም ኤርትራ የገባችሁት። ስለዚ ትላንት ሆ ብሎ እዬጨፈረ የተቀበላችሁ አካል፡ ዛሬ አንፈልጋችሁም እያላችሁ ነው። ይህንን ሁሉ ጣጣ ግን ምን አመጣው! . . .

ኢትዮጵያ በጓደኛዬ በፕሮፌሰር በርሀ ሃብተጊዮርጊስ አመለካከት፡ ወደ ዩጎዝላቪያነትም ልታመራ ትችላለች፡ ከኤርትራ ካልተማረችና በቅጡ ችግሯን ካልፈታች። የኔ የዶ/ር በላይ ጊዮርጊስ (ጆርጆ) አመለካከት ደግሞ ይህን ይመስላል። ታሪኩና ትርክቱ እንዲህ ነው።

ኢትዮጵያዊያን ሊቀበሉት የማይሹ አንድ ሓቅ አለ።

ኤርትራና ኢትዮጵያ ባንድላይ ነው የተፈጠሩት። ኢትዮጵያን የፈጠራት ምኒልክ ነው። ኤርትራን የፈጠራት ደግሞ የኢጣልያና የምኒልክ የስምምነት ፌርማ ነው። ምኒልክ ጣልያንን፡ ወደእዚህ አትምጭብኝ እንጂ፡ ኤርትራ የምትባለው ሃገር ያንቺ ናት ብሎ፡ ግጥም አድርጎ ፈርሟል። ከዚያ በኋላ ሃይለስላሴ ነው የመጣው፡ ሃይለስላሴ ሲመጣ እዚህ በነበርነው በኛ ድጋፍ፡ ባህሩን ሳይዋጋ ራሳችን አስረክበነዋል። ባህር ካገኘ ብኋላስ ምን ፈለገ፡ ምድሩንና ባህሩን እንጂ፡ ህዝቡን አልፈለገም ሃይለስላሴ።

ሃይለስላሴ የተሳሳቱት፡ ትልቅ ስህተት የኤርትራን ህዝብ ለመግዛት ፈለጉ። የኤርትራ ህዝብ በሙሉ ቅኝ ግዛትን ኣይቀበልም። ሃይለስላሴ በፈጸሙት ግፍ ምክንያት ቀዬዎችንና ህዝቡን አጠፉት። ታዲያ ቅኝ ለመገዛት ለመገዛትማ፡ ከኢትዮጵያ ይልቅ በጣልያን ወይም በእንግሊዝ መገዛት አይሻልም እንዴ? ለመገዛት ለመገዛትማ ካንተ የማይሻል፡ ወንድሜ ብለህ ያስገባው አካል፡ ልግዛህ ሲልህ እንዴት ብሎ ይሆናል? ይህ ነበር ግን የነበረው።

የኢትዮጵያዉያን አንድ ችግር፡ የኤርትራዉያንን ባህርይ አለማወቃቸው ነው። ኤርትራዊን መግዛት አይቻልም። ቀኝ ግዛት በፍጹም የማይቀበል ህዝብ ነው። ኤርትራዉያን በጋራ ያሳለፍነው ታሪክ ይበልጥ አንድ አድርጎናል። ሃይለስላሴ ቀጥሎም ደርግ “ቀይባህራችን በቀይ ደማችን እያሉ” አልፈዋል። የሚገርመው ጉዳይ “ህዝቤ” አላሉም፡ ስለ ህዝቡ ምንም አልተጨነቁም፡ ጭንቀታቸውና ጥያቄያቸው ስለ ባህሩ ብቻ ነበር!

እኔ ከብዙ ሰዎች ጋር የማልስማማበት ነገር አለ። ፕሮፌሰር መስፍንን ኤርትራዉያን ይጠሉታል፡ ዮኒቨርሲቲ ውስጥ ጸረ ኤርትራ ነው ተብሎ ይታማል። እኔ ግን በአንድ ብርቱ ጉዳይ ከሱ ጋር እስማማለው። እሱ ባህር ምናምን አይልም፡ የባድሜ ግዜም፡ ያን ያህል ጸረ ኤርትራ ነው እዬተባለ፡ ባድሜ የኢትዮጵያ አይደለም ያለ ሰው ነው።

