Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6852
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የኢትዮጵያ ህዳሴ/እዴሰ ቀልድ ኣይዴለም። ጽንሰ ሀሳቡ ከባድ ኣይዴለም።

Post by Naga Tuma » 18 Oct 2024, 14:33

የህዳሴ/እዴሰ ጽንሰ ሀሳብ ከባድ ኣለመሆኑን በቀላሉ ማወቅ የሚቻለዉ ከክርስቶስ ልደት በፊት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰዎች ይኖሩ እንደነበረ ማስታወስ በቂ ነዉ። ለዚህ ከክርስቶስ የበለጠ ምስክር ኣያስፈልግም።

የኢትዮጵያ ህዳሴ/እዴሰ ቀልድ ኣለመሆኑን ከሚከተሉት ቃላት ብቻ ማስተዋል ይቻላል።

እዴሰ ህዳሴ
ሐቀ ሐቅ
ሴቄ ሳቀ
ሴሴ ሳሳ
ሃሳ ሂስ
አዳ አደይ
ሙጫ ሙጬ
አንገፈ አንጋፋ
ሴረ ሴራ
ሰዴ ዘዴ

እነዚህ ቃላት ለምሳሌ ያህል ነዉ።

ቀጥሎ የሚመጣ ጥያቄ እነዚህ ቃላት ከክርስቶስ መወለድ በፊት የተፈጠሩ ከሆነ ተወራርሰዉ ነዉ ወይስ ኣንድ መሠረት ቢኖራቸዉ ነዉ?

የኢትዮጵያ ህዳሴ/እዴሰ ኣንዱ ቁምነገር ይህን ኣጥንቶ ማበጠር ነዉ።

ስለ ኢትዮጵያ ባህል በጥልቀት ማሰላሰል የጀመርኩኝ ኢትዮጵያ ዉስጥ የኮሌጅ ትምህርት ሳላገባድድ ነበር። ለራሴ ሳይሆን ለሌሎች።

ማሰላሰሉ ቀጥሎ ባገኘሁ ትርፍ ግዜ ያገኘሁትን ኣንብቤ በርካታ የታርክ ቁምነገሮች ካስተዋልኩ እና እዚህ ፎረም ላይ መሳተፍ ሳልጀምር ነበር የኢትዮጵያ ህዳሴ ማለት የጀመርኩኝ።

ሆረስ እና ያበሎን በአካል ኣላዉቃቸዉም። ሁለቱም እኔ የገባኝን ከፊል ዕዉነት ይዘዉ ሲከራከሩ እና ሲፎካኮሩ ሰነበቱ።

እኔ ካስተዋልኩ የሰነበትኩትን ያበሎ የበለጠ ኣዉቃለሁ ብሎ ሲከራከረኝ ሰነበተ።

ኣንድ ቀን ኣዲስ ያስተዋልኩትን እዚህ ፎረም ላይ ጻፍኩኝ። ሰለ ሴቄ እና ሳቀ መመሳሰል ነበር ኣዲስ የጨመርኩለት።

ምን መልስ ይኖረዋል ብዬ እያሰብኩ ነበር የጻፍኩኝ። ከዛ በኋላ እዚህ ፎረም ላይ በዛ ስም ስጽፍ ኣይቼ ኣላዉቅም። ለምን በዛ ስም መጻፍ እንዳቆመ ኣላዉቅም። ቢሆንም ክርክሩን ሁሉ ፉርሽ ያደርጋል ብዬ ያሰብኩትን ከጻፍኩኝ በኋላ በዛ ስም ስጽፍ ኣለማየቴ ሲገርመኝ ሰነበትኩኝ።

ሆረስ ስለ ኢትዮጵያ ረጅም ግዜ ታሪክ የበለጠ ኣዉቃለሁ ብሎ ክርክሩን ቀጥሏል።

እላይ የጻፍኩኝ ቀላል ምሳሌዎች ይህን እያየን ለኢትዮጵያ ህዳሴ/እዴሰ እንተባበራለን እንጂ እንከራከራለን ማለት ኣያስችልም ወይ ለማለት ነዉ።

በእኔ አስተያየት የኢትዮጵያ ህዳሴ/እዴሰ የማይቧጥጠዉ ተራራ፣ የማይቆነጥጠዉ ስህተት ኣይኖሩም።