-
ዶሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት ይባላል። ሲሲ ኢሳያስ ሲፎግረው ለመጀመሪያ ግዜ የግብጽ መሪ (የሻቢያ አለቃ) አስመራ ሄደ። የኢሳያስ ተላላኪነት ስለ ተሰለቸ ማለት ነው! መሳለቂያ ስለሆነ ማለት ነው ።
ግብጽ ኢትዮጵያ ደካማ አገር በነበረችባቸው ያሉት 100 አመታት ያላደረገችው ነገር አሁን ማድረግ በፍጹም አትችልም!!! ዛሬ እንደ ኤርትራ ባለ ደካማና አናሳ መንግስና በፈረሰች ሱማሌ ሃዊዬ ጎሳ ላይ ቆማ ከዚህ ቀደም የላቀ ጥቃት ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ማድረግ የምትችለው ነገር የለም።
ይህ ያስመራ ድራማ በጥልቀት ላሰበው የግብጽን ሽንፈትና የኢሳያስ ተስፋ መቁረጥን የሚያረጋግጥ እንጂ ግብጽ በምስጢር በኢትዮጵያ ላይ ከምትሰራው ደባ የተለየ ነገር አስመራ በመሄድ የምታመጣ ፋይዳ የለም።
የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት የግብጽና ኤርትራ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላትነት ላንዴም ለሁሌም ተገንዝበው አገራቸውን መጠበቅ ብቻ ነው ያለባቸው ።
ታሪካዊ ንብረታቸው የሆነው አሰብን በግዜውና በሂደት ማስመለስ ነው ያለባቸው ሃላፊነት!
ሱማሌ በተመለከተ ከሱማሌ ክልሎች ጋር በማበር የሃዊዬን ጎሳ ከስልጣን በማስወገድ ነው ኢትዮጵያና የሱማሌ ሕዝብ አብረው የሚያድጉትና የሚኖሩት!
ፈላስፋው እንዳለው ነገሮች በተለወጡ ቁጥር እንዳሉ ይቀጥላሉ! THE MORE THINGS CHANGE, THE MORE THE SAME THEY STAY!
ዞሮ ዞሮ ባህር አልባ ኢትዮጵያ እያለች ያፍሪካ ቀንድ ላንዲት ለሊት እንኳ በሰላም መተኛት የለባትም!
እናም የኢትዮጵያ ጠላቶች እዚም እዛም ሲራወጡ እንደ ማየት ልብን የሚያሞቅ ነገር የለም!!!
የስብሰባቸውና የጫጫታቸው መጠን የሽንፈታቸው መለኪያ ነውና!!!