የኢትዮጵያዉያን ትልቅ ስህተት ስለ ባህር ስለ ምድር ስለ አሰብ ማሰባቸው ነው፡ የኤርትራን ህዝብ አካሌ ነው የኔ ነው አለማለታቸው ነው። ባህር ያስፈልገናል ይልሃል፡ በዬት በዬት በኩል? ማንን ረግጠህ? በዬትስ አልፈህ? ደርግ እንዲያ ነበር ያደረገው። ከዚያ በኋላ ወያኔ መጣች። ወያኔ ትረካውን ቀየረችው፡ ባህር አያስፈልገንም፡ ባህር ሸቀጥ ነው፡ ስለሆነም በገንዘባችን ልንጠቀምበት እንችላለን አለች። እኛም ተጠቀሙበት ወንድሞቻችን ናችሁ አልናቸው፡ ሳይከፍሉም እንዳሻቸው እንዲፈነጩበት ተደረገ። ነገር ግን በአፍ እንደዚያ ቢሉም እንኳ፡ በውስጣቸው ግን ሌላ አጀንዳና ዓላማ ስለነበራቸው ችግር ፈጠሩ። መጀመርያ መላዋን ኤርትራ መቆጣጠር ፈለጉ፡ አልቻሉም። መጨረሻም ቢያንስ ቢያንስ አሰብን እንኳ ይዘን ኤርትራን እንቆርምማት ብለው አሰቡ። ይህንንም መተግበር አልተቻለም። ትረካቸው ግን ባህር አያስፈልገንም የምትል ነበረች፡ ሲሸነፉም “ባህር አያስፈልገንም” እንደማለት፡ “ሲፈልጉ ግመላቸውን ውሃ ያጠጡበት” እስከማለት ደረሱ። ግመል እንደሆነ የባህር ውሃ አይጠጣም። ከዚያ ሃይለማርያም የሚባል መጣ ለጥቂት ግዜ ቆዬ። ከዚያም አሁን ያለው ሰው መጣ። አሁን ያለው ነገር ነው ደግሞ ሁሉን ሰው እያነጋገረ ያለው።

ይህ ሰው መጀመርያ አምኖ ያላንዳች እንካ ስላንትያ ሁሉንም ውል እተገብራለሁ ብሎ የሰላም ስምምነት ፈጽሟል። ይህ እንደተደረገ ደግሞ ትርክቷ ተቀየረች። ባህርን የማይፈልግ መስሎ ታዬ። ከዓመት በፊት ደግሞ አዲስ ትርክት አመጣ። ባህር ያስፈልገናል የሚል ትርክት። በኔ አመለካከት አሁን ያለው የኢትዮጵያ መሪ፡ “ባህር እንደማያገኝ ጠንቅቆ ያውቃል። ያቺን ሃገር ለመግዛት ካሰብክ ግን ባህርን ፈላጊ ሆነህ ካልተገኘህ፡ ሁሉግዜ ያስቸግሩሃል። ስለሆነም “ባህር እንደማያገኝ ጠንቅቆ እያወቀ፡ ባህር ፈላጊ መስሎ ተናግሯል”

ሲጠቃለል፡ ኢትዮጵያ ወዴት ነው እያመራች ያለችው ለሚለው ጥያቄህ፡ ከጓደኛዬ ከበርሀ ጋር ባንዲት ጉዳይ ብቻ እስማማለው። ኢትዮጵያ ከኤርትራ መማር ይገባታል በሚለው ሃሳቡ እኔም እስማማለው። በሌላው ግን ትልቅ ልዩነት ነው ያለን።

