Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6847
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ህልም ሳይንስ ኣለዉ?

Post by Naga Tuma » 02 Dec 2024, 11:21

እኔ ኣልፎ ኣልፎ ነዉ ህልም የማየዉ። ካየሁ ኣብዛኛዉን ግዜ ግልጥ ብሎ ነዉ የሚታየኝ።

ኣፕሪል ኣስራ ዘጠኝ ወይም እዝያ አከባቢ ለሊት ኣንድ ግልጽ ህልም ኣየሁ።

ህልሙ ማይክ ታይሰን ከሌላ ሰዉ ጋር ቦክስ የሚገጥምበት ቦታ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተቀምጬ ይጀምራል።

ግጥምያዉን እያየሁኝ ማይክ ታይሰን ግንባሩን በሀይል ሲመታ ኣስተዋልኩ።

ደነገጥኩለት እና ድምጼን ከፍ ኣድርጌ ተናገርኩለት። ሲንገዳገድም ኣየሁ።

ያዩት እና የሰሙኝ የእስፖርት ጫወታ ነዉ ብለዉ ማየት ቀጠሉ።

ብዙም ሳይቆይ ከአናቱ ጀርባ ከመሃል ወደ ቀኙ የቡጢ የምያክል እስኩዌር ክፍት ብሎ ደሙ መፍሰስ ሲጀምር ኣየሁ።

ደንግጬለት ያዉ ያዉ እያልኩ ሌላ ተመሳሳይ ቅርጽ ከጉሮሮዉ ጀርባ በተጨማሪ ተከፍቶ ደሙ በዛ በኩልም ሲፈስ ኣየሁ።

የበለጠ ደንግጬ ከእንቅልፌ ነቃሁ።

የዛን ቀን ወይም የዛን ቀን አከባቢ ስለ ኣዕምሮ አስተሳሰብ እና ስለ ቋንቋ እንደመከርኩኝ ኣስታዉሳለሁ። ምክሮቹ ተስተዉለዉ ይሁን ተቀባይነት ማግኘታቸዉን እስከዛሬ ኣላዉቅም።

ህልሙን ብዙ ግዜ እያስታወስኩኝ ህልም ሳይንስ ኣለዉ ወይ እላለሁ።

የሰዉን ትዕግስት ህልም ያገነፍለዋል ወይ እላለሁ።

ስለ ህልም ከመላ ምት ያለፈ ይህ ነዉ የሚባል ሳይንስ ኣለ?

Abere
Senior Member
Posts: 14835
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ህልም ሳይንስ ኣለዉ?

Post by Abere » 02 Dec 2024, 11:36


የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ በወንድሞቹ ተላልፎ በባርነት ወደ ግብፅ የተሸጠው በህልም ምክንያት ነው። ለቤተ መንግስት ሹመት የበቃውም የፈርዖንን ህልም ለመፍታ በመቻሉ ነው።

ታዲያ እንድህ ወለል ብሎ የሚታይህ ከሆነ እኮ 7ኛው ንጉስ 4 ኪሎ ክፍት የስራ ቦታ ይኖረዋል። አሁን ካሉት የጴንጤ ነብያት የተሻለ ዕድል ይኖርሃል። ምናልባት እርሱም ነብይ ነኝ - በነብይ ላይ ነብይ በሚል ችግር ካልፈጠረ።

ወደ ቁም ነገሩ እንግባ፡ ዓለም እንቆቅልሽ ናት። ዓለም የተሰራችው በሂሳብ ነው። የተደረሰበት እንዳለ ሁሉ ያልተደረሰብት ቀመር አለ። የምናውቀው የምናየውን ብቻ ስለሆነ - የማናየውን ለማወቅ እንቸገራለን እንጅ ያላየነውም ገሀድ ነገር አለ።
ለመሆኑ በዚህ አለም ላይ የሰው ልጅ ብቻውን ነው ወይ? እግዜር ዘፍጥረት ላይ ለአዳም ይህን ሁሉ ለአንተ ብሎ ከፈቀደለት ውጭ?

Naga Tuma
Member+
Posts: 6847
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ህልም ሳይንስ ኣለዉ?

Post by Naga Tuma » 03 Dec 2024, 15:47

አበረ፥

ቀልዱን ኣልፈን ቁም ነገሩን ብናወጋ የኣዕምሮ ሜሞሪ ወይም ማስታወስ መቻልን ለብቻ፣ የመለኮት ነገርን ለብቻ፣ ሳይንስን ለብቻ ነዉ የማያቸዉ።

ስለ ዮሴፍ ህልም አፈ ታሪክ ልጅ ሆኜ ያነበብኩኝ የመጀመርያ ትንሽ መጽሓፍ ነበር። የሴቷን ፈተና ኣለፈ በደህና የሚል ነበር። ማንበብ እንደ ጀመርኩኝ ነበር በኣጋጣሚ ቤት ዉስጥ ኣይቼ ኣንስቼ ያነበብኩት።

የዚህ ህልም ጥያቄ ለኣዕምሮ ሜሞሪ በህልም መገለጽ መቻል ሳይንስ የደረሰበት ኣለ ወይ ነዉ።

ሳይንስ ማረጋገጫን ይሰጣል። ኣንዴ ሳይንስ ያረጋገጠዉ ነገር ይጸናል። ለምሳሌ የመሬት ክባዊነት፣ የመሬት ግራቪቲ መኖር፣ የኦክስጂን መኖር፣ ወዘተ።

ይህን ሁሉ ሳይንስ ያልደረሰባቸዉ በጣም ረጅም ዘመናት ነበሩ።

ሳይንስን ኣወኩ ብለህ ስትረጋጋ መለኮት ከሳይንስ በላይ እጅግ በጣም ገዝፎ ይመጣብሃል።

ካልዘነጋሁ ከኣሁን በፊት እጆችዋን ትዘረጋለች የሚለዉ ትንቢት የተነበየዉ ማን እንደ ሆነ እና መቼ እንደተጻፈ ታዉቃለህ ብዬ ጠይቄህ ነበር። ታዉቃለህ? መልሰህ ከሆነ እስከኣሁን ኣላየሁትም ማለት ነዉ።

Digital Weyane
Member+
Posts: 9838
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: ህልም ሳይንስ ኣለዉ?

Post by Digital Weyane » 03 Dec 2024, 16:07

ለሃያ ሰባት አመታት የለፋንበት የታላቋን ትግራይ የመመስረት ህልማችን ቅዠት ብቻ ሆኖ ቀረ። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ :cry: :cry: :cry:

ችግራችን ሳይንሳዊ መፍትሄ እንዲፈለግለት እንማፀናለን። :roll:

Post Reply