ከኤርትራ መማር ይገባቸዋል ያለው እውነት ነው! ኤርትራ ውስጥ ከነጻነት በኋላ ትልቅ ስራ ተሰርቷል። 9 ብሄሮች አለን፡ ዘጠኙ ብሄር እኩል መብት አላቸው። ብሄሮች ራሳቸው ሳይጠይቁ መብታቸው ተረጋግጧል። እያንዳንዱ ብሄር በቋንቋየ ልናገር በቋንቋየ ልማር ብሎ ሳይጠይቅ፡ አስቀድሞ መብቱን ተጎናጽፏል። በቋንቋህ መማር ይገበሃል፡ ቋንቋንህን ማሳደግ ይገባሀል ተብሏል እያንዳንዱ ብሄር። ኤርትራ ውስጥ አንድ ቋንቋ ብሎ ነገር የለም፡ ሁሉም ዘጠኙ ቋንቋዎች እኩል መብት አላቸው። የሃይማኖት ጉዳይም ምንም ጥያቄ ሳይነሳ፡ አስቀድሞ መፍትሄውን አግኝቷል። እስላምናና ክርስትና ያለ አንዳች ልዩነት መብታቸው ተረጋግጧል ያለ አንዳች ጥያቄ። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን፡ ይህ መብት የተሰጠው ብሄሮችና ሃይማኖቶች ጥያቂያቸውን ካቀረቡ በኋላ ነው። ኤርትራ ውስጥ ገና ሳትጠየቅ አስቀድሞ (Proactive) ነው የሚባለው። ይህ በመሆኑም ኤርትራዊነት የበለጠ ጎመራች። ይህ የተደረገለትም ኤርትራዊነቱ እየጎለበተ፡ ቋንቋውና ባህሉንም እያደገ ሄደ። የጾታ ጉዳይና እኩልነትም በግሩም መልኩ ተሰርቶበታል። ሴቶች በፍቃዳቸው ብቻ ሳይሆን በግድ እኩል መሆናቸው እንዲረጋገጥ ጥረት ተደርጓል። ይህም የህብረተሰብ ግማሽ ክፍል በመሆናቸው ነው። ይህ በመደረጉ ኤርትራ ሃይል ለማደለብ አስችሏታል። ኤርትራ ችግርና ትንኮሳ አላት ወይ ካልከኝ፡ አዎን አላት። ኤርትራ ለወደፊትስ ችግርና ትንኮሳ ይገጥማታል ወይ ካልከኝም፡ አዎን ሊገጥማት ይችላል። ነገር ግን አንድ ከሆንክና ከተባበርክ፡ ሁሌም አሸናፊ ነው የምትሆን።

በነገራችን ላይ ብርቱ ውጊያ የተደረገው፡ ከነጻነት በፊት ሳይሆን ከነጻነት በኋላ በወያኔ ዘመን ያጋጠመን ውጊያ ነው። ምክንያቱም ድፍን ኢትዮጵያ አምኖበት ነው ከወያኔ ጋር ተባብሮ የወረረን። ወያኔ ብቻዋን አይደለችም የወረረችን።፡ ድፍን ኢትዮጵያ፡ ዓለም በመላ፡ ያቺ የተማርኩባት እስራኤልም ሳትቀር ከወያኔ ጋር ወግና ዓለም በመላ ተረባርቦብናል። ሊታመን ከማይችለው ግዙፍ ወረራ አንጻር ግዙፍ ለማመን የሚያዳግት ኤርትራዊ ስራ ተሰርቶ፡ ወረራው በሙሉ ከንቱ ሆኖ ቀርቷል። በተለይ 3ኛው ዙር ወረራ ግዙፍ ነው የነበረው፡ በኤርትራዊ ክንድ ግን ዋጋውን አግኝቶ መና ሆኖ ቀርቷል። መቼም ኢትዮጵያዉያን ተሸንፈናል የምትለው ቃል አትወጣቸው። አንድ ሰው ከወደቀ በኋላ፡ ለመነሳት ከፈለገ፡ መውደቁን ማመን የግድ ነው። መውደቁን ካላመነ ግን በምንም ዓይነት መልኩ ሊነሳ አይችልም። እስከ አሁን ድረስ እነ ካሳዬ ጨመዳና ወዘተ “አልተሸነፍንም” ይላሉ! ወይ አለማፈር! በታንክ እንደልብህ ትርመሰመስበት ከነበረው ከኤርትራ ምድር ታድያ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተህ፡ ታንኮችህን በሙሉ አስረክበህ ባዶ እጅህን ምን ልታደርግ ነው ኢትዮጵያ የሄድከው። መሸነፍህን መጀመርያ ካላመንክ ዳግም ልትነሳ አትችልም። መውደቁን ያላመነ ዳግም ሊነሳ አይችልም።


አሁን ያለው የኢትዮጵያ መሪ፡ በ3ኛው የወያኔ ወረራ ጊዜም የነበረ ነው። በአካል የተሳተፈ ነው። በምንም ዓይነት መልኩ ኤርትራንና ባህሯን መቆጣጠር እንደማይቻል ጠንቅቆ ከማንም በላይ ያውቀዋል። አይቶታ’ላ። ባህር የሚለው ጉዳይ፡ እዛ ያለውን ባህር ናፋቂ ህዝብ ለማማለል የተጠቀመበት ሴራ ነው። የሶማሌላንድ የተደረገችው ስምምነትም አትሰራም። የኤርትራን ሆነ የጅቡቲን የፖርት ሱዳንንም ማግኘት አይቻልም።

በኔ አመለካከት፡ ኢትዮጵያውያን ቀድሞ ወደነበረው አሓዳዊነታቸውን ለመመለስ አይችሉም። የኦሮሞ ህዝብ ተጨቁኖና ተደፍጥጦ ነው የነበረው ሃይማኖቱን ሆነ ቋንቋውን ሳይሸማቀቅ ማራመድና መናገር አይችልም ነበር፡ ዳግም ወደዚያ ዘመን መመለስ አይፈልግም። በኔ አመለካከት “ብሄርን መሰረት ያደረገ የፌደራል ስርዓት ካልተተገበረ፡ አንዲት ኢትዮጵያ ልትኖር አትችልም። ትበታተናለች።” ስለሆነም ኢትዮጵያ አንድ መሆን ካስፈለጋት፡ እያንዳንዱ የሚገባውን በእኩልነት ያለ አድልዎ ማግኘትና በስምምነት መኖር ይገባዋል። ይህን ማድረግም ይችላሉ። ይህ የሚሆን ይመስለኛል። ኢትዮጵያን እንዳትበታተን ያደረገች አንዲት ሃገር ነች። እሷም ኤርትራ የተባለችው ሃገር ነች፡ ኢትዮጵያ እንዳትበታተን ያደረገች። ያኔ ኮ ጉዳዩ ተጨርሶ ነበር። ኤርትራ ግን ሊያጠፋት ያስብ የነበረው ሃይል፡ ያደረገውን ግፍ ግምት ውስጥ አስገብቶ፡ ተጸጽቶ ይቅርታ መጠየቅና ስህተቱን ማመን እንደሚገባው ምክር ሲሰጠው፡ አሻፈረኝ ስላለ፡ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ እንዳያንሰራራ ተደርጎ ድባቅ ተመትቷል። ስለዚ ኢትዮጵያ አንድ መሆንን የምትፈልግ ከሆነች፡ አሁን ቡራ ከረዩ ያዙን ልቀቁን እያሉ ያሉት አካላት፡ በኔ አመለካከት የሚያዛልቃቸው አይመስለኝም። በኔ ነጻ አመለካከትም ረዢም የሚጓዙ አይመስለኝም። በኔ አመለካከት ኢትዮጵያ ትቀጥላለች። ልትበታተን የምትችለው፡ ኤርትራ ኢትዮጵያ እንድትበታተን የፈለገች ለታ ነው። ኤርትራ ደግሞ ይህን የምትሻ አትመስልም።

ታዲያ አስሬ ባህርና አስሬ የኤርትራን መሬት የመመኘት አባዜ ግን ኤርትራዊያንን የኢትዮጵያን መበታተን እንዲሹ ኣይገፋፋምን? ተብሎ ሲጠየቁም፡ ብየሃለው እኮ፡ በዝተናል፡ በሰላም ካላገኘነው በሌላ መንገድ እናገኘዋለን ምናምን የሚለው አባባል በመሰረቱ ነውረኛ አባባል ነው፡ እንዲያ ሊባል አይገባውም።፡ ትልቅ ስህተት ነው። የኤርትራ ህዝብ አሁን የኢትዮጵያ መሪ የሚባለውን ወደ ኤርትራ በመጣበት ወቅት እንዴት አድርጎ በደማቅ ሁኔታ እንደተቀበለው በአካል ስለነበርኩ አይቸዋለው። አሁን በመላዋ ኤርትራ ሄደህ ስለዚህ ሰው አስተያየት ብትጠይቅ፡ የሚገርም መልስ ነው የምታገኘው። ሁሉም ሰው ጠልቶታል አይንህን ላፈር ብሎታል። ራሱ ያመጣው መዘዝ ነው። የተናገረው አስቀያሚ ንግግር ነው ይሄን ሁሉ ያመጣው። ያን አስቀያሚ ንግግር የተናገረበት ምክንያትም ባህር ለማግኘት ብሎ አይደለም፡ ባህር ናፋቂዎችን እኔ ባህር አስገኝላችኋለው ብሎ ለማማለል ብሎ የተናገረው ነው እንጂ፡ ባህር ማግኘት እንደማይችል ጠንቅቆ ያውቃል። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ ይደረጋል፡ “ባህርን ትሸጣለህ!” የሚለው አንዳችም ፖለቲካዊ አካል የለም። ለዚህች ‘ትርፍ’ ብሎ ያደረገው ነው እንጂ ባህር ማግኘት እንደማይችል ጠንቅቆ ያውቀዋል፡ ባህር ማግኘት በፍጹም አይቻልም

ክፍል 1
https://youtu.be/d5qLI7ibH1g?si=mLzG_f1U6wctGRbk


ክፍል 2
https://youtu.be/1nYjog4RBoM?si=OLYtY1aRXd4IvXdT


ኣገናዕ ወዲ ሃብተጊዮርጊስ - ፕሮፌሰር በርሀ ሃብተጊዮርጊስ!

ኣገናዕ ወዲ ደጊያት ጆርጆ ሃብቲት- ኮሎነል ዶ/ር በላይ ጊዮርጊስ!

Meleket
Member
Posts: 4772
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የሁለት ኤርትራዉያን የሃረር አካዳሚ ካዴቶች ብርቅ ወግ

Post by Meleket » 12 Nov 2025, 09:29

ጋዜጠኛ ኤፍሬም ግደ፦ ፕሮፌሰር በርሀ ሃብተጊዮርጊስ፡ ጅቡቲ ነጻነቷን ባወጀችበት ወቅት አንተ ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደር ስለነበርክ፡ “ጅቡቲን ለመውረር ተዘጋጁ ተብለን ነበር” ብለህ አንድ ሰሚናር ላይ ስትናገር ሰምቸ ነበር፡ እስቲ ያኔ የነበረውን ሁኔታ አጫውተን።

ፕሮፌሰር በርሀ፦ 1966 ወይም 67 (እ.አ.ኣ.) አካባቢ ይመስለኛል፡ ያኔ ጅቡቲ ረፈረንደም ታካሄድ ነበር። ነጻነት ወይስ ከፈረንሳይ ጋር መቆየት የሚል ምርጫ ነበራት። ያኔ ባንድ በኩል ኢትዮጵያ በሌላ በኩል ደግሞ ሱማሊያ ጅቡቲን ለመውረር ተዘጋጅተው ነበር። ባሌ በነበርኩበት ግዜ ነው፡ እኔ በነበርኩበት ስፍራ የዘመቻ ክፍል ሃላፊ ነበርኩ። የሚስጢር ኮድ የምንፈታውም እኔና ሌሎች ሁለት ወታደሮች ነበርን። የተመሰጠረ መልእኽት አለ ተብሎ ስንፈታው ጅቡቲን ለመውረር እንድንዘጋጅ፡ በአውሮፕላን ከጊሚሪ ወደ ድሬድዋን አልፎ በሚገኝ ጅቡቲን በሚያዋስን ስፍራ ተጓጉዘን፡ ግንባር ተሰጥቶን እንድናጠቃ፡ ሻለቃችን በሙሉ መታዘዟን የሚገልጽ ነበር መልእኽቱ። በአውሮፕላን ከመጓጓዝህ በፊት ሊደረግ የሚገባ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተን ተዘጋጀን በተጠንቀቅ ቆምን። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ስናይ፡ የረፈረንደሙ ውጤት፡ ጅቡቲ ከፈረንሳይ ጋር ለመቆዬት ወስናለች ተባለ። በዚህ ምክንያት ታቅዶ የነበረው የወረራ ውጊያ ሳይተገበር ቀረ። ያኔ ፈረንሳዮች፡ ጅቡቲ ነጻነት ከመረጠች፡ ያኔውኑ ጠቅልለው ከጅቡቲ እንደሚወጡ፡ ጅቡቲንም ራሷን እንድተከላከል ነግረው ጓዛችውን ጠቅልለው ለመውጣት ወስነው ነበር። እንዲያ ቢሆን ኖሮ፡ እኛ ባንድ በኩል፡ ሱማሌዎችም በሌላ በኩል ጥቃት በመሰንዘር፡ የየያዝነውን ስፍራ ተቆጣጥረን፡ ጅቡቲ የምትባለው ሃገር ከታሪክ በተፋቀች ነበር። ይህን ይመስል ነበር አጠቃላይ እቅዱ። ጅቡቲዎችም ይህን ዕቅድ በማወቃቸው ከነጻነት ይልቅ በፈረንሳይ ጥላ ስር ማደርን መረጡ። ያኔ ኢትዮጵያና ሱማሌ ጅቡቲን እንወራለን ብለውም በግልጽ ይናገሩ ነበር። ያኔ ኢትዮጵያ ወደብ ያስፈልገናል ሲሉ፡ ሱማሌዎች ደግሞ ጅቡቲ አካላችን ነው፡ ገሚሱ ህዝቧ ሱማሌኛ ስለሚናገር ሱማሌ ነው ብለው ያምኑ ነበር። ያኔ ኢትዮጵያና ሱማሌ ሃያላኖች ነን ብለው ያምኑ ነበር። ሱማሌ የሶቭዬት ህብረትን መሳርያ ታጥቃ ነበር። ኢትዮጵያም ሃይል አለኝ ማንኛውንም ነገር ማድረግ እችላለሁ ብላ ታስብ የነበረች ሃገር ነበረች።

ሃረር ኣካዳሚ ውስጥ ለጠቅላላ እውቀት የሚረዳን ያልተማርነው ነገር አልነበረም። ለምሳሌ የኤርትራ ፌደረሽን በፈረሰበት ወቅት፡ ሃረር አካዳሚ በነበርኩበት ወቅት፡ ፕሮፌሰር አሉላ የተባለው መምህራችን ጉዳዩን ተወያዩበት ብሎ ለውይይት ጋብዞን ነበር። ኢትዮጵያዉያን ያኔ ስለጉዳዩ ምንም ነገር ዕውቀት አልነበራቸውም። ይታያቸው የነበረው አንድ አማራጭ አንድነት ብቻ ነበር። እንደ ተራ ጉዳይ ነበር የሚቆጥሩት። እኛ ደግሞ ነገርዬውን ልናብራራላቸው እንሞክር ነበር፡ ግን አልገባቸውም። በኋላ ጉዳዩን በግልጽ ደጋግመን እንነግራቸው ነበር። “ረጋ ብላችሁ በጥሞና አስተውሉ፡ ኤርትራ ውስጥ ችግር ተፈጥሯል፡ ችግሩ ዓይኑን አፍጥቶና ጥርሱን አግጥጦ እዬመጣብን ነው፡ አቆርደት ውስጥ ቦንብ ተወርውሯል፡፡ እንደራሴ የነበረውን ለማጥፋት ተሞክሯል፡ ሌላም ሌላም እንቅስቃሴ በነ ዓዋተ ተጀማምሯል። እንቅስቃሴና ነውጥ ተጀምሯል፡ በግዜ እና በመላ ካልተፈታ፡ እኛ የችግሩ ሰለባ እንሆናለን” ብለን ነገርናቸው። እነሱ ደግሞ “አንድነትን” አትፈልጉም ማለት ነውን? ይሉን ነበር።

ለምሳሌ አንድ እውነተኛ ታሪክና ፍጻሜ ላጫውትህ፡ ከአስራ ምናምን ዓመታት በኋላ በ1978 እ.ኣ.ኣ. አንድ በዚህ ውይይት ወቅት አብሮን የነበረው የክፍላችን ልጅ፡ አስመራ እምበርት፡ ኒያላ ሆቴል ውስጥ ከብዙ የራሻ ዜጎች ጋር በመካከላቸው ሆኖ አገኘሁት። እንዴ አንተ እዚህ ምን ትሰራለህ ሲለኝ፡ እኔም አንተ እንጂ እዚህ ምን ትሰራለህ ብዬ ኣዙሬ ስጠይቀው፡ ና ና ብሎ ገለል ካልን በኋላ “እኔማ እዚህ ትኖራለህ ብዬ መቼ አስቤ!” አለኝ። እኔም ታዲያ የት ይኖራል ብለህ አስበህ ነበር አልኩት። እሱም “ከነ መብራህቱ ጋር ተቀላቅለህ ይሆናል አለኝ።” የኋላ ኋላ የተሰዋው ሻምበል መብራህቱ ተወልደመድህን ያኔ ከታጋዮች ጋር ተቀላቅሎ ነበር። እንዲህ ሲለኝ ያኔ ተደናግሬ ነበር፡ ምን እያለ እንደነበር በቅጡ ሊገባኝ አልቻለም። እሱ ግን ቀጥሎ “ያኔ ሃረር አካዳሚ ውስጥ ምን ትሉን እንደነበር ትዝ ይልሃልን? አንተማ ጭራሽ ትሞጣሞጥ ነበር” አለኝ። የያኔው አነጋገሬ ሁሉ ትዝ ብሎት እና ፍንትው ብሎ ዳግም ታይቶን ነው መሰል። ቀጥሎም “ትልቅ መዓት እዬመጣብን ነው፡ ገፈት ቀማሾቹም እኛው ራሳችን ነን! ብላችሁን ነበር። ይሄው ገፈቱን እዬቀመስነው ነው። ” አለኝ። ያኔ በጣም ሃዘን ተሰማኝ። ጥፋት አንዣብቦብናል ችግር እዬመጣብን ነው ብለናቸው ባለመስማታቸው አዝኛለሁ። ታዲያ መጨረሻ ላይ፡ ይህ ሰው ከአስራ አንድ ዓመታት በኋላ የመላው የናደው ዕዝ የመካናይዝድ ክፍል ጠቅላይ አዛዥ ሆኖ ኮሎኔል ለመሆን በቅቶ ነበር። እዛው ናደው ዕዝ ሲደመሰስ እስከወዲያኛው ላይመለስ ተሰዋ ሞተ። ሁሉም ፍጻሜያቸው ተመሳሳይ ነበር። አንዱም ምጽዋ ላይ ብዙ የሚነገርለት ተሾመ ተሰማ ሃረር ኣካዳሚ ውስጥ የክፍላችን ልጅ ነበር። ከኛ ጋርም ጥሩ ግንኙነት ነበረው። በኋላ ግን በ1990 እ.ኣ.ኣ ምጽዋ መሬቱ ላይ ሳይሆን ቀይ ባህር ላይ ነው ዬምሰዋው ብሎ፡ ባህሩ ይገባኛል ለማለት ባህሩ ላይ ሆኖ ጥይቱን በገዛ እጁ ጠጥቶ ሞተ። አብረውን ከተማሩ ኢትዮጵያዉያን መካከል እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ የነበራቸው ሰዎችም ነበሩ።

አንዳንድ ኢትዮጵያዉያን ገራሚዎች ናቸው፡ ኦጋዴን ቋንቋቸው ከሶማሌ ጋር ስለሆነ ወደ ሱማሊያ ይቀላቀል የሚል ጥያቄ ሲመጣባቸው ጀሮ ዳባ ልበስ ብለው፡ በሌላ በኩል ግን ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ቋንቋዋ ተመሳሳይ ነው ስለዚህ ኤርትራ ትገባናለች ይሉሃል፡ ገራሚዎች።

ደርግ ሊወድቅ በተቃረበበት ማግስት፡ ዋሽንግተን ውስጥ አንድ ትልቅ ኮንፈረንስ ተደርጎ፡ እንድሳተፍ ተወክዬ ከአንድ ወንድሜ ጋር ተካፍለን ነበር። አንድ ትልቅ ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር ጥናታዊ ጽሁፍ ብሎ ያቀረበው ጽሑፍ፡ “ኢትዮጵያ ትልቅ ሃገር ናት ስለዚህ ባህር ያስፈልጋታል” የሚል ፉከራና ቀረርቶ የተቀላቀለበት አሸሼ ገዳሜ ነበር። ያኔ አመለካከቱ አስደግጦኝ፡ በወጉ እጄን አውጥቼ “ምንድን ነው እያልክ ያልሀው፡ እኔ እኮ እዚህ ዬተገኘሁት፡ ትልቅ የውይይትና የስምምነት መድረክን ለማመቻቸት እንጂ፡ ፉከራና ቀረርቶ ለመስማት አይደለም። ይህ አባባል በጀርመኖች አባባል ለበነስራው Lebensraum ይባላል። ለበንስራው ማለት ሃረር አካዳሚ በተማርኩት መሰረት ትርጉሙ፡ አንዲት ሃገር ካደገች ከበለጸገች ከገዘፈች ከሰፋች፡ በአካባቢዋ ያሉትን ሃገራት የመውረር እና የመዋጥ መብት አላት ብሎ የሚያምን ፍልስፍናዊ አመለካከት ነው። ይህን ዓይነት የተንጋደደ ፍልስፍና የምትከተል ከሆንክ፡ ዓላማህም እንዲህ ከሆነ፡ የኛ እዚህ መጎለት ምን ትርጉም አለው? ለአንተ በተግባር መልስ ዬሚሰጡ ጀግኖች እኮ ቦታቸው ላይ እዬጠበቁህ ነው፡ ሂድና እነሱን ሞክራቸው! ብለን መስል ሰጥተነው ወጣን። እንዲህ እንዲህ ለሚያስቡ አካላት፡ በቅጡ የሚገባቸው የሃይል ቋንቋ ብቻ ነው። ፈርጠምና ኮስተር ብለህ የምትሰጣቸው የሃይል ቋንቋ ደህና አድርጎ ይገባቸዋል። ኤርትራ በበነጻነት ትግሉ ወቅት [በናቅፋ፡ በአፍዓበት፡ በምጽዋ፡ በከረን፡ በተሰነይ፡ በአቆርደት፡ በከረን፡ በኣውገት፡ በጊንዳዕ፡ በአፋምቦ፡ በዓዲቐይሕ፡ በደቀምሓረ፡ በሽሬ፡ በአሶሳ፡ በወልድያ በካራ ምሽግ፡ በጉና፡ በጎንደር፡ በባህርዳር፡ በአምቦ፡ በሃረር፡ በሞያሌ በብላቴ በ4ኪሎ፡ በወዘተ] ያደረገችው፡ እንዲሁም ከነጻነት ትግሉ በድል መገባደድ በኋላ [በዓዲምሩግ፡ በባድመ፡ በዛላምበሳ፡ በጸሮና፡ በዓዲበጊዖ፡ በቡሬ፡ በወዘተ] ያደረገችውም ይህንን ነው። ጠላቷቿን እንደዬአስፈላጊነቱ በሚገባቸው የሃይል ቋንቋ ማናገር!

ሙሉ ይዘቱ የፕሮፌሰር በርሀ ሃብተጊዮርጊስ፡ ኤፍሬም ግደ ከተባለ ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ጋር ካደረጉት ቃለመጠይቅ የተቀነጨበ ሆኖ፡ አንዳንድ አብነቶችን ለማብራሪያነት ያህል፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር ቀላቅለንበታል።

Meleket
Member
Posts: 4772
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የሁለት ኤርትራዉያን የሃረር አካዳሚ ካዴቶች ብርቅ ወግ

Post by Meleket » 21 Nov 2025, 04:13

ታሪኽ ብመዓቐኒ ናይቲ ዝተፈጸመሉ ግዜ እናተመዝነ ኪዝንቶ እንከሎ ክንደይ ይምቕር! ናይ ደራሲን ተመራማሪ ታሪኽን ዓለምሰገድ ተስፋይ ሓደ ካብ ብልጫታቱ፡ ንታሪኽ ብመዓቐኒ ናይቲ ዝተፈጸመሉ ግዜ ምምዛኑ ኢዩ!

ገለ ታሪኽ ኤርትራዊ ጀነራል ተድላ ዕቝቢት ከምኡን ኢትዮጵያዊ ጀነራል መንግሥቱ ንዋይ ኣብዚ ምዉካስ ይከኣል ኢዩ።

ሰናይ ንባብ ደቂ ዓበይቲ! viewtopic.php?f=2&t=337572&start=20

ንኤርትራዊ ጋዜጠይና ኤፍሬም ግደ’ዉን፡ ንስለቲ ታሪኽ ኤርትራዉያን ካብ ቀፎኡ ከምዚብርበር መዓር እናበርበርካ፡ በቲ ልሙድ ኤርትራዊ ጭዉነት ሓበንን ፍናንን ንሓፋሽ እትቅርቦ ዛሎኻ ኣካይዳ፡ ብዓቢ ወኒ ንክትቅጽሎ ነተባብዓኻ፡ ንሕና ኤርትራዉያን ደያኑ ማእከልን መስመርን

Post Reply